SlideShare a Scribd company logo
1 of 62
Download to read offline
ለህትመት የተዘጋጀ
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና
2698BE
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
2
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ማውጫ
የስልጠናው አጭር መግለጫ
የስልጠናው መረጃ
ሞዱል 1፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ
ኮምፒውተርን መጠበቅ
ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ
ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት
የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት
የሞዱሉ ማጠቃላያ
መፍትሔ ቃላት
የሞዱሉ መረጃ
ይህ ስልጠና ስለ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና አጭር መግለጫ ይሰጣሃል። ለኮምፒውተርህ ስለሚጎዱ የስጋት ዓይነቶች እና
ከእነዚህን ስጋቶች እንዴት ኮምፒውተርህን መጠበቅ እንደምትችል ትማራለህ። የመረጃ ልውውጥ ህጋዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ኮምፒውተር እና
በይነመረብ ለተጠቃሚዎች ስለሚያቀርቧቸው ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎችም ትማራለህ።
የስልጠናው ማብራሪያ መግለጫ
የተሳታፊዎች መግለጫ ይህ ስልጠና ኮምፒውተር የመጠቀም ችሎታን ለማዳበር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የታለመ ነው።
ቀዳሚ አስፈላጊ ነገሮች ተማሪዎች ቢያንስ አንድ የሀገር ውስጥ ጋዜጣን ለማንበብ የሚያስችል መሰረታዊ የማንበብ እና የመረዳት ችሎታ
ሊኖራቸው ይገባል።
ተማሪዎች የመጀመሪያውን መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል ወይም ተመጣጣኝ የሆነ
የኮምፒውተር ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል።
የስልጠናው ዓላማዎች ይህን ስልጠና ከጨረስክ በኋላ፦
• ለሃርድዌር እና መረጃ ስጋት ስለሆኑት ድንገተኛ አደጋዎች ፣ የመሳሪያ ብልሽት ፣ አካባቢ ፣ የሰዎች
ስህተት እና ጎጂ ተግባሮች ማብራራት እና
• እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
3
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የሞዱሉ ይዘቶች
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ
ኮምፒውተርን መጠበቅ
ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ
ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት
የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት
የሞዱሉ ማጠቃላያ
የሞዱሉ መግቢያ
እንደማንኛውም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ በአጋጣሚዎች ወይም ሆን ተብለው ለሚደረጉ አደጋዎች ሰለባ ነው። ከነዚህ አደጋዎች አንዳንዶቹ
የማይመለሱ ሊሆኑ ይችላሉ። የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ ያለን ውሂብ አንዳንድ የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ
ብዛት ካላቸው ጉዳቶች መታደግ ይቻላል።
ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለተቀመጠው ውሂብ ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ እንድታውቅ ይረዳሃል። አንዳንድ የመከላከያ
ርምጃዎችን በመውሰድ ኮምፒውተርህን ከነዚህ ስጋቶች እንዴት መጠበቅ እንደምትችል ይዳስሳል። በመጨረሻም ይህ ሞዱል ከበይነመረብ
አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮችን ያብራራል።
የሞዱሉ ዓላማዎች
ይህን ሞዱል ከጨረስክ በኋላ፦
• የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ማብራራት እና ለኮምፒውተር ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ ፤
• ኮምፒውተርን ከተለያዩ አደጋዎች የመጠበቂያ ዘዴዎችን ለይተህ ማወቅ ፤
• የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ለማሳደግ የሚጠቅሙ ጥሩ ተሞክሮዎችን ማብራራት ፤
• ኮምፒውተርህ ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት የሚረዱ ቅንጅቶችን እና አማራጮችን ማብራራት እና
• ኮምፒውተር እና በይነመረብ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቧቸውን ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።
በሁሉም የህይወት ተሞክሮዎችህ ውስጥ ኮምፒውተሮችን ትጠቀማለህ። መረጃ ለማስቀመጥ ፣ የሒሳብ ስራዎችን ለማከናወን ፣ ጌሞችን ለመጫወት ፣
ሙዚቃ ለማዳመጥ ፣ በይነመረብን ለመዳሰስ እና በኢ-ሜይል እና በውይይቶች ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ለመሰሉ የተለያዩ ዓላማዎች ኮምፒውተሮችን
ልትጠቀም ትችላለህ።
ነገር ግን ኮምፒውተርህ እና በውስጡ የተከማቹ መረጃዎችህ ለጉዳት እና ለብልሽት የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ በተፍጥሮ አደጋዎች ፣ በሰዎች ስህተት
ወይም በድንገተኛ ክስተት ወይም የሰርጎ ገቦች ወይም ቫይረስ ጥቃቶችን በመሰለ የጥቃት እንቅስቃሴ ከሚፈጠሩ አደጋዎች ኮምፒውተርህን መጠበቅ
ይኖርብሃል።
ኮምፒውተርህን ከነዚህ አደጋዎች ለመጠበቅ የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለህ። ለምሳሌ ተገቢ የሆነ የደህንነት ጥበቃ
ቅንጅቶች እና የዘመነ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር በኮምፒውተርህ ውስጥ እንዲኖርህ በማድረግ። ኮምፒውተርህ በይበልጥ የተጠበቀ መሆኑን ርግጠኛ
ለመሆን የቤተሰብህ አባሎችም ስለ ደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ማወቅ ይኖርባቸዋል።
በበይነመረብ አማካይነት ከሚገኝ መረጃ ጋር በተያያዘ ያሉ መብቶችን ማወቅም አስፈላጊ ነው። በብዙዎቹ የድር ጣቢያዎች የሚገኙ ይዘቶች የቅጂ
መብት ያላቸው ንብረቶች ስለሆኑ ያለፈቃድ እነዚህን መጠቀም በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።
ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የተለያዩ አደጋዎችን ፣ እነዚህ አደጋዎች ስለሚያሳድሩት ተጽዕኖ እንዲሁም መፍትሔዎቻቸው ይዘረዝራል።
ይህ ሞዱል የኮምፒውተርህን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለማዘመን ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎችም ያብራራል። ከዚህ
በተጨማሪም ይህ ሞዱል በይነመረብን በምትጠቀምበት ጊዜ ልብ ልትላቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮች ያብራራል።
ሞዱል 1
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
4
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው?
የተፈጥሮ አደጋዎች
ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች
በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች
ግለ ሙከራ
የትምህርት ክፍሉ መግቢያ
የግብር ወረቀቶችን የመሰሉ አስፈላጊ ሰነዶችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ታስቀምጣቸዋለህ። ስለዚህም
ሰነዶችህ ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጠፉም። ካለፍቃድህም ማንም ሊያገኛቸው/ሊደርስባቸው
እንደማይችል እርግጠኛ ነህ።
ኮምፒውተሮችን ብዙ ጊዜ የምትጠቀም ከሆነ በኮምፒውተር ላይ ሊቀመጥ የሚችል በርካታ መረጃ
ሊኖርህ ይችላል። ይህ መረጃ የግብር ዝርዝር ፣ የግል ደብዳቤዎች ወይም የንግድ ስራ ደብዳቤዎች ሊሆን
ይችላል። ይህ መረጃ ካላንተ ፈቃድ በሌሎች ሰዎች የማይታይ መሆኑን እርግጠኛ ልትሆን ይገባል። ይህ
መረጃ ጉዳት እንዳይደርስበትም መጠበቅ ይኖርብሃል።
በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና ኤሌክትሮኒክ መረጃ ከጉዳት ፣
ከመጥፋት እንዲሁም ከስርቆት የመጠበቅ አስፈላጊነትን ትዳስሳለህ። በተጨማሪም በኮምፒውተርህ ያለን
ውሂብ ለመጠበቅ ልትጠቀምባቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ መፍትሔዎች እና መሳሪያዎች ትማራለህ።
የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች
ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦
• የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመናን ማብራራት ፤
• ተፈጥሮአዊ የኮምፒውተር አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ፤
• ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ፤
• ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የሰዎች ተግባሮችን ለይቶ ማወቅ እና
• ስጋት ከሆኑ የሰዎች ተግባሮች ኮምፒውተርህን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ
ማወቅ ትችላለህ።
ክፍለ ትምህርት 1
የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
5
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው?
ኮምፒውተርን ወይም በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ሊያበላሽ የሚችል መንስኤ የኮምፒውተር ስጋት ነው። እንደ ርዕደ መሬት ወይም ከፍተኛ
አውሎንፋስ ያሉ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች መጠነ ሰፊ አካላዊ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። አንተ ወይም ሌላ ሰው ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ
ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ አስፈላጊ ፋይሎችን በአጋጣሚ ወይም ባለማወቅ ልታጠፉ ትችላላችሁ። ኮምፒውተርህ ከአውታረመረብ ጋር ሲገናኝ
ኮምፒውተርህ የበለጠ ለኮምፒውተር ስጋቶች የተጋለጠ ይሆናል። ለምሳሌ ሌላ ተጠቃሚ ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመዳረስ አውታረመረቡን
ሊጠቀም ይችላል።
እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ እና በጉዳት ምክንያት ሊደርሱ የሚችለውን የመጥፋት ዕድል ለመቀነስ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች
አሉ። መሰረታዊ የሆኑ መመሪያዎችን በመከተል በኮምፒውተርህ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጉዳት መጠን መቀነስ እና ስለደህንነቱ እና ክብረ ገመናው
እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።
የኮምፒውተር ደህንነት
የኮምፒውተር ሃርድዌር በሰዎች ቸልተኝነት አልያም በተፈጥሮ
አደጋዎች ምክንያት ሊበላሽ ይችላል። በተጨማሪም በኮምፒውተር
ውስጥ ያለ ውሂብ እና ሶፍትዌር በአጋጣሚ ወይም ሆን ተብሎ
ከሚደረግ ጥፋት እና ብልሽት መጠበቅ አለባቸው። የኮምፒውተር
ደህንነት ጥበቃ በኮምፒውተር ላይ እና በውስጡ በሚገኘው ውሂብ
ላይ የሚደርስን እንደዚህ ያለ ጉዳት ለማስወገድ ስለሚወሰዱ
ርምጃዎች ያወሳል።
የኮምፒውተር ክብረ ገመና
በኮምፒውተርህ ላይ የግል ፋይሎችህንና ወይም ሰነዶችህን
ታስቀምጣለህ እናም ማንም ሰው እንዲያነብብህ አትፈልግም።
የኮምፒውተር ክብረ ገመና ማለት የግል ፋይሎች እና የኢ-ሜይል
መልዕክቶች የመሳሰሉ መረጃዎችን ካለአንተ ፈቃድ ማንም
እንዳይደርስባቸው ማድረግ ማለት ነው። የኮምፒውተር ክብረ
ገመና ውሂብህን የመዳረስ ፈቃድን ለመገደብ ልትወስዳቸው
ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያወሳል። የኮምፒውተር ክብረ ገመና
በተጨማሪም ማንኛውም የግል የሆነ መረጃን በበይነመረብ ላይ
ለማውጣት የሚደረግ ጥንቃቄን ያካትታል። እንደዚህ ያለ መረጃ
እንደ ኢ-ሜይል እና የባንክ መለያዎች ያሉ የግል መለያዎችህን
ለመዳረስ ሲባል ያልአግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
6
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ የተፈጥሮ አደጋዎች
ርዕደ መሬት ፣ ጎርፍ ፣ አውሎንፋስ እና የመሳሰሉት ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ኮምፒውተርህን በማንኛውም ጊዜ ሊያበላሹብህ ይችላሉ። የተፈጥሮ
አደጋዎች ኮምፒውተሮች ላይ አካላዊ ጉዳት ሊያደርሱ እና ውሂብ እንዲጠፋ የሚያደርጉ እንደ እሳት ፣ ከመጠን ያለፈ ሙቀት አንዲሁም ፍንዳታዎችን
ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ይህ ስዕላዊ ማስረጃ ለኮምፒውተር ደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋት የሆኑ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ይገልፃል።
1.
አብዛኞቹ የኮምፒውተር ክፍሎች በተወሰነ የሙቀት ክልል ብቻ መስራት እንዲችሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። ከመጠን ያለፈ ሙቀት ወይም
ቅዝቃዜ በሚኖርበት ጊዜ አንዳንድ የኮምፒውተር አካሎች በትክክል ያለመስራት ሊጀምሩ ይችላሉ እንዲሁም እነዚህን ክፍሎች በሌላ መተካት
ሊያስፈልግህ ይችላል። ኮምፒውተርህ ከመጠን ላለፈ ሙቀት የተጋለጠ ከሆነ ከማስጀመርህ በፊት መደበኛ ሙቀት ወዳለበት ክፍል ውሰደው።
2.
እሳት ኮምፒውተርህን ሊጠገን በማይችልበት ሁኔታ ሊጎዳው ይችላል። ኮምፒውተሩ በቀጥታ እሳት ሊይዘው ባይችልም ሊፈጠር የሚችለው
ሙቀት በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎችን ለማቅለጥ በቂ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጭስ የሲፒዩ ፋንን ሊያበላሽ ይችላል ይህም
ሲፒዩ እንዲግልና እንዲበላሽ ያደርገዋል።
3.
ከፍተኛ በሆነ የኤሌክትሪክ ፍሰት የሚከሰት ፍንዳታ/ብልጭታ የኃይል መጨመርን ያስከትላል። የኃይል መጨመር ወይም መቆራረጥ
የኮምፒውተርህን አንዳንድ ክፍሎች ዳግም እንዳይሰሩ አድርጎ ሊጎዳ የሚችል ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር ነው። ለምሳሌ ድንገተኛ
የኃይል አቅርቦት መጨመር የኮምፒውተርህን ማዘርቦርድ ሊያቃጥል ይችላል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
7
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
የተፈጥሮ አደጋዎች ኮምፒውተርህ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ ውሂብህን እና ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮአዊ
አደጋዎች ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ያብራራል።
ርምጃ መግለጫ
የውሂብ ምትክ መያዝ የውሂብ ምትክ መያዝ የውሂብህን ቅጂዎች በዛ አድርጎ መያዝን ያካትታል። አንደ ጎርፍ እና ርዕደ መሬት ያሉ
አደጋዎች በድንገት ሊከሰቱ ይችላሉ። ምትክ መያዝ በማንኛውም ሁኔታ የሚከሰትን የውሂብ መጥፋት መልሰህ
እንድታገኘው ይረዳሃል። ውሂብህን በጥሩ ሁኔታ እንደገና ለማግኘት ምትክ አድርገህ የያዝከውን አስፈላጊ የሆነ
መረጃህን ቅጂ ሌላ ህንፃ ወይም ከተማ ላይ ለይተህ በጥንቃቄ አስቀምጥ።
ኮምፒውተሮችን ደህንነቱ
በተጠበቀ ስፍራ ማስቀመጥ
ኮምፒውተርህን ለተፈጥሮ ተጽዕኖዎች ሊጋለጥ እና ሊበላሽ በማይችልበት ስፍራ ላይ አስቀምጥ። ለምሳሌ
ኮምፒውተሮችን አቧራ የሚበዘበት ወይም እርጥበት ያለበት ክፍል ውስጥ ከማስቀመጥ ተቆጠብ።
ጠባቂ የኤሌክትሪክ
መሳሪያዎችን መትከል
የማይቋረጥ ኃይል አቅራቢ (Uninterruptible Power Supply) (UPS) የመሰሉ መሳሪያዎችን መትከል ጊዜያዊ
የኃይል መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ በምትኩ የባትሪ ኃይልን ማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋል። UPS በድንገተኛ
የኮምፒውተር መዘጋት ምክንያት የሚከሰትን የሶፍትዌር ብልሽት ይከላከላል። UPS የኃይል መብዛት እና የኃይል
አስተላላፊ መስመሮችንም ይቆጣጠራል። ይህም በኃይል መተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚከሰት የኃይል መብዛት
እና መቆራረጥ ኮምፒውተርህን እንዳይጎዳ ይረዳል። የኃይል መብዛት ጠባቂዎችን እና የመስመር ተቆጣጣሪዎችን
ለየብቻ መትከልም ትችላለህ። ነገር ግን እንደ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ያሉ ክስተቶች ምክንያት በሚፈጠር ከፍተኛ
የሆነ የኃይል መብዛት ሁኔታ ጊዜ አደጋን ለማስወገድ ኮምፒውተርህን ማጥፋ እና ከኃይል ምንጩ መንቀል
ይኖርብሃል ።
ኮምፒውተሮችን ከእሳት
መጠበቅ
የእሳት ሂደትን በሚቀንስ ነገር ዙሪያውን በማጠር ኮምፒውተርን ከእሳት መጠበቅ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በቂ
የሆነ የእሳት መከላከያ መሳሪያዎችን እና ፈጣን የአደጋ መቆጣጠሪያ ርምጃ መውሰጃዎችን መትከል ትችላለህ።
ተገቢ የሆነን ሙቀት እና
የአየር ሁኔታ መጠበቅ
የኮምፒውተርህ አገልግሎት አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ ተስማሚ የሆነውን ሙቀት እና የአየር ሁኔታ
መጠበቅ ይኖርብሃል። ይህንንም የአየር ማቀዝቀዣዎችን እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎችን የመሰሉ መሳሪያዎችን
በመጠቀም ማድረግ ትችላለህ።
ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች
አንዱ የኮምፒውተር ስጋት ዓይነት በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት ነው። በቢሮህ ውስጥ የሚሰራ አንድ የተከፋ ሰራተኛ ሆን ብሎ በኮምፒውተርህ ውስጥ
ያለን መረጃ ለማበላሸት ሊነሳሳ ወይም ለማጥፋት ሊሞክር ይችላል። ሰርጎ ገብ ከበይነመረብ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ህገወጥ በሆነ መንገድ
ኮምፒውተርህን ለመድርስ የሚሞክር ሰው ነው። ኮምፒውተርህን ከደረሰ በኋላ ሰርጎ ገብ በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ሊሰርቅ ወይም ሊያበላሽ
ይችላል። በሰዎች ከሚፈጠር ጉዳት በተጨማሪ እንደ ድንገተኛ የውሂብ ማጥፋት እና አካላዊ ጉዳት ያሉ የሰዎች ስህተት ለኮምፒውተርህ ስጋት
ናቸው። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት እና በሰዎች ስህተት የሚመጡ የተለያዩ የኮምፒውተር ስጋቶችን ይገልፃል።
አደጋ መግለጫ
ስርቆት ማንኛውም ሰው ኮምፒውተህን መዳረስ የሚችል ከሆነ ኮምፒውተርህን ወይም የኮምፒውተሩን ክፍሎች ሊሰርቅህ
ይችላል። እንደ ላፕቶፕ ያሉ ተንቀሳቃሽ ኮምፒውተሮችን የሚጠቀሙ ሰዎች ከመብዛታቸው አንፃር አካላዊ
የኮምፒውተሮች ስርቆት የተለመደ ሆኗል።
ኮምፒውተርህ ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ጊዜም የምናባዊ ስርቆት ሰለባ ልትሆን ትችላለህ። አንዱ የምናባዊ ስርቆት
ምሳሌ የሚሆነው የማንነት መለያ ስርቆት ነው ፤ በዚህም ሰርጎ ገቦች መለያህን በመጠቀም እና አንተን በመምሰል የግል
መረጃዎችህን ሊሰርቁህ ይችላሉ። ይህን የሐሰት የማንነት መለያ በመጠቀም ሰርጎ ገቦች ፋይናንስህን መዳረስ ሊችሉ
ወይም ህገ ወጥ ስራዎችን ሊያከናውኑበት ይችላሉ። ሌላው የምናባዊ ስርቆት ምሳሌ የሚሆነው የሶፍትዌር ህገ-ወጥ ቅጂ
ነው ፤ ይህም የኮምፒውተር ንድፍ ወይም ፕሮግራም ስርቆት ነው። በተጨማሪም ይህ የኮምፒውተር ፕሮግራምን እና
ምስጢራዊ ሰነዶችን ያለፍቃድ ማሰራጨት እና መጠቀም ማለት ሊሆን ይችላል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
8
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ቫይረሶች ፣ ተውሳኮች
እና ትሮጃን ሆርሶች
ቫይረሶች በኮምፒውተርህ ላይ ያለን ውሂብ ወይም ሶፍትዌር ሊያበላሹ እንዲሁም በኮምፒውተረህ ውስጥ የተቀመጠ
መረጃን ሊሰርቁ የሚችሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች ናቸው። እነዚህ ቫይረሶች ካላንተ ዕውቅና ፣ በበይነመረብ ወይም
እንደ ፍሎፒ ዲስኮች እና ሲዲዎች ባሉ የማከማቻ መሳሪያዎች አማካይነት ወደ ኮምፒውተርህ ሊገቡ ይችላሉ።
