SlideShare une entreprise Scribd logo
1  sur  1
Télécharger pour lire hors ligne
ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር
ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የቀረበ የትግል አንድነት ጥሪ
በአገራችን መዲና የገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖቻችንን ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለአስከፊ ድህነት ብሎም ለጎዳና ተዳዳሪነት
የዳረገዉንና የሚዳርገዉን፣ ጥቂት ባለጊዜዎችን፣ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎችንና የዉጭ አገራት ባለሀብቶችን ግን የሚያበለፅገዉንና «የአዲስ
አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የጋራ የተቀናጀ ማስተር ፕላን» በሚል ስም የወጣዉን የድሆችን መሬት የመንጠቅ ጭካኔ የተመላበት መንግሥታዊ
ዕቅድ በመቃወም በመላዉ ኦሮሚያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሳምንታትን ከማስቆጠሩም በላይ ለብዙ ንፁሃን ዜጎች ሕይወት
መጥፋት ምክንያት ሆኗል። ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ተጠናክሮ እየተካሄደ ያለዉ በብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ቢሆንም የተቃዉሞዉ ምክንያት
የሆነዉ ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነካዉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መብት የተነፈገዉን መላዉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ።
ለዚህም ነዉ ይህ አሁን እየተካሄደ ያለዉ የኦሮሞ ሕዝብ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ላለፉት ሃያ-አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለፍትህ፣
ለነፃነት፣ ለእኩልነት፤ ለሰብዓዊ መብት መከበርና ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ በአገሪቱ መስፈን ካደረጉትና አሁንም በተለያየ መንገድ እያደረጉ
ካሉት ትግል ተነጥሎ የሚታይ መሆን የለበትም ብለን የምናምነዉ። በተለይም በፊንፊኔ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ዜጎችን የብሔር-ብሔረሰብ
ስብጥር ግምት ዉስጥ ስናስገባ የማስተር ፕላን ተብዬዉ ዕቅድ መተግበር የሚጎዳዉ ኦሮሞዎችን ብቻ አለመሆኑን እንረዳለን። ይህ ደግሞ
የተቀጣጠለዉ ትግል የኦሮሞ ሕዝብ የተናጠል ትግል ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዉያን የጋራ ትግል መሆን እንዳለበት ያመለክታል።
ነገር ግን ትግሉ የጋራ ሳይሆን ቀርቶ ትናንት በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልሎች
ተቀጣጥለዉ የነበሩ የመብት ጥያቄዎች በጠመንጃ ኃይል ሲታፈኑና ንፁሃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ ጥያቄዎቻቸዉ የእኛም ጥያቄዎች እንደሆኑ
አምነን ከጎናቸዉ ሆነን አብረን መታገል ሲገባን የሌላዉ ሕዝብ ጥያቄ አይመለከተንም የማለትን ያህል ከሩቅ ሆነን መመልከትን የምንመርጥ
ከሆነ ለዚህ የጭቆና፣ የአፈናና የግፍ አገዛዝ የተመቻቸን እንሆናለን። በስልጣን ላይ ያለዉ ቡድንም የሕዝብን ጥያቄዎች በአግባቡ ከመመለስ
ይልቅ በመሣሪያ ኃይል ማፈንን አጠናክሮ ይቀጥላል። አሁን እየተካሄደ ላለዉ የኦሮሞ ሕዝብ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ እየተሰጠ ያለዉም
መልስ እስከ ዛሬ ካየናቸዉ የሥርዓቱ ጭፍን አቀራረቦች የተለየ ሆኖ አላገኘነዉም።
እንግዲህ የዚያች አገር ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛዉም ግለሰብ፣ ድርጅትና ተቋም፤ በአጠቃላይ የሚያስብ አዕምሮ ያለዉ
እያንዳንዱ ዜጋ «እስከመቼ ድረስ እየታሠርን፣ እየተደበደብን፣ ከገዛ አገራችን እየተሰደድን፣ ከምንም በላይ ደግሞ በግፍ እየተገደልን በዚህ
የጥቂቶች አገዛዝ ሥር እንቀጥላለን?» ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። ያለምንም ማጋነን የአገራችንና የሕዝቦቻችን መከራና ስቃይ ከልክ ያለፈ
ሆኗል። ስለዚህ አንዱ ሕዝብ ሲጠቃ ሌላዉ ከሩቅ ሆኖ የማየት በሽታ ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ዘላቂ ሊሆን የሚችለዉ
መፍትሔ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን ለጋራ ድል በጋራ ሆነን መታገል ብቻ ነዉ። ምክንያቱም በጋራ ትግል ከሚገኙት ድሎች
ሕዝቦቻችን የጋራ ተጠቃሚ ከመሆናቸዉም በላይ ድሉን ተከትሎ የሚመጣዉ የፖለቲካ ሥርዓትም እንደ ዛሬዉ ሕወሐት-መራሽ
የኢህአዴግ ሥርዓት ትዕቢተኛና አንባገነን ሥርዓት ሳይሆን ለሁሉም ሕዝቦች እኩል የሚቆምና ሁሉንም በእኩልነት የሚያገለግል ሚዛናዊ
የፖለቲካ ሥርዓት እንደሚሆን ስለምናምን ነዉ።
ስለሆነም እዉነተኛ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነት፣ ዕድገትና ብልፅግና የሰፈነባት፣ ለጥቂት ባለጊዜዎች ገነት ለብዙሃን ዜጎቿ
ግን ሲዖል ያልሆነችና ሁላችንም በመከባበርና በመፈቃቀር በጋራ የምንኖርባት፤ ብሎም ለተተኪዉ ትዉልድ በኩራት የምናስረክባት የጋራ
አገር እንዲኖረን የምንፈልግ ወገኖች ሁሉ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በትዉልድ አካባቢም ሆነ በፖለቲካ አመለካከት ሳንለያይ አንድ ላይ
ሆነን በኦሮሞ ሕዝብ የተጀመረዉንና ተጠናክሮ የቀጠለዉን ሕዝባዊ ትግል ከግብ እንድናደርስ የትግል አንድነት ጥሪያችንን ለሁሉም
የኢትዮጵያ ህዝቦች እናቀርባለን።
በዚህ አጋጣሚም ገዢዉ ቡድን የከፋፍሎ መግዛት ፖሊሲዉን መሠረት በማድረግ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት፣ በተለይም
የኦሮሞና የአማራ ብሔሮችን እጅግ በረቀቀ መንገድ አጋጭቶ የገዢነት ዕድሜዉን ለማራዘም፣ የጀመረዉን የተንኮል አካሄድ ተረድቶ
ሕዝባችን በጥቂት ገዢዎች ሴራ ሳይነጣጠል አብሮ በመሆን የጋራ አገሩን፣ ነፃነቱን፣ የዜግነት መብቱንና ከምንም በላይ ደግሞ ያልተሸራረፈ
ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር በአንድነት ጠንክሮ እንዲታገል አበክረን እናሳስባለን።
ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት ለሁሉም ሕዝቦች!!
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር

Contenu connexe

Tendances (8)

Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
 
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
 
Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01
 
Abiy ahmed vs hailemariam desalegn
Abiy ahmed vs hailemariam desalegnAbiy ahmed vs hailemariam desalegn
Abiy ahmed vs hailemariam desalegn
 
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a countryEnde hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
 
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
 
News 03-04-2014
News 03-04-2014News 03-04-2014
News 03-04-2014
 
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs  Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
 
Plus de Ethio-Afric News en Views Media!!

VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Plus de Ethio-Afric News en Views Media!! (20)

History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in AmharicHistory of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
 
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
 
Thanks/ Misgana
Thanks/ MisganaThanks/ Misgana
Thanks/ Misgana
 
The ark of the covenant
The ark of the covenant The ark of the covenant
The ark of the covenant
 
Arkofthecovenent
ArkofthecovenentArkofthecovenent
Arkofthecovenent
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
 
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
Coment on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  melesComent on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  meles
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
 
Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
 
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
 
King of kings yohannes 2.
King of kings yohannes 2.King of kings yohannes 2.
King of kings yohannes 2.
 
King of kings yohannes & Ethiopian unity
King of kings yohannes &  Ethiopian unityKing of kings yohannes &  Ethiopian unity
King of kings yohannes & Ethiopian unity
 
