SlideShare a Scribd company logo
1 of 29
Download to read offline
ሚያዝያ 2011
የስኳር
ኢንዱስትሪ
በኢትዮጵያ
0115527475 info@ethiopiansugar.com www.ethiopiansugar.com
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በሀገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት
የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል
አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች
በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም
ላይ በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና
የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ
የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን
ልማት መደገፍ፡፡
ራዕይ ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም
ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት
ተርታ መሰለፍ፣
ተልዕኮ
እሴቶች •	 የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት
•	 መልካም ሥነ ምግባር
•	 ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው!
•	 ህዝባዊነት መለያችን ነው!
•	 መማር አናቋርጥም!
•	 ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን!
•	 በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው!
•	 አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው!
•	 የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ
ነው!
የስኳር
ኮርፖሬሽን
ተልዕኮ፣ ራዕይ
እና እሴቶች
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር
192/2003 መሰረት ስኳር ኮርፖሬሽን
የተቋቋመበት ዓላማ
•	 የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ
ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣
•	 ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር
ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ
ምርት ውጤቶችን በፋብሪካ ማዘ
ጋጀትና ማምረት፣
•	 ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን
ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ
ማቅረብ፣
•	 አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር
ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት
ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክ
ኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና
ኮሚሽኒንግ ሥራዎች እንዲካሄዱ
ማድረግ፣
•	 ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመ
ተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር
አመራረት ቴክኖሎጂ ጥናትና
ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤ
ቶችን በስራ ላይ ማዋል፣
•	 አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ
ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመን
ግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያ
ስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና
መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬ
ሽን ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲ
ከናወኑ ማድረግ፣
•	 በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስ
ፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና
ማልማት፣
•	 የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት
የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ
አገዳ አብቃዮችን ማበረታታትና
መደገፍ፣
•	 ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን
የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው
አይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍ
ራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው
የትምህርት ተቋማት ጋር መተባ
በር፣
•	 የገንዘብ ሚኒስቴር የሚያወጣ
ውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ
መሰረት በማድረግ ቦንድ
መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና
ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ
ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራ
ደርና መፈራረም፣
•	 አላማውን ከግብ ለማድረስ
የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎ
ችን መስራት ናቸው፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት
ደረጃ ሲታይ የዛሬ 65 ዓመት ገደማ በላንድሮቨር መኪና
ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በገበያ ቀናት ስኳርን ለማስተዋ
ወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡
በወቅቱ ቡናና ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ
ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ
ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡
በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ
ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለችው የኢኮ
ኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት ሆኗል፡፡
በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው
የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆ
ላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት
ከ1943 ዓ.ም. አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሺ ሄክታር የሸ
ንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመ
ረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምት
ገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር
ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946 ዓ.ም. ስራ አስ
ጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በወቅቱ በቀን 1 ሺ 400 ኩንታል
ስኳር እያመረተ ምዕዙን ስኳር እና ባለ 10 ሳንቲም እሽግ
ስኳር ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡
በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ ምርት ከሚ
ያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ
ስለነበር ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞ
የወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ ሰኔ 1953 ዓ.ም. ተቋቁሞ ደስታ
ከረሜላ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ
ሥራ ከጀመረ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ደግሞ በ1955 ዓ.ም.
እዛው ወንጂ ላይ የተቋቋመው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ በቀን
1 ሺ 700 ኩንታል ስኳር ያመርት ነበር፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ
በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ
መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር
ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ
ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750
ሺ ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደ
ነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂ
እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ
ምዕተ ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ በእ
ርጅና ምክንያት እንደቅደም ተከተላ
ቸው በ2004 ዓ.ም. እና በ2005 ዓ.ም.
መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካ
ቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ
ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ስኳር እያመረተ
ይገኛል።
በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረ
ዳው የሆላንዱ ኩባንያ ኤች ቪ ኤ በተ
መሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን
ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት
ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ ሰኔ 26
ቀን 1957 ዓ.ም. በአክሲዮን መልክ
በመመስረት በ1962 ዓ.ም. ፋብሪካ
ውን ሥራ አስጀመረ፡፡
ይሁንና እነዚህ ፋብሪካዎች በ1967
ዓ.ም. በሀገሪቱ በተደረገው የመንግ
ሥት ለውጥ ምክንያት ሙሉ በሙሉ
በመንግሥት ይዞታ ስር ወደቁ፡፡ ይህን
ተከትሎ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሕግ
ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 58/1970
የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖ
ሬሽን ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር
ፋብሪካዎችን ጨምሮ አዲስ ከተማና
አስመራ ከረሜላ ፋብሪካዎችን እንዲያ
ስተዳድር ተደረገ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት
ጋር በተያያዘ በፊንጫአ ሸለቆ በ1967
ዓ.ም. በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ
ጥናት አካባቢው ለስኳር ምርት
አዋጭ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህን ተከትሎም
ለአገሪቱ ሦስተኛ የሆነውን የፊንጫአ
ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት ጠለቅ ያለ
ጥናት እንዲካሄድ ተወስኖ ቡከርስ አግ
ሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ
በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ አማካይነት
ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ ዝርዝር ጥናት
ተካሄደ፡፡
በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ተጓቶ የነ
በረው የፋብሪካው ግንባታ በ1981
ዓ.ም.፤ የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራው
ደግሞ በ1984 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ከስም
ንት ዓመት በኋላ የፋብሪካው ግንባታ
ተጠናቆ በ1991 ዓ.ም. ወደ መደበኛ
የማምረት ስራ ተሸጋገረ፡፡
ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ
ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር
ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል
ግንባታ ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና
አሶሽየትስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያና
በእርሱ ስር የፋብሪካውን ተከላ ያካ
ሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ
የሆላንድ ኩባንያ ሲሆኑ፣ በግንባታው
በርካታ የሀገር በቀል ድርጅቶች ተሳት
ፈዋል፡፡
ልማቱ በዚህ መልክ እየተካሄደ ባለበት
ወቅት የወንጂ ሸዋና የመተሐራ ስኳር
ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአዲስ ከተ
ማንና የአስመራ ከረሜላ
ፋብሪካዎችን ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከ14 ዓመታት
ቆይታ በኋላ በ1984 ዓ.ም. በሕግ ፈረሰ፡፡ በምትኩም በደንብ ቁጥር 88/85
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፤ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና
በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ እራሳቸውን የቻሉ የመንግሥት
ልማት ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡
ኋላም ለስኳር ፋብሪካዎቹ የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱ
ስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል አክስዮን ማህበር በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት
ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር 1990 ዓ.ም. ተቋቋመ፡፡ ከዓ
መታት በኋላም በማዕከሉ ምትክ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ በአዋጅ
ቁጥር 504/98 ተመስርቶ የስኳር ፋብሪካዎቹን በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣
በሥልጠናና በግብይት ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡
በዚህ ጊዜ ውስጥ የኢፌዲሪ መንግሥት የስኳር ልማቱን ለማስፋፋት በማቀድ
በአፋር ክልል አራተኛውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98
አቋቋመ፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ግነባታ በቀን 13 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት
አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባው ይህ ግዙፍ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ከጀመ
ረበት ከ2007 ዓ.ም. አንስቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀም
ርም በ25 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠ
ቀም በዓመት እስከ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እና 27 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል
የማምረት አቅም ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ልማት እንቅስቃሴው በዚህ መልክ
ከቀጠለ በኋላ ከጥቅምት 19 ቀን 2003
ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት
ኤጀንሲ እንዲፈርስ ተደርጎ በምትኩ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር
192/2003 የስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቋመ፡፡
በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በ ስራ አመራር
ቦርድ የሚተዳደር ሆኖ፣ የፌዴራል መን
ግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና
ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
1097/2011 መሰረት ተጠሪነቱ ለመንግ
ሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳ
ደር ኤጀንሲ ሆኗል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት
ከጥቅምት 2003 ዓ.ም. አንስቶ
የስኳር ልማቱ የሚካሄድባ
ቸው አካባቢዎች ማህበረሰቦችን
የልማት ተጠቃሚ በማድረግ፣ የተ
ለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮች
እና ማህበራዊ ተቋማትን በማስ
ፋፋት፣ መጠነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ
ልማት በማካሄድ፣ የፋብሪካዎ
ችን ቁጥር በማሳደግ እና ከፍተኛ
የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ
የተሻለ አፈጻጸም ማረጋገጡን
ማየት ቢቻልም፤ በቤቶች ግንባታ
እንዲሁም የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶ
ችን አቅርቦት በማሳደግ ረገድ ግን
ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ
በት ለማየት ተችሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ
በእቅድ የያዛቸውን ትላልቅ ግቦች
ከማሳካት አንጻር በዘርፉ የተገኙ
ስኬቶችን ለማስቀጠልና ያጋጠሙ
ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ
የለውጥ አሠራሮችን በመተግበር
ላይ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን በሀገር
ውስጥና በውጭ ሀገር የአቅም
ግንባታ ሥልጠናዎችን ለባለሙያ
ዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ
ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ
አገዳ ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ
መፍጨት የሚችል የስኳር ፋብሪካ
ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡
በቂ የቅድመ ዝግጅት ጥናትና የፋይና
ንስ አቅርቦት በሌለበት፣ ልማቱ እንዲ
ካሄድባቸው በታቀዱ አካባቢዎች አስቀ
ድሞ ምንም አይነት የመሠረተ ልማት
አውታሮች ባልተዘረጉበት እንዲሁም
“እየተማርን እንሰራለን” በሚል እሳቤ
በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች
በአንድ ጊዜ 10 ግዙፍና ከፍተኛ የኢንቨ
ስትመንት ካፒታል የሚጠይቁ የስኳር
ፋብሪካዎችን ለመገንባት በተወሰነበት
ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ኢንዱስትሪ
በብሩህ ተስፋና በበርካታ ተግዳሮቶች
ታጅቦ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡
ምንም እንኳ በበርካታ ፈታኝ ሁኔታ
ዎች ሳቢያ በዘርፉ ከተቀመጡ ግቦች
አንጻር በእስካሁኑ የልማት ጥረት
የተገኙ ስኬቶች የተጠበቀውን ያህል
ባይሆኑም የኢንዱስትሪውን ተስፋ
ግን አሻግረው የሚያሳዩ ናቸው ማለት
ይቻላል፡፡ ይህ ሲባል ያለምክንያት አይ
ደለም፤ እስከ 2007 ዓ.ም. መጨረሻ
ድረስ ሦስት ብቻ የነበሩትን ስኳር ፋብ
ሪካዎች አሁን ላይ ስምንት ከማድ
ረስ ባሻገር ነባሮቹን ፋብሪካዎች በማ
ዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማ
ሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነ
ዋል፡፡
በአጠቃላይ በእቅድ ተይዘው ከነበሩ
አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ
የከሰም፣ የተንዳሆ፣ የአርጆ ዲዴሳ፣
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብ
ሪካዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ስኳር
በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ
ውን መሬት በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ
ከነበረበት 30 ሺ 397 ሄክታር ከሦስት
እጥፍ በላይ በማሳደግ ወደ 102 ሺ
741 ሄክታር መሬት ማድረስ የተቻለ
ውም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ
በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ነው፡፡
በተመሳሳይ የመስኖ መሰረተ ልማትን
በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተደረገው
ጥረትም ውጤት አስገኝቷል፡፡ በሌላ
በኩል ከፕሮጀክቱ ግንባታ ጎን ለጎን
የአካባቢውን ማህበረሰብ የልማቱ
ተቋዳሽ ለማድረግ የተጀመረው እንቅ
ስቃሴም በአበረታችነቱ ተጠቃሽ ነው፡፡
የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
•	 ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎን በስኳር
ኮርፖሬሽን እና በውሃ መስኖና
ኢነርጂ ሚኒስቴር በተገነቡ 255
የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ
ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ ጤና
ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ) እና የመ
ሰረተ ልማት አውታሮች (ንጹህ
መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ)
በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ
የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ
እየሆኑ በመምጣታቸው የኑሮ ደረ
ጃቸው መለወጥ ጀምሯል፡፡
•	 ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች
ቅድሚያ በመስጠት በትራክተር
የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው
ውስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት
የላቀ አስተዋጽኦ ካላቸው ግዙፍ ፕሮ
ጀክቶች መካከል አንዱ የስኳር ልማት
ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህን ኤክስ
ፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ ኢን
ዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማ
ነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ
የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡
በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት
ተስማሚ የአየር ንብረት፣ በመስኖ
ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ
የሆነ 1.4 ሚሊዮን ሄክታር ለም
መሬት፣ ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት
እንዲሁም ለመስኖ ልማት የሚውሉ
በርካታ ወንዞች እና ሰፊ ቁጥር ያለው
አምራች የሰው ሃይል ያላት በመሆኑ
መንግሥት ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ
ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም
ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር
ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት
ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15
ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል
አገዳ ይመረታል፡፡ ይህ አሃዝ በአለምአ
ቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ
ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄክ
ታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት
ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄክታር
በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸን
ኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም የ23
ኩንታል ብልጫ አለው፡፡
ይህንን ታሳቢ ያደረገው የኢፌዲሪ መን
ግሥት በወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር
ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት
ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱ
ስትሪ በተለይም ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ
በደቡብ ብ/ብ/ህ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣
በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስ
ፋፋ ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረት በአማራ ክልል በጣና
በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ40 ሺ
ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ
አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ እያ
ንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ
መፍጨት የሚችሉ ሁለት የስኳር ፋብ
ሪካዎች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨ
ማሪም በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ፣ ቤንች
ማጂ እና ካፋ ዞኖች በኦሞ ኩራዝ ስኳር
ልማት ፕሮጀክት በ100 ሺ ሄክታር
መሬት የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግ
ብዓትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳ
ቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት
የሚችሉ ሦስት ፋብሪካዎችን እንዲ
ሁም በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍ
ጨት አቅም ያለውን አንድ ፋብሪካ
ለመገንባት ከተያዘው እቅድ ውስጥ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለትና ሶስት ፋብ
ሪካዎች ስኳር ማምረት ጀምረዋል፡፡
የቀሩት ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች ግንባ
ታም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በወል
ቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት 40 ሺ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ
ኦፕሬተርነት፣ በግምበኛነት፣ በአ
ናጺነት፣ በጥበቃና በመሳሰሉት
ሙያዎች በማሰልጠን በየፕሮጀክ
ቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ ተደር
ጓል፡፡ ወደፊትም ለአካባቢው ተወ
ላጆች የሥራ ዕድል የመፍጠሩ
ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
•	 የአካባቢው ወጣቶች በጥቃቅንና
አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው
በልማቱ እንዲሳተፉና ገቢ እንዲ
ገኙ ድጋፍ ተደርጓል፤አሁንም በመ
ደረግ ላይ ይገኛል፡፡
•	 በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው
ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ
በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀ
ክቶች አካባቢ የሚገኘው ማህበረ
ሰብ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎ
ችን በየአመቱ አምርቶ እንዲጠቀ
ምና በቀጣይም በዘላቂነት ሸንኮራ
አገዳ አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያ
ቀርብ ለማስቻል ከወንጂ ሸዋ
ስኳር ፋብሪካ አገዳ አብቃይ አርሶ
አደሮች (አውትግሮወር) ልምድ
እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡
•	 ስኳር ኮርፖሬሽን ከ2003 ዓ.ም.
እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ በስኳር
ልማቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማ
ኅበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት
ለሚውሉ 174 የማኅበራዊ አገል
ግሎት መስጫ ተቋማት እና የመ
ሰረተ ልማት አውታሮች ግንባታ
ማስፈጸሚያ፣ ለሃብት/ንብረት
ካሳ፣ ለሙያ ሥልጠና እና ለሌሎች
ተያያዥ ሥራዎች 1.2 ቢሊዮን ብር
የሚጠጋ ወጪ አድርጓል፡፡
•	 በአጠቃላይ ልማቱ በይፋ ከተጀ
መረ ከ2003 ዓ.ም. አንስቶ እስከ
2010 ዓ.ም.መጨረሻ ድረስ
በዘርፉ በተፈጠረ ቀጥተኛና ተዘዋ
ዋሪ የሥራ እድል ከ450 ሺ በላይ
ዜጎች በቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንት
ራት የሥራ መደቦች ተቀጥረው
የልማቱ ተቋዳሽ መሆን ችለዋል፡፡
የማህበረሰብ
ተጠቃሚነት
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት
ምንም እንኳ የስኳር ኢንዱስትሪው ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆ
ጠረ ቢሆንም፣
•	 የስኳር ልማቱ በሚፈልገው ፍጥነት አለማደግ፣
•	 ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለቸው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ የህብረ
ተሰቡ የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት፣
•	 የሕዝብ ቁጥር ማደግ እና
•	 ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከመስፋ
ፋት ጋር ተያይዞ የስኳር ፍላጎትና አቅርቦት ሳይጣጣም ቆይቷል፡፡
አሁን ያለው ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት መጠን በዓመት ከ6.5 እስከ 7 ሚሊዮን
ኩንታል ያህል ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ባለፉት ዓመታት ከ3.25 ሚሊዮን እስከ 4
ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ስኳር በሀገር ውስጥ የተመረተ ሲሆን፣ በፍላጎ
ትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላትም በዓመት ከ2 ሚሊዮን
እስከ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ
ይገባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የአንድ ሰው አመታዊ የስኳር ፍጆታ 12 ኪሎ
ግራም እንደሚደርስ ቢገመትም፣ እየቀረበ ያለው መጠን ግን ከ 5 እስከ 6 ኪሎ
ግራም ያህል ነው፡፡
ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ
ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣ
ጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር
ከውጭ መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይ
ቻል ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራ
ችን ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ
የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡
በዚህ መሰረት መንግሥት፡-
•	 የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም፣
•	 በዘርፉ ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣
•	 በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ
እና
•	 ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት “የስኳር አብዮት”
በሚያስብል ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የስኳር
ልማት ፕሮጀክቶች እያካሄደ ነው፡፡
የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የጋራ
ማልማት (joint investment) መስኮች
ኢንቨስትመንት
መ
ንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም
በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን
ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ
ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ
ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል
ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ
ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ስኳር ኮርፖሬሽን በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባ
ንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወ
ቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮነው፡፡
በዚህ መሰረት እስከ ጥር 2011 ዓ.ም. ድረስ 30 ኩባንያዎች ከስኳር ኮርፖሬሽን
ጋር በሽርክና ለመስራት የኩባንያቸውን አቅምና ማንነት የሚገልጽ ማስረጃ /ፕሮ
ፋይል/ አቅርበው ከአንዳንዶቹ ጋር ውይይት ተደርጎ የመግባቢያ ሰነድና የጋራ
ልማት ኮንትራት መፈራረም ተችሏል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በስኳርና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በጋራ ማልማት ወይም
በግል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የተፈጠሩ ምቹ
ሁኔታዎች
•	 የመንግሥት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣
•	 በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መሰረት የተመቻቹ የኢንቨስትመንት ማበ
ረታቻዎች/Incentives ፣
•	 የሀገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት፣
•	 የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል፣
ኢትዮጵያ የሸንኮራ አገዳና የስኳር ተጓዳኝ ምርቶችን በስፋት
ለማምረት፡-
•	 በመሰኖ ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ የሆነ 1.4 ሚሊዮን
ሄክታር ለም መሬት
•	 ተስማሚ የአየር ንብረት
•	 ለመስኖ ልማት የሚውሉ በርካታ ወንዞች
•	 ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት እና
•	 ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች የሰው ኃይል አላት፡፡
•	 ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር
ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15
ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል አገዳ ይመረታል፡፡ ይህ አሃዝ በአለምአ
ቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄ
ክታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄ
ክታር በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸንኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም
የ23 ኩንታል ብልጫ አለው፡፡
•	 የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ (ትላልቅ ግድቦችና የመስኖ መሰረተ
ልማት፣ መንገድ፣ የአየር ማረፊያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን
ወዘተ)፣
•	 102 ሺ ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት፣
•	 በሀገር ደረጃ ስኳር እና ኢታኖል በማምረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስ
ቆጠረ ልምድ፣
•	 ወደ ሥራ የገቡና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ 10 አዳዲስ ግዙፍ የስኳር ፋብሪ
ካዎች እና በስራ ላይ የመገኙ ሦስት ነባር ስኳር ፋብሪካዎች፣
•	 እያደገ የመጣ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ
ሰፊ የሀገር ውስጥ ገበያ፣
•	 በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ የመጡ ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢን
ዱስትሪዎች፣
•	 ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት (የእንስሳት መኖ ማቀነባበርና ማድለብ ይቻላል)፣
የስኳር ዋንኛ ተረፈ ምርቶች (Major Sugar By-products)
•	 ሞላሰስ (Molasses)
•	 ኢታኖል (Ethanol)
•	 ባጋስ (Bagasse)
የሀገራችን ተሞክሮ በስኳር ተጓዳኝ ምርቶች (Sugar Co-
products)
•	 የኤሌክትሪክ ኃይል (Electricity)
•	 ፍራፍሬ (Fruits) ; Orange, Banana, Mango
•	 የእንስሳት መኖ (Animal feed)
•	 ከብት ማድለብ (Cattle Fattening)
•	 ጥጥ (Cotton)
•	 ሩዝ (Rice)
•	 አኩሪ አተር (Soya bean)
•	 ሰሊጥ (Sesame)
•	 ስንዴ (Wheat)
•	 ቦሎቄ (Haricot bean)
•	 ማሾ (Mung bean)
በሽርክና (Joint venture) ወይም በግል ኢንቨስት የሚደረግባ
ቸው መስኮች
•	 የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ፣
•	 ስኳር ፋብሪካ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
•	 የኢታኖል ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
•	 የተለያዩ የስኳር ተጓዳኝ ምርቶች ልማት፣
•	 የመስኖ ዝርጋታ፣ የመሬት ዝግጅት እና የሸንኮራ አገዳ ልማት ፕሮጀክቶች፣
•	 የስኳር ፋብሪካ የመለዋወጫ እቃዎች ማምረቻ ኢንደስትሪ፣
•	 የእንስሳት መኖ ልማትና ማድለብ ሥራ፣
•	 የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ፣
•	 የችፕቦርድ ማምረቻ ፋብሪካ፣
•	 የአልክሆል መጠጥ ኢንደስትሪ፣
•	 የስኳር ማሸጊያ ከረጢት/ጆንያ ማምረቻ ፋብሪካ፣
•	 የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ ወዘተ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በመጀመሪያውና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ ዘመን በዘርፉ የተከናወኑ አበይት ተግባራት
•	 በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ነባር ስኳር ፋብ
ሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡
•	 በእቅድ የተያዘው አመታዊ የስኳር ምርት መጠን ግብ ለጊዜው ሙሉ
በሙሉ ባይሳካም በማስፋፊያ ሥራዎችና በአዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች አማካ
ይነት ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ ከነበረበት 2
ሚሊዮን 903 ሺ 740 ኩንታል ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ተችሏል፡፡
•	 የከሰም፣የተንዳሆ፣ የአርጆ ዲዴሳ፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 አዳዲስ ስኳር
ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር ተችሏል፡፡
•	 የሸንኮራ አገዳ ልማትን በተመለከተም እስከ 2002 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ
በአገዳ የተሸፈነው 30 ሺ 397 ሄክታር መሬት አስከ ታህሳስ 2011 ዓ.ም.
ድረስ ወደ 102 ሺ 74 1 ሄክታር አድጓል፡፡
•	 የኤታኖል የምርት መጠንም በ2002 ዓ.ም. ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሺ
ሊትር ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሺ ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ
መጠን ያለው ኤታኖል ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
•	 የአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡
•	 የትላልቅ ግድቦች፣ የሰፋፊ መስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የመንገድ፣
የቤቶች እና የግዙፍ አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም የመሬት ዝግጅት
ሥራዎች በስፋት ተካሂደዋል፡፡
•	 ይሁንና በመሰረተ ልማት አውታሮች አለመሟላት፣ በመፈጸምና ማስፈጸም
አቅም ማነስ፣ በፋይናንስና የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ በመለዋወጫና ማሽነሪ
አቅርቦት ችግር እና ሌሎች ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት
ማግኘት ባይቻልም፣ በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ
ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ሀገሪቱ ወደፊት ከዓለም 10 ከፍተኛ የስኳር አምራች
ሃገራት ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ የሚያስችሉ
መደላድሎችን ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡
•	 በአጠቃላይ በግንባታ ላይ የሚገኙ አምስት ስኳር ፋብሪካዎች ወደፊት
ተጠናቀው አሁን በማምረት ተግባር ላይ ካሉት ስምንት ፋብሪካዎች ጋር
ሲደመሩ በ13 ስኳር ፋብሪካዎች ሀገሪቱ የምታመርተው አመታዊ የስኳር
መጠን እስከ 22.5 ሚሊዮን ኩንታል ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በስኳር ኢንዱስትሪ የታዩ እድገቶች ንጽጽራዊ መግለጫ
ተ.ቁ እድገቱ የታየበት
ርዕስ
1983 ዓ.ም. 2011 ዓ.ም.
1 የስኳር ፋብሪካዎች
ብዛት
ሁለት (ወንጂ
ሸዋና መተሐራ
ስኳር ፋብሪካዎች)
በማምረት ላይ ያሉ
ስምንት (ወንጂ ሸዋ፣
መተሐራ፣ ፊንጫአ፣
ከሰም፣ ተንዳሆ፣ አርጆ
ዲዴሳ፣ ኦሞ ኩራዝ 2 እና
ኦሞ ኩራዝ 3)
2 በግንባታ ላይ የሚገኙ ፊንጫአ ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ
5፣ ጣና በለስ 1፣ ጣና
በለስ 2 እና ወልቃይት
3 አመታዊ የስኳር ምርት
መጠን
1 ሚሊዮን 496 ሺ
580 ኩንታል
5 ሚሊዮን 200 ሺ
ኩንታል ስኳር ለማምረት
ታቅዷል፤
4. አመታዊ የኤታኖል
ምርት መጠን
አልነበረም 22 ሚሊዮን 355 ሺ ሊትር
ይመረታል ተብሎ ይጠበ
ቃል፤
5. በቀን በአማካይ
የሚፈጭ የአገዳ መጠን
6ሺ 213 ቶን አገዳ አሁን በስራ ላይ የሚገኙ
ስምንት ስኳር ፋብሪካዎች
በቀን በአማካይ 62,500
ቶን የሚጠጋ አገዳ የመፍ
ጨት አቅም አላቸው፤
6. በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ
መሬት
15ሺ 501 ሄክታር 102,741 ሄክታር
7. የሰው ኃይል 11ሺ 452 ቋሚ፣
ኮንትራትና ጊዜያዊ
ሠራተኞች
የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትን
ጨምሮ በስኳር ፋብሪካዎ
ችና ፕሮጀክቶች ከ40 ሺህ
በላይ ቋሚ፣ ኮንትራትና
ጊዜያዊ ሠራተኞች ይገኛሉ፤
8. የመኖሪያ ቤቶች 7ሺ 483 የመኖሪያ
ቤቶች
21 ሺ 147 የመኖሪያ
ቤቶች እና 311 የተለ
ያዩ አገልግሎት መስጫ
ብሎኮች
9. በስኳር ልማት አካባቢ
ዎች ለሚገኙ የማህበ
ረሰብ ክፍሎች የተገነቡ
የማህበራዊ አገልግሎት
መስጫ ተቋማትና የመ
ሰረተ ልማት አውታሮች
ብዛት
31 ተቋማት 255 ተቋማት (ትምህርት
ቤት፣ የጤና ተቋማት፣
ወፍጮ ቤት፣ ንጹህ
መጠጥ ውሃ፣ መንገድ፣
የእንስሳት ጤና ኬላ፣ የእ
ንስሳት ውሃ ማጠጫ፣
የአርሶ/አርብቶ አደር ማሠ
ልጠኛ ማዕከል፣ ህብረት
ሱቅ፣ የእምነት ተቋማት
ወዘተ)
10. በወንጂና አካባቢው በሸ
ንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ (አውት ግሮ
ወርስ) የህብረት ስራ
ማህበራት ታቅፈው
ተጠቃሚ የሆኑ አባላት
ብዛት
በሰባት ማህበራት
የታቀፉ 1ሺ200
አባላት
በ31 ማኅበራት የታቀፉ 9
ሺ319 አባላት
11. በስኳር ልማት ዘርፍ በሸ
ንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ (አውትግሮወር)
የህብረት ስራ ማህበራት
አጠቃላይ ብዛት
በሰባት ማህበራት
የታቀፉ 1ሺ200
አባላት
በ70 ማኅበራት የታቀፉ
15 ሺ 316 አባላት
12. በወንጂና አካባቢው በሸ
ንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ (አውትግሮወር)
የህብረት ስራ ማህበራት
የተሸፈነ የሸንኮራ አገዳ
መሬት ስፋት
1ሺ 20 ሄክታር 7ሺ ሄክታር
13. በስኳር ኢንደስትሪው
በተደራጁ የሸንኮራ አገዳ
አብቃይና አቅራቢ (አው
ትግሮወር) የህብረት ስራ
ማህበራት የተሸፈነ አጠ
ቃላይ የሸንኮራ አገዳ
መሬት ስፋት
1ሺ 20 ሄክታር 17 ሺ 246.82 ሄክታር
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ስ ኳ ር ፋ ብ ሪ ካ ዎ ች
I. ወንጂ ሸዋ
ስኳር ፋብሪካ
በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና
ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ
በ1946 ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ
ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር
ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ
በ1955 ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ
ሌላኛው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም
ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ
የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባን
ያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት
በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡
በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ
ስኳር ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ
ፋብሪካዎች በእርጅና ምክንያት ሥራ
ቸውን እስካቆሙበት ጊዜ ማለትም
ወንጂ እስከ 2004 ዓ.ም. እንዲሁም
ሸዋ እስከ 2005 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ
የነበራቸው አማካይ አመታዊ ስኳር
የማምረት አቅም 75 ሺ ቶን ወይም
750 ሺ ኩንታል ነበር፡፡
ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአ
ዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማ
ስፋፊያ ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ
ዘርፍ ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ
ስራው በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ
ተጠናቆ በ2006 ዓ.ም. መጀመሪያ
ላይ ፋብሪካው ስራ ጀመረ፡፡ አዲሱ
ስኳር ፋብሪካ የተገነባው ነባሮቹ በሚ
ገኙበት የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ
ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ
ማህበር ነው፡፡
ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
የሚገኘው ይህ ፋብሪካ በቀን 6 ሺ 250
ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት ከ1
ሚሊዮን 740 ሺ ኩንታል በላይ ስኳር
የማምረት አቅም አለው፡፡ ወደፊት
የማምረት አቅሙን በሂደት በማሳደግ
በቀን ወደ 12 ሺ 500 ቶን አገዳ እየፈጨ
ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን እስከ
2 ሚሊዮን 227 ሺ ኩንታል እንደሚያ
ሳድግ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡
ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ
ምርት በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን 800
ሺ ሊትር የሚደርስ ኤታኖል ለማምረት
የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ ለመገን
ባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በማ
መንጨት ረገድም 31 ሜጋ ዋት የኤሌ
ክትሪክ ኃይል በማመንጨት 11 ሜጋ
ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ፣ ቀሪውን 20
ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት እያ
ስገባ ይገኛል፡፡
የፋብሪካው የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ
ፕሮጀክት ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና
ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባ
ቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የእርሻ ማስ
ፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ
ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠ
ቃላይ 16 ሺ ሄክታር የሸንኮራ
አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከለማው 12
ሺ 800 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ
መሬት ውስጥ 7 ሺ ሄክታሩ
በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ
በ31 የሸንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ ማኀበራት በታቀፉ 9
ሺ 319 አርሶ አደሮች የለማ
ነው፡፡ በዚህም አባላቱ በሚ
ያገኙት ከፍተኛ ገቢ ከልማቱ
ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለአብነትም
በአንዳንድ ማህበራት በአማካይ
በየ18 ወራት በሚደረግ የትርፍ
ክፍፍል አባላት እንደየስራቸው
መጠን በነፍስ ወከፍ ከ50 ሺ
እስከ 240 ሺ ብር ድረስ ገቢ
ያገኙበትን አጋጣሚ መጥቀስ
ይቻላል፡፡
ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ
በመስኖ የለማ መሬት በማዘጋ
ጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት በማ
መቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ
ድጋፍ በመስጠት አርሶ አደሮቹ
ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብ
ሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲ
ሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
II.መተሐራ ስኳር ፋብሪካ
ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀ
ጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ
በ1962 ዓ.ም. ወደ ስራ የገባው የመ
ተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ
በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከ10
ሺ ሄክታር በላይ በሸንኮራ አገዳ የተሸ
ፈነ መሬት ያለው ይህ ፋብሪካ በቀን
5100 ቶን አገዳ እየፈጨ በዓመት 1.3
ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት
አቅም አለው፡፡
ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ
ፕሮጀክት የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ
ከ2003 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል
በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኤታኖል
የማምረት ዓመታዊ አቅሙም
በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር
ይደርሳል፡፡ በሌላ በኩል "ባጋስ” ተብሎ
ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ 9
ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመ
ንጨት የራሱን የኃይል ፍላጎት እያሟላ
የሚገኝ እድሜ ጠገብ ፋብሪካ ነው፡፡
ስለ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሲነገር
የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን
ማንሳት የግድ ይላል፡፡ ፋብሪካው ካይ
ዘንን በሚገባ በመተግበርና ውጤት
በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው፡፡ ከዚህ
የተነሳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመ
ሪያ ጊዜ በተካሄደው የካይዘን ውድድር
በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ
አንደኛ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ
ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡
በዚህ ብቻ አላበቃም በተመሳሳይ
መስከረም 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ
ሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ
የካይዘን ውድድር ላይ ካይዘንን በማስ
ቀጠል በተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ
በድጋሚ የአንደኝነት የክብር ሜዳሊያ
ዎችንና ዋንጫዎችን ከቀድሞው የኢ
ፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማር
ያም ደሳለኝ እጅ ተቀብሏል፡፡
III. ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካየፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ ርቀት
ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ
ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡
የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካል
ቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ
የቦታው አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥና የአፈር ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር
ጥናት ተካሂዶ አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ የስውዲን፣ የአውስትራሊያና
የስፔን መንግሥታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆ
ናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ ግንባታ ጥር 1981 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡
ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ የሚገኘውን ቦታ ጨምሮ የፊ
ንጫአ ስኳር ፋብሪካ ጠቅላላ ይዞታ (ኮማንድ ኤሪያ) 67 ሺ 98 ሄክታር
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ተጠናቆ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ማምረት ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን፣ በእርሻ
ማስፋፊያ ሥራም ከ19 ሺ ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ ለመሸፈን ተችሏል፡፡
በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 6 ሺ 600 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 1
ሚሊዮን 600 ሺ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ስኳር የማምረት አቅም ያለው
አንድ ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካ ተገንብቷል፡፡ ይህ ደግሞ ነባሩ ፋብሪካ ካለው
አቅም ጋር ተዳምሮ አጠቃላይ በሁለቱም ፋብሪካዎች የሚመረተውን አመታዊ
የስኳር መጠን 2 ሚሊዮን 700 ሺ ኩንታል እንደሚያደርሰው ይጠበቃል፡፡
ፋብሪካው ከሚያመነጨው 31 ሜጋ ዋት ውስጥ ለ17 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ
ቀሪውን 14 ሜጋ ዋት ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ያስገባል፡፡
ነው፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ
በማለፍ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ
ማመንጫነት ከዋለ በኋላ ሸለቆውን
ከሁለት ከፍሎ ወደ ሰሜን በመጓዝ
ከአባይ ወንዝ ጋር በሚቀላቀለው የፊ
ንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ ክፍል
(ዌስት ባንክ) ያለውን 6 ሺ 476.72
ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማ
ልማት እና የፋብሪካ ተከላ በማከና
ወን ነበር ፋብሪካው የካቲት 1990
ዓ.ም. የሙከራ ምርት እንዲጀምርና
ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ወደ
መደበኛ የማምረት ሥራ ውስጥ እን
ዲገባ የተደረገው፡፡
የአካባቢው ከፍታ ከባህር ወለል
በላይ ከ1 ሺ 350 እስከ 1 ሺ 600
ሜትር ይደርሳል፡፡ በሸለቆው ውስጥ
ያለው ከፍተኛው የሙቀት መጠን
31 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን፣ ዝቅተ
ኛው 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይሆናል፡
፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም በአማ
ካይ 1 ሺ 300 ሚሊ ሊትር ይጠጋል፡
፡ ይህም የተፈጥሮ ሁኔታ የፊንጫአ
ስኳር ፋብሪካ አካባቢን "ለምለም
በረሃ" በሚል ልዩ ስም እንዲታወቅ
አድርጎታል፡፡
ፋብሪካው ኢታኖል አምርቶ ከቤን
ዚል ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች
በነዳጅነት እንዲውል ከሚሰጠው
አገልግሎት በተጨማሪ ለሌሎች ኢን
ዱስትሪዎችም በግብዓትነት በማ
ቅረብ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ
ድርሻ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡
የፋብሪካው አጠቃላይ የማስፋ
ፊያ ፕሮጀክት
የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ የማ
ስፋፊያ ፕሮጀክት የተጀመረው በ1998
ዓ.ም. ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በአገዳ
ልማት በኩል በዌስት ባንክ 8 ሺ 300
ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት እና የኢስት
ባንክና ነሼ አካባቢዎችን በማከል ወደ
21 ሺ ሄክታር መሬት ለማሳደግ የታቀደ
ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 7 ሺ ሄክታር በኢስት
ባንክ እንዲሁም 4 ሺ 670 ሄክታር በነሼ
አካባቢ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የፋብሪ
ካውን አገዳ የመፍጨት አቅም በማሳደግ
አመታዊ የስኳር ምርቱን ከ1.1 ሚሊዮን
ኩንታል ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል
እንዲሁም የኤታኖል ምርትን ከ8 ሚሊዮን
ሊትር ወደ 20 ሚሊዮን ሊትር ከፍ ለማድ
ረግ ታቅዶ የማስፋፊያ ሥራው ተካሄደ፡፡
የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በ25 ሺ ሄክታር መሬት ላይ
የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በግዙፍነቱ
እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር
ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተም
ስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300
ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት
ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
በ1998 ዓ.ም. የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የግዙፉ የተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች
ውስጥ ይገኛል፡፡ OIA (Overseas Infrastructure Alliance) በተባለ
የህንድ ኩባንያ የተገነባው ይህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ፋብሪካ የሙከራ
ምርት ከጀመረበት ጥቅምት 2007 ዓ.ም. አንስቶ በመደበኛ የምርት ሂደት
ውስጥ ይገኛል፡፡
ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በቀን 13 ሺ ቶን አገዳ በመ
ፍጨት በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ስኳር ያመርታል ተብሎ
ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የመጀመሪያው ምእራፍ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር ከሚያመነጨው 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 15
ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ 25 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት በማስ
ገባት እንዲሁም 27 ሚሊዮን ሊትር ያህል ኤታኖል በማምረት ዘርፈ ብዙ
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን እንደሚያረጋግጥ ይታመናል፡፡
የመጀመሪያው ምእራፍ ፋብሪካ በግብአትነት የሚጠቀመው የሸንኮራ
አገዳ ልማት በመከናወን ላይ የሚገኘው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው የተ
ንዳሆ ግድብ አማካይነት ነው፡፡ ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ
የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ 60 ሺ ሄክታር መሬት እንደሚያለማ
ይጠበቃል፡፡
ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመ
ቻቸቱም አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ
IV. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
ሁኔታ ተፈጥሮ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 ከ42 ኪ/ሜ በላይ የዋና ቦይና ተያያዥ
ስትራክቸሮች ግንባታ ተከናውኗል፤
•	 22,835 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤
የአገዳ ልማት
•	 17,683 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 8,997 የመኖሪያ ቤቶች እና 146 አገልግ
ሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተው አገልግ
ሎት እየሰጡ ናቸው፤
የማኀበረሰብ ተጠቃሚነት
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣
በኮንትራክተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና አነ
ስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይነት 77,035
ለሚሆኑ ዜጎች በቋሚ፣ በኮንትራትና በጊዜያ
ዊነት የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ 84 የጥ
ቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም ተደራጅ
ተዋል፡፡
እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ አደ
ሮችን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድ
ረግ በዱብቲ 1,667 አባላት ያሏቸውና ህጋዊ
ሰውነት ያገኙ 16 የሸንኮራ አገዳ አምራቾች
መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ከፋብ
ሪካው ጋር በአውትግሮወር ሞዳሊቲ ትስስር
በመፍጠር ሸንኮራ አገዳ በማምረት ላይ
ይገኛሉ፡፡ ለህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት
ሥራዎች በስኳር ኮርፖሬሽን 1.6 ሚሊዮን
ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
V. ከሰም ስኳር ፋብሪካ
በአፋር ክልል በዞን ሦሥት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች በከሰም ቀበና
ሸለቆ ውስጥ ውስጥ የሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣
ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ. ያህል ይርቃል፡፡
ለመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ በ2003 ዓ.ም. የግ
ንባታው ቅድመ ዝግጅት የተጀመረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ ካለው ርቀትና ከአዋጪነት አንፃር ተጠንቶ ኋላ ላይ ራሱን ችሎ እንደ
አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡
ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ብድር ኮምፕላንት በተባለ
የቻይና ኩባንያ የተገነባው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ
የሙከራ ምርቱን አጠናቆ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በመደበኛ ሥራ ላይ ይገኛል፡፡
በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 6 ሺ ቶን
አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ፣ በቀጣይ በሚደረግ የማስፋፊያ ሥራ
10 ሺ ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚ
ፈጭበት ደረጃ እያደገ ይሄዳል፡፡ ፋብሪ
ካው በመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሉ የማ
ምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ 1 ሚሊዮን
530 ሺ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን
500 ሺ ሊትር ኢታኖል በዓመት ያመር
ታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም
26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማ
መንጨት እና 10 ሜጋ ዋቱን ለኦፕሬ
ሽን ተጠቅሞ ቀሪውን 16 ሜጋ ዋት
ለብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) በማቅ
ረብ ተጨማሪ ገቢ የማስገኘት አቅም
አለው፡፡
ወደፊት በሚደረግ የማስፋፊያ ሥራም
ፋብሪካው በዓመት 2 ሚሊዮን 600
ሺ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን
ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ላይ
ሊደርስ እንደሚችል የፋብሪካው የዲዛ
ይን አቅም ያመለክታል፡፡
የፋብሪካው አካባቢ 500 ሚሊዮን
ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም
ባለው የከሰም ግድብ አማካይነት
በ20,000 ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ
አገዳ የሚለማበት ነው፡፡ የአገዳ ልማቱ
ከከሰም ሌላ ቦልሀሞን በተሰኘ አካባ
ቢም ይከናወናል፡፡ በፋብሪካው ከሚለ
ማው የሸንኮራ አገዳ በተጨማሪ ከአሚ
ባራ እርሻ ልማት አክሲዮን ማኅበር ጋር
በተገባው ውል መሠረት ማኅበሩ በስ
ድስት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ
አገዳ እያለማ ለፋብሪካው በማቅረብ
ላይ ይገኛል።
የመስኖ መሠረተ ልማት
ግንባታ
•	 2,946 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደ
ርጓል፤
•	 የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ
ተጠናቋል፤
የአገዳ ልማት
•	 በፋብሪካው አማካይነት 2,823
ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚ
ባራ እርሻ ልማት (አውት ግሮወር)
6 ሺ ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍ
ኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 648 መኖሪያ ቤቶችና 25 የአገልግ
ሎት መስጫ ብሎኮች ተጠናቀው
ለአገልግሎት ቀርበዋል፤
የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት
ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምጣኔ ሃብታ
ዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታ እያስገኘ የሚ
ገኘው የከሰም ፋብሪካ ግንባታው ከተ
ጀመረ ጊዜ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣ በኮን
ትራክተሮች እንዲሁም በ29 ጥቃቅ
ንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይ
ነት 42,773 ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣ
ቶችና ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ
የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምክንያት
ሆኗል፡፡
ከዚህ ባሻገር 399 አባላት ያሏቸው
አምስት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ መሠ
ረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ከፋብ
ሪካው ጋር በአውትግሮወር ሞዳሊቲ
ትስስር በመፍጠርና ሸንኮራ አገዳ
አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ
የልማቱ ተቋዳሽ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
VI.አርጆዲዴሳስኳርፋብሪካ
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀ
ክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ
ክልል በምስራቅ ወለጋ፣ በቡኖ በደሌና
በጅማ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ
ከአዲስ አበባ ነቀምት በደሌ በሚወስ
ደው መንገድ በ395 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
ይገኛል፡፡
የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ
በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር
ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ
አማካይ የዝናብ መጠኑም 1400 ሚሊ
ሜትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ሥርጭቱ
ደግሞ ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘል
ቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ
ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ
አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ
ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ
እንዲሆን አስችሎታል፡፡
AL-Habasha Sugar Mills PLC
ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ በ2005
ዓ.ም. በግዢ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን
ይዞታነት የተሸጋገረው ይህ ፋብሪካ
በ16 ሺ ሄክታር መሬት የሚለማ የሸ
ንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም
በቀን 8 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን በተረከበ
በት ወቅት ሳይጠናቀቅ የቆየ የፋብሪካ
ግንባታ ሥራን በአጭር ጊዜ ውስጥ
በማጠናቀቅ እንዲሁም በወቅቱ ያልነ
በሩ የልማት ሥራዎችን (የህዝብ አደረ
ጃጀት ሥራ፣ የግድብ ግንባታ፣ የመሬት ዝግጅት፣ የመስኖና የአገዳ ልማት፣ የማ
ህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች) በማ
ከናወን ፋብሪካውን ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ምርት ማስገባት ተችሏል፡፡
ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ከፍተኛ ኢታኖል የማምረት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ
ባጋስ ከተባለ ተረፈ ምርት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል
አልፎ ቀሪውን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) እንደሚያስገባ ይጠበቃል፡፡
አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በቀድሞው የኢፌ
ዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ስኳር በማምረት ላይ
ይገኛል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 ፋብሪካው ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያውለውን ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ ያገኛል፤
•	 በኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን አማካይነት ለፋብሪካው ግብዓት
የሚውል የሸንኮራ አገዳ ለማልማት በዲዴሳ ወንዝ ላይ ግድብ እየተገነባ
ነው፤
•	 በተጨማሪ 2 ሺ 300 ሄክታር መሬት የሚያለማ የመስኖ መሠረተ ልማት
ግንባታ በኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ተካሂዶ 1,600 ሄ/ር መሬት
ውሃ ገብ ተደርጓል፤
የአገዳ ልማት
•	 3 ሺ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 124 የመኖሪያ ቤቶችና 11 አገልግሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተዋል፤
የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት
በምስራቅ ወለጋና በቡኖ በደሌ ዞኖች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ
ማህበራዊ ተቋማት ተገንብተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶም
ለ17,547 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ በተለይም የአካባቢው ወጣቶች ልማቱ
ባስገኘው የሥራ እድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠ
ናዎች ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር 71 የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች በአካባቢው ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማ
ርተዋል፡፡
በሌላ በኩል ለአገዳ ማሳ ማስፋፊያ ከአርሶ አደሩ ለተገኘ መሬት የሃብት ንብረትና
ምርት ካሳ ክፍያ እንዲሁም ለህብረተሰብ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች 65.66
ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
VII. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2
ስኳር ፋብሪካ
በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ
ከአዲስ አባባ 825 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6.67 ቢሊዮን
ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም. ግንባታው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ
ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 14/2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርቱን ካሳካ በኋላ
ወደ መደበኛ ምርት ተሸጋግሯል፡፡
ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ
10,000 ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፋብሪካው እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ አንጻርም የአለም ገበያ ፍላጎትን መሰረት
በማድረግ ጥሬ ስኳር (Raw sugar)፣ ነጭ ስኳር (Plantation white sugar)
እና የተጣራ ስኳር (Refined sugar) ማምረት ይችላል፡፡
VIII. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3
ስኳር ፋብሪካ
የኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ
ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 874 ከ.ሜ ይርቃል፡፡ ፋብሪካው ጥቅምት
4 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቆ
ሥራ ጀምሯል፡፡
የፋብሪካው ግንባታ በይፋ የተጀመረው መጋቢት 2/2008 ዓ.ም ከቻይና ልማት
ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ነው፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና
ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ 10,000 ኩንታል ስኳር የማ
ምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ አንጻርም
የአለም ገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ጥሬ ስኳር (Raw sugar)፣ ነጭ ስኳር
(Plantation white sugar) እና የተጣራ ስኳር (Refined sugar) ማምረት
ይችላል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ወደ ሥራ መግባት ስኳር የሚያመርቱ
ትን ፋብሪካዎች ቁጥር ወደ ስምንት (ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰም፣
ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3) አድርሶታል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
I. ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን (ሰላማጎ እና ኛንጋቶም ወረዳዎች)፣ በቤንች ማጂ ዞን
(ሱርማ እና ሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች) እና በካፋ ዞን (ዴቻ ወረዳ) የተመረጡ አካባ
ቢዎች እየተካሄደ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡
በፕሮጀክቱ ስር እየተገነቡ ከሚገኙ አራት የስኳር ፋብሪካዎች በተሽከርካሪ ለመ
ድረስ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና - አርባ ምንጭ - ጂንካ መስመር ከ825-954 ኪሎ
ሜትር ወይም ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ - አርባ ምንጭ - ጂንካ መንገድ ከ859-
988 ኪሎ ሜትር መጓዝን ይጠይቃል፡፡ በአየር ትራንስፖርት ከሆነ ደግሞ ከአዲስ
አበባ ጂንካ ለአንድ ሰዓት ያህል በመብረር ከጂንካ ፋብሪካዎቹ ያሉበት ድረስ
ከ80-220 ኪሎ ሜትር በተሽከርካሪ መጓዝ የግድ ይላል፡፡
በፕሮጀክቱ በ100 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ተጠቅመው
በቀን 60 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው አራት ስኳር ፋብሪካዎች እየተ
ገነቡ ሲሆን፣ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ ሶስቱ እያንዳንዳቸው በቀን
12 ሺ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 2 ሚሊዮን 500 ሺ ኩንታል ስኳር እና እያ
ንዳንዳቸው በዓመት 28 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም እያንዳንዳቸው ከሚያመነጩት 45 ሜጋ ዋት ውስጥ 29 ሜጋ ዋቱን
ወደ ብሔራዊ ቋት ይልካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ አንደኛው ፋብሪካ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት
5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እና 56 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል እንደሚያመርት
ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪ ከሚያመነጨው 90 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል
ውስጥ 32ቱን ለራሱ ተጠቅሞ 58 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ ቋት እንደሚልክ
ይጠበቃል፡፡
ከእነዚህ አራት ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ በቻይናው ኮምፕላንት ኩባንያ የተገነ
ቡት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት እና ቁጥር ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት
ገብተዋል፡፡ የተቀሩት የቁጥር አንድና አምስት ስኳር ፋብሪካዎች በግንባታ ላይ
ናቸው፡፡
የኢንቨስትመንት ወጪ
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ ለሚገኙ አራት ስኳር ፋብሪካ
ዎች እስከ መጋቢት 30/2010 ዓ.ም ድረስ ለካፒታል ኢንቨስትመንት (ለመስኖ
መሰረተ ልማት፣ ለመሬት ዝግጅት፣ ለአገዳ ልማት፣ ለቤቶች ግንባታ፣ ለፋብሪካ
ግንባታ ወዘተ)፣ ለፕሮጀክቶች ቅድመ ኦፕሬሽንና ለሥራ ማስኬጃ 34.8 ቢሊዮን
ብር የሚጠጋ ወጪ ተደርጓል፡፡
የማህበሰብ ተጠቃሚነት
ስኳር ኮርፖሬሽን ስኳር ከማምረት ባሻገር በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀ
ክት አካባቢ የሚኖረውን የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻልና በዘላቂነት
የልማት ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ ቀጣናዊ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት እንዲ
ቻል በርካታ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ መጠነ ሰፊ
ሥራዎችን ከደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል መንግሥት ጋር በመቀናጀት ሲሰራ ቆይታል፡፡
በዚህ መሰረት ኮርፖሬሽኑ የመስኖ መሰረተ ልማት ወጪን ሳይጨምር ለአካባ
ቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት 86 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አድ
ርጓል፡፡ ይህ በመሆኑም ከ50 በላይ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና
የመሰረተ ልማት አውታሮች (ት/ቤት፣ ጤና ኬላ፣ የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ጽ/ቤት፣
የቀበሌ ጽ/ቤት፣ የህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ የእንስሳት ጤና
ኬላ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ በመስኖ የለማ መሬት
ወዘተ) ተገንብተው ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የካሳ ክፍያ
በኮፈር ዳም የመስኖ ግድብ ምክንያት የንብ ቀፎ እና ሰብላቸው ለተነ
ካባቸው አርብቶ አደሮች የንብ ቀፎ ግምት እና የምርት ማካካሻ ካሳ 1
ሚሊዮን 141 ሺህ 165 ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡
የህዝብ ውይይቶችና ሞብላይዜሽን
በልማቱ አካባቢ ከሚገኘው የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማቱ ጥቅ
ሞችና ፋይዳ ዙሪያ በተለያየ ጊዜ ለተደረጉ ውይይቶች 2 ሚሊዮን 584
ሺ 309.30 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
የክህሎት ስልጠና
የአካባቢው ህብረተሰቡ ልማቱ በሚፈጠረው የስራ እድል ተሳታፊና
ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ለመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች
ብር 2 ሚሊዮን 866 ሺህ 658 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
የሥራ ዕድል
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ከ2003 ዓ.ም. አንስቶ በፕሮጀክት፣ በኮንትራክ
ተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በቋሚ፣ በኮንትራትና
ጊዜያዊነት ከ110 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶችና ዜጎች
የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከ300 በላይ የጥ
ቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን አደራጅቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ተችሏል፡፡
ሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኅ
በራት (አውትግሮወር)
በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙትን አርብቶ አደሮች በዘላቂነት የልማቱ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በአራት ማኅበ
ራት ለተደራጁ 2 ሺ 205 አባ/እማ ወራዎች ለእያንዳንዳቸው በመስኖ
የለማ 0.75 ሄ/ር መሬት በመስጠት በድምሩ 1 ሺ 653.75 ሄ/ር
መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በሽያጭ እንዲያ
ቀርቡ ሁኔታዎች እየተመቻቸላቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባገኙት
መሬት በቆሎና የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርተው መጠቀም ጀምረዋል፡፡
በዚህም ወደ ከፊል አርሶ አደርነት ሽግግር ላይ ይገኛሉ፡፡
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ
በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ
ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 863
ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ
ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC)
መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮን
ትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት
ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ
ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት
ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበረው
ኮንትራት በ2010 ዓ.ም. እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ
ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋ
ገጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈጻጸም 80%
ነበር፡፡
በቀጣይ የፋብሪካው ቀሪ የግንባታ ሥራ ልምድ
ባለውና በተመረጠ የውጭ ሀገር ኮንትራክተር የሚ
ጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ
በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12 ሺ ቶን
አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ
በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቷም ወረዳ የሚካለለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር
ፋብሪካ ከአዲስ አባባ በ954 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ JJIEC በተባለ የቻይና
ኩባንያ ከህዳር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ የሚገኘው ይህ
ፋብሪካ፣ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ
ይጠበቃል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት የመስኖ መሠረተ
ልማት ግንባታ
በፕሮጀክቱ በዋናነት የኦሞ ወንዝን
መሠረት በማድረግ 100 ሺህ ሄክታር
መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት
የሚያስችል መጠነ ሰፊ የመስኖ
መሰረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደ
ይገኛል፡፡
ጊዜያዊ ግድብ/Coffer
Dam
ለፕሮጀክቱ ውሃ ለማቅረብ በኦሞ
ወንዝ ላይ ጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም)
ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ
ነው፡፡
የዋና ቦይ ግንባታ
በኦሞ ኩራዝ የሸንኮራ አገዳ ለማልማት
ከኦሞ ወንዝ በስተግራ (left bank)
የ55 ኪ.ሜ ዋና ቦይ (main canal)
የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠናቆ አገ
ልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ በተ
መሳሳይ በቀኝ በኩል (right bank)
እየተገነባ ከሚገኘው 134 ኪ.ሜ የዋና
ቦይ (main canal) ግንባታ ውስጥ 43
ኪሎ ሜትሩ ተጠናቆ አገልግሎት በመ
ስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የቀሪው
91 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ቁፋሮ ተጠናቆ የስ
ትራክቸር ስራ ይቀራል፡፡
በአጠቃላይ በኦሞ ኩራዝ መስኖ
ልማት ፕሮጀክት የተጀመረውን የዋና
ቦይ የመሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎች
ተያያዥ ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ
አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት 22.3
ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡
የሸንኮራ አገዳ ልማት
በፕሮጀክቱ እስካሁን 30 ሺህ ሄክታር
መሬት ውሃ ገብ ማድረግ የተቻለ
ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 16 ሺህ ሄክታር
መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ተተክሏል፡፡
የቤቶች ግንባታ
በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1,140 የመኖ
ሪያ ቤቶች እና 52 አገልግሎት መስጫ
ብሎኮች ተገንብተው አገልግሎት
እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
II. ጣና በለስ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት
ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ
ወረዳ ላይ የተቋቋመ ሲሆን፣ የፕሮጀ
ክቱ ጽ/ቤትም ፋንዲቃ ከምትባለው
የጃዊ ወረዳ ከተማ አጠገብ ከአዲስ
አበባ በ650 ኪ.ሜ እንዲሁም ከባህር
ዳር በ225 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን
12 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ያላቸው ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች በኢ
ትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ
ኮርፖሬሽን (METEC) ግንባታቸው
ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ
የግንባታ መጓተት ምክንያት በስኳር
ኮርፖሬሽንና በሜቴክ መካከል በ2004
ዓ.ም. ተደርሶ የነበረው የጣና በለስ
ቁጥር 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎች የግ
ንባታ ውል እንደ ቅደም ተከተላቸው
በ2010 ዓ.ም. እና 2009 ዓ.ም. በመ
ንግሥት ውሳኔ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡
የፋብሪካዎቹ ቀሪ የግንባታ ሥራዎች
ተጠናቀው ወደ ምርት ሲገቡ
በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚ
ለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት
ይጠቀማሉ፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት
የሚውለው የመስኖ ውሃ የሚገኘው
በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውሃ መቀ
ልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡
ፋብሪካዎቹ ሙሉ የማምረት አቅማ
ቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው
በዓመት 2 ሚሊዮን 420 ሺ ኩንታል
ስኳር እና 20 ሚሊዮን 827 ሺ ሊትር
ኢታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸ
ዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካዎቹ
የተጣራ (ሪፋይንድ) ስኳር ለማምረት
ዲዛይን ከመደረጋቸው ባሻገር እያንዳ
ንዳቸው 45 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ
ኃይል የማመጨንት አቅም ሊኖራቸው
እንደሚችል ታሳቢ ተደርጓል፡፡ ከዚህ
አኳያ እያንዳንዱ ፋብሪካ 16 ሜጋ ዋት
ለኦፕሬሽን ተጠቅሞ ቀሪውን 29 ሜጋ
ዋት ወደ ብሔራዊ ግሪድ በመላክ ገቢ
ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ
በቀጣይ የፋብሪካው ቀሪ የግንባታ ሥራ ልምድ ባለውና በተመረጠ የውጭ ሀገር
ኮንትራክተር የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ
ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ
ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬ
ሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004
ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት
መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18
ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እን
ደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና
በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት
በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበ
ረው ኮንትራት በ2010 ዓ.ም. እንዲቋ
ረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ ሲቋረጥ በስኳር
ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋገ
ጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈ
ጻጸም 65% ነበር፡፡
ጣና በለስ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ
በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
(METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋ
ብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ
ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ
ከሜቴክ ጋር የነበረው ኮንትራት በ2009 ዓ.ም. እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ
ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋገጠው የፋብሪካው የግንባታ
ሥራ አፈጻጸም 25% ነበር፡፡
በአሁኑ ወቅት አንድ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ፋብሪካውን ለመግዛት ፍላጎት
ያሳየ ሲሆን፣ ከስምምነት ላይ ከተደረሰም ፋብሪካው ወደ ግል ይዞታነት የሚሸ
ጋገር ይሆናል፡፡
ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመስኖ መሠረተ
ልማት ግንባታ
ለፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚሆን የመስኖ ውሃ የተጠለፈው ከበለስ
ወንዝ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 30 ኪ/ሜ ርዝመት ያለውና 60 ሜ/ኩ
(cubic metre) ውሃ በሰከንድ ማስተላለፍ የሚችል የወንዝ መቀልበሻ (ዊር)፣
መቆጣጠሪያ፣ የደለል ማስወገጃ እና የዋና ቦያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመ
ስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከተወሰኑ ማሳዎች በስተቀር አብዛኛው የ--እርሻ ማሳ ውሃ
የሚጠጣው በኦቨር ሄድ ኢሪጌሽን (በስፕሪንክለር) የመስኖ ዘዴ ነው፡፡
•	 16,146 ሄ/ር ማሳ ውሃ ገብ ተደርጓል፤
የአገዳ ልማት
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 13 ሺ 248 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1 ሺ 469 መኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ
ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
በፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማቱ ጥቅምና ፋይዳ
ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት ውይይቶች በመደረጋቸው ልማቱን የጋራ ለማድረግ የሚ
ያግዙ ሥራዎችን ለማከናወን ተችሏል፡፡ በዚህም ተግባር ለልማቱ ተነሽ ለሆኑ የህ
ብረተሰብ ክፍሎች ት/ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ መካካለኛ የመጠጥ ውሃ ተቋማት፣
መንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት
ተገንብተው አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ለሀብት ንብረት፣ ለቋሚ ተክል እና ለእምነት ተቋማት ግምት
ካሳ 152.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ የሥራ ዕድልን በተመለከተም ፕሮ
ጀክቱ ከተጀመረ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣ በኮንትራክተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይነት ለ91 ሺ 493 የአካባቢው ወጣቶችና ዜጎች
ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
1,253 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው የሥራ ትስስር ተፈ
ጥሯል፡፡
በአጠቃላይ በስኳር ኮርፖሬሽን ለህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች
178.68 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
III. ወልቃይት ስኳር ልማት
ፕሮጀክት
የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ በ1 ሺ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በትግራይ ክልል
በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ
የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ያለው ይህ ፋብሪካ CAMC በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ነው፡፡
በዚህ መሰረት ፋብሪካው በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት
አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን
654 ሊትር ኢታኖል ያመርታል ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከሚያመነ
ጨው 120 ሜጋ ዋት ውስጥ 56 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ 64 ሜጋ ዋቱን ወደ
ብሔራዊ ግሪድ በመላክ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፕሮጀክቱ ለአገዳ ልማት የሚያስፈልገውን የመስኖ ውሃ አቅርቦት ከተከዜ፣
ከቃሌማ እና ከዛሬማ ወንዞች የሚያገኝ ይሆናል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 3.5 ቢሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው “የሜይ-ዴይ” ግድብ
በዛሬማ ወንዝ ላይ እየተገነባ ነው፡፡ ግድቡ ሲጠናቀቅ 840 ሜትር ስፋት እና
135.5 ሜትር ቁመት ይኖረዋል፤
•	 ከግድብ ግንባታው ጎን ለጎን በጠብታ መስኖ 7 ሺ ሄ/ር መሬት ለማል
ማት NETAFIM ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ የመስኖ መሠረተ ልማት ሥራ
ተቋራጭ ጋር ውል ተገብቶ ሥራው ተጀምሯል፤
•	 የ10 ኪ/ሜትር የዋና ቦይ (Main canal) ግንባታ ተጠናቋል፤
•	 3 ሺ ሄ/ር መሬት ከቃሌማ ወንዝ በፓምፕ ጠልፎ በsprinkler ለማልማት
የግንባታ ሥራው እየተከናወነ ነው፤የመስኖ ውሃው እስከሚደርስ ድረስም
የጥጥ ልማት እየተካሄደ ይገኛል፤
•	 260 ሄ/ር መሬት ለዘር አገዳ ውሃ ገብ ሆኗል፤
የአገዳ ልማት
•	 ውሃ ገብ ከሆነው መሬት ውስጥ 140 ሄክታሩ ላይ የዘር አገዳ ተተክሏል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 1,066 መኖሪያ ቤቶችና 53 የአገልግሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተው ለአ
ገልግሎት ቀርበዋል፡፡
የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
የአካባቢው ህብረተሰብ ልማቱ በሚ
ፈጠረው የሥራ እድል ተሳታፊና
ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የመለስ
ተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሰጥ
ተውት ለ84 ሺ 659 የአካባቢው ወጣ
ቶችና ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ
የሥራ ዕድሎች ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም 161 የጥቃቅንና አነስ
ተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲደራጁና
በሥራ እንዲተሳሰሩ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል በልማቱ ምክንያት ተነሺ
ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሃብት
ንብረት ግምት ካሳ እና የምርት
ማካካሻ ካሳ ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ ከዚህ
ባሻገር በፕሮጀክቱ ክልል ውስጥ ይኖሩ
ለነበሩና በመጀመሪያው ዙር ወደ
ቆራሪት ሰፈራ መንደር መልሰው ለተቋ
ቋሙ 2 ሺ 621 የህብረተሰብ ክፍሎች
ስምንት የማህበራዊ አገልግሎት
መስጫ ተቋማት (ት/ቤቶች፣ የሰውና
እንስሳት ህክምና መስጫ ተቋማት፣
የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ወዘተ)፣ 14
የመጠጥ ውሃ ተቋማትና 62 ኪሎ
ሜትር መንገድ ተገንብቶላቸው አገል
ግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻች
ተዋል፡፡
በአጠቃላይ በስኳር ኮርፖሬሽን ለህ
ብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት
ሥራዎች 407.68 ሚሊዮን ብር ወጪ
ተደርጓል፡፡
ስኳር በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች/
ፕሮጀክቶች
ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት
አቅም /በቀን፣ በቶን
የሚገኝበት
ክልል
ለሸንኮራ አገዳ
የሚውል መሬት/በሄ
ክታር
ወንጂ ሸዋ 6,250 ኦሮሚያ 12,800
መተሐራ 5,372 ኦሮሚያ 10,230
ፊንጫአ 12,000 ኦሮሚያ 21,000
ተንዳሆ 13,000 አፋር 25,000
ከሰም 6,000 አፋር 20,000
አርጆ ዲዴሳ 8,000 ኦሮሚያ 16,000
ኦሞ ኩራዝ
ቁጥር 2
12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000
ኦሞ ኩራዝ
ቁጥር 3
12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000
ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ የመ
ፍጨት አቅም /
በቀን፣ በቶን
የሚገኝበት ክልል ለሸንኮራ አገዳ
የሚውል መሬት/
በሄክታር
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር
1
12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር
5
24,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 40,000
ጣና በለስ 1 12,000 አማራ 20,000
ጣና በለስ 2 12,000 አማራ 20,000
ወልቃይት 24,000 ትግራይ 40,000
በግንባታ ላይ የሚገኙ
ፋብሪካዎች/ፕሮጀክቶች
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ምርምርና ልማት ዋና ማዕከል
በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ሥራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ
የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአም
ስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ጠንካራ ድጋፍ
ይሰጥ ነበር፡፡
ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ.
ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለ
ክታሉ፡፡ ኋላ ላይ የፋብሪካዎቹን ወደ መንግሥት ይዞታነት መሸጋገር ተከትሎ የም
ርምር ሥራው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ
ቁጥር 192/2003 ሲቋቋም ለምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥ
ቶት የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
•	 ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የማምረቻ ወጪን መቀነስ የሚያስችል
እንዲሁም ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied research)
በማካሄድ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ ተችሏል፤
•	 የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል የተገኘው የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ
ስኳር ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል፤
•	 በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እር
ምጃዎች (optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት ተሰ
ጥቷል፤
•	 ሥራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙ
ትን ፋይዳ እና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ በመገምገም
አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችና ስትራቴጂዎች ተነድፈዋል፤
•	 ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር
ይዘት ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን እን
ዲሁም የተሻሻሉ የሸንኮራ አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና
ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በማስተዋወቅ
ሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፤
•	 በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ደረጃቸው (ስታንዳ
ርድ) ሳይጓደል ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሠራር በመቀየስ
ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመርና ለማስተግበር ተሞክሯል፤
•	 በስኳር ቴክኖሎጂ የተለያዩ የምርምር ውጤቶችን በማው
ጣት የስኳር ብክነትን (Sugar loss) እና የማምረቻ ጊዜ ብክነ
ትን (Down time) በመቀነስ የስኳር ግኝት አቅምን (Overall
recovery) የመጨመር ሥራዎች ተከናውነዋል፤
•	 ከስኳር ተረፈ ምርቶችና ከኤታኖል ተያያዥ ምርቶችን ለማም
ረት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅና ማላመድ ተችሏል፤
•	 ኢንዱስትሪውን በሠለጠነና ውጤታማ በሆነ የሰው ኃይል ለመ
ደገፍ የሚያስችሉ ሥልጠናዎች ለባለሙያዎች ተሰጥተዋል፤
ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ወንጂ ላይ የሚገኘው የምርምርና
ልማት ዋና ማዕከል እነዚህን ተግባራት የበለጠ በብቃት ለመወጣት
በ2008 ዓ.ም. በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡
በዚህ መሰረት ዋና ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣
ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና
በለስ፣ ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የምር
ምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር
ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥና ከአካ
ባቢ ጋር ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በአስተማማኝ
ደረጃ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሶስት ፍኖተ ካርታዎችን (በባዮሪፋ
ይነሪ፣ በስኳር ቴክኖሎጂ እና በደቂቅ ዘአካላት) በማዘጋጀት ወደ
ትግበራ ተገብቷል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

More Related Content

What's hot

Maple Leaf Cement Company Ltd 2
Maple Leaf Cement Company Ltd 2Maple Leaf Cement Company Ltd 2
Maple Leaf Cement Company Ltd 2Talha Choudhary
 
Analysis of Pakistan cement industry 2019
Analysis of Pakistan cement industry 2019Analysis of Pakistan cement industry 2019
Analysis of Pakistan cement industry 2019Sãäd ÑäSîr
 
supply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cementsupply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cementZuhair Bin Jawaid
 
Sugar industry in pakistan
Sugar industry in pakistanSugar industry in pakistan
Sugar industry in pakistanphulcritude
 
Management in cement industry in pakistan
Management in cement industry in pakistanManagement in cement industry in pakistan
Management in cement industry in pakistanPari Doll
 
Final project Report on cement industry
Final project Report on cement industryFinal project Report on cement industry
Final project Report on cement industryMudassar Nazar
 
Cement industry of pakistan
Cement industry of pakistanCement industry of pakistan
Cement industry of pakistanSaad Afridi
 
DG cement Operations management
DG cement Operations management DG cement Operations management
DG cement Operations management Mubasher Fiaz
 
Mineral Resources of Afghanistan
Mineral Resources of AfghanistanMineral Resources of Afghanistan
Mineral Resources of AfghanistanPierre Memheld
 
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptx
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptxA study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptx
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptxSyedaRinumFatima
 
Cement Industry of Pakistan
Cement Industry of PakistanCement Industry of Pakistan
Cement Industry of PakistanNadeem Akram
 
Minerals of somalia
Minerals of somaliaMinerals of somalia
Minerals of somaliaNuuh Hubiye
 
Lucky cement factory internship report
Lucky cement factory internship reportLucky cement factory internship report
Lucky cement factory internship reportMohammad Younus
 
Fauji Fertilizer Corporation
Fauji Fertilizer CorporationFauji Fertilizer Corporation
Fauji Fertilizer CorporationMuneeb Abid
 
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENET
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENETMinería en argentina, Geografia 3 4 ENET
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENETLuciano Chiosso
 

What's hot (20)

Maple Leaf Cement Company Ltd 2
Maple Leaf Cement Company Ltd 2Maple Leaf Cement Company Ltd 2
Maple Leaf Cement Company Ltd 2
 
Analysis of Pakistan cement industry 2019
Analysis of Pakistan cement industry 2019Analysis of Pakistan cement industry 2019
Analysis of Pakistan cement industry 2019
 
supply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cementsupply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cement
 
Sugar industry in pakistan
Sugar industry in pakistanSugar industry in pakistan
Sugar industry in pakistan
 
Management in cement industry in pakistan
Management in cement industry in pakistanManagement in cement industry in pakistan
Management in cement industry in pakistan
 
Project of lucky cement .
Project of lucky cement .Project of lucky cement .
Project of lucky cement .
 
Final project Report on cement industry
Final project Report on cement industryFinal project Report on cement industry
Final project Report on cement industry
 
Cement industry of pakistan
Cement industry of pakistanCement industry of pakistan
Cement industry of pakistan
 
DG cement Operations management
DG cement Operations management DG cement Operations management
DG cement Operations management
 
Mineral Resources of Afghanistan
Mineral Resources of AfghanistanMineral Resources of Afghanistan
Mineral Resources of Afghanistan
 
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptx
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptxA study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptx
A study on Maple Leaf Cement Company Limited.pptx
 
Cement Sector Report - January 2019
Cement Sector Report - January 2019Cement Sector Report - January 2019
Cement Sector Report - January 2019
 
Nestle
NestleNestle
Nestle
 
Kbl water pumps
Kbl   water pumpsKbl   water pumps
Kbl water pumps
 
Cement Industry of Pakistan
Cement Industry of PakistanCement Industry of Pakistan
Cement Industry of Pakistan
 
Minerals of somalia
Minerals of somaliaMinerals of somalia
Minerals of somalia
 
Lucky cement factory internship report
Lucky cement factory internship reportLucky cement factory internship report
Lucky cement factory internship report
 
Fauji Fertilizer Corporation
Fauji Fertilizer CorporationFauji Fertilizer Corporation
Fauji Fertilizer Corporation
 
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENET
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENETMinería en argentina, Geografia 3 4 ENET
Minería en argentina, Geografia 3 4 ENET
 
Project Olpers
Project OlpersProject Olpers
Project Olpers
 

Similar to የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006 Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ምMeresa Feyera
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008Ethiopian Sugar Corporation
 

Similar to የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ (20)

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (18)

Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
 
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profileEthiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profile
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

  • 2. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን ልማት መደገፍ፡፡ ራዕይ ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት ተርታ መሰለፍ፣ ተልዕኮ እሴቶች • የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት • መልካም ሥነ ምግባር • ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው! • ህዝባዊነት መለያችን ነው! • መማር አናቋርጥም! • ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን! • በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው! • አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው! • የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ ነው! የስኳር ኮርፖሬሽን ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች
  • 3. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 መሰረት ስኳር ኮርፖሬሽን የተቋቋመበት ዓላማ • የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣ • ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን በፋብሪካ ማዘ ጋጀትና ማምረት፣ • ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣ • አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክ ኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ሥራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣ • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመ ተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤ ቶችን በስራ ላይ ማዋል፣ • አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመን ግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያ ስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬ ሽን ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲ ከናወኑ ማድረግ፣ • በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስ ፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣ • የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን ማበረታታትና መደገፍ፣ • ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍ ራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባ በር፣ • የገንዘብ ሚኒስቴር የሚያወጣ ውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራ ደርና መፈራረም፣ • አላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎ ችን መስራት ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 65 ዓመት ገደማ በላንድሮቨር መኪና ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በገበያ ቀናት ስኳርን ለማስተዋ ወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ቡናና ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለችው የኢኮ ኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት ሆኗል፡፡ በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆ ላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት ከ1943 ዓ.ም. አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሺ ሄክታር የሸ ንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመ ረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምት ገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946 ዓ.ም. ስራ አስ ጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በወቅቱ በቀን 1 ሺ 400 ኩንታል ስኳር እያመረተ ምዕዙን ስኳር እና ባለ 10 ሳንቲም እሽግ ስኳር ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡ በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ ምርት ከሚ ያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ስለነበር ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞ የወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ ሰኔ 1953 ዓ.ም. ተቋቁሞ ደስታ ከረሜላ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ከጀመረ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ደግሞ በ1955 ዓ.ም. እዛው ወንጂ ላይ የተቋቋመው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ በቀን 1 ሺ 700 ኩንታል ስኳር ያመርት ነበር፡፡ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 4. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ሺ ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደ ነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂ እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ በእ ርጅና ምክንያት እንደቅደም ተከተላ ቸው በ2004 ዓ.ም. እና በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካ ቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል። በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረ ዳው የሆላንዱ ኩባንያ ኤች ቪ ኤ በተ መሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ ሰኔ 26 ቀን 1957 ዓ.ም. በአክሲዮን መልክ በመመስረት በ1962 ዓ.ም. ፋብሪካ ውን ሥራ አስጀመረ፡፡ ይሁንና እነዚህ ፋብሪካዎች በ1967 ዓ.ም. በሀገሪቱ በተደረገው የመንግ ሥት ለውጥ ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ይዞታ ስር ወደቁ፡፡ ይህን ተከትሎ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 58/1970 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖ ሬሽን ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ አዲስ ከተማና አስመራ ከረሜላ ፋብሪካዎችን እንዲያ ስተዳድር ተደረገ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በፊንጫአ ሸለቆ በ1967 ዓ.ም. በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አካባቢው ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህን ተከትሎም ለአገሪቱ ሦስተኛ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት ጠለቅ ያለ ጥናት እንዲካሄድ ተወስኖ ቡከርስ አግ ሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ አማካይነት ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ ዝርዝር ጥናት ተካሄደ፡፡ በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ተጓቶ የነ በረው የፋብሪካው ግንባታ በ1981 ዓ.ም.፤ የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራው ደግሞ በ1984 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ከስም ንት ዓመት በኋላ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በ1991 ዓ.ም. ወደ መደበኛ የማምረት ስራ ተሸጋገረ፡፡ ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል ግንባታ ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና አሶሽየትስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያና በእርሱ ስር የፋብሪካውን ተከላ ያካ ሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ የሆላንድ ኩባንያ ሲሆኑ፣ በግንባታው በርካታ የሀገር በቀል ድርጅቶች ተሳት ፈዋል፡፡ ልማቱ በዚህ መልክ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የወንጂ ሸዋና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአዲስ ከተ ማንና የአስመራ ከረሜላ ፋብሪካዎችን ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከ14 ዓመታት ቆይታ በኋላ በ1984 ዓ.ም. በሕግ ፈረሰ፡፡ በምትኩም በደንብ ቁጥር 88/85 መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፤ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ እራሳቸውን የቻሉ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡ ኋላም ለስኳር ፋብሪካዎቹ የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱ ስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል አክስዮን ማህበር በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር 1990 ዓ.ም. ተቋቋመ፡፡ ከዓ መታት በኋላም በማዕከሉ ምትክ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 504/98 ተመስርቶ የስኳር ፋብሪካዎቹን በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣ በሥልጠናና በግብይት ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የኢፌዲሪ መንግሥት የስኳር ልማቱን ለማስፋፋት በማቀድ በአፋር ክልል አራተኛውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 አቋቋመ፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ግነባታ በቀን 13 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባው ይህ ግዙፍ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ከጀመ ረበት ከ2007 ዓ.ም. አንስቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀም ርም በ25 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠ ቀም በዓመት እስከ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እና 27 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • 5. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የስኳር ልማት እንቅስቃሴው በዚህ መልክ ከቀጠለ በኋላ ከጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ እንዲፈርስ ተደርጎ በምትኩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 የስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቋመ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በ ስራ አመራር ቦርድ የሚተዳደር ሆኖ፣ የፌዴራል መን ግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት ተጠሪነቱ ለመንግ ሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳ ደር ኤጀንሲ ሆኗል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ከጥቅምት 2003 ዓ.ም. አንስቶ የስኳር ልማቱ የሚካሄድባ ቸው አካባቢዎች ማህበረሰቦችን የልማት ተጠቃሚ በማድረግ፣ የተ ለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮች እና ማህበራዊ ተቋማትን በማስ ፋፋት፣ መጠነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ ልማት በማካሄድ፣ የፋብሪካዎ ችን ቁጥር በማሳደግ እና ከፍተኛ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ማረጋገጡን ማየት ቢቻልም፤ በቤቶች ግንባታ እንዲሁም የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶ ችን አቅርቦት በማሳደግ ረገድ ግን ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ በት ለማየት ተችሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በእቅድ የያዛቸውን ትላልቅ ግቦች ከማሳካት አንጻር በዘርፉ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የለውጥ አሠራሮችን በመተግበር ላይ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ለባለሙያ ዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡
  • 6. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ አገዳ ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል የስኳር ፋብሪካ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡ በቂ የቅድመ ዝግጅት ጥናትና የፋይና ንስ አቅርቦት በሌለበት፣ ልማቱ እንዲ ካሄድባቸው በታቀዱ አካባቢዎች አስቀ ድሞ ምንም አይነት የመሠረተ ልማት አውታሮች ባልተዘረጉበት እንዲሁም “እየተማርን እንሰራለን” በሚል እሳቤ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች በአንድ ጊዜ 10 ግዙፍና ከፍተኛ የኢንቨ ስትመንት ካፒታል የሚጠይቁ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት በተወሰነበት ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ኢንዱስትሪ በብሩህ ተስፋና በበርካታ ተግዳሮቶች ታጅቦ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ምንም እንኳ በበርካታ ፈታኝ ሁኔታ ዎች ሳቢያ በዘርፉ ከተቀመጡ ግቦች አንጻር በእስካሁኑ የልማት ጥረት የተገኙ ስኬቶች የተጠበቀውን ያህል ባይሆኑም የኢንዱስትሪውን ተስፋ ግን አሻግረው የሚያሳዩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ሲባል ያለምክንያት አይ ደለም፤ እስከ 2007 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ሦስት ብቻ የነበሩትን ስኳር ፋብ ሪካዎች አሁን ላይ ስምንት ከማድ ረስ ባሻገር ነባሮቹን ፋብሪካዎች በማ ዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማ ሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነ ዋል፡፡ በአጠቃላይ በእቅድ ተይዘው ከነበሩ አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ የከሰም፣ የተንዳሆ፣ የአርጆ ዲዴሳ፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብ ሪካዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ስኳር በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ ውን መሬት በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ ከነበረበት 30 ሺ 397 ሄክታር ከሦስት እጥፍ በላይ በማሳደግ ወደ 102 ሺ 741 ሄክታር መሬት ማድረስ የተቻለ ውም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ነው፡፡ በተመሳሳይ የመስኖ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተደረገው ጥረትም ውጤት አስገኝቷል፡፡ በሌላ በኩል ከፕሮጀክቱ ግንባታ ጎን ለጎን የአካባቢውን ማህበረሰብ የልማቱ ተቋዳሽ ለማድረግ የተጀመረው እንቅ ስቃሴም በአበረታችነቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት • ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎን በስኳር ኮርፖሬሽን እና በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተገነቡ 255 የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ) እና የመ ሰረተ ልማት አውታሮች (ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ) በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እየሆኑ በመምጣታቸው የኑሮ ደረ ጃቸው መለወጥ ጀምሯል፡፡ • ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች ቅድሚያ በመስጠት በትራክተር የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦ ካላቸው ግዙፍ ፕሮ ጀክቶች መካከል አንዱ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህን ኤክስ ፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ ኢን ዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማ ነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚ የአየር ንብረት፣ በመስኖ ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ የሆነ 1.4 ሚሊዮን ሄክታር ለም መሬት፣ ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት እንዲሁም ለመስኖ ልማት የሚውሉ በርካታ ወንዞች እና ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች የሰው ሃይል ያላት በመሆኑ መንግሥት ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15 ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል አገዳ ይመረታል፡፡ ይህ አሃዝ በአለምአ ቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄክ ታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄክታር በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸን ኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም የ23 ኩንታል ብልጫ አለው፡፡ ይህንን ታሳቢ ያደረገው የኢፌዲሪ መን ግሥት በወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱ ስትሪ በተለይም ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ በደቡብ ብ/ብ/ህ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስ ፋፋ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በአማራ ክልል በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ40 ሺ ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ እያ ንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሁለት የስኳር ፋብ ሪካዎች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨ ማሪም በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ማጂ እና ካፋ ዞኖች በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ100 ሺ ሄክታር መሬት የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግ ብዓትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳ ቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሦስት ፋብሪካዎችን እንዲ ሁም በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍ ጨት አቅም ያለውን አንድ ፋብሪካ ለመገንባት ከተያዘው እቅድ ውስጥ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለትና ሶስት ፋብ ሪካዎች ስኳር ማምረት ጀምረዋል፡፡ የቀሩት ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች ግንባ ታም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በወል ቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት 40 ሺ
  • 7. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ ኦፕሬተርነት፣ በግምበኛነት፣ በአ ናጺነት፣ በጥበቃና በመሳሰሉት ሙያዎች በማሰልጠን በየፕሮጀክ ቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ ተደር ጓል፡፡ ወደፊትም ለአካባቢው ተወ ላጆች የሥራ ዕድል የመፍጠሩ ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ • የአካባቢው ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው በልማቱ እንዲሳተፉና ገቢ እንዲ ገኙ ድጋፍ ተደርጓል፤አሁንም በመ ደረግ ላይ ይገኛል፡፡ • በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀ ክቶች አካባቢ የሚገኘው ማህበረ ሰብ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎ ችን በየአመቱ አምርቶ እንዲጠቀ ምና በቀጣይም በዘላቂነት ሸንኮራ አገዳ አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያ ቀርብ ለማስቻል ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች (አውትግሮወር) ልምድ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡ • ስኳር ኮርፖሬሽን ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ በስኳር ልማቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማ ኅበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት ለሚውሉ 174 የማኅበራዊ አገል ግሎት መስጫ ተቋማት እና የመ ሰረተ ልማት አውታሮች ግንባታ ማስፈጸሚያ፣ ለሃብት/ንብረት ካሳ፣ ለሙያ ሥልጠና እና ለሌሎች ተያያዥ ሥራዎች 1.2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ አድርጓል፡፡ • በአጠቃላይ ልማቱ በይፋ ከተጀ መረ ከ2003 ዓ.ም. አንስቶ እስከ 2010 ዓ.ም.መጨረሻ ድረስ በዘርፉ በተፈጠረ ቀጥተኛና ተዘዋ ዋሪ የሥራ እድል ከ450 ሺ በላይ ዜጎች በቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንት ራት የሥራ መደቦች ተቀጥረው የልማቱ ተቋዳሽ መሆን ችለዋል፡፡ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
  • 8. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት ምንም እንኳ የስኳር ኢንዱስትሪው ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆ ጠረ ቢሆንም፣ • የስኳር ልማቱ በሚፈልገው ፍጥነት አለማደግ፣ • ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለቸው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ የህብረ ተሰቡ የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት፣ • የሕዝብ ቁጥር ማደግ እና • ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከመስፋ ፋት ጋር ተያይዞ የስኳር ፍላጎትና አቅርቦት ሳይጣጣም ቆይቷል፡፡ አሁን ያለው ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት መጠን በዓመት ከ6.5 እስከ 7 ሚሊዮን ኩንታል ያህል ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ባለፉት ዓመታት ከ3.25 ሚሊዮን እስከ 4 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ስኳር በሀገር ውስጥ የተመረተ ሲሆን፣ በፍላጎ ትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላትም በዓመት ከ2 ሚሊዮን እስከ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የአንድ ሰው አመታዊ የስኳር ፍጆታ 12 ኪሎ ግራም እንደሚደርስ ቢገመትም፣ እየቀረበ ያለው መጠን ግን ከ 5 እስከ 6 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣ ጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር ከውጭ መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይ ቻል ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራ ችን ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ መሰረት መንግሥት፡- • የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም፣ • በዘርፉ ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ • በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና • ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት “የስኳር አብዮት” በሚያስብል ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች እያካሄደ ነው፡፡ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የጋራ ማልማት (joint investment) መስኮች ኢንቨስትመንት መ ንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ስኳር ኮርፖሬሽን በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባ ንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወ ቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮነው፡፡ በዚህ መሰረት እስከ ጥር 2011 ዓ.ም. ድረስ 30 ኩባንያዎች ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በሽርክና ለመስራት የኩባንያቸውን አቅምና ማንነት የሚገልጽ ማስረጃ /ፕሮ ፋይል/ አቅርበው ከአንዳንዶቹ ጋር ውይይት ተደርጎ የመግባቢያ ሰነድና የጋራ ልማት ኮንትራት መፈራረም ተችሏል፡፡
  • 9. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በስኳርና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በጋራ ማልማት ወይም በግል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች • የመንግሥት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ • በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መሰረት የተመቻቹ የኢንቨስትመንት ማበ ረታቻዎች/Incentives ፣ • የሀገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት፣ • የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል፣ ኢትዮጵያ የሸንኮራ አገዳና የስኳር ተጓዳኝ ምርቶችን በስፋት ለማምረት፡- • በመሰኖ ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ የሆነ 1.4 ሚሊዮን ሄክታር ለም መሬት • ተስማሚ የአየር ንብረት • ለመስኖ ልማት የሚውሉ በርካታ ወንዞች • ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት እና • ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች የሰው ኃይል አላት፡፡ • ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15 ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል አገዳ ይመረታል፡፡ ይህ አሃዝ በአለምአ ቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄ ክታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄ ክታር በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸንኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም የ23 ኩንታል ብልጫ አለው፡፡ • የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ (ትላልቅ ግድቦችና የመስኖ መሰረተ ልማት፣ መንገድ፣ የአየር ማረፊያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ወዘተ)፣ • 102 ሺ ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት፣ • በሀገር ደረጃ ስኳር እና ኢታኖል በማምረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስ ቆጠረ ልምድ፣ • ወደ ሥራ የገቡና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ 10 አዳዲስ ግዙፍ የስኳር ፋብሪ ካዎች እና በስራ ላይ የመገኙ ሦስት ነባር ስኳር ፋብሪካዎች፣ • እያደገ የመጣ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ሰፊ የሀገር ውስጥ ገበያ፣ • በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ የመጡ ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢን ዱስትሪዎች፣ • ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት (የእንስሳት መኖ ማቀነባበርና ማድለብ ይቻላል)፣ የስኳር ዋንኛ ተረፈ ምርቶች (Major Sugar By-products) • ሞላሰስ (Molasses) • ኢታኖል (Ethanol) • ባጋስ (Bagasse) የሀገራችን ተሞክሮ በስኳር ተጓዳኝ ምርቶች (Sugar Co- products) • የኤሌክትሪክ ኃይል (Electricity) • ፍራፍሬ (Fruits) ; Orange, Banana, Mango • የእንስሳት መኖ (Animal feed) • ከብት ማድለብ (Cattle Fattening) • ጥጥ (Cotton) • ሩዝ (Rice) • አኩሪ አተር (Soya bean) • ሰሊጥ (Sesame) • ስንዴ (Wheat) • ቦሎቄ (Haricot bean) • ማሾ (Mung bean) በሽርክና (Joint venture) ወይም በግል ኢንቨስት የሚደረግባ ቸው መስኮች • የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ • ስኳር ፋብሪካ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣ • የኢታኖል ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣ • የተለያዩ የስኳር ተጓዳኝ ምርቶች ልማት፣ • የመስኖ ዝርጋታ፣ የመሬት ዝግጅት እና የሸንኮራ አገዳ ልማት ፕሮጀክቶች፣ • የስኳር ፋብሪካ የመለዋወጫ እቃዎች ማምረቻ ኢንደስትሪ፣ • የእንስሳት መኖ ልማትና ማድለብ ሥራ፣ • የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ፣ • የችፕቦርድ ማምረቻ ፋብሪካ፣ • የአልክሆል መጠጥ ኢንደስትሪ፣ • የስኳር ማሸጊያ ከረጢት/ጆንያ ማምረቻ ፋብሪካ፣ • የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ ወዘተ
  • 10. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በመጀመሪያውና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በዘርፉ የተከናወኑ አበይት ተግባራት • በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ነባር ስኳር ፋብ ሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡ • በእቅድ የተያዘው አመታዊ የስኳር ምርት መጠን ግብ ለጊዜው ሙሉ በሙሉ ባይሳካም በማስፋፊያ ሥራዎችና በአዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች አማካ ይነት ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ ከነበረበት 2 ሚሊዮን 903 ሺ 740 ኩንታል ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ተችሏል፡፡ • የከሰም፣የተንዳሆ፣ የአርጆ ዲዴሳ፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር ተችሏል፡፡ • የሸንኮራ አገዳ ልማትን በተመለከተም እስከ 2002 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ በአገዳ የተሸፈነው 30 ሺ 397 ሄክታር መሬት አስከ ታህሳስ 2011 ዓ.ም. ድረስ ወደ 102 ሺ 74 1 ሄክታር አድጓል፡፡ • የኤታኖል የምርት መጠንም በ2002 ዓ.ም. ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሺ ሊትር ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሺ ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ኤታኖል ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ • የአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡ • የትላልቅ ግድቦች፣ የሰፋፊ መስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የመንገድ፣ የቤቶች እና የግዙፍ አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተካሂደዋል፡፡ • ይሁንና በመሰረተ ልማት አውታሮች አለመሟላት፣ በመፈጸምና ማስፈጸም አቅም ማነስ፣ በፋይናንስና የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ በመለዋወጫና ማሽነሪ አቅርቦት ችግር እና ሌሎች ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት ባይቻልም፣ በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ሀገሪቱ ወደፊት ከዓለም 10 ከፍተኛ የስኳር አምራች ሃገራት ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ • በአጠቃላይ በግንባታ ላይ የሚገኙ አምስት ስኳር ፋብሪካዎች ወደፊት ተጠናቀው አሁን በማምረት ተግባር ላይ ካሉት ስምንት ፋብሪካዎች ጋር ሲደመሩ በ13 ስኳር ፋብሪካዎች ሀገሪቱ የምታመርተው አመታዊ የስኳር መጠን እስከ 22.5 ሚሊዮን ኩንታል ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡
  • 11. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በስኳር ኢንዱስትሪ የታዩ እድገቶች ንጽጽራዊ መግለጫ ተ.ቁ እድገቱ የታየበት ርዕስ 1983 ዓ.ም. 2011 ዓ.ም. 1 የስኳር ፋብሪካዎች ብዛት ሁለት (ወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች) በማምረት ላይ ያሉ ስምንት (ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰም፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ኦሞ ኩራዝ 2 እና ኦሞ ኩራዝ 3) 2 በግንባታ ላይ የሚገኙ ፊንጫአ ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ ጣና በለስ 1፣ ጣና በለስ 2 እና ወልቃይት 3 አመታዊ የስኳር ምርት መጠን 1 ሚሊዮን 496 ሺ 580 ኩንታል 5 ሚሊዮን 200 ሺ ኩንታል ስኳር ለማምረት ታቅዷል፤ 4. አመታዊ የኤታኖል ምርት መጠን አልነበረም 22 ሚሊዮን 355 ሺ ሊትር ይመረታል ተብሎ ይጠበ ቃል፤ 5. በቀን በአማካይ የሚፈጭ የአገዳ መጠን 6ሺ 213 ቶን አገዳ አሁን በስራ ላይ የሚገኙ ስምንት ስኳር ፋብሪካዎች በቀን በአማካይ 62,500 ቶን የሚጠጋ አገዳ የመፍ ጨት አቅም አላቸው፤ 6. በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት 15ሺ 501 ሄክታር 102,741 ሄክታር 7. የሰው ኃይል 11ሺ 452 ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ ሠራተኞች የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትን ጨምሮ በስኳር ፋብሪካዎ ችና ፕሮጀክቶች ከ40 ሺህ በላይ ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ ሠራተኞች ይገኛሉ፤ 8. የመኖሪያ ቤቶች 7ሺ 483 የመኖሪያ ቤቶች 21 ሺ 147 የመኖሪያ ቤቶች እና 311 የተለ ያዩ አገልግሎት መስጫ ብሎኮች 9. በስኳር ልማት አካባቢ ዎች ለሚገኙ የማህበ ረሰብ ክፍሎች የተገነቡ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመ ሰረተ ልማት አውታሮች ብዛት 31 ተቋማት 255 ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ቤት፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ፣ የእንስሳት ጤና ኬላ፣ የእ ንስሳት ውሃ ማጠጫ፣ የአርሶ/አርብቶ አደር ማሠ ልጠኛ ማዕከል፣ ህብረት ሱቅ፣ የእምነት ተቋማት ወዘተ) 10. በወንጂና አካባቢው በሸ ንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ (አውት ግሮ ወርስ) የህብረት ስራ ማህበራት ታቅፈው ተጠቃሚ የሆኑ አባላት ብዛት በሰባት ማህበራት የታቀፉ 1ሺ200 አባላት በ31 ማኅበራት የታቀፉ 9 ሺ319 አባላት 11. በስኳር ልማት ዘርፍ በሸ ንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ (አውትግሮወር) የህብረት ስራ ማህበራት አጠቃላይ ብዛት በሰባት ማህበራት የታቀፉ 1ሺ200 አባላት በ70 ማኅበራት የታቀፉ 15 ሺ 316 አባላት 12. በወንጂና አካባቢው በሸ ንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ (አውትግሮወር) የህብረት ስራ ማህበራት የተሸፈነ የሸንኮራ አገዳ መሬት ስፋት 1ሺ 20 ሄክታር 7ሺ ሄክታር 13. በስኳር ኢንደስትሪው በተደራጁ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ (አው ትግሮወር) የህብረት ስራ ማህበራት የተሸፈነ አጠ ቃላይ የሸንኮራ አገዳ መሬት ስፋት 1ሺ 20 ሄክታር 17 ሺ 246.82 ሄክታር
  • 12. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስ ኳ ር ፋ ብ ሪ ካ ዎ ች I. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946 ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955 ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላኛው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባን ያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡ በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ ስኳር ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች በእርጅና ምክንያት ሥራ ቸውን እስካቆሙበት ጊዜ ማለትም ወንጂ እስከ 2004 ዓ.ም. እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ የነበራቸው አማካይ አመታዊ ስኳር የማምረት አቅም 75 ሺ ቶን ወይም 750 ሺ ኩንታል ነበር፡፡ ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአ ዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማ ስፋፊያ ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ ዘርፍ ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራው በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ተጠናቆ በ2006 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ፋብሪካው ስራ ጀመረ፡፡ አዲሱ ስኳር ፋብሪካ የተገነባው ነባሮቹ በሚ ገኙበት የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ በቀን 6 ሺ 250 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት ከ1 ሚሊዮን 740 ሺ ኩንታል በላይ ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ወደፊት የማምረት አቅሙን በሂደት በማሳደግ በቀን ወደ 12 ሺ 500 ቶን አገዳ እየፈጨ ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን እስከ 2 ሚሊዮን 227 ሺ ኩንታል እንደሚያ ሳድግ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡ ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ ምርት በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን 800 ሺ ሊትር የሚደርስ ኤታኖል ለማምረት የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ ለመገን ባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በማ መንጨት ረገድም 31 ሜጋ ዋት የኤሌ ክትሪክ ኃይል በማመንጨት 11 ሜጋ ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ፣ ቀሪውን 20 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት እያ ስገባ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባ ቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የእርሻ ማስ ፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠ ቃላይ 16 ሺ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከለማው 12 ሺ 800 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ 7 ሺ ሄክታሩ በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ በ31 የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበራት በታቀፉ 9 ሺ 319 አርሶ አደሮች የለማ ነው፡፡ በዚህም አባላቱ በሚ ያገኙት ከፍተኛ ገቢ ከልማቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለአብነትም በአንዳንድ ማህበራት በአማካይ በየ18 ወራት በሚደረግ የትርፍ ክፍፍል አባላት እንደየስራቸው መጠን በነፍስ ወከፍ ከ50 ሺ እስከ 240 ሺ ብር ድረስ ገቢ ያገኙበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ በመስኖ የለማ መሬት በማዘጋ ጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት በማ መቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት አርሶ አደሮቹ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብ ሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲ ሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡
  • 13. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ II.መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀ ጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962 ዓ.ም. ወደ ስራ የገባው የመ ተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከ10 ሺ ሄክታር በላይ በሸንኮራ አገዳ የተሸ ፈነ መሬት ያለው ይህ ፋብሪካ በቀን 5100 ቶን አገዳ እየፈጨ በዓመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ ከ2003 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኤታኖል የማምረት ዓመታዊ አቅሙም በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ይደርሳል፡፡ በሌላ በኩል "ባጋስ” ተብሎ ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ 9 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመ ንጨት የራሱን የኃይል ፍላጎት እያሟላ የሚገኝ እድሜ ጠገብ ፋብሪካ ነው፡፡ ስለ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሲነገር የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን ማንሳት የግድ ይላል፡፡ ፋብሪካው ካይ ዘንን በሚገባ በመተግበርና ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመ ሪያ ጊዜ በተካሄደው የካይዘን ውድድር በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ አንደኛ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም በተመሳሳይ መስከረም 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድር ላይ ካይዘንን በማስ ቀጠል በተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ በድጋሚ የአንደኝነት የክብር ሜዳሊያ ዎችንና ዋንጫዎችን ከቀድሞው የኢ ፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማር ያም ደሳለኝ እጅ ተቀብሏል፡፡ III. ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካየፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካል ቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የቦታው አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥና የአፈር ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ የስውዲን፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግሥታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆ ናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ ግንባታ ጥር 1981 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ የሚገኘውን ቦታ ጨምሮ የፊ ንጫአ ስኳር ፋብሪካ ጠቅላላ ይዞታ (ኮማንድ ኤሪያ) 67 ሺ 98 ሄክታር
  • 14. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ተጠናቆ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ማምረት ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን፣ በእርሻ ማስፋፊያ ሥራም ከ19 ሺ ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ ለመሸፈን ተችሏል፡፡ በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 6 ሺ 600 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 1 ሚሊዮን 600 ሺ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ስኳር የማምረት አቅም ያለው አንድ ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካ ተገንብቷል፡፡ ይህ ደግሞ ነባሩ ፋብሪካ ካለው አቅም ጋር ተዳምሮ አጠቃላይ በሁለቱም ፋብሪካዎች የሚመረተውን አመታዊ የስኳር መጠን 2 ሚሊዮን 700 ሺ ኩንታል እንደሚያደርሰው ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው ከሚያመነጨው 31 ሜጋ ዋት ውስጥ ለ17 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪውን 14 ሜጋ ዋት ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ያስገባል፡፡ ነው፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ በማለፍ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫነት ከዋለ በኋላ ሸለቆውን ከሁለት ከፍሎ ወደ ሰሜን በመጓዝ ከአባይ ወንዝ ጋር በሚቀላቀለው የፊ ንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ ክፍል (ዌስት ባንክ) ያለውን 6 ሺ 476.72 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማ ልማት እና የፋብሪካ ተከላ በማከና ወን ነበር ፋብሪካው የካቲት 1990 ዓ.ም. የሙከራ ምርት እንዲጀምርና ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ውስጥ እን ዲገባ የተደረገው፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ1 ሺ 350 እስከ 1 ሺ 600 ሜትር ይደርሳል፡፡ በሸለቆው ውስጥ ያለው ከፍተኛው የሙቀት መጠን 31 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን፣ ዝቅተ ኛው 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይሆናል፡ ፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም በአማ ካይ 1 ሺ 300 ሚሊ ሊትር ይጠጋል፡ ፡ ይህም የተፈጥሮ ሁኔታ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ አካባቢን "ለምለም በረሃ" በሚል ልዩ ስም እንዲታወቅ አድርጎታል፡፡ ፋብሪካው ኢታኖል አምርቶ ከቤን ዚል ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት እንዲውል ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለሌሎች ኢን ዱስትሪዎችም በግብዓትነት በማ ቅረብ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ ድርሻ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው አጠቃላይ የማስፋ ፊያ ፕሮጀክት የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ የማ ስፋፊያ ፕሮጀክት የተጀመረው በ1998 ዓ.ም. ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በአገዳ ልማት በኩል በዌስት ባንክ 8 ሺ 300 ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት እና የኢስት ባንክና ነሼ አካባቢዎችን በማከል ወደ 21 ሺ ሄክታር መሬት ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 7 ሺ ሄክታር በኢስት ባንክ እንዲሁም 4 ሺ 670 ሄክታር በነሼ አካባቢ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የፋብሪ ካውን አገዳ የመፍጨት አቅም በማሳደግ አመታዊ የስኳር ምርቱን ከ1.1 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል እንዲሁም የኤታኖል ምርትን ከ8 ሚሊዮን ሊትር ወደ 20 ሚሊዮን ሊትር ከፍ ለማድ ረግ ታቅዶ የማስፋፊያ ሥራው ተካሄደ፡፡ የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ
  • 15. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በ25 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተም ስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በ1998 ዓ.ም. የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ OIA (Overseas Infrastructure Alliance) በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው ይህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ከጀመረበት ጥቅምት 2007 ዓ.ም. አንስቶ በመደበኛ የምርት ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በቀን 13 ሺ ቶን አገዳ በመ ፍጨት በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም የመጀመሪያው ምእራፍ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከሚያመነጨው 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 15 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ 25 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት በማስ ገባት እንዲሁም 27 ሚሊዮን ሊትር ያህል ኤታኖል በማምረት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን እንደሚያረጋግጥ ይታመናል፡፡ የመጀመሪያው ምእራፍ ፋብሪካ በግብአትነት የሚጠቀመው የሸንኮራ አገዳ ልማት በመከናወን ላይ የሚገኘው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው የተ ንዳሆ ግድብ አማካይነት ነው፡፡ ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ 60 ሺ ሄክታር መሬት እንደሚያለማ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመ ቻቸቱም አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ IV. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሁኔታ ተፈጥሮ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • ከ42 ኪ/ሜ በላይ የዋና ቦይና ተያያዥ ስትራክቸሮች ግንባታ ተከናውኗል፤ • 22,835 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤ የአገዳ ልማት • 17,683 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 8,997 የመኖሪያ ቤቶች እና 146 አገልግ ሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተው አገልግ ሎት እየሰጡ ናቸው፤ የማኀበረሰብ ተጠቃሚነት ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣ በኮንትራክተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና አነ ስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይነት 77,035 ለሚሆኑ ዜጎች በቋሚ፣ በኮንትራትና በጊዜያ ዊነት የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ 84 የጥ ቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም ተደራጅ ተዋል፡፡ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ አደ ሮችን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድ ረግ በዱብቲ 1,667 አባላት ያሏቸውና ህጋዊ ሰውነት ያገኙ 16 የሸንኮራ አገዳ አምራቾች መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ከፋብ ሪካው ጋር በአውትግሮወር ሞዳሊቲ ትስስር በመፍጠር ሸንኮራ አገዳ በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች በስኳር ኮርፖሬሽን 1.6 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
  • 16. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ V. ከሰም ስኳር ፋብሪካ በአፋር ክልል በዞን ሦሥት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች በከሰም ቀበና ሸለቆ ውስጥ ውስጥ የሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ. ያህል ይርቃል፡፡ ለመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ በ2003 ዓ.ም. የግ ንባታው ቅድመ ዝግጅት የተጀመረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀትና ከአዋጪነት አንፃር ተጠንቶ ኋላ ላይ ራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ብድር ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ የሙከራ ምርቱን አጠናቆ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በመደበኛ ሥራ ላይ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 6 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ፣ በቀጣይ በሚደረግ የማስፋፊያ ሥራ 10 ሺ ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚ ፈጭበት ደረጃ እያደገ ይሄዳል፡፡ ፋብሪ ካው በመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሉ የማ ምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ 1 ሚሊዮን 530 ሺ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን 500 ሺ ሊትር ኢታኖል በዓመት ያመር ታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማ መንጨት እና 10 ሜጋ ዋቱን ለኦፕሬ ሽን ተጠቅሞ ቀሪውን 16 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) በማቅ ረብ ተጨማሪ ገቢ የማስገኘት አቅም አለው፡፡ ወደፊት በሚደረግ የማስፋፊያ ሥራም ፋብሪካው በዓመት 2 ሚሊዮን 600 ሺ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ላይ ሊደርስ እንደሚችል የፋብሪካው የዲዛ ይን አቅም ያመለክታል፡፡ የፋብሪካው አካባቢ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካይነት በ20,000 ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ የሚለማበት ነው፡፡ የአገዳ ልማቱ ከከሰም ሌላ ቦልሀሞን በተሰኘ አካባ ቢም ይከናወናል፡፡ በፋብሪካው ከሚለ ማው የሸንኮራ አገዳ በተጨማሪ ከአሚ ባራ እርሻ ልማት አክሲዮን ማኅበር ጋር በተገባው ውል መሠረት ማኅበሩ በስ ድስት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ እያለማ ለፋብሪካው በማቅረብ ላይ ይገኛል። የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • 2,946 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደ ርጓል፤ • የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤ የአገዳ ልማት • በፋብሪካው አማካይነት 2,823 ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚ ባራ እርሻ ልማት (አውት ግሮወር) 6 ሺ ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍ ኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 648 መኖሪያ ቤቶችና 25 የአገልግ ሎት መስጫ ብሎኮች ተጠናቀው ለአገልግሎት ቀርበዋል፤ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምጣኔ ሃብታ ዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታ እያስገኘ የሚ ገኘው የከሰም ፋብሪካ ግንባታው ከተ ጀመረ ጊዜ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣ በኮን ትራክተሮች እንዲሁም በ29 ጥቃቅ ንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይ ነት 42,773 ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣ ቶችና ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከዚህ ባሻገር 399 አባላት ያሏቸው አምስት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ መሠ ረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ከፋብ ሪካው ጋር በአውትግሮወር ሞዳሊቲ ትስስር በመፍጠርና ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ የልማቱ ተቋዳሽ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡
  • 17. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ VI.አርጆዲዴሳስኳርፋብሪካ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀ ክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ፣ በቡኖ በደሌና በጅማ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ ነቀምት በደሌ በሚወስ ደው መንገድ በ395 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑም 1400 ሚሊ ሜትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ሥርጭቱ ደግሞ ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘል ቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ AL-Habasha Sugar Mills PLC ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ በ2005 ዓ.ም. በግዢ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ይዞታነት የተሸጋገረው ይህ ፋብሪካ በ16 ሺ ሄክታር መሬት የሚለማ የሸ ንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም በቀን 8 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን በተረከበ በት ወቅት ሳይጠናቀቅ የቆየ የፋብሪካ ግንባታ ሥራን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ እንዲሁም በወቅቱ ያልነ በሩ የልማት ሥራዎችን (የህዝብ አደረ ጃጀት ሥራ፣ የግድብ ግንባታ፣ የመሬት ዝግጅት፣ የመስኖና የአገዳ ልማት፣ የማ ህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች) በማ ከናወን ፋብሪካውን ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ምርት ማስገባት ተችሏል፡፡ ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ከፍተኛ ኢታኖል የማምረት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ ባጋስ ከተባለ ተረፈ ምርት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል አልፎ ቀሪውን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) እንደሚያስገባ ይጠበቃል፡፡ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በቀድሞው የኢፌ ዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ስኳር በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • ፋብሪካው ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያውለውን ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ ያገኛል፤ • በኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን አማካይነት ለፋብሪካው ግብዓት የሚውል የሸንኮራ አገዳ ለማልማት በዲዴሳ ወንዝ ላይ ግድብ እየተገነባ ነው፤ • በተጨማሪ 2 ሺ 300 ሄክታር መሬት የሚያለማ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ በኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ተካሂዶ 1,600 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤ የአገዳ ልማት • 3 ሺ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 124 የመኖሪያ ቤቶችና 11 አገልግሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተዋል፤ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት በምስራቅ ወለጋና በቡኖ በደሌ ዞኖች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ ማህበራዊ ተቋማት ተገንብተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶም ለ17,547 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ በተለይም የአካባቢው ወጣቶች ልማቱ ባስገኘው የሥራ እድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠ ናዎች ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር 71 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በአካባቢው ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማ ርተዋል፡፡ በሌላ በኩል ለአገዳ ማሳ ማስፋፊያ ከአርሶ አደሩ ለተገኘ መሬት የሃብት ንብረትና ምርት ካሳ ክፍያ እንዲሁም ለህብረተሰብ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች 65.66 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
  • 18. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ VII. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 825 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6.67 ቢሊዮን ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም. ግንባታው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 14/2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርቱን ካሳካ በኋላ ወደ መደበኛ ምርት ተሸጋግሯል፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ 10,000 ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፋብሪካው እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ አንጻርም የአለም ገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ጥሬ ስኳር (Raw sugar)፣ ነጭ ስኳር (Plantation white sugar) እና የተጣራ ስኳር (Refined sugar) ማምረት ይችላል፡፡ VIII. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 874 ከ.ሜ ይርቃል፡፡ ፋብሪካው ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በይፋ የተጀመረው መጋቢት 2/2008 ዓ.ም ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ነው፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ 10,000 ኩንታል ስኳር የማ ምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ አንጻርም የአለም ገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ጥሬ ስኳር (Raw sugar)፣ ነጭ ስኳር (Plantation white sugar) እና የተጣራ ስኳር (Refined sugar) ማምረት ይችላል፡፡ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ወደ ሥራ መግባት ስኳር የሚያመርቱ ትን ፋብሪካዎች ቁጥር ወደ ስምንት (ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰም፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3) አድርሶታል፡፡
  • 19. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች I. ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን (ሰላማጎ እና ኛንጋቶም ወረዳዎች)፣ በቤንች ማጂ ዞን (ሱርማ እና ሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች) እና በካፋ ዞን (ዴቻ ወረዳ) የተመረጡ አካባ ቢዎች እየተካሄደ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ስር እየተገነቡ ከሚገኙ አራት የስኳር ፋብሪካዎች በተሽከርካሪ ለመ ድረስ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና - አርባ ምንጭ - ጂንካ መስመር ከ825-954 ኪሎ ሜትር ወይም ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ - አርባ ምንጭ - ጂንካ መንገድ ከ859- 988 ኪሎ ሜትር መጓዝን ይጠይቃል፡፡ በአየር ትራንስፖርት ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ ጂንካ ለአንድ ሰዓት ያህል በመብረር ከጂንካ ፋብሪካዎቹ ያሉበት ድረስ ከ80-220 ኪሎ ሜትር በተሽከርካሪ መጓዝ የግድ ይላል፡፡ በፕሮጀክቱ በ100 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ተጠቅመው በቀን 60 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው አራት ስኳር ፋብሪካዎች እየተ ገነቡ ሲሆን፣ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ ሶስቱ እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 2 ሚሊዮን 500 ሺ ኩንታል ስኳር እና እያ ንዳንዳቸው በዓመት 28 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ከሚያመነጩት 45 ሜጋ ዋት ውስጥ 29 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ ቋት ይልካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ አንደኛው ፋብሪካ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እና 56 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል እንደሚያመርት ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪ ከሚያመነጨው 90 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ውስጥ 32ቱን ለራሱ ተጠቅሞ 58 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ ቋት እንደሚልክ ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህ አራት ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ በቻይናው ኮምፕላንት ኩባንያ የተገነ ቡት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት እና ቁጥር ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት ገብተዋል፡፡ የተቀሩት የቁጥር አንድና አምስት ስኳር ፋብሪካዎች በግንባታ ላይ ናቸው፡፡ የኢንቨስትመንት ወጪ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ ለሚገኙ አራት ስኳር ፋብሪካ ዎች እስከ መጋቢት 30/2010 ዓ.ም ድረስ ለካፒታል ኢንቨስትመንት (ለመስኖ መሰረተ ልማት፣ ለመሬት ዝግጅት፣ ለአገዳ ልማት፣ ለቤቶች ግንባታ፣ ለፋብሪካ ግንባታ ወዘተ)፣ ለፕሮጀክቶች ቅድመ ኦፕሬሽንና ለሥራ ማስኬጃ 34.8 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ተደርጓል፡፡ የማህበሰብ ተጠቃሚነት ስኳር ኮርፖሬሽን ስኳር ከማምረት ባሻገር በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀ ክት አካባቢ የሚኖረውን የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻልና በዘላቂነት የልማት ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ ቀጣናዊ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት እንዲ ቻል በርካታ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ከደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል መንግሥት ጋር በመቀናጀት ሲሰራ ቆይታል፡፡ በዚህ መሰረት ኮርፖሬሽኑ የመስኖ መሰረተ ልማት ወጪን ሳይጨምር ለአካባ ቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት 86 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አድ ርጓል፡፡ ይህ በመሆኑም ከ50 በላይ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች (ት/ቤት፣ ጤና ኬላ፣ የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ጽ/ቤት፣ የቀበሌ ጽ/ቤት፣ የህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ የእንስሳት ጤና ኬላ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ በመስኖ የለማ መሬት ወዘተ) ተገንብተው ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
  • 20. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የካሳ ክፍያ በኮፈር ዳም የመስኖ ግድብ ምክንያት የንብ ቀፎ እና ሰብላቸው ለተነ ካባቸው አርብቶ አደሮች የንብ ቀፎ ግምት እና የምርት ማካካሻ ካሳ 1 ሚሊዮን 141 ሺህ 165 ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ የህዝብ ውይይቶችና ሞብላይዜሽን በልማቱ አካባቢ ከሚገኘው የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማቱ ጥቅ ሞችና ፋይዳ ዙሪያ በተለያየ ጊዜ ለተደረጉ ውይይቶች 2 ሚሊዮን 584 ሺ 309.30 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ የክህሎት ስልጠና የአካባቢው ህብረተሰቡ ልማቱ በሚፈጠረው የስራ እድል ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ለመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች ብር 2 ሚሊዮን 866 ሺህ 658 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ የሥራ ዕድል ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ከ2003 ዓ.ም. አንስቶ በፕሮጀክት፣ በኮንትራክ ተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በቋሚ፣ በኮንትራትና ጊዜያዊነት ከ110 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶችና ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከ300 በላይ የጥ ቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን አደራጅቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ተችሏል፡፡ ሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኅ በራት (አውትግሮወር) በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙትን አርብቶ አደሮች በዘላቂነት የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በአራት ማኅበ ራት ለተደራጁ 2 ሺ 205 አባ/እማ ወራዎች ለእያንዳንዳቸው በመስኖ የለማ 0.75 ሄ/ር መሬት በመስጠት በድምሩ 1 ሺ 653.75 ሄ/ር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በሽያጭ እንዲያ ቀርቡ ሁኔታዎች እየተመቻቸላቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባገኙት መሬት በቆሎና የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርተው መጠቀም ጀምረዋል፡፡ በዚህም ወደ ከፊል አርሶ አደርነት ሽግግር ላይ ይገኛሉ፡፡ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 863 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮን ትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበረው ኮንትራት በ2010 ዓ.ም. እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋ ገጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈጻጸም 80% ነበር፡፡ በቀጣይ የፋብሪካው ቀሪ የግንባታ ሥራ ልምድ ባለውና በተመረጠ የውጭ ሀገር ኮንትራክተር የሚ ጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • 21. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቷም ወረዳ የሚካለለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ በ954 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ JJIEC በተባለ የቻይና ኩባንያ ከህዳር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ፣ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ በፕሮጀክቱ በዋናነት የኦሞ ወንዝን መሠረት በማድረግ 100 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የሚያስችል መጠነ ሰፊ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ጊዜያዊ ግድብ/Coffer Dam ለፕሮጀክቱ ውሃ ለማቅረብ በኦሞ ወንዝ ላይ ጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡ የዋና ቦይ ግንባታ በኦሞ ኩራዝ የሸንኮራ አገዳ ለማልማት ከኦሞ ወንዝ በስተግራ (left bank) የ55 ኪ.ሜ ዋና ቦይ (main canal) የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠናቆ አገ ልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ በተ መሳሳይ በቀኝ በኩል (right bank) እየተገነባ ከሚገኘው 134 ኪ.ሜ የዋና ቦይ (main canal) ግንባታ ውስጥ 43 ኪሎ ሜትሩ ተጠናቆ አገልግሎት በመ ስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የቀሪው 91 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ቁፋሮ ተጠናቆ የስ ትራክቸር ስራ ይቀራል፡፡ በአጠቃላይ በኦሞ ኩራዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የተጀመረውን የዋና ቦይ የመሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት 22.3 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ የሸንኮራ አገዳ ልማት በፕሮጀክቱ እስካሁን 30 ሺህ ሄክታር መሬት ውሃ ገብ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 16 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ተተክሏል፡፡ የቤቶች ግንባታ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1,140 የመኖ ሪያ ቤቶች እና 52 አገልግሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
  • 22. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ II. ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ላይ የተቋቋመ ሲሆን፣ የፕሮጀ ክቱ ጽ/ቤትም ፋንዲቃ ከምትባለው የጃዊ ወረዳ ከተማ አጠገብ ከአዲስ አበባ በ650 ኪ.ሜ እንዲሁም ከባህር ዳር በ225 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች በኢ ትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) ግንባታቸው ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በስኳር ኮርፖሬሽንና በሜቴክ መካከል በ2004 ዓ.ም. ተደርሶ የነበረው የጣና በለስ ቁጥር 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎች የግ ንባታ ውል እንደ ቅደም ተከተላቸው በ2010 ዓ.ም. እና 2009 ዓ.ም. በመ ንግሥት ውሳኔ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የፋብሪካዎቹ ቀሪ የግንባታ ሥራዎች ተጠናቀው ወደ ምርት ሲገቡ በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚ ለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው የመስኖ ውሃ የሚገኘው በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውሃ መቀ ልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡ ፋብሪካዎቹ ሙሉ የማምረት አቅማ ቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 2 ሚሊዮን 420 ሺ ኩንታል ስኳር እና 20 ሚሊዮን 827 ሺ ሊትር ኢታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸ ዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካዎቹ የተጣራ (ሪፋይንድ) ስኳር ለማምረት ዲዛይን ከመደረጋቸው ባሻገር እያንዳ ንዳቸው 45 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመጨንት አቅም ሊኖራቸው እንደሚችል ታሳቢ ተደርጓል፡፡ ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ፋብሪካ 16 ሜጋ ዋት ለኦፕሬሽን ተጠቅሞ ቀሪውን 29 ሜጋ ዋት ወደ ብሔራዊ ግሪድ በመላክ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በቀጣይ የፋብሪካው ቀሪ የግንባታ ሥራ ልምድ ባለውና በተመረጠ የውጭ ሀገር ኮንትራክተር የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬ ሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እን ደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበ ረው ኮንትራት በ2010 ዓ.ም. እንዲቋ ረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋገ ጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈ ጻጸም 65% ነበር፡፡ ጣና በለስ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋ ብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበረው ኮንትራት በ2009 ዓ.ም. እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋገጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈጻጸም 25% ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት አንድ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ፋብሪካውን ለመግዛት ፍላጎት ያሳየ ሲሆን፣ ከስምምነት ላይ ከተደረሰም ፋብሪካው ወደ ግል ይዞታነት የሚሸ ጋገር ይሆናል፡፡ ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ
  • 23. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ለፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚሆን የመስኖ ውሃ የተጠለፈው ከበለስ ወንዝ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 30 ኪ/ሜ ርዝመት ያለውና 60 ሜ/ኩ (cubic metre) ውሃ በሰከንድ ማስተላለፍ የሚችል የወንዝ መቀልበሻ (ዊር)፣ መቆጣጠሪያ፣ የደለል ማስወገጃ እና የዋና ቦያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመ ስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከተወሰኑ ማሳዎች በስተቀር አብዛኛው የ--እርሻ ማሳ ውሃ የሚጠጣው በኦቨር ሄድ ኢሪጌሽን (በስፕሪንክለር) የመስኖ ዘዴ ነው፡፡ • 16,146 ሄ/ር ማሳ ውሃ ገብ ተደርጓል፤ የአገዳ ልማት • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 13 ሺ 248 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1 ሺ 469 መኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት በፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማቱ ጥቅምና ፋይዳ ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት ውይይቶች በመደረጋቸው ልማቱን የጋራ ለማድረግ የሚ ያግዙ ሥራዎችን ለማከናወን ተችሏል፡፡ በዚህም ተግባር ለልማቱ ተነሽ ለሆኑ የህ ብረተሰብ ክፍሎች ት/ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ መካካለኛ የመጠጥ ውሃ ተቋማት፣ መንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለሀብት ንብረት፣ ለቋሚ ተክል እና ለእምነት ተቋማት ግምት ካሳ 152.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ የሥራ ዕድልን በተመለከተም ፕሮ ጀክቱ ከተጀመረ አንስቶ በፕሮጀክቱ፣ በኮንትራክተሮች እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካይነት ለ91 ሺ 493 የአካባቢው ወጣቶችና ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 1,253 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው የሥራ ትስስር ተፈ ጥሯል፡፡ በአጠቃላይ በስኳር ኮርፖሬሽን ለህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች 178.68 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ III. ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ በ1 ሺ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ CAMC በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ፋብሪካው በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል ያመርታል ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከሚያመነ ጨው 120 ሜጋ ዋት ውስጥ 56 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ 64 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ ግሪድ በመላክ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአገዳ ልማት የሚያስፈልገውን የመስኖ ውሃ አቅርቦት ከተከዜ፣ ከቃሌማ እና ከዛሬማ ወንዞች የሚያገኝ ይሆናል፡፡
  • 24. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • 3.5 ቢሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው “የሜይ-ዴይ” ግድብ በዛሬማ ወንዝ ላይ እየተገነባ ነው፡፡ ግድቡ ሲጠናቀቅ 840 ሜትር ስፋት እና 135.5 ሜትር ቁመት ይኖረዋል፤ • ከግድብ ግንባታው ጎን ለጎን በጠብታ መስኖ 7 ሺ ሄ/ር መሬት ለማል ማት NETAFIM ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ የመስኖ መሠረተ ልማት ሥራ ተቋራጭ ጋር ውል ተገብቶ ሥራው ተጀምሯል፤ • የ10 ኪ/ሜትር የዋና ቦይ (Main canal) ግንባታ ተጠናቋል፤ • 3 ሺ ሄ/ር መሬት ከቃሌማ ወንዝ በፓምፕ ጠልፎ በsprinkler ለማልማት የግንባታ ሥራው እየተከናወነ ነው፤የመስኖ ውሃው እስከሚደርስ ድረስም የጥጥ ልማት እየተካሄደ ይገኛል፤ • 260 ሄ/ር መሬት ለዘር አገዳ ውሃ ገብ ሆኗል፤ የአገዳ ልማት • ውሃ ገብ ከሆነው መሬት ውስጥ 140 ሄክታሩ ላይ የዘር አገዳ ተተክሏል፤ የቤቶች ግንባታ • 1,066 መኖሪያ ቤቶችና 53 የአገልግሎት መስጫ ብሎኮች ተገንብተው ለአ ገልግሎት ቀርበዋል፡፡ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት የአካባቢው ህብረተሰብ ልማቱ በሚ ፈጠረው የሥራ እድል ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የመለስ ተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሰጥ ተውት ለ84 ሺ 659 የአካባቢው ወጣ ቶችና ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎች ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 161 የጥቃቅንና አነስ ተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲደራጁና በሥራ እንዲተሳሰሩ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል በልማቱ ምክንያት ተነሺ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሃብት ንብረት ግምት ካሳ እና የምርት ማካካሻ ካሳ ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ ከዚህ ባሻገር በፕሮጀክቱ ክልል ውስጥ ይኖሩ ለነበሩና በመጀመሪያው ዙር ወደ ቆራሪት ሰፈራ መንደር መልሰው ለተቋ ቋሙ 2 ሺ 621 የህብረተሰብ ክፍሎች ስምንት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ት/ቤቶች፣ የሰውና እንስሳት ህክምና መስጫ ተቋማት፣ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ወዘተ)፣ 14 የመጠጥ ውሃ ተቋማትና 62 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶላቸው አገል ግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻች ተዋል፡፡ በአጠቃላይ በስኳር ኮርፖሬሽን ለህ ብረተሰቡ ተሳትፎ እና የልማት ሥራዎች 407.68 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ ስኳር በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች/ ፕሮጀክቶች ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት አቅም /በቀን፣ በቶን የሚገኝበት ክልል ለሸንኮራ አገዳ የሚውል መሬት/በሄ ክታር ወንጂ ሸዋ 6,250 ኦሮሚያ 12,800 መተሐራ 5,372 ኦሮሚያ 10,230 ፊንጫአ 12,000 ኦሮሚያ 21,000 ተንዳሆ 13,000 አፋር 25,000 ከሰም 6,000 አፋር 20,000 አርጆ ዲዴሳ 8,000 ኦሮሚያ 16,000 ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000 ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000 ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ የመ ፍጨት አቅም / በቀን፣ በቶን የሚገኝበት ክልል ለሸንኮራ አገዳ የሚውል መሬት/ በሄክታር ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 12,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 20,000 ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 24,000 ደቡብ ብ/ብ/ህ 40,000 ጣና በለስ 1 12,000 አማራ 20,000 ጣና በለስ 2 12,000 አማራ 20,000 ወልቃይት 24,000 ትግራይ 40,000 በግንባታ ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች/ፕሮጀክቶች
  • 25. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ምርምርና ልማት ዋና ማዕከል በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ሥራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአም ስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለ ክታሉ፡፡ ኋላ ላይ የፋብሪካዎቹን ወደ መንግሥት ይዞታነት መሸጋገር ተከትሎ የም ርምር ሥራው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋም ለምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥ ቶት የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ • ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የማምረቻ ወጪን መቀነስ የሚያስችል እንዲሁም ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied research) በማካሄድ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ ተችሏል፤ • የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል የተገኘው የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ ስኳር ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል፤ • በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እር ምጃዎች (optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት ተሰ ጥቷል፤ • ሥራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙ ትን ፋይዳ እና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ በመገምገም አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችና ስትራቴጂዎች ተነድፈዋል፤ • ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን እን ዲሁም የተሻሻሉ የሸንኮራ አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በማስተዋወቅ ሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፤ • በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ደረጃቸው (ስታንዳ ርድ) ሳይጓደል ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሠራር በመቀየስ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመርና ለማስተግበር ተሞክሯል፤ • በስኳር ቴክኖሎጂ የተለያዩ የምርምር ውጤቶችን በማው ጣት የስኳር ብክነትን (Sugar loss) እና የማምረቻ ጊዜ ብክነ ትን (Down time) በመቀነስ የስኳር ግኝት አቅምን (Overall recovery) የመጨመር ሥራዎች ተከናውነዋል፤ • ከስኳር ተረፈ ምርቶችና ከኤታኖል ተያያዥ ምርቶችን ለማም ረት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅና ማላመድ ተችሏል፤ • ኢንዱስትሪውን በሠለጠነና ውጤታማ በሆነ የሰው ኃይል ለመ ደገፍ የሚያስችሉ ሥልጠናዎች ለባለሙያዎች ተሰጥተዋል፤ ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ወንጂ ላይ የሚገኘው የምርምርና ልማት ዋና ማዕከል እነዚህን ተግባራት የበለጠ በብቃት ለመወጣት በ2008 ዓ.ም. በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ በዚህ መሰረት ዋና ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና በለስ፣ ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የምር ምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥና ከአካ ባቢ ጋር ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በአስተማማኝ ደረጃ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሶስት ፍኖተ ካርታዎችን (በባዮሪፋ ይነሪ፣ በስኳር ቴክኖሎጂ እና በደቂቅ ዘአካላት) በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