ተውሳኮች አንዴ ኮምፒውተር ውስጥ ከገቡ በኋላ ራሳቸውን የሚያባዙ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ይህም እነርሱን
ለማስወገድ ከባድ እንዲሆን ያደርገዋል። ትሮጃን ሆርሶች ራሳቸውን እንደጠቃሚ ሶፍትዌር የሚያስመስሉ የቫይረስ
ዓይነቶች ናቸው። ለምሳሌ እንደ ጌም ወይም መገልገያ ሶፍትዌር ሊመስሉ ይችላሉ። ትሮጃን ሆርስ አንዴ ኮምፒውተር
ውስጥ ከገባ በኋላ የኮምፒውተር ውሂብን ማበላሸት ይጀምራል።
ስፓይዌር ስፓይዌር የሚባሉት ካላንተ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ ፕሮግራሞች ናቸው። ስለ ድር አሰሳ ልምዶችህ
ወይም ሌላ የግል መረጃ ዝርዝሮችህ ወደ ሌላ በአውታረመረቡ ላይ ያለ ኮምፒውተር በድብቅ/በሚስጥር መረጃ ሊልኩ
ይችላሉ።
የበይነመረብ
አጭበርባሪዎች
በይነመረብ በምትጠቀምበት ጊዜ በኢሜይል መልዕክቶች ወይም በውይይት መድረኮች አንዳንድ ሳቢ የሆኑ ነገሮች
ሊላኩልህ/ሊቀርቡልህ ይችላሉ። እንደዚህ አይነት አቅርቦቶችን ከመቀበልህ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል ፤
ምክንያቱም እነዚህ አቅርቦቶች የገንዘብ ጥፋት የሚያስከትሉ በሚገባ የታቀዱ የአጭበርባሪዎች አካል ሊሆኑ ይችላሉና።
የመስመር ላይ አዳኞች የመስመር ላይ አዳኞች በመስመር ላይ ያለ ማንኛውንም ሰው አግባብ ባልሆነ መንገድ ወይም ስነምግባር በጎደለው
ሁኔታ ወዳጅነት በመፍጠር የሚያማልሉ ግለሰቦች ናቸው። አንተ ወይም ቤተሰቦችህ የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ
ልትሆኑ ትችላላችሁ። የመስመር ላይ አዳኞች ኢሜይል ወይም የውይይት መድረኮችን በመጠቀም በፈለጉት አላማ
ዙሪያ ከሰዎች ጋር ግንኙነታቸውን ያዳብራሉ።
ድንገተኛ የውሂብ
መጥፋት
ብዙ ጊዜ ድንገተኛ በሆነ የሰዎች ስህተት ምክንያት የኮምፒውተር ብልሽት ሊደርስ ይችላል። ድንገተኛ የሆነ የአስፈላጊ
ፋይል መጥፋት የውሂብን አንድነት ሊያዛባ ወይም ሌሎች ፋይሎች ወይም ፕሮግራሞች እንዳይሰሩ ሊያግድ ይችላል።
ለምሳሌ ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ የሚያደርግን ፋይል በድንገት/ሳታውቅ ልታጠፋ ትችላለህ።
ድንገተኛ የሃርድዌር
ብልሽት
በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎች በቸልተኝነት ለሚከሰቱ ብልሽቶች የተጋለጡ ናቸው። ለምሳሌ በድንገት
ላፕቶፕ ኮምፒውተርህ ቢወድቅብህ እንደ ማዘርቦርድ ወይም ሲዲ-ሮም ያሉ የኮምፒውተሩ ክፍሎችን ሊጎዳብህ/
ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህም በኮምፒውተርህ ውስጥ ያለን መረጃ ያሳጣሃል። ከዚህ በተጨማሪም በማከማቻ
መሳሪያዎች ወይም ተገጣሚዎች ላይ በምግብ ወይም መጠጥ መፍሰስ ምክንያት የሚደርስ አካላዊ ጉዳት ኮምፒውተርህ
ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ጋር በተያያዘ የሚመጡ ስጋቶችን ለመቀነስ አንዳንድ ቀላል ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ። ቀጥሎ
ያለው ሰንጠረዥ ኮምፒውተርህን በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች ይገልፃል።
መፍትሔ መግለጫ
መረጃን አስተማማኝ በሆነ
ቦታ ማስቀመጥ
መረጃህን አስተማማኝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ማለትም ሌሎች በማይደርሱበት ሁኔታ አስቀምጥ። ይህም
መረጃው የሚሰረቅበትን እና የሚበላሸበትን እድል ይቀንሰዋል።
ውሂብን መመስጠር የWindows 7 ቢትሎከር (BitLocker) ባህሪ ውሂብን በአንፃፊ-ደረጃ ለለመስጠር ይረዳሃል። ይህን ባህሪ
በመጠቀም ውሂብን በምትመሰጥርበት ጊዜ ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ደረቅ አንፃፊውን (ሃርድ ድራይቩን)
በመንቀል እና ከሌላ ኮምፒውተር ጋር በማገናኘት ውሂቡን ማግኘት አይችሉም።
ፀረ ቫይረስ እና ፀረ
ስፓይዌር ፕሮግራሞችን
መጫን
ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በኮምፒውተር ማህደረ ትውስታ ውስጥ ቫይረስ እና ስፓይዌር እንዳለ
የመፈተሽ እንዲሁም አዲስ ወደ ኮምፒውተሩ እንዳይገባ የመከላከል አቅም አለው። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር
ሶፍትዌርን በየጊዜው ማዘመን አለብህ ፤ ይህም አዳዲስ ቫይረሶችን እና ስፓይዌሮችን መለየት እንዲችሉ
ያስችላቸዋል። አብዛኛው ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር የዘመነውን የሶፍትዌር ስሪት በራሱ ወደ
ኮምፒውተር የሚጭን የራስ ማዘመኛ ባህሪ ያቀርባል።
እንደ Windows Mail ባለ የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ውስጥ አብረው የተሰሩ ባህሪያት አይፈለጌ የኢ-ሜይል
መልዕክቶችን ለማገድ ያስችሉሃል ፤ እንዲሁም ቫይረሶችን እና ተውሳኮችን የሚፈትሹ ባህሪያትን ያቀርባሉ።
Windows 7 Windows መከታ የሚባል በወቅቱ የመከላከል አቅም ያለው አብሮ የተሰራ ፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም
አካቷል።
ኬላ (firewall) መጫን ኬላ መጫን የኮምፒውተር ጎጂ ስጋቶችን ለመከላከል ልትወስደው የምትችለው ውጤታማ መፍትሔ ነው። ኬላ
(firewall) የበይነመረብ ፍሰትን ኮምፒውተርህን ወይም የግል አውታረመረብህን ከመድረሱ በፊት ለማጣራት
ያስችልሃል። እንደ ሰርጎ ገቦች እና ቫይረሶች ያሉ ስጋቶችን የመከላከያ ተጨማሪ አገልግሎቶችንም ይሰጣል። ኬላ
ባልተፈቀደ ተጠቃሚ ማንኛውም ከውጪ የሚደረግን መዳረስ በማገድ የኮምፒውተርህን ደህንነት እንድታረጋግጥ
ይረዳሃል። በWindows 7 የሚገኘው Windows ኬላ የማይፈለግ የኮምፒውተር መዳረስን ያግዳል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
9
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ምትክ ውሂብ መያዝ አስፈላጊ የሆነን የኮምፒውተር ውሂብ በየጊዜው ምትክ ያዝ። የውሂብን ምትክ ቅጂዎችን በዛ አድርጎ መያዝ
በድንገት መጥፋት ወይም መበላሸት ምክንያት የሚከሰትን የውሂብ ማጣት ይከላከላል።
ኮምፒውተርን አስተማማኝ
በሆነ ስፍራ ማስቀመጥ
ኮምፒውተርህን ከአቧራ ነፃ በሆነ ፣ ንቅናቄ በሌለበት እና ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች የጸዳ ስፍራ ላይ አስቀምጥ።
የኮምፒውተሩ ማስቀመጫ ጠረጴዛ ወይም መደርደሪያ የማይነቃነቅ እና ቋሚ መሆን ይኖርበታል። ይህም
ኮምፒውተሩ በድንገት ቢገፋ እንኳ እንዳይወድቅ ይረዳዋል።
ኮምፒውተርህን ከመግኔጢሳዊ ዕቃ እና ፈሳሽ ነገር አርቅ። ለምሳሌ ኮምፒውተርህን መሬት ላይ ወይም ምንጣፍ
ላይ አታስቀምጥ። በቁልፍ ሰሌዳ አቅራቢያ ሆነህ አትመገብ ወይም አትጠጣ እንዲሁም የቁልፍ ሰሌዳህን በድንገት
ከሚፈስ ነገር ለመከላከል መሸፈኛ ተጠቀም።
ርዕስ፦ የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች
የሚከተሉትን የተለያዩ አይነት አደጋዎችን ለመከላከል የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ
የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው።
ዓረፍተ ነገር
1 የኃይል መብዛትን መከላከያ እና የኤሌክተሪክ መስመር መቆጣጠሪያ
2 የውሂብ ምስጠራ
3 የእሳት ሂደትን የሚቀንስ ነገር
4 የማይነቃነቅ ጠረጴዛ
5 ከመግኔጢሳዊ ዕቃዎች ማራቅ
6 ፀረ ቫይረስ
7 የአየር ማቀዝቀዣዎች እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎች
8 የስፓይዌር መከላከያ
9 የቁልፍ ሰሌዳ መሸፈኛ
10 ኬላ
ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3
የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች
ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
10
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3
የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች
7, 3, 1 10, 8, 6, 2 9, 5, 4
ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ
ጥያቄ 1
ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው?
ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ።
ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ።
ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል።
ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ።
ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ።
ጥያቄ 2
ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው
የቱ ነው?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ።
ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር።
ኬላ።
የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ።
ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
11
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
መልስ 1
ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው?
ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ።
ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ።
ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል።
ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ።
ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ።
መልስ 2
ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው
የቱ ነው?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ።
ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር።
ኬላ።
የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
12
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች
ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች
የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች
የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
ግለ ሙከራ
የትምህርት ክፍሉ መግቢያ
የባንክ ወይም የአስተማማኝ ገንዘብ ማጠራቀሚያ ሳጥንህን ለመድረስ የማንነት መለያህን መስጠት
ይኖርብሃል። ይህ የማንነት መለያ ያንተን ንብረት ሌላ ሰው መድረስ እንደማይችል ርግጠኛ እንድትሆን
ያደርገሃል።
በተመሳሳይ ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለሚገኘው መረጃህ አስጊ የሆኑ አደጋዎችን ለመቀነስ የተለያዩ
የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የኮምፒውተርህን
ስርዓት ክወና ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ለመጠበቅ የሚያግዙህን አንዳንድ መሰረታዊ
ምርጥ ተሞክሮዎች ያስተዋውቅሃል።
የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች
ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦
• ኮምፒውተርህን የመጠበቂያ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ፤
• የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግንኙነቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎችን
ለይተህ ማወቅ እና
• የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክት ልውውጥ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን
ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።
ክፍለ ትምህርት 2
ኮምፒውተርን መጠበቅ
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
13
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች
አንድ ሚስጥራዊ ፕሮጅክት ኮምፒውተርህ ላይ አስቀምጠሃል ብለህ አስብ። ይህን ሪፖርት ለማዘጋጀት ለሳምንታት ስሰራ ቆይተሃል እናም አሁን
የፕሮጅክትህን ሪፖርት ለሱፐርቫይዘርህ ማሳየት ፈልገሃል። የዚህ ሪፖርት አንድ ቅጂ ብቻ በኮምፒውተርህ ላይ ይገኛል። ይህ ሪፖርት እንዳይበላሽ
ወይም እንዳይሰረዝ ደህንነቱን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ሌላ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ የሆነ ሰው አንተ በማትኖርበት ጊዜ ኮምፒውተርህን
ይጠቀም ነበርና የፕሮጀክቱን ሪፖርት ከኮምፒውተርህ ላይ አጠፋው። እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎችን ለማስቀረት በኮምፒውተርህ ላይ የሚገኝን መረጃ
ደህንነት ለመጠበቅ ርምጃዎችን መውሰድ ይኖርብሃል። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ በኮምፒውተርህ የሚገኘውን ስርዓተ ክወና እና መረጃ ለመጠበቅ
ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያብራራል።
መመሪያ መግለጫ
የተጠቃሚ መለያ
ተግብር
የስርዓተ ክወናህን እና የመረጃህን አደጋ ለመቀነስ ውጤታማ የሆነው
መንገድ ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች ኮምፒውተርህን እንዳይደርሱ
መጠበቅ ነው። ይህን ለማሳካት አንደኛው ዘዴ ኮምፒውተርህን
ለመድረስ ለተፈቀደላቸው ሰዎች መለያዎችን ማቀናበር ነው። በዚህ
መሰረትም እያንዳንዱ ተጠቃሚ በየደረጃው ተገቢ የሆነ የመዳረስ
ፍቃድ ያገኛል።
ለምሳሌ በWindows 7 ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወይም ሌላ
ተጠቃሚ መለያዎችን ማቀናበር ትችላለህ። ለራስህ አብላጫውን
መብት መወሰን እንዲሁም ልጆች ካሉህ የልጆች መለያን አቅም
መገደብ ትችላለህ።
የተጠቃሚ ስም እና
የይለፍ ቃል አዋቅር
የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በማቀናበር የደህንነት ጥበቃህን
ከፍ ማድረግ እና ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎችን ኮምፒውተርህን
እንዳይደርሱ ማገድ ትችላለህ። በብዙዎቹ መስሪያቤቶች ውስጥ
እያንዳንዱ ሰራተኛ የተለየ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አለው።
ሰራተኞቹ ኮምፒውተሮቻቸውን ለመድረስ ትክክል የሆነ የተጠቃሚ
ስም እና የይለፍ ቃል ማስገባት ይኖርባቸዋል። በWindows 7
የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ማቀናበር ትችላለህ።
የይለፍ ቃልን
በሚስጥር መጠበቅ
የይለፍ ቃልህ ለኮምፒውተርህ እንደ ቁልፍ ያገለግላል። የይለፍ
ቃልህን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ኮምፒውተርህን ሊደረስ እና
መረጃህን ሊያበላሽብህ ስለሚችል የይለፍ ቃልህን በሚስጥር መያዝ
ይኖርብሃል።
የይለፍ ቃልህን በምታስገባበት ጊዜ ማንም እንዳያይ ጥንቃቄ
አድርግ። የይለፍ ቃልህን ለሌሎች አታጋራ። የይለፍ ቃልህን ጽፈህ
በኮምፒውተርህ ወይም በጠረጴዛህ ላይ አትተው። የይለፍ ቃልህ
ተጋልጧል ብለህ ካሰብህ ሌሎች ያላግባብ ሳይጠቀሙበት በፊት
በፍጥነት ቀይር።
ኮምፒውተርህን ቆልፍ ማንም ሰው በሌለበት ሁኔታ ኮምፒውተርህን እንደበራ ትተህ
በምትሄድበት ጊዜ ሌላ ሰው የኮምፒውተርህን ሶፍትዌር ወይም
መረጃ ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህንን በማትኖርበት ወቅት
ኮምፒውተርህን ለጊዜው በመቆለፍ መከላከል ትችላለህ።
ኮምፒውተር በሚቆለፍበት ጊዜ ወዲያውኑ የገጽ ማሳያውን ይዘቶች
ይደብቅና በትክክለኛው የተጠቃሚ ስም እና የይልፍ ቃል
እስኪከፈት ድረስ ምንም ስራ እንዲከናወን አይፈቅድም።
ኮምፒውተርን የመቆለፍ አካሄዶች እንደምትጠቀመው ስርዓተ ክወና
ይወሰናል። ለምሳሌ በWindows 7 CTRL+ALT+DEL በመጫን
እና ይህን ኮምፒውተር ቆልፍ የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ በማድረግ
ኮምፒውተሩን መቆለፍ ትችላለህ። ይህ ኮምፒውተርን የሚቆልፍ
ባህሪ በሁሉም ስርዓተ ክወናዎች ላይ እንደሌላ አስታውስ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
14
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የመጠበቂያ ሶፍትዌር
ጫን እንዲሁም
አዘምን
ኮምፒውተርህን እንደ ቫይረሶች እና ስፓይዌር ባሉ ስጋቶች
እንዳይጠቃ ክትትል ማድረግ ይኖርብሃል። በአሁኑ ጊዜ በቫይረስ
የሚመጣ ጉዳት ትኩርት የሚያስፈልገው ነው። በጣም አስፈላጊ
የሆነ መረጃ ልታጣ ትችላለህ እንዲሁም የስርዓተ ክወናህን እና ሌላ
ሶፍትዌርን እንደገና መጫን ሊያስፈልግህ ይችላል። ፀረ ቫይረስ እና
ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በመጫን ኮምፒውተርህን ከቫይረሶች እና
ስፓይዌር መከላከል ትችላለህ። እነዚህ ጠባቂ የሶፍትዌር
ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ የሚገኝን ቫይረስ እና ስፓይዌር
ለማግኘት እና ለማስወገድ ያግዙሃል። አዲስ ቫይረስ እና ስፓይዌር
ኮምፒውተርህን እንዳያጠቃውም ይከላከላሉ።
ኬላ መጫንም ሌላው ጥሩ ተሞክሮ ነው። ይህም ወደ ኮምፒውተርህ
የሚደርሱትን አጣርቶ ያወጣል። ኬላ መጫን በመስመር ላይ
ተጠቃሚዎች የሚደረግን የመድረስ ሙከራን በመገደብም ከሰርጎ
ገቦች ይከላከላል።
በየጊዜው አዳዲስ ስጋቶች እየተፈጠሩ ስለሆነም የሶፍትዌር
ኩባንያዎች በኮምፒውተርህ ልትጭናቸው የምትቻላቸው ዝምኖችን
በየጊዜው ይፈጥራሉ። እነዚህ ዝምኖች በኮምፒውተርህ በተጫነው
ሶፍትዌር ወይም ስርዓተ ክወና ላይ ጭማሪዎችን በማድረግ
የኮምፒውተርህን በደህንነት ስጋቶች የመጋለጥ አቅም ይቀንሳል።
የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌርህ አዳዲስ ቫይረሶችን እንዲያገኝልህ በየጊዜው
ማዘመንህን አረጋግጥ።
Windows 7 ኮምፒውተርህን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል
Windows ኬላን አካቷል። ከዚህ በተጨማሪም ኮምፒውተርህን
ከብቅ-ባዮች እና ሌሎች የደህንነት ስጋቶች የሚከላከል Windows
መከታ የሚባል የፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም አካቷል።
ውሂብ መስጥር ውሂብን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል ሲባል ውሂብን
ወደማይነበብ ቅርጸት መቀየር ምስጠራ ተብሎ ይጠራል።
የተፈቀደለት ተጠቃሚ የተመሰጠረውን ውሂብ ወደሚነበብ እና
የሚጠቅም ቅርጸት ዳግም መመልስ ይችላል። ይህም ሚስጠር
መፍታት ይባላል። ዛሬ የተለያዩ የሶፍትዌር ምርቶች ውሂብን
የመመስጠሪያ ዘዴዎችን አካተዋል።
በWindows 7 ምስጠራ ፋይልን ለሚመሰጥረው ተጠቃሚ በግልጽ
የሚታይ ሲሆን ፣ ይህም ፋይሉን ከመጠቀም በፊት ምስጠራውን
መፍታት አይኖርብህም ማለት ነው። ሁሌ እንደምታደርገው ፋይሉን
መክፈት እና መለወጥ ትችላለህ።
ምትክ ውሂብ ያዝ አስፈላጊ የሆኑ ፋይሎችን ቅጂ በሲዲ ፣ ዲቪዲ ወይም ፍሎፒ ዲስክ
የመሳሰሉ የማከማቻ መሳሪያዎች ላይ በማስቀመጥ ፋይሎችህን
ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት ልትታደጋቸው ትችላለህ። ይህ ሂደት
ምትክ ውሂብ መያዝ ይባላል። የተያዙትን ምትኮችም አስተማማኝ
በሆነ ቦታ በማስቀመጥ ዋናው ፋይል በሚበላሽበት ወይም
በሚጠፋት ጊዜ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
15
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች
ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ማገናኘት ከአለም መረጃ እና መዝናኛ ጋር ያስተዋውቀዋል። ነገር ግን ኮምፒውተርህን ለመስመር ላይ አደጋዎች
የተጋለጠ እንዲሆንም ያደርገዋል። ለምሳሌ ቫይረሶች ከተጠቃ ኮምፒውተር ወደ አንተ ኮምፒውተር በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ። ኮምፒውተርህ
በእነዚህ የመስመር ላይ አደጋዎች የሚደርስበትን ጉዳት ለመቀነስ እንደ ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር ፣ ውሂብ መመስጠር እና የፀረ ቫይረስ
ሶፍትዌር መጠቀም ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን አጣምረህ መጠቀም ትችላለህ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ
ግንኙነቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች ያብራራል።
ርምጃ መግለጫ
ጠንካራ የይለፍ ቃል
ተጠቀም
ጠንካራ የይለፍ ቃል ማለት በቀላሉ ሊገመት የማይችል ውስብስብ የይለፍ
ቃል ነው። የይለፍ ቃል የዓብይ እና ንዑስ ሆሄያትን ፣ ቁጥሮችን እና እንደ
ስርዓተ ነጥቦች እና የቁጥር ምልክት ያሉ ልዩ ቁንፊዎችን አጣምሮ የያዘ
እንዲሁም ሙሉ ቃላትን ወይም ስሞችን ያላካተት ሊሆን ይገባል።
ጠንካራ የይለፍ ቃል የደህንነት እና ክብረ ገመና ጥቃቶች ዋንኛ መከላከያህ
ነው። ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ጠንካራ የይለፍ ቃላት ሊፈጠርላቸው ይገባል።
• ያልተገናኙ ኮምፒውተሮችን ለመዳረስ
• አውታረመረቦችን ለመዳረስ
• የግል እና የገንዘብ ሁኔታ ዝርዝር የመሰለ አንገብጋቢ መረጃ
ያላቸውን ድረ ጣቢያዎች ለመዳረስ
• ማንኛውም አስፋለጊ የሆነን መረጃ ለመዳረስ
• ኮምፒውተር ላይ ለተቀመጠ የግል መረጃ
ከሰርጎ ገቦች እና ስፓይዌር
መከላከል
በይንመረብን በምትዳስስበት ወቅት በኮምፒውተርህ ላይ የተጫነ ፕሮግራም
በሌላ አገር ላይ ለሚገኝ ሰርጎ ገብ የግል መረጃህን አሳልፎ ሊሰጥብህ
ይችላል። እንደዚህ ያሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች የስፓይዌር ምሳሌዎች
ናቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ያለንታ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ ይጫኑና
ምስጢራው የሆነ መረጃን ከኮምፒውተርህ ወደ ሰርጎ ገቦች በድብቅ
ያስተላልፋሉ። አንዳንድ ጊዜ ቀጣሪዎች ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸው
ኮምፒውተሮች ላይ ሆን ብለው ስፓይዌር በመጫን የሰራተኞቻቸውን
የኮምፒውተር ስራ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይጠቀሙበታል።
Windows 7 በኮምፒውተርህ ላይ ስፓይዌር በድብቅ እንዳይጫን
የሚከለክል Windows መከታ የሚባል አብሮ የተሰራ ፀረስፓይዌር
ፕሮግራም አካቶ ይዟል።
ለመስመር ላይ ደህንነት ጥበቃ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ (ISP)
ደጋፊን ተጠቀም። ይህ ድጋፍ ፀረቫይረስ እና ፀረስፓይዌር ሶፍትዌር ሊሆን
ይችላል። አንዳንድ ISPs የኬላ መከላከያ ፣ የኢ-ሜይል ቫይረስ መለያ እና
የአይፈለጌ መልዕክት መከላከያን ያቀርባሉ።
የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው
አጽዳ
በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ የምትጎበኛቸው የድር ጣቢያዎች እና ድረ-
ገፆች በአሳሽህ ታሪክ ላይ ይቀመጣሉ። እንዲሁም በይነመረብን
በምትዳስስበት ጊዜ በርካታ ፋይሎች በኮምፒውተርህ ጊዜያዊ ማህደረ
ትውስታ ላይ ይቀመጣሉ። ይህ ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ መሸጎጫ ማህደረ
ትውስታ ይባላል። በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ላይ የሚከማቹት ፋይሎች
ስለ ጎበኛሃቸው ድረ-ገፆች መረጃ ይመዘግባሉ።
ነገር ግን የተወሰኑት የእነዚህ ጊዜያዊ የበይነመረብ ፋይሎች በሰርጎ ገቦች
ሊገኙ የሚችሉ እንደ የተጠቃሚ ስምህ እና የይለፍ ቃልህ ያለ የአንተ የግል
መረጃን ሊይዙ ይችላሉ። ሰርጎ ገቦች የግል መረጃህን እንዳያገኙ ለመከላከል
በአሳሽ ታሪክ እና በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ውስጥ የሚገኙ ይዘቶችን
በየጊዜው አጥፋ።
የድር ጣቢያዎችን በምትጎበኝበት ጊዜ ስምህን የሚያሳይ ማስታወቂያ
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
16
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ልትመለከት ትችላለህ። ይህ የሚሆነውም ኩኪዎችን በመጠቀም ነው።
ኩኪዎች ቀድሞ የጎበኘሃቸው የድር ጣቢያዎች አማራጮችህን ለመለየት እና
ለመከታተል ሲሉ በኮምፒውተርህ ላይ የሚፈጥሯቸው ትናንሽ ፋይሎች
ናቸው። ዋና ዓላማቸው የድር ጣቢያውን በምትጎበኝበት ጊዜ የበለጠ ላንተ
የሚሆን መረጃ ለማቅረብ ነው። ነገር ግን ኩኪዎች የግል መረጃህን
ስለሚይዙ ለኮምፒውተርህ ደህንነት ስጋት ሊሆኑም ይችላሉ። ለምሳሌ
የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ ኩኪዎች የክሬዲት ካርድህን
ዝርዝር መረጃ ሊይዙብህ ይችላሉ። በእነዚህ ምክንያቶች የግል መረጃህ
ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል በየጊዜው ኩኪዎችን ማጥፋት
ጥሩ ልምድ ነው።
የግል መረጃን ከማጋራት
ተቆጠብ
አንዳንድ የድር ጣቢያዎች እንደ ስም ፣ ፆታ እና እድሜ ያለ የግል መረጃን
በቅፆች ላይ እንድትሞላ ይጠይቃሉ። በኢ-ኮሜርስ ጣቢያዎች ደግሞ የባንክ
መለያ ዝርዝሮችን ወይም የክሬዲት ካርድ ቁጥርህን ልትጠየቅ ትችላለህ።
ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ይህን መረጃ ሊያገኙት እና ላልተገባ ዓላማ
ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አስታውስ። አንዳንድ ኩባንያዎች ያልተፈለጉ
የንግድ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን ወደ አንተ ለመላክም ይህን መረጃ
ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ስለዚህ በድር ጣቢያ ላይ ማንኛውንም የግል መረጃ
ከማጋራትህ በፊት የድር ጣቢያው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና
መረጃውን መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አረጋግጥ።
የመስመር ላይ ግብይቶችን
ደህንነታቸው በተጠበቀ
ጣቢያዎች ላይ ብቻ
አድርግ
የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ እንደ ባንከ መለያ ቁጥር እና
ክሪዲት ካርድ ዝርዝሮች ያለ ወሳኝ መረጃን መስጠት ያስፈልግሃል።
ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችን የምታካሂደው አስተማማኝ በሆኑ የድር
ጣቢያዎች ላይ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። አንድ የድር ጣቢያ
አስተማማኝ ነው የሚባለው የስሙ ቅድመ ቅጥያ https ከሆነ ነው። ቅድመ
ቅጥያው የድር ጣቢያው Secure Sockets Layer (SSL) ፕሮቶኮልን
እንደሚተገብር ያመለክታል። SSL የሚተላለፈውን መረጃ በመመስጠር
አስተማማኝ የመረጃ ግንኙነትን የሚያረጋግጥ የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ
ፕሮቶኮል ነው። SSL ፕሮቶኮል የድር ጣቢያው እውነተኛ መሆኑን እና
ለጣቢያው የምትሰጠው መረጃ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደማይውል
ያረጋግጣል።
አስተማማኝ የሆነ የድር ጣቢያ ስታስገባ አብዛኞቹ የድር አሳሾች የስገባሃው
የድር ጣቢያ አስተማማኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ መልዕክት ያሳዩሃል።
በአድራሻ አሞሌ ውስጥ የሚታይ የተቆለፈ ትንሽ የቁልፍ አዶ አስተማማኝ
የሆነ የድር ጣቢያን ለመለየት ያግዝሃል። በተጨማሪም ማንኛውንም
የመስመር ላይ ግብይት ከማካሄድህ በፊት የድር ጣቢያውን የደህንነት
ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መመልከት ትችላለህ።
Windows የደህንነት
ጥበቃ ማዕከልን
በመጠቀም የደህንነት
ጥበቃ ክፍሎችን አዋቅር
Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በWindows 7 የሚገኝ ባህሪ ሲሆን
አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን ሁኔታ ለመመርመር እና
በኮምፒውተርህ የተጫነውን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ለመከታተል የሚረዳ
ምቹ የሆነ መገልገያ ይሰጣል። የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ከመቆጣጠሪያ
ፓኔል መክፈት ትችላለህ። የደህንነት ጥበቃ ማዕከል አራት ክፍሎች አሉት
እነርሱም፦
• ኬላ፦ በWindows 7 ውስጥ Windows ኬላ በራሱ የሚሰራ
ነው። ኬላ እንደ ቨይረሶች እና ተውሳኮች ያሉ ጎጂ ይዘቶች ወደ
ኮምፒውተርህ እንዳይገቡ ለመከላከል ይረዳል።
• ራስ-ሰር ማዘመኛ፦ ይህ ባህሪ ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዙ
አስፈላጊ ዝምኖችን በMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ ላይ
መኖራቸውን ይፈትሻል። ይህን ባህሪ ማንቃት ኮምፒውተርህ
የዘመነ እና በበይነመረብ ላይ ከሚገኙ አዳዲስ የደህንነት ስጋቶች
የተጠበቀ ሆኖ እንደሚቆይ ያረጋግጣል።
• የማልዌር መከላከያ፦ ስፓይዌር እና ሌላ የማይፈለግ ሶፍትዌር
ያንተን ፈቃድ በአግባቡ ሳይጠይቅ በኮምፒውተርህ ላይ ራሱን
ሊጭን ይችላል። Windows መከታ ከበይነመረብ ጋር
በምትገናኝበት ጊዜ ወቅታዊ የመከላከል ስራ ይሰራል።
• ሌሎች የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች፦ ሌሎች የደህንነት ጥበቃ
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
17
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ቅንጅቶች የበይነመረብ ቅንጅቶችን እና የተጠቃሚ መለያ
መቆጣጠሪያ ቅንጅቶችን ያጠቃልላል። የበይነመረብ
አማራጮችን በመጠቀም የደህንነት ጥበቃ ደረጃውን መካከለኛ ፣
መካከለኛ-ከፍተኛ ወይም ከፍተኛ ማድረግ ትችላለህ። Internet
Explorer 8 ከቀድሞዎቹ ስሪቶች የበለጠ ከፍተኛ የሆነ
የደህንነት ጥበቃ ደረጃዎች አሉት። የተጠቃሚ መለያ
መቆጣጠሪያ በኮምፒውተርህ ላይ ለውጥ ከመደረጉ በፊት
የይለፍ ቃል በመጠየቅ ያልተፈቀዱ ለውጦችን ይከላከላል።
ተዋናይ ይዘትን አሰናክል ተዋናይ ይዘት በይነመረብ በምታስስበት ጊዜ በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ
ትናንሽ ፕሮግራሞችን ያመለክታል። የእነዚህ ፕሮግራሞች ዋና አገልግሎት
በቪዲዮች እና በሰሪ አሞሌዎች የታገዘ የበይነመረብ ተሞክሮ ግንኙነት
ለአንተ ማቅረብ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች እነዚህን ፕሮግራሞች
በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ለማበላሸት ወይም ያለአንተ ፈቃድ ጎጂ
የሆነ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። እንደዚህ አይነት
ፕሮግራሞች እንዳይጫኑ ለመከላከል ተዋናይ ይዘትን ማሰናክል ትችላለህ።
ርዕስ፦ የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
ኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ለንግድ ስራ እና ለግል ግንኙነት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ፣ የመስመር ላይ አዳኞች
እንዲሁም ተውሳኮችን እና ቫይረሶችን የሚፈጥሩ ሰዎች ኢ-ሜይልን እና ፈጣን መልዕክትን ለጥቃት ዓለማ ይጠቀሙባቸዋል። ለምሳሌ እነዚህ ሰዎች
ጎጂ ሶፍትዌር አያይዘው ኢ-ሜይል ሊልኩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች አስፈላጊ መረጃን ለመጠየቅ ወይም በተሳሳቱ አቅርቦቶች አንተን ለማማለል ኢ-
ሜይልን ሊጠቀሙም ይችላሉ። ለዚህም ነው የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ደህንነትን ለማረጋገጥ አንዳንድ ርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ
የሆነው።
የኢ-ሜይል ደህንነትን ለማረጋገጥ አባሪ ያለውን ኢ-ሜይል ከመክፈት ተቆጠብ ፣ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ አትስጥ ፣ ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ
መልዕክት ምላሽ አትስጥ እንዲሁም ራስህን ከአስጋሪዎች ጠብቅ። የፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለማረጋገጥ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት
አድርግ እንዲሁም በፈጣን መልዕክት የሚደርሱ አባሪዎችን አትክፈት። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት
ለማረጋገጥ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ያብራራል።
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።
አብሪዎች የያዙ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ አድርግ
ፋይሎችን ለጓደኞችህ ለማጋራት የኢሜይል አባሪዎችን ልትልክ ትችላለህ። በኢ-ሜይል መልዕክትህ ውስጥ እንደአባሪ ሆኖ የፎቶ ወይም
የሙዚቃ ፋይል ሊደርስህ ይችላል። ነገር ግን አባሪ የያዘ መልዕክትን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፍልጋሃል ምክንያቱም ይህ በብዛት
የተለመደው ቫይረሶችን የማሰራጫ መንገድ ነውና።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
18
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።
ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ መልዕክት ምላሽ አትስጥ
ምርቶቻቸውን ወይም አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁ ግለሰቦችን እና ኩባንያዎችን ጨምሮ ካልታወቁ ላኪዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው
ያልተፈለጉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ልትቀበል ትችላለህ። እነዚህ መልዕክቶች ያንተን የግል መረጃ እንድትሞላ የሚፈልጉ የመስመር ላይ
መጠይቆች ሊሆኑም ይችላሉ። እነዚህ ሳይፈለጉ የሚመጡ መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት በመባልም ይታወቃሉ።
ብዙ ጊዜ አይፈለጌ መልዕክት ለኮምፒውተርህ ጎጂ የሆነ ይዘትን ሊያካትት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም አይፈለጌ መልዕክትን ብዙ ጊዜ
የማንነት መለያዎችን ለመስረቅ ስለሚጠቀሙበት ለእንደዚህ አይነት መልዕክቶች ምላሽ በምትሰጥበት ወቅት ወሳኝ የሆነ መረጃን ሳታውቀው
ልታጋራ ትችላለህ። ስለዚህ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ ከመስጠት መቆጠብ ይኖርብሃል። አይፈለጌ መልዕክት በደረሰህ ጊዜም ወዲያው
ማጥፋት ይኖርብሃል። እንደ Windows መልዕክት ያለ የኢ-ሜይል ፕሮግራም የአይፈለጌ መልዕክትን ለማዛወር እና በቀጣይ ለማጥፋት ይረዳ
ዘንድ የአይፈለጌ መልዕክት አቃፊ አካቷል።
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።
ራስህን ከአስጋሪ ጠብቅ
ማስገር ከኮምፒውተር ተጠቃሚዎች የግል መረጃን በማውጣት ጎጂ ለሆኑ ዓላማዎች ለመጠቀም የሚደረግ የተለመደ ተግባር ነው። ለምሳሌ
የሆነ ሰው ከባንክ ወይም ከሌላ የሚታመን ድርጅት የመጣ መልዕክት በማስመሰል የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለአንተ ላከልህ ከዚያም እንደ
ክሬዲት ካርድ ወይም የይለፍ ቃል ያለ ወሳኝ መረጃን ጠየቅህ። በቀጣይ ይህ መረጃ ስለሚሸጥ ወይም ጥቅም ላይ ስለሚውል ለገንዘብ ኪሳራ
ይዳርግሃል። ስለዚህ ለእንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች የግል መረጃህን የያዘ ምላሽ ከመስጠትህ በፊት ህጋዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ
ይገባሃል።
የተለያዩ የአስጋሪ ድር ጣቢያዎች እንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ይጠቀማሉ። Internet Explorer 8 በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ
ከጀርባ ሆኖ የሚሰራ እና አስጋር ድር ጣቢያዎችን ለይቶ የሚያገኝ Microsoft አስጋሪ ማጣሪያ የሚባል ባህሪን አካቷል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
19
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።
ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ
የውይይት ተግባርህ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ የተወሰነ መሆን አለበት። ከአዳዲስ እና ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር ግንኑነትን ማዳበር እንደ
የመስመር ላይ አዳኞች እና አጭበርባሪዎች ላሉ ስጋቶች እንድትጋለጥ ያደርግል።
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።
የፈጣን መልዕክት አባሪዎችን ከመክፈት ተቆጠብ
የፈጣን መልዕክት ዋንኛ ጎጂ የሆኑ አባሪዎችን ማስተላለፊያ መንገድ ነው። ላኪውን በሚገባ ካላወቅህ በስተቀር በፈጣን መልዕክት የደረሰህን
ማንኛውም አባሪ ከመክፈት መቆጠብ አለብህ። የፈጣን መልዕክት አባሪ ኮምፒውተርህን ሊጎዳ የሚችል ቫይረስ ወይም ስፓይዌር ሊይዝ
ይችላል።
ርዕስ፦ ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
የሚከተሉትን ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን
ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው።
ዓረፍተ ነገር
1 የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው ማጽዳት
2 ምትክ ውሂብ መያዝ
3 የግል መረጃን ከማጋራት መቆጠብ
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
20
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
4 ጠባቂ ሶፍትዌር መጫን እና ማዘመን
5 የተጠቃሚ ማንነት መለያ መተግበር
6 ከሰርጎ ገብ እና ስፓይዌር መከላከል
7 የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ
8 ተዋናይ ይዘትን ማሰናከል
ምርጫ 1 ምርጫ 2
የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ
ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ ኮምፒውተርን መጠበቅ
ጥያቄ 1
በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም
ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ስርዓተ ክወናህን ማዘመን።
የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር።
ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን።
የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ።
ጥያቄ 2
በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ
ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ኩኪ
ቫይረስ
የተዋናይ ይዘት ፋይሎች
ተውሳክ
ጥያቄ 3
ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት።
ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ።
ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት።
በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ።
ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
21
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
መልሶች
ምርጫ 1 ምርጫ 2
የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ
8, 6, 3, 1 7, 5, 4, 2
መልስ 1
በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም
ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ስርዓተ ክወናህን ማዘመን።
የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር።
ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን።
የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ።
መልስ 2
በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ
ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ኩኪ
ቫይረስ
የተዋናይ ይዘት ፋይሎች
ተውሳክ
መልስ 3
ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ?
ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።
ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት።
ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ።
ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት።
በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
22
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች
ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
የመስመር ላይ አዳኞች
ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች
ግለ ሙከራ
የትምህርት ክፍሉ መግቢያ
ኮምፒውተሮች በትምህርት ቤቶች ፣ ኮሌጆች እና መስሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በቤቶች ውስጥም በብዛት
ያገለግላሉ። ኮምፒውተሮችን ለተለያዩ ዓላማዎች ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። ለምሳሌ የቤት ውስጥ
ወጪዎችን ለመያዝ ፣ ከቤተሰቦችህና ጓደኞችህ ጋር የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለመመለዋወጥ ፣
በይነመረብን ለመዳሰስ እንዲሁም ጌሞችን ለመጫወት እና ሙዚቃ ለማደመጥ ልትጠቀምባቸው
ትችላለህ። እያንዳንዱ የቤተሰብህ አባልም የኮምፒውተሩን የተወሰነ ጥቅም ሊያገኝ ይችላል።
ኮምፒውተሮችን በቤት እና በስራ ቦታ የመጠቀም ሁኔታ ከመጨመሩ አንፃር አንተ እና የአንተ ቤተሰቦች
ኮምፒውተሮችን እና በይነመረብን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ስለሚያጋጥሙ የተለያዩ ስጋቶች መረዳት
አስፈላጊ ነው። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ ኮምፒውተርህን ከእነዚህ ስጋቶች ለመጠበቅ ስለሚረዱ
የተለያዩ ርምጃዎች ትማራለህ።
የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች
ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦
• ክብረ ገመናህን ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ለይተህ ማወቅ
• የመስመር ላይ አዳኞች እንዴት እንደሚሰሩ ማብራራት እና
• ቤተሰቦችህን ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ የሚረዱ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ
ትችላለህ።
ክፍለ ትምህርት 3
ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
23
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች
እያደገ በመጣው የኮምፒውተሮች እና የበይነመረብ ተፈላጊነት የክብረ ገመና ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት በርካታ ሁኔታዎች አሉ። አንተ እና
የአንተ ቤተሰቦች እነዚህን የክብረ ገመና ስጋቶች መከላከል ይጠበቅባችኋል። ራስህን እና ቤተሰቦችህን ከክብረ ገመና ጥቃት ለመከላከል የሚከተሉትን
ቀላል ርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ።
ማንነትህን ደብቅ
የግል መረጃህን ከምታውቃቸው ሰዎች ውጪ ለማንም ከማጋራት ተቆጠብ። ይህ ክበረ ገመናን ለመጠበቅ ምርጥ ህግ ነው። የኢ-ሜይል
መልዕክቶችን በምትለዋወጥበት ወይም የፈጣን መልዕክትን በመጠቀም በምትወያይበት ጊዜ የአንተን ወይም የምታውቃቸውን ሰዎች የግል መረጃ
ዝርዝሮች አለማሳወቅህን አረጋግጥ። እንዲሁም ኮምፒውተርህን እና የኢ-ሜይል ግንኙነቶችን ለመዳረስ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን ተጠቀም።
የኮምፒውተርህን እና የአስፈላጊ መረጃህን ምትክ በየጊዜው ያዝ
በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሁሉንም አስፈላጊ እና ወሳኝ መረጃ ምትክ ቅጂ መያዝ ጥሩ ልምድ ነው። አስፈላጊ መረጃ የሚባለው ሰነዶች ፣ የውሂ
ጎታዎች ወይም የዕውቂያ መረጃ ሊሆን ይችላል። የመረጃህን ምትክ ለመያዝ እንደ ሰዲ እና ሃርድ ዲስክ ያሉ የተለያዩ የማከማቻ መሳሪያዎች
መጠቀም ትችላለህ። በኮምፒውተርህ ላይ ያለን መረጃ ምትክ በየጊዜው የምትይዝ ከሆነ የመጀመሪያው መረጃ በአጋጣሚ በሚበላሽበት ወይም
በሚጠፋበት ጊዜ መረጃውን እንደገና ልታገኘው ትችላለህ። እንዲሁም የተያዘውን ምትክ መረጃ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እና የይለፍ
ቃላትን እና መስጠራን በመጠቀም ተገኝነቱን መገደብ ይመከራል።
የስርዓትህን ወቅታዊ ደህንነት በየጊዜው ፈትሽ
የኮምፒውተርህን ወቅታዊ የደህንነት ደረጃ በየጊዜው ፈትሽ። የዘመኑ ስርዓተ ክወናዎች የተለያዩ የደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋቶችን ለመከላከል
የኮምፒውተርህን አቅም ለመከታተል የሚረዱ አብረዋቸው የተሰሩ ባህሪያት አሏቸው።ለምሳሌ Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል የኬላ ቅንጅቶችን
ለማዋቀር ፣ የሶፍትዌር ማዘመኛ መረሃግብሮችን ለማቀናበር እና በኮምፒውተርህ የተጫነን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ውጤታማነት ለመፈተሽ የሚረዳህ
በWindows 7 ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው።
የቫይረስ ቅኝቶችን በየዕለቱ አካሂድ
በይነመረብ በምትጠቀምበት እያንዳንዱ ቀን ሁሉ ኮምፒውተርህ በቫይረሶች ሊጠቃ የሚችልበት ዕድል አለ። ስለዚህ በኮምፒውተርህ ላይ የቫይረስ
ቅኝት በየቀኑ ማካሄድ አስፈላጊ ነው። ኮምፒውተርህን ከአዳዲስ ቫይረሶች ለመከላከልም በኮምፒውተርህ ያለን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር እንደዘመነ
ማቆየት ይኖርብሃል።
ፀረ ስፓይዌር
ስፓይዌር ፕሮግራሞች ወደ ኮምፒውተርህ በድብቅ በመግባት የአንተን እና የቤተሰቦችህን ግላዊ መረጃ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። እነዚህን ጎጂ
ፕሮግራሞች ለመከላከል ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ተጠቀም ፤ እንዲሁም ሶፍትዌሩን በየጊዜው አዘምን።
የመስመር ላይ ግብይቶችን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ከሚታመኑ ሻጮች ጋር አድርግ
የመስመር ላይ ግብይትን በምታደርግበት ጊዜ እንደ ክሬዲት ካርድ ወይም የባንክ ሒሳብ መለያህን ዝርዝሮች ያለ የግል መረጃን ለድር ጣቢያው
መስጠት ያስፈልግሃል። ይህ መረጃ ለሌሎች የተጋለጠ ከሆነ ለገንዘብ መጭበርበር ሊዳረግ ይችላል። ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችህን
አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ብቻ ማድረግ ጠቃሚ ነው።
ጥቃትን ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው አሳውቅ
ብዙዎቹ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች ስነ-ምግባር የጎደለው ወይም ህገወጥ ተግባራት በደንበኞቻቸው ላይ እንዲደርሱ የማይፈቅዱ የተዘጋጁ
ውሎች እና ደንቦች አሏቸው። አንድ ሰው አይፈለጌ መልዕክትን በመላክ የመስመር ላይ ክብረ ገመናህን ለማጥቃት በሚሞክርበት ጊዜ ወይም
ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመጠቀም ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው ማሳወቅ ይኖርብሃል። ይህ የበይነመረብ
አገልግሎት አቅራቢው በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንዲወስድ ያስችልዋል።
የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ካልታወቁ/ስም የለሽ ላኪዎች አጣራ
ከማታውቃቸው ግለሰቦች በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢ-ሜይል መልዕክቶች ሊደርስህ ይችላል። እነደዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች አይፈለጌ
መልዕክት በመባል የሚታወቁ ሲሆን ብዙ ጊዜ ቫይረሶችን ወይም ስፓይዌር የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። የግል መረጃህን ለማግኘት የሚሞክሩ ሰርጎ
ገቦችም አይፈለጌ መልዕክት ሊልኩልህ ይችላሉ። ስለዚህ ከእነርሱ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በኢ-ሜይል ሶፍትዌር
ፕሮግራሞች አይፈለጌ መልዕክትን ለማገድ የሚረዱ ማጣሪያዎችን መፍጠር ትችላለህ። ለአይፈለጌ መልዕክት በጭራሽ ምላሽ መስጠት የለብህም።
ምክንያቱም የማይፈለጉ መልዕክቶች ቁጥር እንዲጨምር እና የግል መረጃን በድንገት እንድታጋራ ሊያደርግህ ይችላል።
ከተቻለ ወሳኝ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን መስጥር
ምስጠራን መጠቀም የኢ-ሜይል ግንኙነትን ምስጢራዊነት የሚያረጋግጥ ቀላል እና ውጤታማ መንገድ ነው። ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ
የመክተት ሂደት ሲሆን በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የተላከ ኢ-ሜይል እንዲያነብ ከታሰበው ሰው በስተቀር ለማንም የማይነበብ ሆኖ ይታያል። ብዙዎቹ
የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ፕሮግራሞች ለምሳሌ Windows መልዕክት ይህን የኢ-ሜይል ምስጠራ ባህሪ ያቀርባሉ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
24
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ርዕስ፦ የመስመር ላይ አዳኞች
በይነመረብ በሁሉም የአለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ታዋቂ የሆነ የመገናኛ ዘዴ ነው። ስለ ማንነቱ ወይም ስለ
ዓለማዎቹ በቅጡ ከማታወቀው ግለሰብ ጋር ልትግባባ እና ወዳጅነት ልትመሰርት ትችላለህ። በዚህ መሰሉ
የበይነመረብ ግንኙነት ሰዎች ወጣቶችን በማለል አግባብ ላልሆነ ወይም አደገኛ ግንኙነት ሊጠቀሙባቸው
ይችላሉ። በዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች የመስመር ላይ አዳኞች ይባላሉ።
የመስመር ላይ አዳኞች በጥቅሉ ልጆችን በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ዒላማቸው ያደርጋሉ። ልጆች የወጣትነት
ዕድሜያቸው ሲደርስ ቀስ በቀስ ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጪ እየሆኑ እና አዳዲስ ግንኙነቶችን እየፈለጉ
ይመጣሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከእነዚህ ልጆች ጋር የታማኝነት እና የወዳጅነት ግንኙነቶችን
ይመሰርታሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከገንዘብ ጋር ለተያያዘ ጥቅም አዋቂዎችንም ኢላማ ሊያደርጉ ይችላሉ።
የመስመር ላይ አዳኞች በውይይት ክፍሎች ፣ በፈጣን መልዕክት ፣ በኢ-ሜይል ወይም በውይይት መድረኮች
በመጠቀም ሰለባዎቻቸውን ያጠምዳሉ። ከእነዚህ መገልገያዎች ውስጥ የውይይት ክፍሎችን አዳኞች በብዛት
ይጠቀሙባቸዋል። የመስመር ላይ አዳኞች ብዙ ጊዜ የአንድ የውይይት ክፍል አባል እንደሆኑ በማስመሰል
የሐሰት ማንነት ያቀርባሉ። ለምሳሌ የውይይት ክፍሉ ለልጆች ብቻ የተዘጋጀ ከሆነ የመስመር ላይ አዳኙ
በውይይት ክፍሉ ውስጥ ለመሳተፍ ማንነቱን ልጅ አስመስሎ በቀላሉ ሊቀርብ ይችላል።
ርዕስ፦ ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች
አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ። እነዚህ አዳኞች ለገንዘብ ጥቅም ሲሉ ከአንተ ወይም ከቤተሰብህ
አባሎች ጋር ግንኑነት ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ። አዳኞች አንተ እና የቤተሰብህ አባሎችን አግባብ የሌለው ግንኙነት ውስጥ ለማስገባትም ሊሞክሩ
ይችላሉ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ ራስህን እና የቤተሰብህን አባሎች ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ ልትከተላቸው የምትችላቸውን የተወሰኑ
መመሪያዎች ይዘረዝራል።
መመሪያ መግለጫ
የአዳኝን ባህሪ የሚገልጹ
ምልክቶችን እወቅ
የመስመር ላይ አዳኞች አንዳንድ የሚጠበቁ ባህሪያት አሏቸው ፤ እነዚህም እነርሱን በቀላሉ ለመለየት ሊረዱህ
ይችላሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወደጅነትን መፍጠር ይወዳሉ። እንዲሁም ሁልጊዜ ወደ አላማቸው ያዘነበለ
ፍላጎታቸውን እና ስሜታቸውን ይገልፃሉ። አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር
የሚደረግ ግንኙነትን ለማቆም እንደዚህ ያለ ባህሪን ለይታችሁ ስለማወቃችሁ ማረጋገጥ ይጠበቅብሃል።
በመስመር ላይ ባሉ እንግዳ
ሰዎች ለሚመጡ አቅርቦቶች
ጥንቃቄ አድርግ
የመስመር ላይ አዳኞች በስጦታዎች ወይም በአጓጊ አቅርቦቶች ኢላማዎቻቸውን ያማልላሉ። ለእንደዚህ ዓይነት
ስጦታዎች ወይም አቅርቦቶች ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል። እንዲሁም በበይነመረብ የሚቀርቡ ስጦታዎችን
እንዲጠራጠሩ የቤተሰብህን አባላት አስተምር።
ስለ መስመር ላይ ደህንነት
ርምጃዎች ቤተሰብህን
አስተምር
የቤተሰብህ አባላት የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ከመሆን እንዲርቁ ስለ ትክክለኛው የውይይት ክፍል ባህሪ
አስተምራቸው። ገላጭ ባልሆኑ እና ነፃ በሆኑ የገጽ ስሞች እንዲጠቀሙ ንገራቸው። የገጽ ስሞች ትክክለኛ ስምን ፣
ዕድሜን ፣ ፆታን ወይም የመገኛ መረጃን የሚሰጡ መሆን የለባቸውም ምክንያቱም ይህ መረጃ አግባብ ለሌለው
ጥቅም ሊውል ይችላል።
አንዳንድ የድር ጣቢያዎች በሀሰተኛ አስተያየቶች መረጃን ለማውጣት ይሞክራሉ። ለእንዚህ የድር ጣቢያዎች
ምንም ዓይነት የግል መረጃ ካላንተ ፈቃድ እንዳያሳውቁ ለቤተሰብህ አባላት ንገራቸው። እንዲሁም እንደ ስም ፣
የአያት ስም ፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ያሉ የግል መረጃ ዝርዝሮችን በውይይት ክፍሎች እና የማስታወቂያ
ሰሌዳዎች ውስጥ አሳልፈው እንደማይሰጡ አረጋግጥ። የቤተሰብህ አባላት የተጠቀሚ ስማቸውን እና የይልፍ
ቃላቸውን ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ለማንም ማጋራት የለባቸውም።
ልጆች የድር ጣቢያዎችን
ሲጎበኙ መመሪያዎችን
ስጣቸው
እንደ ወላጅነት ወጣት ልጆች አግባብ ያልሆኑ ወይም ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር የሚያገናኙ የድር
ጣቢያዎችን እንዳይጎበኙ ከልክላቸው። ወላጆች ልጆች ማንኛውንም የድር ጣቢያ በሚጎበኙበት ወቅት
መመሪያዎችን ለልጆቻቸው እንዲሰጡ ይመከራል።
እንደ ወላጅ ልጆች የማይመች ዓይነት ወይም ደስ የማይል ይዘት ያለው የድር ጣቢያን እየጎበኙ ከሆነ እንዲተዉ
ወይም ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠጥ ያስፈልጋል። እንዲሁም ከመጠን ያለፈ የግል መረጃን የሚጠይቁ የድር
ጣቢያዎችን እንዳይጠቀሙ ልጆችህን አስተምራቸው።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
25
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ልጆች የሚጎበኟቸውን የድር
ጣቢያዎችን እወቅ
ወላጆች ልጆቻቸው የሚጎበኟቸውን የድር ጣቢያ ዓይነቶች በየጊዜው መፈተሸ ይኖርባቸዋል። ቀድሞ ተጎብኝተው
የነበሩ የድር ጣቢያዎችን የአሳሹን ታሪክ በማየት መከታተል ትችላለህ። ወይም የኮምፒውተርን የመስመር ላይ
እንቅስቃሴ ለመከታተል የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራችሞችን መጠቀም ትችላለህ።
አግባብነት የሌላቸውን የድር
ጣቢያዎች ከመዳረስ አግድ
የአሳሽህን የይዘት አማካሪ ባህሪ እንዲሰራ በማድረግ የቤተሰብህ አባላት ሊጎበኟቸው የሚችሉትን የድር ጣቢያዎች
መቆጣጠር ትችላለህ። ይህን ባህሪ በመጠቀም ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን የድር ጣቢያዎች ልጆች እንዳይጎበኙ
ማገድ ትችላለህ። የድር ጣቢያዎችን ለይቶ ለማገድ የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራሞችን መጫንም ትችላለህ።
የውይይት እንቅስቃሴዎችን
ተቆጣጠር
በልዩ ሁኔታ የተሰራ ሶፍትዌር የውይይት እንቅስቃሴዎችን ሊቆጣጠር እና በኮምፒውተርህ ላይ አግባብነት
የሌለውን የመረጃ ልውውጥ ሊያመለክት ይችላል። ይህን ሶፍትዌር በመጫን የልጆችህን የውይይት
እንቅስቃሴዎች መከታተል ትችላለህ።
ርዕስ፦ ግለ ሙከራ
እያንዳንዱን ጥንድ ዓረፍተ ነገር እውነት እና ሐሰት የሆኑ ዓረፍተ ነገሮችን ይዟል። እውነት የሆነውን ዓረፍተ ነገር በቀኝ በኩል በሚገኘውና እውነት
በሚለው አምድ ስር ምልክት በማድረግ አመልክት።
ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት
1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል።
2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም።
3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ።
4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም።
5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።
6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።
7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል።
8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም።
9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።
10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።
11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም።
12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ።
13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል።
14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም።
15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም።
16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ።
17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም።
18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል።
ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
26
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት
1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል።
2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም።
3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ።
4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም።
5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።
6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።
7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል።
8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም።
9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።
10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።
11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም።
12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ።
13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል።
14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም።
15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም።
16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ።
17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም።
18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል።
ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
27
© 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች
የኮምፒውተር ደህንነት ቅንጅቶችን ማወቀር
ኮምፒውተርን እንደዘመነ ማቆየት
ግለ ሙከራ
የትምህርት ክፍሉ መግቢያ
ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ስታገናኝ የኮምፒውተርህ ሶፍትዌር እና መረጃ በቀሪው አለም መገኘት
የሚችሉ ይሆናሉ። ከበይነመረብ መገናኘት የኮምፒውተርህን በቫይረሶች ፣ ስፓይዌር እና ሰርጎ ገቦች
የመጠቃት አቅም ከፍ ያደርገዋል። ነገር ግን በኮምፒውተርህ ላይ ያሉትን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች
በማዋቀር እና ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ሶፍትዌርን እንደዘመነ በማቆየት እንዚህን የደህንነት ስጋቶች
መቀነስ ትችላለህ።
በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ በስርዓተ ክወናህ ያሉትን የደህንነት ቅንጅቶች በማዋቀር የኮምፒውተርህን
ደህንነት እንዴት ከፍ እንደምታደርግ ትማራለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌርን
በራስ ሰር ለማዘመን ኮምፒውተርህን እንዴት እንደምታዋቅርም ያብራራል።
የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች
ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦
• በኮምፒውተርህ ያሉ የተለያዩ የደህንነት ጥበቃ ቅንጀቶችን ማብራራት እና
• ኮምፒውተርህ እንደዘመነ ለማቆየት ያሉትን አማራጮች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።
ክፍለ ትምህርት 4
ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security
ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

More Related Content

Featured

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by HubspotMarius Sescu
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTExpeed Software
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsPixeldarts
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthThinkNow
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfmarketingartwork
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024Neil Kimberley
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)contently
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024Albert Qian
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsKurio // The Social Media Age(ncy)
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Search Engine Journal
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summarySpeakerHub
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Tessa Mero
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentLily Ray
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best PracticesVit Horky
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementMindGenius
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...RachelPearson36
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

  • 1. ለህትመት የተዘጋጀ ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና 2698BE የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
  • 2. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 2 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ማውጫ የስልጠናው አጭር መግለጫ የስልጠናው መረጃ ሞዱል 1፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ ኮምፒውተርን መጠበቅ ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት የሞዱሉ ማጠቃላያ መፍትሔ ቃላት የሞዱሉ መረጃ ይህ ስልጠና ስለ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና አጭር መግለጫ ይሰጣሃል። ለኮምፒውተርህ ስለሚጎዱ የስጋት ዓይነቶች እና ከእነዚህን ስጋቶች እንዴት ኮምፒውተርህን መጠበቅ እንደምትችል ትማራለህ። የመረጃ ልውውጥ ህጋዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ኮምፒውተር እና በይነመረብ ለተጠቃሚዎች ስለሚያቀርቧቸው ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎችም ትማራለህ። የስልጠናው ማብራሪያ መግለጫ የተሳታፊዎች መግለጫ ይህ ስልጠና ኮምፒውተር የመጠቀም ችሎታን ለማዳበር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የታለመ ነው። ቀዳሚ አስፈላጊ ነገሮች ተማሪዎች ቢያንስ አንድ የሀገር ውስጥ ጋዜጣን ለማንበብ የሚያስችል መሰረታዊ የማንበብ እና የመረዳት ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል። ተማሪዎች የመጀመሪያውን መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የኮምፒውተር ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል። የስልጠናው ዓላማዎች ይህን ስልጠና ከጨረስክ በኋላ፦ • ለሃርድዌር እና መረጃ ስጋት ስለሆኑት ድንገተኛ አደጋዎች ፣ የመሳሪያ ብልሽት ፣ አካባቢ ፣ የሰዎች ስህተት እና ጎጂ ተግባሮች ማብራራት እና • እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ።
  • 3. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 3 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የሞዱሉ ይዘቶች የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ ኮምፒውተርን መጠበቅ ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት የሞዱሉ ማጠቃላያ የሞዱሉ መግቢያ እንደማንኛውም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ በአጋጣሚዎች ወይም ሆን ተብለው ለሚደረጉ አደጋዎች ሰለባ ነው። ከነዚህ አደጋዎች አንዳንዶቹ የማይመለሱ ሊሆኑ ይችላሉ። የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ ያለን ውሂብ አንዳንድ የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ብዛት ካላቸው ጉዳቶች መታደግ ይቻላል። ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለተቀመጠው ውሂብ ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ እንድታውቅ ይረዳሃል። አንዳንድ የመከላከያ ርምጃዎችን በመውሰድ ኮምፒውተርህን ከነዚህ ስጋቶች እንዴት መጠበቅ እንደምትችል ይዳስሳል። በመጨረሻም ይህ ሞዱል ከበይነመረብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮችን ያብራራል። የሞዱሉ ዓላማዎች ይህን ሞዱል ከጨረስክ በኋላ፦ • የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ማብራራት እና ለኮምፒውተር ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ ፤ • ኮምፒውተርን ከተለያዩ አደጋዎች የመጠበቂያ ዘዴዎችን ለይተህ ማወቅ ፤ • የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ለማሳደግ የሚጠቅሙ ጥሩ ተሞክሮዎችን ማብራራት ፤ • ኮምፒውተርህ ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት የሚረዱ ቅንጅቶችን እና አማራጮችን ማብራራት እና • ኮምፒውተር እና በይነመረብ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቧቸውን ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። በሁሉም የህይወት ተሞክሮዎችህ ውስጥ ኮምፒውተሮችን ትጠቀማለህ። መረጃ ለማስቀመጥ ፣ የሒሳብ ስራዎችን ለማከናወን ፣ ጌሞችን ለመጫወት ፣ ሙዚቃ ለማዳመጥ ፣ በይነመረብን ለመዳሰስ እና በኢ-ሜይል እና በውይይቶች ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ለመሰሉ የተለያዩ ዓላማዎች ኮምፒውተሮችን ልትጠቀም ትችላለህ። ነገር ግን ኮምፒውተርህ እና በውስጡ የተከማቹ መረጃዎችህ ለጉዳት እና ለብልሽት የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ በተፍጥሮ አደጋዎች ፣ በሰዎች ስህተት ወይም በድንገተኛ ክስተት ወይም የሰርጎ ገቦች ወይም ቫይረስ ጥቃቶችን በመሰለ የጥቃት እንቅስቃሴ ከሚፈጠሩ አደጋዎች ኮምፒውተርህን መጠበቅ ይኖርብሃል። ኮምፒውተርህን ከነዚህ አደጋዎች ለመጠበቅ የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለህ። ለምሳሌ ተገቢ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች እና የዘመነ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር በኮምፒውተርህ ውስጥ እንዲኖርህ በማድረግ። ኮምፒውተርህ በይበልጥ የተጠበቀ መሆኑን ርግጠኛ ለመሆን የቤተሰብህ አባሎችም ስለ ደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ማወቅ ይኖርባቸዋል። በበይነመረብ አማካይነት ከሚገኝ መረጃ ጋር በተያያዘ ያሉ መብቶችን ማወቅም አስፈላጊ ነው። በብዙዎቹ የድር ጣቢያዎች የሚገኙ ይዘቶች የቅጂ መብት ያላቸው ንብረቶች ስለሆኑ ያለፈቃድ እነዚህን መጠቀም በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል። ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የተለያዩ አደጋዎችን ፣ እነዚህ አደጋዎች ስለሚያሳድሩት ተጽዕኖ እንዲሁም መፍትሔዎቻቸው ይዘረዝራል። ይህ ሞዱል የኮምፒውተርህን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለማዘመን ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎችም ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪም ይህ ሞዱል በይነመረብን በምትጠቀምበት ጊዜ ልብ ልትላቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮች ያብራራል። ሞዱል 1 የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
  • 4. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 4 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው? የተፈጥሮ አደጋዎች ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች ግለ ሙከራ የትምህርት ክፍሉ መግቢያ የግብር ወረቀቶችን የመሰሉ አስፈላጊ ሰነዶችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ታስቀምጣቸዋለህ። ስለዚህም ሰነዶችህ ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጠፉም። ካለፍቃድህም ማንም ሊያገኛቸው/ሊደርስባቸው እንደማይችል እርግጠኛ ነህ። ኮምፒውተሮችን ብዙ ጊዜ የምትጠቀም ከሆነ በኮምፒውተር ላይ ሊቀመጥ የሚችል በርካታ መረጃ ሊኖርህ ይችላል። ይህ መረጃ የግብር ዝርዝር ፣ የግል ደብዳቤዎች ወይም የንግድ ስራ ደብዳቤዎች ሊሆን ይችላል። ይህ መረጃ ካላንተ ፈቃድ በሌሎች ሰዎች የማይታይ መሆኑን እርግጠኛ ልትሆን ይገባል። ይህ መረጃ ጉዳት እንዳይደርስበትም መጠበቅ ይኖርብሃል። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና ኤሌክትሮኒክ መረጃ ከጉዳት ፣ ከመጥፋት እንዲሁም ከስርቆት የመጠበቅ አስፈላጊነትን ትዳስሳለህ። በተጨማሪም በኮምፒውተርህ ያለን ውሂብ ለመጠበቅ ልትጠቀምባቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ መፍትሔዎች እና መሳሪያዎች ትማራለህ። የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦ • የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመናን ማብራራት ፤ • ተፈጥሮአዊ የኮምፒውተር አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ፤ • ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ፤ • ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የሰዎች ተግባሮችን ለይቶ ማወቅ እና • ስጋት ከሆኑ የሰዎች ተግባሮች ኮምፒውተርህን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። ክፍለ ትምህርት 1 የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና
  • 5. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 5 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው? ኮምፒውተርን ወይም በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ሊያበላሽ የሚችል መንስኤ የኮምፒውተር ስጋት ነው። እንደ ርዕደ መሬት ወይም ከፍተኛ አውሎንፋስ ያሉ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች መጠነ ሰፊ አካላዊ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። አንተ ወይም ሌላ ሰው ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ አስፈላጊ ፋይሎችን በአጋጣሚ ወይም ባለማወቅ ልታጠፉ ትችላላችሁ። ኮምፒውተርህ ከአውታረመረብ ጋር ሲገናኝ ኮምፒውተርህ የበለጠ ለኮምፒውተር ስጋቶች የተጋለጠ ይሆናል። ለምሳሌ ሌላ ተጠቃሚ ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመዳረስ አውታረመረቡን ሊጠቀም ይችላል። እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ እና በጉዳት ምክንያት ሊደርሱ የሚችለውን የመጥፋት ዕድል ለመቀነስ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች አሉ። መሰረታዊ የሆኑ መመሪያዎችን በመከተል በኮምፒውተርህ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጉዳት መጠን መቀነስ እና ስለደህንነቱ እና ክብረ ገመናው እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። የኮምፒውተር ደህንነት የኮምፒውተር ሃርድዌር በሰዎች ቸልተኝነት አልያም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ሊበላሽ ይችላል። በተጨማሪም በኮምፒውተር ውስጥ ያለ ውሂብ እና ሶፍትዌር በአጋጣሚ ወይም ሆን ተብሎ ከሚደረግ ጥፋት እና ብልሽት መጠበቅ አለባቸው። የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ በኮምፒውተር ላይ እና በውስጡ በሚገኘው ውሂብ ላይ የሚደርስን እንደዚህ ያለ ጉዳት ለማስወገድ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ያወሳል። የኮምፒውተር ክብረ ገመና በኮምፒውተርህ ላይ የግል ፋይሎችህንና ወይም ሰነዶችህን ታስቀምጣለህ እናም ማንም ሰው እንዲያነብብህ አትፈልግም። የኮምፒውተር ክብረ ገመና ማለት የግል ፋይሎች እና የኢ-ሜይል መልዕክቶች የመሳሰሉ መረጃዎችን ካለአንተ ፈቃድ ማንም እንዳይደርስባቸው ማድረግ ማለት ነው። የኮምፒውተር ክብረ ገመና ውሂብህን የመዳረስ ፈቃድን ለመገደብ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያወሳል። የኮምፒውተር ክብረ ገመና በተጨማሪም ማንኛውም የግል የሆነ መረጃን በበይነመረብ ላይ ለማውጣት የሚደረግ ጥንቃቄን ያካትታል። እንደዚህ ያለ መረጃ እንደ ኢ-ሜይል እና የባንክ መለያዎች ያሉ የግል መለያዎችህን ለመዳረስ ሲባል ያልአግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
  • 6. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 6 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ የተፈጥሮ አደጋዎች ርዕደ መሬት ፣ ጎርፍ ፣ አውሎንፋስ እና የመሳሰሉት ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ኮምፒውተርህን በማንኛውም ጊዜ ሊያበላሹብህ ይችላሉ። የተፈጥሮ አደጋዎች ኮምፒውተሮች ላይ አካላዊ ጉዳት ሊያደርሱ እና ውሂብ እንዲጠፋ የሚያደርጉ እንደ እሳት ፣ ከመጠን ያለፈ ሙቀት አንዲሁም ፍንዳታዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህ ስዕላዊ ማስረጃ ለኮምፒውተር ደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋት የሆኑ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ይገልፃል። 1. አብዛኞቹ የኮምፒውተር ክፍሎች በተወሰነ የሙቀት ክልል ብቻ መስራት እንዲችሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። ከመጠን ያለፈ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ በሚኖርበት ጊዜ አንዳንድ የኮምፒውተር አካሎች በትክክል ያለመስራት ሊጀምሩ ይችላሉ እንዲሁም እነዚህን ክፍሎች በሌላ መተካት ሊያስፈልግህ ይችላል። ኮምፒውተርህ ከመጠን ላለፈ ሙቀት የተጋለጠ ከሆነ ከማስጀመርህ በፊት መደበኛ ሙቀት ወዳለበት ክፍል ውሰደው። 2. እሳት ኮምፒውተርህን ሊጠገን በማይችልበት ሁኔታ ሊጎዳው ይችላል። ኮምፒውተሩ በቀጥታ እሳት ሊይዘው ባይችልም ሊፈጠር የሚችለው ሙቀት በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎችን ለማቅለጥ በቂ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጭስ የሲፒዩ ፋንን ሊያበላሽ ይችላል ይህም ሲፒዩ እንዲግልና እንዲበላሽ ያደርገዋል። 3. ከፍተኛ በሆነ የኤሌክትሪክ ፍሰት የሚከሰት ፍንዳታ/ብልጭታ የኃይል መጨመርን ያስከትላል። የኃይል መጨመር ወይም መቆራረጥ የኮምፒውተርህን አንዳንድ ክፍሎች ዳግም እንዳይሰሩ አድርጎ ሊጎዳ የሚችል ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር ነው። ለምሳሌ ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር የኮምፒውተርህን ማዘርቦርድ ሊያቃጥል ይችላል።
  • 7. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 7 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች የተፈጥሮ አደጋዎች ኮምፒውተርህ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ ውሂብህን እና ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮአዊ አደጋዎች ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ያብራራል። ርምጃ መግለጫ የውሂብ ምትክ መያዝ የውሂብ ምትክ መያዝ የውሂብህን ቅጂዎች በዛ አድርጎ መያዝን ያካትታል። አንደ ጎርፍ እና ርዕደ መሬት ያሉ አደጋዎች በድንገት ሊከሰቱ ይችላሉ። ምትክ መያዝ በማንኛውም ሁኔታ የሚከሰትን የውሂብ መጥፋት መልሰህ እንድታገኘው ይረዳሃል። ውሂብህን በጥሩ ሁኔታ እንደገና ለማግኘት ምትክ አድርገህ የያዝከውን አስፈላጊ የሆነ መረጃህን ቅጂ ሌላ ህንፃ ወይም ከተማ ላይ ለይተህ በጥንቃቄ አስቀምጥ። ኮምፒውተሮችን ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ማስቀመጥ ኮምፒውተርህን ለተፈጥሮ ተጽዕኖዎች ሊጋለጥ እና ሊበላሽ በማይችልበት ስፍራ ላይ አስቀምጥ። ለምሳሌ ኮምፒውተሮችን አቧራ የሚበዘበት ወይም እርጥበት ያለበት ክፍል ውስጥ ከማስቀመጥ ተቆጠብ። ጠባቂ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን መትከል የማይቋረጥ ኃይል አቅራቢ (Uninterruptible Power Supply) (UPS) የመሰሉ መሳሪያዎችን መትከል ጊዜያዊ የኃይል መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ በምትኩ የባትሪ ኃይልን ማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋል። UPS በድንገተኛ የኮምፒውተር መዘጋት ምክንያት የሚከሰትን የሶፍትዌር ብልሽት ይከላከላል። UPS የኃይል መብዛት እና የኃይል አስተላላፊ መስመሮችንም ይቆጣጠራል። ይህም በኃይል መተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚከሰት የኃይል መብዛት እና መቆራረጥ ኮምፒውተርህን እንዳይጎዳ ይረዳል። የኃይል መብዛት ጠባቂዎችን እና የመስመር ተቆጣጣሪዎችን ለየብቻ መትከልም ትችላለህ። ነገር ግን እንደ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ያሉ ክስተቶች ምክንያት በሚፈጠር ከፍተኛ የሆነ የኃይል መብዛት ሁኔታ ጊዜ አደጋን ለማስወገድ ኮምፒውተርህን ማጥፋ እና ከኃይል ምንጩ መንቀል ይኖርብሃል ። ኮምፒውተሮችን ከእሳት መጠበቅ የእሳት ሂደትን በሚቀንስ ነገር ዙሪያውን በማጠር ኮምፒውተርን ከእሳት መጠበቅ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በቂ የሆነ የእሳት መከላከያ መሳሪያዎችን እና ፈጣን የአደጋ መቆጣጠሪያ ርምጃ መውሰጃዎችን መትከል ትችላለህ። ተገቢ የሆነን ሙቀት እና የአየር ሁኔታ መጠበቅ የኮምፒውተርህ አገልግሎት አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ ተስማሚ የሆነውን ሙቀት እና የአየር ሁኔታ መጠበቅ ይኖርብሃል። ይህንንም የአየር ማቀዝቀዣዎችን እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎችን የመሰሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ማድረግ ትችላለህ። ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች አንዱ የኮምፒውተር ስጋት ዓይነት በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት ነው። በቢሮህ ውስጥ የሚሰራ አንድ የተከፋ ሰራተኛ ሆን ብሎ በኮምፒውተርህ ውስጥ ያለን መረጃ ለማበላሸት ሊነሳሳ ወይም ለማጥፋት ሊሞክር ይችላል። ሰርጎ ገብ ከበይነመረብ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ህገወጥ በሆነ መንገድ ኮምፒውተርህን ለመድርስ የሚሞክር ሰው ነው። ኮምፒውተርህን ከደረሰ በኋላ ሰርጎ ገብ በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ሊሰርቅ ወይም ሊያበላሽ ይችላል። በሰዎች ከሚፈጠር ጉዳት በተጨማሪ እንደ ድንገተኛ የውሂብ ማጥፋት እና አካላዊ ጉዳት ያሉ የሰዎች ስህተት ለኮምፒውተርህ ስጋት ናቸው። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት እና በሰዎች ስህተት የሚመጡ የተለያዩ የኮምፒውተር ስጋቶችን ይገልፃል። አደጋ መግለጫ ስርቆት ማንኛውም ሰው ኮምፒውተህን መዳረስ የሚችል ከሆነ ኮምፒውተርህን ወይም የኮምፒውተሩን ክፍሎች ሊሰርቅህ ይችላል። እንደ ላፕቶፕ ያሉ ተንቀሳቃሽ ኮምፒውተሮችን የሚጠቀሙ ሰዎች ከመብዛታቸው አንፃር አካላዊ የኮምፒውተሮች ስርቆት የተለመደ ሆኗል። ኮምፒውተርህ ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ጊዜም የምናባዊ ስርቆት ሰለባ ልትሆን ትችላለህ። አንዱ የምናባዊ ስርቆት ምሳሌ የሚሆነው የማንነት መለያ ስርቆት ነው ፤ በዚህም ሰርጎ ገቦች መለያህን በመጠቀም እና አንተን በመምሰል የግል መረጃዎችህን ሊሰርቁህ ይችላሉ። ይህን የሐሰት የማንነት መለያ በመጠቀም ሰርጎ ገቦች ፋይናንስህን መዳረስ ሊችሉ ወይም ህገ ወጥ ስራዎችን ሊያከናውኑበት ይችላሉ። ሌላው የምናባዊ ስርቆት ምሳሌ የሚሆነው የሶፍትዌር ህገ-ወጥ ቅጂ ነው ፤ ይህም የኮምፒውተር ንድፍ ወይም ፕሮግራም ስርቆት ነው። በተጨማሪም ይህ የኮምፒውተር ፕሮግራምን እና ምስጢራዊ ሰነዶችን ያለፍቃድ ማሰራጨት እና መጠቀም ማለት ሊሆን ይችላል።
  • 8. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 8 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ቫይረሶች ፣ ተውሳኮች እና ትሮጃን ሆርሶች ቫይረሶች በኮምፒውተርህ ላይ ያለን ውሂብ ወይም ሶፍትዌር ሊያበላሹ እንዲሁም በኮምፒውተረህ ውስጥ የተቀመጠ መረጃን ሊሰርቁ የሚችሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች ናቸው። እነዚህ ቫይረሶች ካላንተ ዕውቅና ፣ በበይነመረብ ወይም እንደ ፍሎፒ ዲስኮች እና ሲዲዎች ባሉ የማከማቻ መሳሪያዎች አማካይነት ወደ ኮምፒውተርህ ሊገቡ ይችላሉ። ተውሳኮች አንዴ ኮምፒውተር ውስጥ ከገቡ በኋላ ራሳቸውን የሚያባዙ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ይህም እነርሱን ለማስወገድ ከባድ እንዲሆን ያደርገዋል። ትሮጃን ሆርሶች ራሳቸውን እንደጠቃሚ ሶፍትዌር የሚያስመስሉ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ለምሳሌ እንደ ጌም ወይም መገልገያ ሶፍትዌር ሊመስሉ ይችላሉ። ትሮጃን ሆርስ አንዴ ኮምፒውተር ውስጥ ከገባ በኋላ የኮምፒውተር ውሂብን ማበላሸት ይጀምራል። ስፓይዌር ስፓይዌር የሚባሉት ካላንተ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ ፕሮግራሞች ናቸው። ስለ ድር አሰሳ ልምዶችህ ወይም ሌላ የግል መረጃ ዝርዝሮችህ ወደ ሌላ በአውታረመረቡ ላይ ያለ ኮምፒውተር በድብቅ/በሚስጥር መረጃ ሊልኩ ይችላሉ። የበይነመረብ አጭበርባሪዎች በይነመረብ በምትጠቀምበት ጊዜ በኢሜይል መልዕክቶች ወይም በውይይት መድረኮች አንዳንድ ሳቢ የሆኑ ነገሮች ሊላኩልህ/ሊቀርቡልህ ይችላሉ። እንደዚህ አይነት አቅርቦቶችን ከመቀበልህ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል ፤ ምክንያቱም እነዚህ አቅርቦቶች የገንዘብ ጥፋት የሚያስከትሉ በሚገባ የታቀዱ የአጭበርባሪዎች አካል ሊሆኑ ይችላሉና። የመስመር ላይ አዳኞች የመስመር ላይ አዳኞች በመስመር ላይ ያለ ማንኛውንም ሰው አግባብ ባልሆነ መንገድ ወይም ስነምግባር በጎደለው ሁኔታ ወዳጅነት በመፍጠር የሚያማልሉ ግለሰቦች ናቸው። አንተ ወይም ቤተሰቦችህ የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ። የመስመር ላይ አዳኞች ኢሜይል ወይም የውይይት መድረኮችን በመጠቀም በፈለጉት አላማ ዙሪያ ከሰዎች ጋር ግንኙነታቸውን ያዳብራሉ። ድንገተኛ የውሂብ መጥፋት ብዙ ጊዜ ድንገተኛ በሆነ የሰዎች ስህተት ምክንያት የኮምፒውተር ብልሽት ሊደርስ ይችላል። ድንገተኛ የሆነ የአስፈላጊ ፋይል መጥፋት የውሂብን አንድነት ሊያዛባ ወይም ሌሎች ፋይሎች ወይም ፕሮግራሞች እንዳይሰሩ ሊያግድ ይችላል። ለምሳሌ ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ የሚያደርግን ፋይል በድንገት/ሳታውቅ ልታጠፋ ትችላለህ። ድንገተኛ የሃርድዌር ብልሽት በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎች በቸልተኝነት ለሚከሰቱ ብልሽቶች የተጋለጡ ናቸው። ለምሳሌ በድንገት ላፕቶፕ ኮምፒውተርህ ቢወድቅብህ እንደ ማዘርቦርድ ወይም ሲዲ-ሮም ያሉ የኮምፒውተሩ ክፍሎችን ሊጎዳብህ/ ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህም በኮምፒውተርህ ውስጥ ያለን መረጃ ያሳጣሃል። ከዚህ በተጨማሪም በማከማቻ መሳሪያዎች ወይም ተገጣሚዎች ላይ በምግብ ወይም መጠጥ መፍሰስ ምክንያት የሚደርስ አካላዊ ጉዳት ኮምፒውተርህ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ጋር በተያያዘ የሚመጡ ስጋቶችን ለመቀነስ አንዳንድ ቀላል ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ ኮምፒውተርህን በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች ይገልፃል። መፍትሔ መግለጫ መረጃን አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ መረጃህን አስተማማኝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ማለትም ሌሎች በማይደርሱበት ሁኔታ አስቀምጥ። ይህም መረጃው የሚሰረቅበትን እና የሚበላሸበትን እድል ይቀንሰዋል። ውሂብን መመስጠር የWindows 7 ቢትሎከር (BitLocker) ባህሪ ውሂብን በአንፃፊ-ደረጃ ለለመስጠር ይረዳሃል። ይህን ባህሪ በመጠቀም ውሂብን በምትመሰጥርበት ጊዜ ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ደረቅ አንፃፊውን (ሃርድ ድራይቩን) በመንቀል እና ከሌላ ኮምፒውተር ጋር በማገናኘት ውሂቡን ማግኘት አይችሉም። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ፕሮግራሞችን መጫን ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በኮምፒውተር ማህደረ ትውስታ ውስጥ ቫይረስ እና ስፓይዌር እንዳለ የመፈተሽ እንዲሁም አዲስ ወደ ኮምፒውተሩ እንዳይገባ የመከላከል አቅም አለው። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌርን በየጊዜው ማዘመን አለብህ ፤ ይህም አዳዲስ ቫይረሶችን እና ስፓይዌሮችን መለየት እንዲችሉ ያስችላቸዋል። አብዛኛው ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር የዘመነውን የሶፍትዌር ስሪት በራሱ ወደ ኮምፒውተር የሚጭን የራስ ማዘመኛ ባህሪ ያቀርባል። እንደ Windows Mail ባለ የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ውስጥ አብረው የተሰሩ ባህሪያት አይፈለጌ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለማገድ ያስችሉሃል ፤ እንዲሁም ቫይረሶችን እና ተውሳኮችን የሚፈትሹ ባህሪያትን ያቀርባሉ። Windows 7 Windows መከታ የሚባል በወቅቱ የመከላከል አቅም ያለው አብሮ የተሰራ ፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም አካቷል። ኬላ (firewall) መጫን ኬላ መጫን የኮምፒውተር ጎጂ ስጋቶችን ለመከላከል ልትወስደው የምትችለው ውጤታማ መፍትሔ ነው። ኬላ (firewall) የበይነመረብ ፍሰትን ኮምፒውተርህን ወይም የግል አውታረመረብህን ከመድረሱ በፊት ለማጣራት ያስችልሃል። እንደ ሰርጎ ገቦች እና ቫይረሶች ያሉ ስጋቶችን የመከላከያ ተጨማሪ አገልግሎቶችንም ይሰጣል። ኬላ ባልተፈቀደ ተጠቃሚ ማንኛውም ከውጪ የሚደረግን መዳረስ በማገድ የኮምፒውተርህን ደህንነት እንድታረጋግጥ ይረዳሃል። በWindows 7 የሚገኘው Windows ኬላ የማይፈለግ የኮምፒውተር መዳረስን ያግዳል።
  • 9. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 9 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ምትክ ውሂብ መያዝ አስፈላጊ የሆነን የኮምፒውተር ውሂብ በየጊዜው ምትክ ያዝ። የውሂብን ምትክ ቅጂዎችን በዛ አድርጎ መያዝ በድንገት መጥፋት ወይም መበላሸት ምክንያት የሚከሰትን የውሂብ ማጣት ይከላከላል። ኮምፒውተርን አስተማማኝ በሆነ ስፍራ ማስቀመጥ ኮምፒውተርህን ከአቧራ ነፃ በሆነ ፣ ንቅናቄ በሌለበት እና ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች የጸዳ ስፍራ ላይ አስቀምጥ። የኮምፒውተሩ ማስቀመጫ ጠረጴዛ ወይም መደርደሪያ የማይነቃነቅ እና ቋሚ መሆን ይኖርበታል። ይህም ኮምፒውተሩ በድንገት ቢገፋ እንኳ እንዳይወድቅ ይረዳዋል። ኮምፒውተርህን ከመግኔጢሳዊ ዕቃ እና ፈሳሽ ነገር አርቅ። ለምሳሌ ኮምፒውተርህን መሬት ላይ ወይም ምንጣፍ ላይ አታስቀምጥ። በቁልፍ ሰሌዳ አቅራቢያ ሆነህ አትመገብ ወይም አትጠጣ እንዲሁም የቁልፍ ሰሌዳህን በድንገት ከሚፈስ ነገር ለመከላከል መሸፈኛ ተጠቀም። ርዕስ፦ የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች የሚከተሉትን የተለያዩ አይነት አደጋዎችን ለመከላከል የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው። ዓረፍተ ነገር 1 የኃይል መብዛትን መከላከያ እና የኤሌክተሪክ መስመር መቆጣጠሪያ 2 የውሂብ ምስጠራ 3 የእሳት ሂደትን የሚቀንስ ነገር 4 የማይነቃነቅ ጠረጴዛ 5 ከመግኔጢሳዊ ዕቃዎች ማራቅ 6 ፀረ ቫይረስ 7 የአየር ማቀዝቀዣዎች እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎች 8 የስፓይዌር መከላከያ 9 የቁልፍ ሰሌዳ መሸፈኛ 10 ኬላ ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3 የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
  • 10. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 10 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3 የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች 7, 3, 1 10, 8, 6, 2 9, 5, 4 ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ ጥያቄ 1 ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው? ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ። ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ። ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል። ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ። ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ። ጥያቄ 2 ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው የቱ ነው? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ። ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር። ኬላ። የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ። ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
  • 11. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 11 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። መልስ 1 ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው? ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ። ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ። ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል። ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ። ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ። መልስ 2 ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው የቱ ነው? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ። ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር። ኬላ። የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ።
  • 12. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 12 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች ግለ ሙከራ የትምህርት ክፍሉ መግቢያ የባንክ ወይም የአስተማማኝ ገንዘብ ማጠራቀሚያ ሳጥንህን ለመድረስ የማንነት መለያህን መስጠት ይኖርብሃል። ይህ የማንነት መለያ ያንተን ንብረት ሌላ ሰው መድረስ እንደማይችል ርግጠኛ እንድትሆን ያደርገሃል። በተመሳሳይ ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለሚገኘው መረጃህ አስጊ የሆኑ አደጋዎችን ለመቀነስ የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የኮምፒውተርህን ስርዓት ክወና ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ለመጠበቅ የሚያግዙህን አንዳንድ መሰረታዊ ምርጥ ተሞክሮዎች ያስተዋውቅሃል። የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦ • ኮምፒውተርህን የመጠበቂያ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ፤ • የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግንኙነቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለይተህ ማወቅ እና • የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክት ልውውጥ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። ክፍለ ትምህርት 2 ኮምፒውተርን መጠበቅ
  • 13. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 13 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች አንድ ሚስጥራዊ ፕሮጅክት ኮምፒውተርህ ላይ አስቀምጠሃል ብለህ አስብ። ይህን ሪፖርት ለማዘጋጀት ለሳምንታት ስሰራ ቆይተሃል እናም አሁን የፕሮጅክትህን ሪፖርት ለሱፐርቫይዘርህ ማሳየት ፈልገሃል። የዚህ ሪፖርት አንድ ቅጂ ብቻ በኮምፒውተርህ ላይ ይገኛል። ይህ ሪፖርት እንዳይበላሽ ወይም እንዳይሰረዝ ደህንነቱን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ሌላ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ የሆነ ሰው አንተ በማትኖርበት ጊዜ ኮምፒውተርህን ይጠቀም ነበርና የፕሮጀክቱን ሪፖርት ከኮምፒውተርህ ላይ አጠፋው። እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎችን ለማስቀረት በኮምፒውተርህ ላይ የሚገኝን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ርምጃዎችን መውሰድ ይኖርብሃል። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ በኮምፒውተርህ የሚገኘውን ስርዓተ ክወና እና መረጃ ለመጠበቅ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያብራራል። መመሪያ መግለጫ የተጠቃሚ መለያ ተግብር የስርዓተ ክወናህን እና የመረጃህን አደጋ ለመቀነስ ውጤታማ የሆነው መንገድ ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች ኮምፒውተርህን እንዳይደርሱ መጠበቅ ነው። ይህን ለማሳካት አንደኛው ዘዴ ኮምፒውተርህን ለመድረስ ለተፈቀደላቸው ሰዎች መለያዎችን ማቀናበር ነው። በዚህ መሰረትም እያንዳንዱ ተጠቃሚ በየደረጃው ተገቢ የሆነ የመዳረስ ፍቃድ ያገኛል። ለምሳሌ በWindows 7 ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወይም ሌላ ተጠቃሚ መለያዎችን ማቀናበር ትችላለህ። ለራስህ አብላጫውን መብት መወሰን እንዲሁም ልጆች ካሉህ የልጆች መለያን አቅም መገደብ ትችላለህ። የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አዋቅር የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በማቀናበር የደህንነት ጥበቃህን ከፍ ማድረግ እና ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎችን ኮምፒውተርህን እንዳይደርሱ ማገድ ትችላለህ። በብዙዎቹ መስሪያቤቶች ውስጥ እያንዳንዱ ሰራተኛ የተለየ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አለው። ሰራተኞቹ ኮምፒውተሮቻቸውን ለመድረስ ትክክል የሆነ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ማስገባት ይኖርባቸዋል። በWindows 7 የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ማቀናበር ትችላለህ። የይለፍ ቃልን በሚስጥር መጠበቅ የይለፍ ቃልህ ለኮምፒውተርህ እንደ ቁልፍ ያገለግላል። የይለፍ ቃልህን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ኮምፒውተርህን ሊደረስ እና መረጃህን ሊያበላሽብህ ስለሚችል የይለፍ ቃልህን በሚስጥር መያዝ ይኖርብሃል። የይለፍ ቃልህን በምታስገባበት ጊዜ ማንም እንዳያይ ጥንቃቄ አድርግ። የይለፍ ቃልህን ለሌሎች አታጋራ። የይለፍ ቃልህን ጽፈህ በኮምፒውተርህ ወይም በጠረጴዛህ ላይ አትተው። የይለፍ ቃልህ ተጋልጧል ብለህ ካሰብህ ሌሎች ያላግባብ ሳይጠቀሙበት በፊት በፍጥነት ቀይር። ኮምፒውተርህን ቆልፍ ማንም ሰው በሌለበት ሁኔታ ኮምፒውተርህን እንደበራ ትተህ በምትሄድበት ጊዜ ሌላ ሰው የኮምፒውተርህን ሶፍትዌር ወይም መረጃ ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህንን በማትኖርበት ወቅት ኮምፒውተርህን ለጊዜው በመቆለፍ መከላከል ትችላለህ። ኮምፒውተር በሚቆለፍበት ጊዜ ወዲያውኑ የገጽ ማሳያውን ይዘቶች ይደብቅና በትክክለኛው የተጠቃሚ ስም እና የይልፍ ቃል እስኪከፈት ድረስ ምንም ስራ እንዲከናወን አይፈቅድም። ኮምፒውተርን የመቆለፍ አካሄዶች እንደምትጠቀመው ስርዓተ ክወና ይወሰናል። ለምሳሌ በWindows 7 CTRL+ALT+DEL በመጫን እና ይህን ኮምፒውተር ቆልፍ የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ በማድረግ ኮምፒውተሩን መቆለፍ ትችላለህ። ይህ ኮምፒውተርን የሚቆልፍ ባህሪ በሁሉም ስርዓተ ክወናዎች ላይ እንደሌላ አስታውስ።
  • 14. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 14 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የመጠበቂያ ሶፍትዌር ጫን እንዲሁም አዘምን ኮምፒውተርህን እንደ ቫይረሶች እና ስፓይዌር ባሉ ስጋቶች እንዳይጠቃ ክትትል ማድረግ ይኖርብሃል። በአሁኑ ጊዜ በቫይረስ የሚመጣ ጉዳት ትኩርት የሚያስፈልገው ነው። በጣም አስፈላጊ የሆነ መረጃ ልታጣ ትችላለህ እንዲሁም የስርዓተ ክወናህን እና ሌላ ሶፍትዌርን እንደገና መጫን ሊያስፈልግህ ይችላል። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በመጫን ኮምፒውተርህን ከቫይረሶች እና ስፓይዌር መከላከል ትችላለህ። እነዚህ ጠባቂ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ የሚገኝን ቫይረስ እና ስፓይዌር ለማግኘት እና ለማስወገድ ያግዙሃል። አዲስ ቫይረስ እና ስፓይዌር ኮምፒውተርህን እንዳያጠቃውም ይከላከላሉ። ኬላ መጫንም ሌላው ጥሩ ተሞክሮ ነው። ይህም ወደ ኮምፒውተርህ የሚደርሱትን አጣርቶ ያወጣል። ኬላ መጫን በመስመር ላይ ተጠቃሚዎች የሚደረግን የመድረስ ሙከራን በመገደብም ከሰርጎ ገቦች ይከላከላል። በየጊዜው አዳዲስ ስጋቶች እየተፈጠሩ ስለሆነም የሶፍትዌር ኩባንያዎች በኮምፒውተርህ ልትጭናቸው የምትቻላቸው ዝምኖችን በየጊዜው ይፈጥራሉ። እነዚህ ዝምኖች በኮምፒውተርህ በተጫነው ሶፍትዌር ወይም ስርዓተ ክወና ላይ ጭማሪዎችን በማድረግ የኮምፒውተርህን በደህንነት ስጋቶች የመጋለጥ አቅም ይቀንሳል። የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌርህ አዳዲስ ቫይረሶችን እንዲያገኝልህ በየጊዜው ማዘመንህን አረጋግጥ። Windows 7 ኮምፒውተርህን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል Windows ኬላን አካቷል። ከዚህ በተጨማሪም ኮምፒውተርህን ከብቅ-ባዮች እና ሌሎች የደህንነት ስጋቶች የሚከላከል Windows መከታ የሚባል የፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም አካቷል። ውሂብ መስጥር ውሂብን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል ሲባል ውሂብን ወደማይነበብ ቅርጸት መቀየር ምስጠራ ተብሎ ይጠራል። የተፈቀደለት ተጠቃሚ የተመሰጠረውን ውሂብ ወደሚነበብ እና የሚጠቅም ቅርጸት ዳግም መመልስ ይችላል። ይህም ሚስጠር መፍታት ይባላል። ዛሬ የተለያዩ የሶፍትዌር ምርቶች ውሂብን የመመስጠሪያ ዘዴዎችን አካተዋል። በWindows 7 ምስጠራ ፋይልን ለሚመሰጥረው ተጠቃሚ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ፣ ይህም ፋይሉን ከመጠቀም በፊት ምስጠራውን መፍታት አይኖርብህም ማለት ነው። ሁሌ እንደምታደርገው ፋይሉን መክፈት እና መለወጥ ትችላለህ። ምትክ ውሂብ ያዝ አስፈላጊ የሆኑ ፋይሎችን ቅጂ በሲዲ ፣ ዲቪዲ ወይም ፍሎፒ ዲስክ የመሳሰሉ የማከማቻ መሳሪያዎች ላይ በማስቀመጥ ፋይሎችህን ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት ልትታደጋቸው ትችላለህ። ይህ ሂደት ምትክ ውሂብ መያዝ ይባላል። የተያዙትን ምትኮችም አስተማማኝ በሆነ ቦታ በማስቀመጥ ዋናው ፋይል በሚበላሽበት ወይም በሚጠፋት ጊዜ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።