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital

  • 1. ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የቀረበ የትግል አንድነት ጥሪ በአገራችን መዲና የገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖቻችንን ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለአስከፊ ድህነት ብሎም ለጎዳና ተዳዳሪነት የዳረገዉንና የሚዳርገዉን፣ ጥቂት ባለጊዜዎችን፣ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎችንና የዉጭ አገራት ባለሀብቶችን ግን የሚያበለፅገዉንና «የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የጋራ የተቀናጀ ማስተር ፕላን» በሚል ስም የወጣዉን የድሆችን መሬት የመንጠቅ ጭካኔ የተመላበት መንግሥታዊ ዕቅድ በመቃወም በመላዉ ኦሮሚያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሳምንታትን ከማስቆጠሩም በላይ ለብዙ ንፁሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ተጠናክሮ እየተካሄደ ያለዉ በብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ቢሆንም የተቃዉሞዉ ምክንያት የሆነዉ ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነካዉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መብት የተነፈገዉን መላዉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። ለዚህም ነዉ ይህ አሁን እየተካሄደ ያለዉ የኦሮሞ ሕዝብ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ላለፉት ሃያ-አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፤ ለሰብዓዊ መብት መከበርና ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ በአገሪቱ መስፈን ካደረጉትና አሁንም በተለያየ መንገድ እያደረጉ ካሉት ትግል ተነጥሎ የሚታይ መሆን የለበትም ብለን የምናምነዉ። በተለይም በፊንፊኔ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ዜጎችን የብሔር-ብሔረሰብ ስብጥር ግምት ዉስጥ ስናስገባ የማስተር ፕላን ተብዬዉ ዕቅድ መተግበር የሚጎዳዉ ኦሮሞዎችን ብቻ አለመሆኑን እንረዳለን። ይህ ደግሞ የተቀጣጠለዉ ትግል የኦሮሞ ሕዝብ የተናጠል ትግል ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዉያን የጋራ ትግል መሆን እንዳለበት ያመለክታል። ነገር ግን ትግሉ የጋራ ሳይሆን ቀርቶ ትናንት በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልሎች ተቀጣጥለዉ የነበሩ የመብት ጥያቄዎች በጠመንጃ ኃይል ሲታፈኑና ንፁሃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ ጥያቄዎቻቸዉ የእኛም ጥያቄዎች እንደሆኑ አምነን ከጎናቸዉ ሆነን አብረን መታገል ሲገባን የሌላዉ ሕዝብ ጥያቄ አይመለከተንም የማለትን ያህል ከሩቅ ሆነን መመልከትን የምንመርጥ ከሆነ ለዚህ የጭቆና፣ የአፈናና የግፍ አገዛዝ የተመቻቸን እንሆናለን። በስልጣን ላይ ያለዉ ቡድንም የሕዝብን ጥያቄዎች በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ በመሣሪያ ኃይል ማፈንን አጠናክሮ ይቀጥላል። አሁን እየተካሄደ ላለዉ የኦሮሞ ሕዝብ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ እየተሰጠ ያለዉም መልስ እስከ ዛሬ ካየናቸዉ የሥርዓቱ ጭፍን አቀራረቦች የተለየ ሆኖ አላገኘነዉም። እንግዲህ የዚያች አገር ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛዉም ግለሰብ፣ ድርጅትና ተቋም፤ በአጠቃላይ የሚያስብ አዕምሮ ያለዉ እያንዳንዱ ዜጋ «እስከመቼ ድረስ እየታሠርን፣ እየተደበደብን፣ ከገዛ አገራችን እየተሰደድን፣ ከምንም በላይ ደግሞ በግፍ እየተገደልን በዚህ የጥቂቶች አገዛዝ ሥር እንቀጥላለን?» ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። ያለምንም ማጋነን የአገራችንና የሕዝቦቻችን መከራና ስቃይ ከልክ ያለፈ ሆኗል። ስለዚህ አንዱ ሕዝብ ሲጠቃ ሌላዉ ከሩቅ ሆኖ የማየት በሽታ ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ዘላቂ ሊሆን የሚችለዉ መፍትሔ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን ለጋራ ድል በጋራ ሆነን መታገል ብቻ ነዉ። ምክንያቱም በጋራ ትግል ከሚገኙት ድሎች ሕዝቦቻችን የጋራ ተጠቃሚ ከመሆናቸዉም በላይ ድሉን ተከትሎ የሚመጣዉ የፖለቲካ ሥርዓትም እንደ ዛሬዉ ሕወሐት-መራሽ የኢህአዴግ ሥርዓት ትዕቢተኛና አንባገነን ሥርዓት ሳይሆን ለሁሉም ሕዝቦች እኩል የሚቆምና ሁሉንም በእኩልነት የሚያገለግል ሚዛናዊ የፖለቲካ ሥርዓት እንደሚሆን ስለምናምን ነዉ። ስለሆነም እዉነተኛ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነት፣ ዕድገትና ብልፅግና የሰፈነባት፣ ለጥቂት ባለጊዜዎች ገነት ለብዙሃን ዜጎቿ ግን ሲዖል ያልሆነችና ሁላችንም በመከባበርና በመፈቃቀር በጋራ የምንኖርባት፤ ብሎም ለተተኪዉ ትዉልድ በኩራት የምናስረክባት የጋራ አገር እንዲኖረን የምንፈልግ ወገኖች ሁሉ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በትዉልድ አካባቢም ሆነ በፖለቲካ አመለካከት ሳንለያይ አንድ ላይ ሆነን በኦሮሞ ሕዝብ የተጀመረዉንና ተጠናክሮ የቀጠለዉን ሕዝባዊ ትግል ከግብ እንድናደርስ የትግል አንድነት ጥሪያችንን ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች እናቀርባለን። በዚህ አጋጣሚም ገዢዉ ቡድን የከፋፍሎ መግዛት ፖሊሲዉን መሠረት በማድረግ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት፣ በተለይም የኦሮሞና የአማራ ብሔሮችን እጅግ በረቀቀ መንገድ አጋጭቶ የገዢነት ዕድሜዉን ለማራዘም፣ የጀመረዉን የተንኮል አካሄድ ተረድቶ ሕዝባችን በጥቂት ገዢዎች ሴራ ሳይነጣጠል አብሮ በመሆን የጋራ አገሩን፣ ነፃነቱን፣ የዜግነት መብቱንና ከምንም በላይ ደግሞ ያልተሸራረፈ ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር በአንድነት ጠንክሮ እንዲታገል አበክረን እናሳስባለን። ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት ለሁሉም ሕዝቦች!! የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር