Ce diaporama a bien été signalé.
Le téléchargement de votre SlideShare est en cours. ×

Corona Virus Disease (Covid 19) training

Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Publicité
Chargement dans…3
×

Consultez-les par la suite

1 sur 28 Publicité

Plus De Contenu Connexe

Publicité

Corona Virus Disease (Covid 19) training

  1. 1. በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባሪነት By: Belachew T Lehulu T. Mulusew Z. ደሴ፣ ኢትዮጵያ ሚያዝያ 2012ዓ.ም 15/10/2020 12:36 PM
  2. 2. መግቢያ COVID- 19: የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ሲሆን በቻይና ዉሃን ከተማ ተከስቶ በአለማቀፉ የጤና ድርጅት(WHO) አለማቀፋዊ ወረርሽኝ(pandemic) ተብሎ መሰየሙ ይታወቃል፡፡ ይህ በሸታ ከጤና በተጨማሪ በማህበራዊ፡ ኢኮኖሚ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያም የበሽታዉን መግባት ተከትሎ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
  3. 3. እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ምልክት ያለባቸዉን ሰዎች መለየት (Case identification) የበሽታዉ ምልከት ከታየበት ሰዉ ጋር ንከኪ ያላቸዉን መፈለግ (contact tracing) በሽታዉ የተገኘባቸዉን ለብቻቸዉ ማድረግ (isolation) ከዉጭ ሀገር የሚመጡ ሰዎችን ለ14 ቀን እንቅስቃሴ ማገድ(quarantine) ለህብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን ማስተማር (preventive measures)
  4. 4.  ወሎ ዩኒቨርስቲም የተለያዩ ሰራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡  ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር  በሽታዉን ለመከላከል የሚዉሉ ሳሙና፣ ሳኒታይዘር፡ አልኮል…. ለህብረተሰቡ ማቅረብ  የለይቶ ማቆያ ቦታዎችን ማዘጋጀት  ለምግብነት የሚያገለግሉ ምግቦችን አዘጋጅቶ ማስቀመጥ  የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ጤና ባለሙያዎችን መልምሎ ዝግጁ ማድረግ እና ለሌሎች ስልጠና እንዲሰጡ ማድረግ
  5. 5. መተላለፊያ መንገዶች አካላዊ ንክኪ(Physical contact) እጅ መጨባበጥ በሽታ የያዘዉ ሰዉ ሲስል፣ሲያነጥስ ቀጥታ ወደ አፍ፣አፍንጫ እና አይን ቫይረሱ ከገባ ሰዉ በበዛበት ቦታ መኖር የእጅን ንጽህና አለመጠበቅ
  6. 6. ዋና ዋና ምልክቶች ትኩሳት (>38 oc) ደረቅ ሳል(ማስነጠስ) ትንፋሽ ማጠር ድካም
  7. 7. Hand washing techniques
  8. 8. Alcohol based antiseptic hand rub
  9. 9. COVID 19ን መከላከልና መቆጣጠር  መከላከልና መቆጣጠር ማለት በጀርምና በህዋስያን የሚመጣ ጉዳትን ከተለያዩ ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች እና የጤና ባለሙያዎችን ለመከላከል የተነደፈ እና ሳይንሳዊና ተግባራዊ መፍትሔን በጋር የሚቀርብበት ማለት ነው። 5/10/2020 9
  10. 10. ኮቪድን መከላከል እችላለሁ??? አዎ እጅን አዘዉትሮ በደንብ መታጠብ (በውሃና ሳሙና ወይም ሳኒታይዘር መጠቀም) የሳልና የትንፋሽን ስነ ምግባርና ንፅህና መጠበቅ ማህበራዊ እርቀትን መጠበቅ (ቢያንስ 1 ሜትር መራራቅ) አይን፣አፍንጫ እና አፍን ከመንካት መቆጠብ የፊት ጭንብል እና የግል መከላከያ ቁሳቁሶችን መጠቀም የመጨባበጥ ሰላምታን ማቆም
  11. 11.  ብዙ ሰው ካለበት ቦታ አለመሄድ  በተደጋጋሚ የምንነካውን ቁስ አካል በዲስኢንፌክታንት ሶሉሽን በደንብ ማፅዳት. አልኮል/ሳኒታይዘር ይዞ መንቀሳቀስ የበሽታው ምልክት የታየበት ሰው ከህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆጠብ ማድረግ
  12. 12. የቀጠለ......  ሙያተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ለህሙማን እንክብካቤ ሲያደርጉ ራሳቸውን ከብክለት ለመከላከል የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን መልበስ ይጠበቅባቸዋል ። ማለትም  የፊት ጭንብል እና መነፅር፣  የእጅ ጓንት እና እጂጌ ረጅም ጋወን)  ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ንቁ የሆነ ቅኝት መስራት
  13. 13. ስለ ኮሮና የተሳሳቱ ትርክቶች (myths)  ኮሮና ህፃናት እና ወጣቶችን አይዝም  አልኮል መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል መድሃኒት ናቸዉ  አረቄ ቫይረሱን ይጠብሰዋል  ሙቀት አካባቢን አያጠቃም  ብዙ ውሃ መጠጣት ወደ GI ይወስደዋል 5/10/2020 13
  14. 14. ፀረ ተባይ እና ማፅዳት (Disinfecting and cleaning) ፅዳት/ማፅዳት ማለት ቆሻሻዎችን እና ንፁህ ያልሆኑ ነገሮችን ማስወገድ ማለት ነው። ማፅዳት ብቻውን ጀርምን መግደል አይችልም ነገር ግን ጀርሞችን በማስወገድ ቁጥርንና ስርጭትን ይቀንሳል ፀረ ተባይ (disinfecting) የሚሰራው ኬሚካሎችን በመጠቀም ላይ ያሉ ጀርሞችን ለመግደል ነው። ፀረ ተባይ ላይ ያሉ ጀርሞችን መግደል እንጅ ማፅዳት ወይም ማስወገድ አይችልም 5/10/2020 14
  15. 15. የበረኪና አዘገጃጀት  0.5% በረኪና በማዘጋጀት ለ 10 ደቂቃ በመዘፍዘፍ መርዝነትን ማስወገድ ይቻላል 1/ በረኪና- Chlorine 5% የተዘጋጀ ከሆነ 1:9 ratio (አንድ እጅ በረኪና/ክሎሪን፡ ዘጠኝ እጅ ዉሃ) ቀመር ፡ 2ለ-1= 2X5-1= 10-1= 9 እጅ 2/ በረኪና- Chlorine 3% የተዘጋጀ ከሆነ 1:5 ratio (አንድ እጅ በረኪና፡ አምስት እጅ ዉሀ) ቀመር፡ 2ለ-1= 2X3-1= 6-1= 5 እጅ 5/10/2020 15
  16. 16. Table 1. the volume of chlorine and water needed for 0.5 % spray solution from 5% chlorine concentration 5/10/2020 16
  17. 17. WE ALL HAVE RESPONSIBILE TO FIGHT AGAINST COVID 19!!! WHAT DO YOU THINK ??? 5/10/2020 17
  18. 18. Quarantines Vs Isolation  Quarantine (ኳራንቲን) እና Isolation (መነጠል) ተላላፊ በሽታን በመገደብ ህብረተሰቡን ለመጠበቅ የሚረዱ የጤና ልምዶች ናቸው::
  19. 19. Quarantine Center (የኳራንቲን ማእከል) ጤነኛ ሰዎችን እንቅስቃሴ ይገድባል::  ተላላፊ ህመሙ ከለባቸዉ ሰዎች ጋር ንክኪ ካለባቸዉ እና ለወድፊት ህመሙ ያላቸዉ መሆኑን ለመለየት ያግዛል፡፡  ምልክቶች ከመታየታቸዉ በፊት አገልግሎት ላይ ይዉላል o
  20. 20. oምክንያቱም ፣ የተጋለጡ መሆናቸውን አላወቁም ወይም o ህመሙ ኑሮባቸዉ ግን ምልክት ያላሳዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ኳራንቲን/Quarantine እስከ መቼ?  ለ14 ቀናት በተመሳሳይ ስፍራ ውስጥ o ወደ ጤነኛ ሰዎች በሽታውን እንዳያሰራጩ
  21. 21. Isolation Center (የመለያ ማእከል) ምልክቶች ከታዩ በኋላ አገልግሎት ላይ ይዉላል፡፡ የሚያገለግለዉ ለታመሙ ሰዎች/+ve test for COID-19 ነው፡፡  የታመሙና ተላላፊ በሽታ ያለባቸዉን ካልታመሙት ሰዎች ለመለየት ያግዛል፡፡  በህክምና ተቋማት ውስጥ በመደበኛ አሰራር ሂደት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
  22. 22. Isolation (መነጠል) እስከ መቼ?  ቢያንስ ለሦስት ቀናት ያህል ከትኩሳት ነፃ ከሆኑ (ትኩሳትን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን ሳይጠቀሙ)  ሌሎች ምልክቶች (ሳል፣ የትንፋሽ እጥረት) መሻሻል ሲያሳዩ የበሽታ ምልክቶች መጀመሪያ ከታዩበት ቢያንስ 7 ቀናት ማለፋቸዉ  ረዘም ላለ ጊዜ መነጠል
  23. 23. Treatment Center (የሕክምና ማእከል) ቀደም ሲል ለታመሙ እና ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች ያገለግላል ፡፡  ምልክቶች ከታዩ በኋላ እና ህመሙ በህክምና ላቦራቶሪ ከተረጋገጠ በኋላ አገልግሎት ላይ ይዉላል
  24. 24. የፊት ጭንብል (Face Mask) እና ጓንት (Glove)  የፊት ጭንብል (Face Mask)  መቼ መልበስ እችላለሁ? 1) የመተንፈሻ አካላት ምልክቶች ሲኖረን 2) የመተንፈሻ አካላት ምልክቶች ካለዉ ሰዉ በቅርብ ላይ ከሆንን (ከ1ሜትር ያነሰ) 3) ወደ ህክምና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜ  እንዴት መልበስ እችላለሁ?  እጅን መታጠብ (ሳኒታይዘር፣ ዉሃናሳሙና)  የተቀደደ፣ ክፍተት ቦታ ካለዉ መመልከት  ትክክለኛ አቀማመጡን ማረጋገጥ (ዉስጥ-ዉጭ፣ ላይ-ታች)  ጭንብሉን ፊታችን ጋር ማስቀመጥ (ማሰሪያ ገመዶችን በጆሮ ጀርባ በኩል ማስቀመጥ)  ከላይ እና ከታች ማስተካከል
  25. 25.  እንዴት ማዉለቅ እችላለሁ?  ማሰሪያ ገመዶችን ማዉለቅ (ፊታችን ሆነ ልብሳችንንም በማይነካን መልኩ)  ከተጠቀምን በኋላ በቆሻሻ ቅርጫት መጣል  እጅን መታጠብ (ሳኒታይዘር፣ ዉሃና ሳሙና)  ጓንት (Glove)  ጓንት ለምን?  ራሳችንን ከተላላፊ በሽታ ለመከላከል (ከሌሎች ወደ እኛ)  ሌሎችን ከተላላፊ በሽታ ለመከላከል (ከእኛ ወደ ሌሎች, ከሌሎች ወደ ሌሎች)
  26. 26. ጓንት መልበስ (Donning Gloves)  ጓንት ከመልበሳችን በፊት እጃችንን መታጠብ መርሳት የለብንም (ሳኒታይዘር፣ ዉሃናሳሙና)
  27. 27. ጓንት ማዉለቅ (Doffing Gloves)  ጓንት ካወለቅን በኋላ እጃችንን መታጠብ መርሳት የለብንም (ሳኒታይዘር፣ ዉሃናሳሙና)

×