  • 15. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 15 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ማገናኘት ከአለም መረጃ እና መዝናኛ ጋር ያስተዋውቀዋል። ነገር ግን ኮምፒውተርህን ለመስመር ላይ አደጋዎች የተጋለጠ እንዲሆንም ያደርገዋል። ለምሳሌ ቫይረሶች ከተጠቃ ኮምፒውተር ወደ አንተ ኮምፒውተር በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ። ኮምፒውተርህ በእነዚህ የመስመር ላይ አደጋዎች የሚደርስበትን ጉዳት ለመቀነስ እንደ ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር ፣ ውሂብ መመስጠር እና የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን አጣምረህ መጠቀም ትችላለህ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግንኙነቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች ያብራራል። ርምጃ መግለጫ ጠንካራ የይለፍ ቃል ተጠቀም ጠንካራ የይለፍ ቃል ማለት በቀላሉ ሊገመት የማይችል ውስብስብ የይለፍ ቃል ነው። የይለፍ ቃል የዓብይ እና ንዑስ ሆሄያትን ፣ ቁጥሮችን እና እንደ ስርዓተ ነጥቦች እና የቁጥር ምልክት ያሉ ልዩ ቁንፊዎችን አጣምሮ የያዘ እንዲሁም ሙሉ ቃላትን ወይም ስሞችን ያላካተት ሊሆን ይገባል። ጠንካራ የይለፍ ቃል የደህንነት እና ክብረ ገመና ጥቃቶች ዋንኛ መከላከያህ ነው። ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ጠንካራ የይለፍ ቃላት ሊፈጠርላቸው ይገባል። • ያልተገናኙ ኮምፒውተሮችን ለመዳረስ • አውታረመረቦችን ለመዳረስ • የግል እና የገንዘብ ሁኔታ ዝርዝር የመሰለ አንገብጋቢ መረጃ ያላቸውን ድረ ጣቢያዎች ለመዳረስ • ማንኛውም አስፋለጊ የሆነን መረጃ ለመዳረስ • ኮምፒውተር ላይ ለተቀመጠ የግል መረጃ ከሰርጎ ገቦች እና ስፓይዌር መከላከል በይንመረብን በምትዳስስበት ወቅት በኮምፒውተርህ ላይ የተጫነ ፕሮግራም በሌላ አገር ላይ ለሚገኝ ሰርጎ ገብ የግል መረጃህን አሳልፎ ሊሰጥብህ ይችላል። እንደዚህ ያሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች የስፓይዌር ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ያለንታ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ ይጫኑና ምስጢራው የሆነ መረጃን ከኮምፒውተርህ ወደ ሰርጎ ገቦች በድብቅ ያስተላልፋሉ። አንዳንድ ጊዜ ቀጣሪዎች ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች ላይ ሆን ብለው ስፓይዌር በመጫን የሰራተኞቻቸውን የኮምፒውተር ስራ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይጠቀሙበታል። Windows 7 በኮምፒውተርህ ላይ ስፓይዌር በድብቅ እንዳይጫን የሚከለክል Windows መከታ የሚባል አብሮ የተሰራ ፀረስፓይዌር ፕሮግራም አካቶ ይዟል። ለመስመር ላይ ደህንነት ጥበቃ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ (ISP) ደጋፊን ተጠቀም። ይህ ድጋፍ ፀረቫይረስ እና ፀረስፓይዌር ሶፍትዌር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ISPs የኬላ መከላከያ ፣ የኢ-ሜይል ቫይረስ መለያ እና የአይፈለጌ መልዕክት መከላከያን ያቀርባሉ። የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው አጽዳ በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ የምትጎበኛቸው የድር ጣቢያዎች እና ድረ- ገፆች በአሳሽህ ታሪክ ላይ ይቀመጣሉ። እንዲሁም በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ በርካታ ፋይሎች በኮምፒውተርህ ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ ላይ ይቀመጣሉ። ይህ ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ መሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ይባላል። በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ላይ የሚከማቹት ፋይሎች ስለ ጎበኛሃቸው ድረ-ገፆች መረጃ ይመዘግባሉ። ነገር ግን የተወሰኑት የእነዚህ ጊዜያዊ የበይነመረብ ፋይሎች በሰርጎ ገቦች ሊገኙ የሚችሉ እንደ የተጠቃሚ ስምህ እና የይለፍ ቃልህ ያለ የአንተ የግል መረጃን ሊይዙ ይችላሉ። ሰርጎ ገቦች የግል መረጃህን እንዳያገኙ ለመከላከል በአሳሽ ታሪክ እና በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ውስጥ የሚገኙ ይዘቶችን በየጊዜው አጥፋ። የድር ጣቢያዎችን በምትጎበኝበት ጊዜ ስምህን የሚያሳይ ማስታወቂያ
  • 16. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 16 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ልትመለከት ትችላለህ። ይህ የሚሆነውም ኩኪዎችን በመጠቀም ነው። ኩኪዎች ቀድሞ የጎበኘሃቸው የድር ጣቢያዎች አማራጮችህን ለመለየት እና ለመከታተል ሲሉ በኮምፒውተርህ ላይ የሚፈጥሯቸው ትናንሽ ፋይሎች ናቸው። ዋና ዓላማቸው የድር ጣቢያውን በምትጎበኝበት ጊዜ የበለጠ ላንተ የሚሆን መረጃ ለማቅረብ ነው። ነገር ግን ኩኪዎች የግል መረጃህን ስለሚይዙ ለኮምፒውተርህ ደህንነት ስጋት ሊሆኑም ይችላሉ። ለምሳሌ የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ ኩኪዎች የክሬዲት ካርድህን ዝርዝር መረጃ ሊይዙብህ ይችላሉ። በእነዚህ ምክንያቶች የግል መረጃህ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል በየጊዜው ኩኪዎችን ማጥፋት ጥሩ ልምድ ነው። የግል መረጃን ከማጋራት ተቆጠብ አንዳንድ የድር ጣቢያዎች እንደ ስም ፣ ፆታ እና እድሜ ያለ የግል መረጃን በቅፆች ላይ እንድትሞላ ይጠይቃሉ። በኢ-ኮሜርስ ጣቢያዎች ደግሞ የባንክ መለያ ዝርዝሮችን ወይም የክሬዲት ካርድ ቁጥርህን ልትጠየቅ ትችላለህ። ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ይህን መረጃ ሊያገኙት እና ላልተገባ ዓላማ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አስታውስ። አንዳንድ ኩባንያዎች ያልተፈለጉ የንግድ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን ወደ አንተ ለመላክም ይህን መረጃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ስለዚህ በድር ጣቢያ ላይ ማንኛውንም የግል መረጃ ከማጋራትህ በፊት የድር ጣቢያው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና መረጃውን መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አረጋግጥ። የመስመር ላይ ግብይቶችን ደህንነታቸው በተጠበቀ ጣቢያዎች ላይ ብቻ አድርግ የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ እንደ ባንከ መለያ ቁጥር እና ክሪዲት ካርድ ዝርዝሮች ያለ ወሳኝ መረጃን መስጠት ያስፈልግሃል። ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችን የምታካሂደው አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። አንድ የድር ጣቢያ አስተማማኝ ነው የሚባለው የስሙ ቅድመ ቅጥያ https ከሆነ ነው። ቅድመ ቅጥያው የድር ጣቢያው Secure Sockets Layer (SSL) ፕሮቶኮልን እንደሚተገብር ያመለክታል። SSL የሚተላለፈውን መረጃ በመመስጠር አስተማማኝ የመረጃ ግንኙነትን የሚያረጋግጥ የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ ፕሮቶኮል ነው። SSL ፕሮቶኮል የድር ጣቢያው እውነተኛ መሆኑን እና ለጣቢያው የምትሰጠው መረጃ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደማይውል ያረጋግጣል። አስተማማኝ የሆነ የድር ጣቢያ ስታስገባ አብዛኞቹ የድር አሳሾች የስገባሃው የድር ጣቢያ አስተማማኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ መልዕክት ያሳዩሃል። በአድራሻ አሞሌ ውስጥ የሚታይ የተቆለፈ ትንሽ የቁልፍ አዶ አስተማማኝ የሆነ የድር ጣቢያን ለመለየት ያግዝሃል። በተጨማሪም ማንኛውንም የመስመር ላይ ግብይት ከማካሄድህ በፊት የድር ጣቢያውን የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መመልከት ትችላለህ። Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በመጠቀም የደህንነት ጥበቃ ክፍሎችን አዋቅር Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በWindows 7 የሚገኝ ባህሪ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን ሁኔታ ለመመርመር እና በኮምፒውተርህ የተጫነውን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ለመከታተል የሚረዳ ምቹ የሆነ መገልገያ ይሰጣል። የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ከመቆጣጠሪያ ፓኔል መክፈት ትችላለህ። የደህንነት ጥበቃ ማዕከል አራት ክፍሎች አሉት እነርሱም፦ • ኬላ፦ በWindows 7 ውስጥ Windows ኬላ በራሱ የሚሰራ ነው። ኬላ እንደ ቨይረሶች እና ተውሳኮች ያሉ ጎጂ ይዘቶች ወደ ኮምፒውተርህ እንዳይገቡ ለመከላከል ይረዳል። • ራስ-ሰር ማዘመኛ፦ ይህ ባህሪ ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ዝምኖችን በMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ ላይ መኖራቸውን ይፈትሻል። ይህን ባህሪ ማንቃት ኮምፒውተርህ የዘመነ እና በበይነመረብ ላይ ከሚገኙ አዳዲስ የደህንነት ስጋቶች የተጠበቀ ሆኖ እንደሚቆይ ያረጋግጣል። • የማልዌር መከላከያ፦ ስፓይዌር እና ሌላ የማይፈለግ ሶፍትዌር ያንተን ፈቃድ በአግባቡ ሳይጠይቅ በኮምፒውተርህ ላይ ራሱን ሊጭን ይችላል። Windows መከታ ከበይነመረብ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ወቅታዊ የመከላከል ስራ ይሰራል። • ሌሎች የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች፦ ሌሎች የደህንነት ጥበቃ
  • 17. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 17 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ቅንጅቶች የበይነመረብ ቅንጅቶችን እና የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ ቅንጅቶችን ያጠቃልላል። የበይነመረብ አማራጮችን በመጠቀም የደህንነት ጥበቃ ደረጃውን መካከለኛ ፣ መካከለኛ-ከፍተኛ ወይም ከፍተኛ ማድረግ ትችላለህ። Internet Explorer 8 ከቀድሞዎቹ ስሪቶች የበለጠ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ደረጃዎች አሉት። የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ በኮምፒውተርህ ላይ ለውጥ ከመደረጉ በፊት የይለፍ ቃል በመጠየቅ ያልተፈቀዱ ለውጦችን ይከላከላል። ተዋናይ ይዘትን አሰናክል ተዋናይ ይዘት በይነመረብ በምታስስበት ጊዜ በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ ትናንሽ ፕሮግራሞችን ያመለክታል። የእነዚህ ፕሮግራሞች ዋና አገልግሎት በቪዲዮች እና በሰሪ አሞሌዎች የታገዘ የበይነመረብ ተሞክሮ ግንኙነት ለአንተ ማቅረብ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች እነዚህን ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ለማበላሸት ወይም ያለአንተ ፈቃድ ጎጂ የሆነ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች እንዳይጫኑ ለመከላከል ተዋናይ ይዘትን ማሰናክል ትችላለህ። ርዕስ፦ የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች ኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ለንግድ ስራ እና ለግል ግንኙነት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ፣ የመስመር ላይ አዳኞች እንዲሁም ተውሳኮችን እና ቫይረሶችን የሚፈጥሩ ሰዎች ኢ-ሜይልን እና ፈጣን መልዕክትን ለጥቃት ዓለማ ይጠቀሙባቸዋል። ለምሳሌ እነዚህ ሰዎች ጎጂ ሶፍትዌር አያይዘው ኢ-ሜይል ሊልኩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች አስፈላጊ መረጃን ለመጠየቅ ወይም በተሳሳቱ አቅርቦቶች አንተን ለማማለል ኢ- ሜይልን ሊጠቀሙም ይችላሉ። ለዚህም ነው የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ደህንነትን ለማረጋገጥ አንዳንድ ርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ የሆነው። የኢ-ሜይል ደህንነትን ለማረጋገጥ አባሪ ያለውን ኢ-ሜይል ከመክፈት ተቆጠብ ፣ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ አትስጥ ፣ ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ መልዕክት ምላሽ አትስጥ እንዲሁም ራስህን ከአስጋሪዎች ጠብቅ። የፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለማረጋገጥ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ እንዲሁም በፈጣን መልዕክት የሚደርሱ አባሪዎችን አትክፈት። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለማረጋገጥ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ያብራራል። ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል። አብሪዎች የያዙ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ አድርግ ፋይሎችን ለጓደኞችህ ለማጋራት የኢሜይል አባሪዎችን ልትልክ ትችላለህ። በኢ-ሜይል መልዕክትህ ውስጥ እንደአባሪ ሆኖ የፎቶ ወይም የሙዚቃ ፋይል ሊደርስህ ይችላል። ነገር ግን አባሪ የያዘ መልዕክትን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፍልጋሃል ምክንያቱም ይህ በብዛት የተለመደው ቫይረሶችን የማሰራጫ መንገድ ነውና።
  • 18. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 18 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል። ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ መልዕክት ምላሽ አትስጥ ምርቶቻቸውን ወይም አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁ ግለሰቦችን እና ኩባንያዎችን ጨምሮ ካልታወቁ ላኪዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ያልተፈለጉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ልትቀበል ትችላለህ። እነዚህ መልዕክቶች ያንተን የግል መረጃ እንድትሞላ የሚፈልጉ የመስመር ላይ መጠይቆች ሊሆኑም ይችላሉ። እነዚህ ሳይፈለጉ የሚመጡ መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት በመባልም ይታወቃሉ። ብዙ ጊዜ አይፈለጌ መልዕክት ለኮምፒውተርህ ጎጂ የሆነ ይዘትን ሊያካትት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም አይፈለጌ መልዕክትን ብዙ ጊዜ የማንነት መለያዎችን ለመስረቅ ስለሚጠቀሙበት ለእንደዚህ አይነት መልዕክቶች ምላሽ በምትሰጥበት ወቅት ወሳኝ የሆነ መረጃን ሳታውቀው ልታጋራ ትችላለህ። ስለዚህ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ ከመስጠት መቆጠብ ይኖርብሃል። አይፈለጌ መልዕክት በደረሰህ ጊዜም ወዲያው ማጥፋት ይኖርብሃል። እንደ Windows መልዕክት ያለ የኢ-ሜይል ፕሮግራም የአይፈለጌ መልዕክትን ለማዛወር እና በቀጣይ ለማጥፋት ይረዳ ዘንድ የአይፈለጌ መልዕክት አቃፊ አካቷል። ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል። ራስህን ከአስጋሪ ጠብቅ ማስገር ከኮምፒውተር ተጠቃሚዎች የግል መረጃን በማውጣት ጎጂ ለሆኑ ዓላማዎች ለመጠቀም የሚደረግ የተለመደ ተግባር ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰው ከባንክ ወይም ከሌላ የሚታመን ድርጅት የመጣ መልዕክት በማስመሰል የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለአንተ ላከልህ ከዚያም እንደ ክሬዲት ካርድ ወይም የይለፍ ቃል ያለ ወሳኝ መረጃን ጠየቅህ። በቀጣይ ይህ መረጃ ስለሚሸጥ ወይም ጥቅም ላይ ስለሚውል ለገንዘብ ኪሳራ ይዳርግሃል። ስለዚህ ለእንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች የግል መረጃህን የያዘ ምላሽ ከመስጠትህ በፊት ህጋዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገባሃል። የተለያዩ የአስጋሪ ድር ጣቢያዎች እንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ይጠቀማሉ። Internet Explorer 8 በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ ከጀርባ ሆኖ የሚሰራ እና አስጋር ድር ጣቢያዎችን ለይቶ የሚያገኝ Microsoft አስጋሪ ማጣሪያ የሚባል ባህሪን አካቷል።
  • 19. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 19 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል። ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ የውይይት ተግባርህ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ የተወሰነ መሆን አለበት። ከአዳዲስ እና ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር ግንኑነትን ማዳበር እንደ የመስመር ላይ አዳኞች እና አጭበርባሪዎች ላሉ ስጋቶች እንድትጋለጥ ያደርግል። ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል። የፈጣን መልዕክት አባሪዎችን ከመክፈት ተቆጠብ የፈጣን መልዕክት ዋንኛ ጎጂ የሆኑ አባሪዎችን ማስተላለፊያ መንገድ ነው። ላኪውን በሚገባ ካላወቅህ በስተቀር በፈጣን መልዕክት የደረሰህን ማንኛውም አባሪ ከመክፈት መቆጠብ አለብህ። የፈጣን መልዕክት አባሪ ኮምፒውተርህን ሊጎዳ የሚችል ቫይረስ ወይም ስፓይዌር ሊይዝ ይችላል። ርዕስ፦ ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች የሚከተሉትን ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው። ዓረፍተ ነገር 1 የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው ማጽዳት 2 ምትክ ውሂብ መያዝ 3 የግል መረጃን ከማጋራት መቆጠብ
  • 20. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 20 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። 4 ጠባቂ ሶፍትዌር መጫን እና ማዘመን 5 የተጠቃሚ ማንነት መለያ መተግበር 6 ከሰርጎ ገብ እና ስፓይዌር መከላከል 7 የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ 8 ተዋናይ ይዘትን ማሰናከል ምርጫ 1 ምርጫ 2 የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ ኮምፒውተርን መጠበቅ ጥያቄ 1 በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ስርዓተ ክወናህን ማዘመን። የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር። ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን። የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ። ጥያቄ 2 በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ኩኪ ቫይረስ የተዋናይ ይዘት ፋይሎች ተውሳክ ጥያቄ 3 ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት። ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ። ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት። በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ። ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
  • 21. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 21 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። መልሶች ምርጫ 1 ምርጫ 2 የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ 8, 6, 3, 1 7, 5, 4, 2 መልስ 1 በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ስርዓተ ክወናህን ማዘመን። የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር። ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን። የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ። መልስ 2 በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ኩኪ ቫይረስ የተዋናይ ይዘት ፋይሎች ተውሳክ መልስ 3 ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ? ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ። ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት። ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ። ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት። በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ።
  • 22. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 22 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች የመስመር ላይ አዳኞች ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች ግለ ሙከራ የትምህርት ክፍሉ መግቢያ ኮምፒውተሮች በትምህርት ቤቶች ፣ ኮሌጆች እና መስሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በቤቶች ውስጥም በብዛት ያገለግላሉ። ኮምፒውተሮችን ለተለያዩ ዓላማዎች ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። ለምሳሌ የቤት ውስጥ ወጪዎችን ለመያዝ ፣ ከቤተሰቦችህና ጓደኞችህ ጋር የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለመመለዋወጥ ፣ በይነመረብን ለመዳሰስ እንዲሁም ጌሞችን ለመጫወት እና ሙዚቃ ለማደመጥ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። እያንዳንዱ የቤተሰብህ አባልም የኮምፒውተሩን የተወሰነ ጥቅም ሊያገኝ ይችላል። ኮምፒውተሮችን በቤት እና በስራ ቦታ የመጠቀም ሁኔታ ከመጨመሩ አንፃር አንተ እና የአንተ ቤተሰቦች ኮምፒውተሮችን እና በይነመረብን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ስለሚያጋጥሙ የተለያዩ ስጋቶች መረዳት አስፈላጊ ነው። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ ኮምፒውተርህን ከእነዚህ ስጋቶች ለመጠበቅ ስለሚረዱ የተለያዩ ርምጃዎች ትማራለህ። የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦ • ክብረ ገመናህን ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ለይተህ ማወቅ • የመስመር ላይ አዳኞች እንዴት እንደሚሰሩ ማብራራት እና • ቤተሰቦችህን ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ የሚረዱ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። ክፍለ ትምህርት 3 ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ
  • 23. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 23 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች እያደገ በመጣው የኮምፒውተሮች እና የበይነመረብ ተፈላጊነት የክብረ ገመና ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት በርካታ ሁኔታዎች አሉ። አንተ እና የአንተ ቤተሰቦች እነዚህን የክብረ ገመና ስጋቶች መከላከል ይጠበቅባችኋል። ራስህን እና ቤተሰቦችህን ከክብረ ገመና ጥቃት ለመከላከል የሚከተሉትን ቀላል ርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ። ማንነትህን ደብቅ የግል መረጃህን ከምታውቃቸው ሰዎች ውጪ ለማንም ከማጋራት ተቆጠብ። ይህ ክበረ ገመናን ለመጠበቅ ምርጥ ህግ ነው። የኢ-ሜይል መልዕክቶችን በምትለዋወጥበት ወይም የፈጣን መልዕክትን በመጠቀም በምትወያይበት ጊዜ የአንተን ወይም የምታውቃቸውን ሰዎች የግል መረጃ ዝርዝሮች አለማሳወቅህን አረጋግጥ። እንዲሁም ኮምፒውተርህን እና የኢ-ሜይል ግንኙነቶችን ለመዳረስ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን ተጠቀም። የኮምፒውተርህን እና የአስፈላጊ መረጃህን ምትክ በየጊዜው ያዝ በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሁሉንም አስፈላጊ እና ወሳኝ መረጃ ምትክ ቅጂ መያዝ ጥሩ ልምድ ነው። አስፈላጊ መረጃ የሚባለው ሰነዶች ፣ የውሂ ጎታዎች ወይም የዕውቂያ መረጃ ሊሆን ይችላል። የመረጃህን ምትክ ለመያዝ እንደ ሰዲ እና ሃርድ ዲስክ ያሉ የተለያዩ የማከማቻ መሳሪያዎች መጠቀም ትችላለህ። በኮምፒውተርህ ላይ ያለን መረጃ ምትክ በየጊዜው የምትይዝ ከሆነ የመጀመሪያው መረጃ በአጋጣሚ በሚበላሽበት ወይም በሚጠፋበት ጊዜ መረጃውን እንደገና ልታገኘው ትችላለህ። እንዲሁም የተያዘውን ምትክ መረጃ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እና የይለፍ ቃላትን እና መስጠራን በመጠቀም ተገኝነቱን መገደብ ይመከራል። የስርዓትህን ወቅታዊ ደህንነት በየጊዜው ፈትሽ የኮምፒውተርህን ወቅታዊ የደህንነት ደረጃ በየጊዜው ፈትሽ። የዘመኑ ስርዓተ ክወናዎች የተለያዩ የደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋቶችን ለመከላከል የኮምፒውተርህን አቅም ለመከታተል የሚረዱ አብረዋቸው የተሰሩ ባህሪያት አሏቸው።ለምሳሌ Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል የኬላ ቅንጅቶችን ለማዋቀር ፣ የሶፍትዌር ማዘመኛ መረሃግብሮችን ለማቀናበር እና በኮምፒውተርህ የተጫነን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ውጤታማነት ለመፈተሽ የሚረዳህ በWindows 7 ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው። የቫይረስ ቅኝቶችን በየዕለቱ አካሂድ በይነመረብ በምትጠቀምበት እያንዳንዱ ቀን ሁሉ ኮምፒውተርህ በቫይረሶች ሊጠቃ የሚችልበት ዕድል አለ። ስለዚህ በኮምፒውተርህ ላይ የቫይረስ ቅኝት በየቀኑ ማካሄድ አስፈላጊ ነው። ኮምፒውተርህን ከአዳዲስ ቫይረሶች ለመከላከልም በኮምፒውተርህ ያለን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር እንደዘመነ ማቆየት ይኖርብሃል። ፀረ ስፓይዌር ስፓይዌር ፕሮግራሞች ወደ ኮምፒውተርህ በድብቅ በመግባት የአንተን እና የቤተሰቦችህን ግላዊ መረጃ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። እነዚህን ጎጂ ፕሮግራሞች ለመከላከል ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ተጠቀም ፤ እንዲሁም ሶፍትዌሩን በየጊዜው አዘምን። የመስመር ላይ ግብይቶችን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ከሚታመኑ ሻጮች ጋር አድርግ የመስመር ላይ ግብይትን በምታደርግበት ጊዜ እንደ ክሬዲት ካርድ ወይም የባንክ ሒሳብ መለያህን ዝርዝሮች ያለ የግል መረጃን ለድር ጣቢያው መስጠት ያስፈልግሃል። ይህ መረጃ ለሌሎች የተጋለጠ ከሆነ ለገንዘብ መጭበርበር ሊዳረግ ይችላል። ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችህን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ብቻ ማድረግ ጠቃሚ ነው። ጥቃትን ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው አሳውቅ ብዙዎቹ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች ስነ-ምግባር የጎደለው ወይም ህገወጥ ተግባራት በደንበኞቻቸው ላይ እንዲደርሱ የማይፈቅዱ የተዘጋጁ ውሎች እና ደንቦች አሏቸው። አንድ ሰው አይፈለጌ መልዕክትን በመላክ የመስመር ላይ ክብረ ገመናህን ለማጥቃት በሚሞክርበት ጊዜ ወይም ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመጠቀም ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው ማሳወቅ ይኖርብሃል። ይህ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንዲወስድ ያስችልዋል። የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ካልታወቁ/ስም የለሽ ላኪዎች አጣራ ከማታውቃቸው ግለሰቦች በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢ-ሜይል መልዕክቶች ሊደርስህ ይችላል። እነደዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት በመባል የሚታወቁ ሲሆን ብዙ ጊዜ ቫይረሶችን ወይም ስፓይዌር የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። የግል መረጃህን ለማግኘት የሚሞክሩ ሰርጎ ገቦችም አይፈለጌ መልዕክት ሊልኩልህ ይችላሉ። ስለዚህ ከእነርሱ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በኢ-ሜይል ሶፍትዌር ፕሮግራሞች አይፈለጌ መልዕክትን ለማገድ የሚረዱ ማጣሪያዎችን መፍጠር ትችላለህ። ለአይፈለጌ መልዕክት በጭራሽ ምላሽ መስጠት የለብህም። ምክንያቱም የማይፈለጉ መልዕክቶች ቁጥር እንዲጨምር እና የግል መረጃን በድንገት እንድታጋራ ሊያደርግህ ይችላል። ከተቻለ ወሳኝ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን መስጥር ምስጠራን መጠቀም የኢ-ሜይል ግንኙነትን ምስጢራዊነት የሚያረጋግጥ ቀላል እና ውጤታማ መንገድ ነው። ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ የመክተት ሂደት ሲሆን በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የተላከ ኢ-ሜይል እንዲያነብ ከታሰበው ሰው በስተቀር ለማንም የማይነበብ ሆኖ ይታያል። ብዙዎቹ የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ፕሮግራሞች ለምሳሌ Windows መልዕክት ይህን የኢ-ሜይል ምስጠራ ባህሪ ያቀርባሉ።
  • 24. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 24 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ርዕስ፦ የመስመር ላይ አዳኞች በይነመረብ በሁሉም የአለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ታዋቂ የሆነ የመገናኛ ዘዴ ነው። ስለ ማንነቱ ወይም ስለ ዓለማዎቹ በቅጡ ከማታወቀው ግለሰብ ጋር ልትግባባ እና ወዳጅነት ልትመሰርት ትችላለህ። በዚህ መሰሉ የበይነመረብ ግንኙነት ሰዎች ወጣቶችን በማለል አግባብ ላልሆነ ወይም አደገኛ ግንኙነት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። በዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች የመስመር ላይ አዳኞች ይባላሉ። የመስመር ላይ አዳኞች በጥቅሉ ልጆችን በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ዒላማቸው ያደርጋሉ። ልጆች የወጣትነት ዕድሜያቸው ሲደርስ ቀስ በቀስ ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጪ እየሆኑ እና አዳዲስ ግንኙነቶችን እየፈለጉ ይመጣሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከእነዚህ ልጆች ጋር የታማኝነት እና የወዳጅነት ግንኙነቶችን ይመሰርታሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከገንዘብ ጋር ለተያያዘ ጥቅም አዋቂዎችንም ኢላማ ሊያደርጉ ይችላሉ። የመስመር ላይ አዳኞች በውይይት ክፍሎች ፣ በፈጣን መልዕክት ፣ በኢ-ሜይል ወይም በውይይት መድረኮች በመጠቀም ሰለባዎቻቸውን ያጠምዳሉ። ከእነዚህ መገልገያዎች ውስጥ የውይይት ክፍሎችን አዳኞች በብዛት ይጠቀሙባቸዋል። የመስመር ላይ አዳኞች ብዙ ጊዜ የአንድ የውይይት ክፍል አባል እንደሆኑ በማስመሰል የሐሰት ማንነት ያቀርባሉ። ለምሳሌ የውይይት ክፍሉ ለልጆች ብቻ የተዘጋጀ ከሆነ የመስመር ላይ አዳኙ በውይይት ክፍሉ ውስጥ ለመሳተፍ ማንነቱን ልጅ አስመስሎ በቀላሉ ሊቀርብ ይችላል። ርዕስ፦ ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ። እነዚህ አዳኞች ለገንዘብ ጥቅም ሲሉ ከአንተ ወይም ከቤተሰብህ አባሎች ጋር ግንኑነት ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ። አዳኞች አንተ እና የቤተሰብህ አባሎችን አግባብ የሌለው ግንኙነት ውስጥ ለማስገባትም ሊሞክሩ ይችላሉ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ ራስህን እና የቤተሰብህን አባሎች ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ ልትከተላቸው የምትችላቸውን የተወሰኑ መመሪያዎች ይዘረዝራል። መመሪያ መግለጫ የአዳኝን ባህሪ የሚገልጹ ምልክቶችን እወቅ የመስመር ላይ አዳኞች አንዳንድ የሚጠበቁ ባህሪያት አሏቸው ፤ እነዚህም እነርሱን በቀላሉ ለመለየት ሊረዱህ ይችላሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወደጅነትን መፍጠር ይወዳሉ። እንዲሁም ሁልጊዜ ወደ አላማቸው ያዘነበለ ፍላጎታቸውን እና ስሜታቸውን ይገልፃሉ። አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ለማቆም እንደዚህ ያለ ባህሪን ለይታችሁ ስለማወቃችሁ ማረጋገጥ ይጠበቅብሃል። በመስመር ላይ ባሉ እንግዳ ሰዎች ለሚመጡ አቅርቦቶች ጥንቃቄ አድርግ የመስመር ላይ አዳኞች በስጦታዎች ወይም በአጓጊ አቅርቦቶች ኢላማዎቻቸውን ያማልላሉ። ለእንደዚህ ዓይነት ስጦታዎች ወይም አቅርቦቶች ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል። እንዲሁም በበይነመረብ የሚቀርቡ ስጦታዎችን እንዲጠራጠሩ የቤተሰብህን አባላት አስተምር። ስለ መስመር ላይ ደህንነት ርምጃዎች ቤተሰብህን አስተምር የቤተሰብህ አባላት የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ከመሆን እንዲርቁ ስለ ትክክለኛው የውይይት ክፍል ባህሪ አስተምራቸው። ገላጭ ባልሆኑ እና ነፃ በሆኑ የገጽ ስሞች እንዲጠቀሙ ንገራቸው። የገጽ ስሞች ትክክለኛ ስምን ፣ ዕድሜን ፣ ፆታን ወይም የመገኛ መረጃን የሚሰጡ መሆን የለባቸውም ምክንያቱም ይህ መረጃ አግባብ ለሌለው ጥቅም ሊውል ይችላል። አንዳንድ የድር ጣቢያዎች በሀሰተኛ አስተያየቶች መረጃን ለማውጣት ይሞክራሉ። ለእንዚህ የድር ጣቢያዎች ምንም ዓይነት የግል መረጃ ካላንተ ፈቃድ እንዳያሳውቁ ለቤተሰብህ አባላት ንገራቸው። እንዲሁም እንደ ስም ፣ የአያት ስም ፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ያሉ የግል መረጃ ዝርዝሮችን በውይይት ክፍሎች እና የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ውስጥ አሳልፈው እንደማይሰጡ አረጋግጥ። የቤተሰብህ አባላት የተጠቀሚ ስማቸውን እና የይልፍ ቃላቸውን ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ለማንም ማጋራት የለባቸውም። ልጆች የድር ጣቢያዎችን ሲጎበኙ መመሪያዎችን ስጣቸው እንደ ወላጅነት ወጣት ልጆች አግባብ ያልሆኑ ወይም ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር የሚያገናኙ የድር ጣቢያዎችን እንዳይጎበኙ ከልክላቸው። ወላጆች ልጆች ማንኛውንም የድር ጣቢያ በሚጎበኙበት ወቅት መመሪያዎችን ለልጆቻቸው እንዲሰጡ ይመከራል። እንደ ወላጅ ልጆች የማይመች ዓይነት ወይም ደስ የማይል ይዘት ያለው የድር ጣቢያን እየጎበኙ ከሆነ እንዲተዉ ወይም ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠጥ ያስፈልጋል። እንዲሁም ከመጠን ያለፈ የግል መረጃን የሚጠይቁ የድር ጣቢያዎችን እንዳይጠቀሙ ልጆችህን አስተምራቸው።
  • 25. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 25 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ልጆች የሚጎበኟቸውን የድር ጣቢያዎችን እወቅ ወላጆች ልጆቻቸው የሚጎበኟቸውን የድር ጣቢያ ዓይነቶች በየጊዜው መፈተሸ ይኖርባቸዋል። ቀድሞ ተጎብኝተው የነበሩ የድር ጣቢያዎችን የአሳሹን ታሪክ በማየት መከታተል ትችላለህ። ወይም የኮምፒውተርን የመስመር ላይ እንቅስቃሴ ለመከታተል የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራችሞችን መጠቀም ትችላለህ። አግባብነት የሌላቸውን የድር ጣቢያዎች ከመዳረስ አግድ የአሳሽህን የይዘት አማካሪ ባህሪ እንዲሰራ በማድረግ የቤተሰብህ አባላት ሊጎበኟቸው የሚችሉትን የድር ጣቢያዎች መቆጣጠር ትችላለህ። ይህን ባህሪ በመጠቀም ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን የድር ጣቢያዎች ልጆች እንዳይጎበኙ ማገድ ትችላለህ። የድር ጣቢያዎችን ለይቶ ለማገድ የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራሞችን መጫንም ትችላለህ። የውይይት እንቅስቃሴዎችን ተቆጣጠር በልዩ ሁኔታ የተሰራ ሶፍትዌር የውይይት እንቅስቃሴዎችን ሊቆጣጠር እና በኮምፒውተርህ ላይ አግባብነት የሌለውን የመረጃ ልውውጥ ሊያመለክት ይችላል። ይህን ሶፍትዌር በመጫን የልጆችህን የውይይት እንቅስቃሴዎች መከታተል ትችላለህ። ርዕስ፦ ግለ ሙከራ እያንዳንዱን ጥንድ ዓረፍተ ነገር እውነት እና ሐሰት የሆኑ ዓረፍተ ነገሮችን ይዟል። እውነት የሆነውን ዓረፍተ ነገር በቀኝ በኩል በሚገኘውና እውነት በሚለው አምድ ስር ምልክት በማድረግ አመልክት። ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት 1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል። 2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም። 3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ። 4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም። 5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል። 6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል። 7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል። 8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም። 9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል። 10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል። 11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም። 12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ። 13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል። 14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም። 15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም። 16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ። 17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም። 18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል። ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።
  • 26. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 26 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት 1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል። 2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም። 3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ። 4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም። 5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል። 6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል። 7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል። 8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም። 9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል። 10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል። 11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም። 12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ። 13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል። 14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም። 15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም። 16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ። 17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም። 18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል።
  • 27. ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና 27 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች የኮምፒውተር ደህንነት ቅንጅቶችን ማወቀር ኮምፒውተርን እንደዘመነ ማቆየት ግለ ሙከራ የትምህርት ክፍሉ መግቢያ ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ስታገናኝ የኮምፒውተርህ ሶፍትዌር እና መረጃ በቀሪው አለም መገኘት የሚችሉ ይሆናሉ። ከበይነመረብ መገናኘት የኮምፒውተርህን በቫይረሶች ፣ ስፓይዌር እና ሰርጎ ገቦች የመጠቃት አቅም ከፍ ያደርገዋል። ነገር ግን በኮምፒውተርህ ላይ ያሉትን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች በማዋቀር እና ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ሶፍትዌርን እንደዘመነ በማቆየት እንዚህን የደህንነት ስጋቶች መቀነስ ትችላለህ። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ በስርዓተ ክወናህ ያሉትን የደህንነት ቅንጅቶች በማዋቀር የኮምፒውተርህን ደህንነት እንዴት ከፍ እንደምታደርግ ትማራለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌርን በራስ ሰር ለማዘመን ኮምፒውተርህን እንዴት እንደምታዋቅርም ያብራራል። የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦ • በኮምፒውተርህ ያሉ የተለያዩ የደህንነት ጥበቃ ቅንጀቶችን ማብራራት እና • ኮምፒውተርህ እንደዘመነ ለማቆየት ያሉትን አማራጮች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። ክፍለ ትምህርት 4 ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት