SlideShare une entreprise Scribd logo
1  sur  7
Télécharger pour lire hors ligne
ትዝብቴን ብገልፅ

(ቁጥር 2)

የህወሐት ኢህአዴግ የፖለቲካ ጭንቀት
ከአስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል (መቀሌ)
ከጠቅላይ ሚንስተር ህመምና ህልፈተ ህይወት ተያይዞ ሃገራችን በወሬና በስብሰባ እየተናጠች እንደ ከረመች
ሁሉም ዜጎች የሚያስታውሱት ነው። ለነበሩ ስብሰባዎችም ብዙ ገንዘብ እንደተጠየቀ የቅርብ ትዝብታችን
ነው። ያ አልበቃም ብሎ አሁንም ለአንድ ፓርቲ ህወሐት ኢህአዴግ ለማጠናከር ተብሎ 80 ሚልዮን
ህዝባችን፣ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ፣ የህወሃት ኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና የአጋር ፓርቲዎች አባላት፣
የከተማ የገጠር ህዝቦች በስብሰባ ተጠምደው እየተናጡ ይገኛሉ።
ለዚሁ ለማስረጃነት ያህል ባለፈው ሳምንታት ከ11/02/05 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል በትግራይ
ዘኖች ወረዳዎች ከተሞች ተንቀሳቅሼ ነበር። በተንቀሳቀስኩባቸው ቦታዎች ያየሁትና የታዘብኩት ቢኖር በዚህ
ፅሑፌ አንድ በአንድ አርእስት በመስጠት ለአንባብያን እንዲደርስ አድርጌላሁ። የትግራይ ህዝብ 100% በግድ
የህወሐት ኢህአዴግ አባል ፓርቲ እንዲሆን እየተገደደ ይገኛል።አሁን ግዜው የመኸር ወቅት ሁኖ የገጠር
ህዝብ የዘራውን ሰብል ለማጨድና ለመውቃት ሌት ተቀን የሚረባረብበት ሰዓት ነበር። ነገር ግን ከጠቅላይ
ሚንስተር መለስ ሞት ጀምሮ ያልተረጋጉ የህወሐት መሪዎች የገጠሩ ህዝብ በየፆታው፣ በየዕድሜው እየለያዩ
ሴቶች ለብቻ በቀን 30 ብር፣ ለወንዶች ለብቻቸው 35 ብር አበል በመስጠት በየአቅራብያቸው በሚገኙ የወረዳና የዞን ከተሞች ጠርተው
በመሰብሰብ የልማት ስልጠና በሚል ሽፋን፣ ሁሉም ሰው የህወሐት ፓርት አባላት መሆን አለበት በማለት ከ4 እስከ 7 ቀናት በመሰብሰብ
የኔትዎርክ አደረጃጀት እያደረጉ ይገኛሉ።
የአደረጃጀቱ ጥበብም ሴቶች ለብቻቸው ያነሰ ህዋስ(ዋህዮ) 1/5 (1/6)፣ ከፍተኛው ኔትዎርክ (ዋህዮ) በአንድ ሁኖው በ4 ለ30 ሴቶች
ይደራጃሉ። ሁሉም ሴቶች በዓመት የህወሐት አባልነት 12 ብር፣ የወይን ጋዜጣ 3 ብር፣ ለሴቶች ማኅበር 6 ብር፣ ለቀይ መስቀል 3 ብር፣
ድምር 24 ብር እንዲያዋጡ ይገደዳሉ። እነዚህ የገጠር ሴቶች ሁሉም የህወሐት የ40 (የ50) ዓመት የመለስ እቅድ (መመርያዎች) ሊተገበሩ
ከሆኑ ከውስጣቸው ከህወሐት ኢህአዴግ እምነቶች ውጭ የሌላ ፖለቲካ እምነቶች እነዳይሰራጩ በጥብቅ እንዲኮንኑዋቸውና ከተገኙ
እንዲለቅሙዋቸው በስልጠናው ተናግረዋል። ሌላ የተሰጣቸው ስልጠና መለስ የተወልን ለ50 ዓመት እቅድና መመርያ የማይተገብር
ማነኛውም ዜጋ እንደ ጠላት እንደሚታይና ክትትል እነዲደረግለት በጥብቅ ተነግረዋል።በዘንድሮው በ2005 ዓ.ም የመስኖ ስራ ከ49
ሚልዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ማፈስ ስላለብን እቅድ ግብ እንዲመታ ሴቶች ወሳኝ ሚና ስላላቸው ለመስኖ የሚሆን
መሬት ይኑራቸው አይኑራቸው መዳበርያ በግድ እንዲወስዱ ተደርጓል። በሌላ በኩል ወንዶች አርሶ አደሮች ልክ እንደሴቶች በ1/5 እና 4
ለ30 ተደራጅተው የመለስ በትግርኛ ሕንፃፃት(እቅድና መመርያ እምነቶች) እነዲተገበሩ ከህወሐት አስተሳሰብ ውጭ እንዳያስቡ
እንዳይተነፍሱ በሚል ለ4(5) ቀን በ35 ብር አበል ሰልጥነዋል።
የሴቶችና የወንዶች አርሶ አደሮች ከላይ እንደገለፅኩት ከመደራጀት አልፈው በየጐጡ ያሉ አባወራዎች ቤት ቁጥር ኣስር ቤት በአንድ
ኔትዎርክ አንድ ለ10 ሲደራጅ በነብስ ወከፍ የአባወራ ቤት ኣባወራና እማወራ ከነ ልጆቻቸው እንዲደራጁ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት
በሚልዮን የሚቆጠር ብር ከ4 ቀናት በላይ ለአንድ ፓርቲ ዕድሜ ማራዘምያ ተብሎ በስብሰባ ወጭ ማድረግ በብዙ ሚልዮን ብር የሚቆጠር
አበል፣ ትራንስፖርት በመክፈል የመንግስት ገንዘብ ማባከን ምን ያህል ስህተት መሆኑ በሌላ በኩል ህዝብ በስብሰባ ሲናጥ የእርሻ ሰብል
ደርቆ መታጨድ የሚገባው እያለ ዝናም ዘንቦ ሰብሉን እያበላሸው የመንግስት ባለስለጣናት፣ የግብርና ባለሙያዎች ስለሚበላሸው ያለው
ሰብል ብዙ ሲቆረቆሩ አይታዩም።
የመንግስት ሰራተኞችም ልክ እንደ አርሶ አደሩ የመንግስት ገንዘብ ከ91 እስከ 220 ብር በቀን አበል እየተሰጣቸው ከ7 ቀን በላይ
ተሰብስበው በአንድ ለአምስት ኔትዎርክ በመደረራጀት ሁሉም አባል ህወሐት እንዲሆኑ ሲገደዱ ለዚሁ ለመተማመኛ ለአባይ ግድብ የአንድ
ወር ደሞዝ እንዲከፍሉ ፎርም እንዲሞሉ ወረቀት ይሰጣቸዋል። በዝያች ፎርም ሞልቶ ያልፈረሙ የመለስን እምነቶችና እቅዶች
የማይተገብር የካደ ተብሎ ይፈረጃሉ። አረ ስንት ነገር አለ ተፅፎ የማያልቅ።
በሁሉም ት/ ቤት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በህወሐት ፓርቲ እንዲደራጅ ግድ ይላል።በአሁኑ ጊዜ እንስሳ ዘቤት ካልሆነ
በስተቀር በህወሐት ፓርቲ ያልተደራጀ አንባገነን የአብዮታዊ ዲሞክራስያዊ አስተሳሰብ ያልተከተለ በዚህች መሬት አይኖራትም ወይ ዳግም
በትግርኛ ቋንቋ ኳኵቶ (በአማርኛ አቃቅማ እሾህ) ማለት ነው ተብለዋል። በአቶ አባይ ወልዱ ተሰይሞ ተመርቆ የተሰጠ ስም የተከበራችሁ
የኢትዮጵያ ህዝቦች ህወሐት ኢህአዴግ 80 ሚልዮን ህዝብ እኛ የተነፈስንበት ካልተነፈስክ አትኖራትም። በማለት በአሁኑ ጊዜ ፍትሃዊና
ታማኝ ዲሞክራሲ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ እንዴት ይታመናል።ይህ የአፈናና የፈላጭ ቆራጭ አደረጃጀት በትግራይ ብቻ ታጥሮ የሚቀር
ቢሆን አይከፋም ነበር። ትልቁ መርዛም ነገር ካሁን በፊት እነደተለመደው በትግራይ ተፈትኖ በህወሐት መሪዎች ብቁ ነው ፈተና አልፈዋል
ተብሎ ከፀደቀ በኋላ ወደ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ከዛ በኋላም ወደ አጋር ድርጅቶች ተላልፎ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ይንጥ እንደነበረ ሁሉ
1
አሁንም በትግራይ ተጀምሮ ፈተና አልፈዋል ተብሎ በትግራይ የሚደረገው ያለው አፈና በሁሉም ክልሎች መተግበር ጀምሮ አርሶ አደሮችና
ምሁራኖች፣ ተማሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች በስብሰባና በቃል ኪዳን መሃላ እየተናጡ እናያለን እየማሉ እናያለን።
ይህ አሰራር የመድብለ ፓርት መኖር አምናለሁ የሚለው የህወሐት ኢህአዴግ ፓርትና መንግስት አሁን በሚከተለው ያለው አፋኝ
አደረጃጀትና የዜጎችን ነፃነት መንጠቅ ዜጎች ተሸማቅቀውና ፈርተው፣ ሰግተው እንዲኖሩ ማድረግ በ2002 ዓም የነበራ ሃገራዊ ምርጫ
99.6% ተመረጥኩ ያለበት የተጭበረበረ ምርጫ ለመጪው 2007 ለሁሉም በሰላማዊ መንገድ ፓርላማ ተወዳድረው ለአንባገነኑ ህወሐት
ኢህአዴግ በህዝብ ዳኝነት በምርጫ አሸንፈን ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንመሰርታለን ለሚሉ ፓርቲዎች ከወዲሁ አስወግዶ 100% ወንበር
ለመያዝ ብቻው ለብቻው በአንድ እጅ እያጨበጨበ በ2007 ዓም ተወዳድሮ ለቀጣይ አምስት ዓመት አንባገነኑ ስርዓቱ ለማራመድ
ስለፈለገ ነው።
ለዚህ የህወሐት ኢህአዴግ ርካሽ ፍላጎት በሃገራችን ያሉ ሰላማዊ ትግል አምነው የሚታገሉ የምርጫ ኃይሎች በመተባበር አንድነት
በመፍጠር ህወሐት ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በነፃ የመንቀሳቀስ እድላቸው ለማፈን የሚከተለው ያለ በህዝብ ላይ ተፅዕኖ መጭው
ውድድር የውድድር ዲሞክራስያዊ መጫወቻ ሜዳው እነዲሰፋ ጠንክረው መታገል አለባቸው። የህወሐት ኢህአዴግ ተስፈኞች የሆኑ
ገልበጥበጥ የሚሉ ተወላዋይ ፓርቲዎችም ህወሐት ኢህአዴግ ለግዜው ተጠቅሞ የሚጥላቸው መሆኑ አውቀው ወደ ትክክለኛ የተቃውሞ
ሃይል ጐራ ቢደባለቁ ወይ በግልፅ ህወሐት ኢህአዴግ ጐራ ወግነው ቢታገሉ፣ ካለበለዝያ ገልበጥበጥ እያሉ ለኢትዮጵያ ሃቀኛ ዲሞክራስያዊ
ሃይሎች ባያምሱ ይሻላል።
በተጨማሪ ምሁራኖች፣ ባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች፣ መላው የሃገራችን አርሶ አደሮች፣ ሰራተኞች፣ የመንግስተ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች ህወሃት
ኢህአዴግ እሚፈፅመው ያለ አስገዳድ የአፈና አደረጃጀት፣ ነፃነታችሁና ስብእናችሁ የመነጠቀ ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለመጭው ትውልድም
ጠንቅ ስለሆነ የዜግነት ግዳጃችሁን ብትወጡ ለሃገራችን ጥቅም በዜጎችም የተረጋጋ ኑሮና ሰላም ይፈጠራል።
በውሸት የልማት አዋጅ ስልጣን ማራዘም አይቻልም
የ ህወሐት መሪዎችና ካድሬዎች ከጠ/ሚንስተር ግብአተ መሬት በኋላ በብዙ ጨለምተኝነት አስተሳሰብ ላይና ታች እያሉ ቆይተው፣
ጠ/ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝና ምክትላቸው ደመቀ መኮነን ስለጣን ከተረከቡ በኋላ የህወሐት መሪዎች እንደተለመደ ሰርቶ ማሳያ
ፕሮጀክታቸውን ሰርተው በሞዴልነታቸው ለሃገራችን ክልሎች ለማበርከት በክልልና በዞን ከተሞች በመከፋፈል በዓይን ሊታይ በማችል ፣
የማይቀመስ የማይዳሰስ የማይሰማ የሃሰት ልማትን አስመልክተው የመንግስተ ብዙሃን መገናኛ በመቆጠቀጠር በየነ መኩሩ በሽሬ በሑሞራ፣
አባይ ወልዱ በአኩሱም፣ ቴድሮስ ሓጎስ በመቀሌ ሓወልት ሰማዕታትና አኩሱም ሂቴል፣ ኪሮስ ቢተው ለእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሰራተኞች፣
ሌሎች መሪዎችም እየዞሩ ሲደስኩሩ ሰንብተዋል።
በሁሉም ቦታ የነበሩ አጀንዳዎች
1)ከላይ የዘረዘርኩት አፋኝና አስገዳጅ አደረጃጀት በስፋትና በጥልቀት በመቀስቀስ የመለስን አደራ በቃል ኪዳን ታጥቀን ካልሰራን፣ የመለስ
የአምሳ ዓመት የተወልን መመርያ በቆራጥነት ካልሰራን፣ ለእድገታችን እነቅፋት የሆኑ በታኞችና አድሃሪዎች፣ ኳኵቶ(አቃቅማ) እንዳይበቅሉ
በመልቀም እንስራ ብለዋል።
2)በዘንድሮ 2005ዓ.ም የመስኖ ልማት 49 ሚልዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ እናፍሳለን በማለት በተለይ ደግሞ የትግራይ ክልል
የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊና የክልሉ መክትል ፕረዚደንት አቶ ኪሮስ ቢተው የተባሉ ለዚህ ሁሉ የእርሻና መአድን ተመራማሪ
ያወረዱለት መመርያ ሙያ የጐደለው በግብታውነት የሰከረ(ኣፕሸሸ) አቀራረብ፣ በዘንድሮው የመስኖ ምርታችን 49 ሚልዮን በላይ ኩንታል
ማፈስ አለበን። ይህን ምርት ለማፈስ ግን ሁሉ የግብርና ሰራተኛ የመለስን ራእይ በመከተል የህወሐት አባል በሆን አለበት ብለዋል። በዚሁ
ግብታውነት የተሞላበት አነጋገርና የመመርያ አሰጣጥ ምሁራኖች በደስታ አልተቀበሉትም። ለምን ለሚለው ጥያቄ 49 ሚልዮን ኩንታል
የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለማፈስ የተመቻቸ ሁኔታ ስለሌለ፣ 50% የትግራይ ታራሽ መሬት በመስኖ አጠጥቶ ምርት ለማፈስ ውሃ የት
አለ ስንት ግድብ አለ? የሚሰጠን ያለመመርያ በትግርኛ ቋንቋ ህንዱድነት(ግብታውነት ነው) አሉት።
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች በትግራይ ክልል ይቅርና የትግራይ ታራሽ መሬት 50% በመስኖ ለማጠጣትስ ይቅር ከመቀሌ ከተማ
ጀምሮ የዞን የወረዳ ከተሞች ለህዝብ የሚጠጣ ውሃ የለም። በትግራይ ክልል ያሉ ግድቦች በቀድሞው የክልሉ አስተዳዳሪ የነበሩ አቶ ገብሩ
አስራት የተሰሩ፣ በአኩሱም እንዳ ንጉስ በሚባል ግድብ በ3.8 ሚልዮን የተሰራ 100 አባወራ አርሶ አደር ያቀፈኘ፣ በሽሬ አውራጃ በዓዲ
ዳዕሮ መስከበት በተባለ ወንዝ በ4 ሚልዮን ብር ግምት በሰው ሃይል የተሰራ 100 ሄክታር ማሳ መስኖ የሚያጠጣ፣ በሳምረ አከባቢ 150
ሄክታር መስኖ የሚያጠጡ ትናንሽ ግድቦች፣ በቤት ማራ የሚገኙ የወንዝ ጠለፋዎች ከ200 ሄክታር የማይበልጡ መስኖ የሚያጠጡ አሉ።
ሌሎች ከጥንት ጀምረው የነበሩ በመኸር ወቅት ብቻ የሚሰሩ ምንጮች ነበሩ። በጋ ሙሉ የሚሰሩ የመንጭና ትናንሽ የጕድጓድ ውሃዎች
አሉ። እነዚህ ምንጮች ሁሉ ተሰብስበው የሚሰጡት የመስኖ ምርት እጅጉን ትንሽ ናቸው። በሌላ በኩል በራያ የተቆፈሩ ጥልቅ ጕድጓዶች
ከ200 በላይ አሉ ይባላል። እነዚህ ጥልቅ ጕድጓዶች እስከ አሁን ግልጋሎት አልሰጡም። ታድያ 6 መቶ ሺ 17 ሄክታር መሬት በየተኛው
ውሃ መስኖ የሚያጠጣ የሚል ጥያቄ አቶ ኪሮስ ቢተው መልስ የላቸውም። ይህልም እንጀራ ከመሆን አልፎ ?
2
አቶ ቴድሮስ ሃጎስም በአኩሱም ሆቴልና በሐወልት ሰማዕታት አዳራሽ ለምሁራኖች ያደረጉት ስብሰባ ተቀባይነት አላገኘም።
አልተሳካላቸውም። በአጠቃላይ የህወሐት መሪዎች ታማኝነት ለማግኘት እየዞሩ የሚያደርጉት ስብሰባ ይቅርና አባል ፓርቲ ባልሆኑ ዜጎች
በአባሎቻቸውና በካድሬዎቻቸውም ተቀባይነት አላገኙም።ሌላ ቀርቶ ለመስኖ ማዳበርያ ውሰድ የተባለ ገበሬውም አልተቀበለውም።እንደ
አብነት ለመጥቀስ በ17/02/2005 ዓም በዓድዋ አውራጃ በሓሓይለ፣ በዓዲ አሕፈሮም ቀበሌዎች በካድሬዎች የቀረበላቸው የውሸት
ልማት በመቃወም በመበተን ወደየስራቸው ሂደዋል።
በሴቶችና በወንደች መካከል የነበረ የውሎ አበል አከፋፈል አድላዊ በመሆኑ ሴቶች አኩርፈዋል። በአጠቃላይ የህወሐት መሪዎች በመቶ
ሚልዮን የሚቆጠር የመንግስት ገንዘብ የመንግስት የስራ ሰዓት የተሰብሳቢ ኣርሶኣደር ሰብሉን እንዳይሰበስብ በስብሰባ መጠመዱ ኪሳራ
በማባከን ለአንድ ፓርት ለማጠናከር ተብሎ በዘመቻ የተሰማሩበት ለህዝብ በሃይለኛ አፈናና የትግራይ ህዝብ እንደሚደርሰው 100%
የደደቢት ብድርና ቁጠባ፣ ፓኬጅ፣ የመዳበርያ እዳ ስላለው ተሎ ክፈል ተብሎ እነዳይገደድ ነው እነጂ ይደረጋል የተባለው በስብሰባ መናጥ
አልተቀበለውም።
በአቶ አባይ ወልዱና በአቶ በየነ ሞኩሩ የተደረገው ቅስቀሳመ ነጋዴው ፣ ባለሃብቱ፣ ምሁራኑ አልተቀበሉትም። ምክንያቱም በተግባር
የማይተገበር ይህልም እነጀራ ስለሆነ።እኔ እሚገርመኝ ሌሎች ዜጎችም እምያሳስባቸው ያለው ህወሐት ለ38 ዓመት ሙሉ የትግራይ ህዝብ
ከህወሐት አስተሳሰብ(እምነት)ሌላ እንዳያመልክ ተደርጎ ቆይቷል። ይህ የትግራይ አፈናና ያለ ፍላጎቱ አምላኪ እንዲሆን ማድረጉ እንደተሳበ
(ወረርሽኝ) በሽታ ወደ ሌሎች ብሄሮች ብሄረሰዎች እንዲዛመት ተደርጎ በብዙ ሚልዮን ዜጎች ለምጥ ፈጥሮ ቆይቷል።አሁንም እየቀጠለበት
ይገኛል።
ለመሆኑ መቋጫው ያት ነው? ህወሐት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በውስጡ የተለያዩ ሐሳብ ላነሱ ወገኖች በዲሞክራሲያዊ መድረክ በመወያየት
ከቂም በቀል በፀዳ መንገድ ግርጭቶች ፈቶ እነደማያውቅ በእርግጠኝነት አውቃለሁ። ነገር ግን ያጊዜ የተዘባረቀ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነበረ
እነበል። ግን ከ38 አመት በኋላ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ሊደረግ የማይገባው ማድረግ ለምን ያደርጋል? ከአመሪካና አውሮፓ ዲሞከራት አገሮች
እኩል ባለስቀምጠውም በአፍሪካ ካሉት ዲሞክራቲክ አገሮች እነኳን ሊማር አይችልም?
እኔ በዚች ዕድሜየ 4ኛ መንግስት የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ምናልባትም እግዚአብሔር ካለው ሁሉም አይሳነውምና 5ኛ መንግስትም
የሚያይ ይምስለኛል። እዚህ ላይ ግን የ4ቱ መንግስታት በማነፃፀር ባህሪያቸው ጠቁሜ ልለፍ።ጃኖሆይ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች
በስብከት፣ በሃይማኖት፣ በከፋፍለህ ግዛ በአምልኮት ህዝብ ጨቁነው በመያዝ ለ40 ዓመት ገዝተውናል። መነግስቱ ሃይለማርያም
መጀመርያ በውሸት አዋጆች የህልም ዲሞክራሲና እንጀራ በማብላት ኋላም የማይደበቅ ፋሽሽታዊ ወታደራዊ ባህርዩን በማጋለጥ
በጠርሙስ ደም በሞምላት በአደባባዮች ደም በመርጨት በወቅቱ 60-70 ሚልዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ስጋትና ሽበራ በመፍጠር 17 ዓመት
በፋሽሽታዊ አፈና ገዛን።
የህውሓት ኢሃደግ መንግስት ሃይለማሪያም ለወታደራዊ መንግስቱ በወታደራዊ ሃይል በማስወገድ ስቢል መስለው ስልጣን ከያዙ በኋላ
ቀስበቀስ ያ ወታደራዊ ባህርያቸው መጣና እንደ መንግስቱ ደም በአደባባይ ባይረጩም ማንም ሰው የፈንጅ ወረዳ ከጣሰ ያገኛታል በሚል
አነጋገርና ስጋትና ሽብር ፈጣሪ ነበሩ።ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝም መደባዊ አመጣጣችው ንፁህ ስቢል ሰው ናቸው። ሆኖ
ግን ከህወሐት ኢህአዴግ ወታደራዊ አመራር የወሰዱት ስልጠና ያለ ይመስለኛል። ተመሳሳይ አነጋገር እሳትን ከነካችሁ ትቃጠላላችሁ
ዎዮላችሁ ማለት ጀምረዋል። በተግባርም በአሁኑ ጊዜ በትግራይ የተጀመረው ሁሉ ሰው የህወሐት አባል ካልሆነ ታማኝነት የለውም የሚል
በሞላው የኢትዮጵያ ህዝብ በ80 ሚልዮን ህዝብ በውድም በግድም የኢህአዴግ አባል መሆን ኣለበት ተብሎ በስብሰባ ይናጣል ።
የጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርምጃው ከመደገፍ ውጭ ኣይሆንም ። ኣንድ ኣንድ መጥፎ እርምጃ ሲወስዱም እናያለን ። ሌላ
በዚህ ኣጭር ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣንም ወራትም ሰው በጥይት ሞሞት ጀምራል ለዚህ ኣብነት በደሴ
በሙስሊም ህብረተሰብ የተጀመረ ግድያ ኣለ። የግድያ ተገቢ ነገር ኣልነበረም ኣይደለም የኔ ጥያቄ ዋና ነገር ግርጭት በመግደል ጥይት
በመተኮስ መፈታት የለበትም ። በትግራይ የሚነገረው ያለው የስድብ ናዳም መቋጫ መኖር ኣለበት እላለሁ። ከስድብ በኃላ ወዴት ነው
ጉዞው?ኣደገኛ ነገር ነው።
ኣሁንም ትእዝብቴ
መቋጫ የሌለው የኢሮፕ ብሄረሰብ ረሃብና የውሃ ጥም
የኢሮብ ብሄረሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኝ ከኣድግራት ከተማ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት
የሚገኝ ሆም የኢሮብ ህዝብ ሲወሰድ ኢሮፕ ኢሮፕ እንዳልጌዳ ኢሮፕ መኩኔቶ ኢሮፕ ሓሳብለ የሚባሉ ዜጎች ናቸው የነዚህ ህዝብ ብዛት
ከ38 ኣመት በፊት ብዛታቸው ከ100ሺ በላይ እንደ ነበር የኣከባቢው መሬት ትላልቅ ተራራዎች ይገኙበታል የኣከባቢ ኢሮፕ የተፈጥሮ
ሃብት የኢሮፕ መልከኣ ምድር ከ38 ኣመት በፈት በጥድ በዌራ በበለስ ሌሎች እፅዋት የተሸፈነ ነበር ።በዚሁ ቦታ እንስሳ ዘቤት ንብ
ነፍሰወከፍ ኣባወራ (ኣርሶ ኣደር) ከ30 ቆፎ በላይ ንብ ነበሩት ፍየል በግ በብዛት ነበሩ የቀንድ ከብትም ቢያንስ በኣንድ ኣባወራ ዝቅተኛ
3
ከ20 በላይ ነበሩት በዚ የሚመረት የምግብ ኣይነት ገብስ የተለያዩ ስንዴ በቆሎ ፤በለስ ፤ማር ቅቤ ነበር ። በዚ ወቅት የኦሮፕ ህዝብ ድርቅ
ረሃብ የሚባል ኣልነበረም ተረጅም ኣልነበረም።
የኢሮፕ ብሄረተሰብ የኣሁኑ ገፅታው
እንስሳ ዘቤት በሚመለከት ከብት ፍዮሎች ንብ ከ38 ኣመት በፊት ከነበረው ብዛት ከ2%በታች ይገኛል እፅዋት በሚመለከት በኣለም
እጁጉን ቀንሳል ሌላ እፅዋት እንደ ጥድ ዌራ ሌሎች ለሙዜም የሚሆንም የሉም ሌላ ቀርቶ የኣሲንባ ተራራ የነበሩ እፅዋት ጠፍተዋል።
የህዝብ ብዘት በሚመለከት ኢሮፕ ብሄረሰብ በዘመነ ህ.ወ.ሃ.ት ኢህኣደግ ስልጣን ወደ ሁለት ወረዳዎች ተከፍሏል እሱም ግማሹ ወደ
ሳዕስዕፃዕዳ እምባ ወረዳ ዕዳጋ ሓሙስ ግማሹ ደግሞ ወረዳ ኢሮፕ ሆኖ ዋና ከተማው ደውሃን ነው። የኢሮፕ ህዝብ ከ100ሺ በላይ
የነበረው በኣሁኑ ግዜ በኢሮፕ ወረዳ ያለ ህዝብ ከ16ሺ ኣይበልጥም የቀረው ህዝብ ኣብዛኛው በተለይ ሙሁር ህብረተሰብ ወደ ውጭ
ኣገርተሰደዋል ፤ጥቂት የማይባልም የምድር በዳ ንሮ የመረረው በኣዲግራትና መቀሌ ይኖራል ወረዳ ኢሮፕ ድሮ የንብ የፍየል የከብት
መንደር ብዙ ህዝብ የሚኖርበት የነበረች በኣሁኑ ጊዜ የወታደር መንደር ሆናለች የኢሮፕ ህዝብ ሻኣብያ ኣፍኖ የወሰዳቸው እስከ ኣሁን
ያልተመለሱ በዛው የቀሩ ኣሉ ።
የኢሮፕ ቋንቋ በትግርኛ ቋንቋ እየተዋጠ ለሙዚየም የማይገኝበት ሁኔታ ተፈጥራል። እንግዱህ ይህ ካልኩ ወደ ዋና ኣጀንዳየ በመምጣት
የኢሮፕ ህዝብ ሃብት እየተመናመነ መጥቶ ድርቅና የዝናብ እጥረትተደምሮበት ባለፉት 21 ኣመታት የእርዳታ ጥገኛ ሆኖ ቢቆይም ግን
ዳግም የማይናቅ የእርሻ ምርት ማር ወተት ወዘተ ያገኝ ነበር ኣሁን እንደ ታዘብኩት እንስሳውም ንቡ ከብት ፍየሉ የሉም ቢኖሩም
የሚጠጣ ውሃ የለም የሚበላ መኖ ሰር የለም ይቅርና ለእንስሳ ለሰውም ውሃየለም የእርሻ ምርትም ጭራሽ ኣልገባም ዝናብ ባለ መዝነቡ
ያለው ህዝብ በእርዳታ ነው የሚነረው ኣሁን ያ የበሰበሰ ስንዴም የለም ህዝቡም እጅጉን ጥቂት ነው የቀረው በደውሃንና ዓሊተና ያሉ
ሰዎችም ከወታደሮች የተሳሰሩ ሴተኛ ኣዳሪና ነጋዴዎች ናቸው ያእርጅና ለኢሮፕ የለም ኣለ የሚባለው ህዝብ ከ21ሺ ኣይበልጥም።
ለኢሮፕ ችግር መፍትሄ የምስራቃዊ ዞን መሪዎች ይሁኑ የክልሉ መንግስት ሲያግዙት ኣይታዩም ታድያ የኢሮፕ ችግር መቸ ይቃጫል ሁሉ
ግዜ ጥያቄ ያስነሳል ያነሳበት የድርቅ ጉዳይ ካነሳሁ በኣሁኑ ግዜ በደቡብና ደቡባዊ ምስራቅ ትግራይ በራያ በመሁኒ መቸር ካለና ፤ዋጅራት
በኣሰርሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተደጋጋሚ ግዜ በዝናብ እጥረት ለብዙ ኣመታት የእርሻ ምርት ያላስገቡ ። የውሃና የምግብችግር ያላቸው
ሆነው በትግራይ መንግስት ለጉዳዩ ኣትኩረት ሰጥቶ እንዳጣ ገዛ ከላይ እንደዘረዘርኩት ስልጣኑ ለመረጋጋት ብቻ የሚረጠው ያለው የራያና
የዋጅራት ህዝብም ኣጋር ከሚሆነው መንግስት ያሰፈልገዋል ኣደጋ ላይ ነው ያለው ። ኣደጋ ብቻ ሳይሆን በኣሁኑ ግዜ ሰውም እንስሳ የሚበላ
ውሃ የሚጠጣው የለውም።የዚህ ችግረኛ ህዝብ ብዛት ቢያንስ ከ30.000 በላይ ነው፡፡
በከሮምና ኣላማጣ ያየሁት የዜጎችን መብት የሚነካ ኣሰራርተከስታል
በጉዘዮ እንዳዩሁ በከሮምና በኣላማጣ ወረዳዎች እድሜ ደረሰና ነዋሪ ህዝብ መታወቅያ ሊሰጠውና ሊታደስለት ሲጠዩቅ ስደት ስለምትሄድ
ኣይታደስላችውም እየተባሉ ይከለከላሉ ያመታወቅያ መስጠት የ ህገ መንግስታዊ የዘግነት መብታቸው እያለ እየተጉላሉ ይገኛሉ።
የመታወቅያ ጥያቄ ጉዳይ በትግራይ ክልል መታወቅያ ለማግኘት ብዙ ቅድሜ ሁኔታ ሟሟላት ግድ ይላል ይህም ማንም ሰው መታወቅያ
ለማግኜት የቀይ መስቀል የትግራይ ልማት ማህበር የወጣት ፤ የግብረ ማህበር ለወይን ጋዜጣ ፤ የህ.ወ.ሃ.ት ኣባልነት ገንዘብ እንዲከፍሉ
ይገደዳሉ ይህ ኣሰራር በመላው የትግራይ ዜጎች ፤ ወረዳዎች ፤ቀበሌዎች የሚተገበር ኣሰራር ነው። ዋና ኣለማውደግም ሁሉ እንቅስቃሴ
ገንዘብ የሚል በሽታ ይመስለኛል ።
ለ ህ.ወ.ሃ.ት ለመጠናከር የሚጠፋ ያለው ገንዘብ ስንት ይሆናል ?በሞቶሺ ወይ በሚሊዮን
በትግራይ ክልል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ህልፈት ተከትሎ በፓሪቲዎች በተፈጠረ ጭንቅንቅ 80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በስብሰባ
ተጠምዶ እየተናጠ እንደከረመ በዚህ ትእዝብቴ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ስብሰባው እንደሞደልነት(መፈተኛ) በትግራይ ስለተፈተነ በነዚህ
ስብሰባዎች በትግራይ ብቻ ለውሎ ኣበል ለትራንስፖርት ለተሰብሳቢዎች ገበሬዎች ሰብላቸው በሚሰበሱቡበትና በሚወቀበት ጊዜ ያባከነ
ጉልበት በገንዘብ ሲታሰብ የመንግስት ሰራተኛ በመንግስት የስራ ስዓት ለህዝቡ ይሰጠው የነበረ ኣገልግሎት ገንዘብ ሰታሰብ የተገልጋይ
ህዝብ ኣገልግሎት በማጣቱ የከሰረው ጊዜና ገንዘብ በገንዘብ ሲታመን ከኣንድ ፓርት ህ.ወ.ሃ.ት ለመጠናከርና ለመረጋጋት በሞቶ ሚሊዮን
የሚገመት ገንዘብ ማባከን ምን ያህል ወንጀል መሆኑ ለህዝብ ግልፅ መሆን ኣለበት ።
በትግራይ ያሉ 5 የሚሆኑ ትናንሽ ግድቦች በህዝብና በትንሽ የማሽነሪ ደጋፊ የተሰኑ ግድቦች ከ20 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ኣልፈጅም በነዚህ
ግድቦች ከ1500 በላይ ኣባወራ ኣርሶ ኣዶሮች ተጠቃሚ ሆነዋል ፤ ኣሁን ለኣበልና ለትራንስፖርት ሌሎችም የባከነ ገንዘብ ሳንጨምር
ለውሎ ኣበል ብቻ የወጣ ገንዘብ ሲተመን ፤ህ.ወ.ሃ.ት ኣንድ ሚሊዮን ኣባል ቢነረው በዝቅተኛ ውሉ ሌላ ኣሁን ኣባል ለማድረግ በስብሰባ
ለ5 ቀን ተጠምዶ የሰነበተው ለኣንድ ሚሊዮን ህዝብ በቀን 35 ብር ሲታሰብ ለ 4ቀን ሲታሰብ የኩፍኛ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኛ 220
በቀን ሲዮን ከ100.000 ሰው ለ 7ቀን ውጪ ሲታሰብ ስንት ይሆናል ስንት መቶ ሚሊየን ኣንባብያን ልብ በሉት፡፡
በግዚዮው ባለ መሰብሰቡ የፈሰስ ስብል የመኸር ዝናብ ያባላሸው በገንዘብ ሲተመን እጅግ ብዙ ገንዘብ ነው ። ስለ ሆነ ሁኔታው ሲታዘብ
ምን እያሉ እና እየሰሩ በማለት እኔም ይገርመኛል ። ህዝቡም የመንግስት ሰራተኛው ለሁኔታወ አግራሞት እየተሰማው ዝምታን መርጦ
ተጨንቆ ይኖራል። በተለይ ሙሁር ክፍል የሚፈጸመው ያለ የመደናገር ስራ እያወቀ እንዳላወቀ ዝም ብሎ መለፍ ለራሱም ለሃገሩም ጎጂ
እንጂ ጠቃሚ አለመሆኑ አውቆ አለመቃወሙ ለወደፊቱ ተወቃሽ እንደሚየደርገው ይታየኛል።
4
የህወሐት ህአዴግ መሪች በአሁኑ ጊዜ የሚፈጽሙት ያሉት ስህተት ቆም ብለው አስበውበት የጥፋት መንገዱ አቁሞው ምን እየተባለ ነው
ብለው ከምሁራኖችና ከከፍተኛ በለሞያዎች የሕግ፣የታሪክ አዋቂዎች የዕድሜ ባለፀጋዎች ቢያማክሩ በግብታውነት ተጉዘው ወደ ጨለማ
ከመግባትያድናቸዋል።
በኔ ትዝብት በሁሉም በትግራይ ከተሞች የፍየሎችና የቀንድ ከብት በሁሉም የእንስሳ ገበያ ረክሰዋል ለምን?
በተንቀሳስኩባቸው ከተማዎች የአርሶአደሩ ፍየሎችና የቀንድ ከብቶች በብዛት ወደ ገበያ ሲሄዱ አየሁ። እኔም ይህ ሁታ ምንድነው ሿጭ
ማነው ገዢውስ ማነው የሚል ጥያቄ አነሳሁ። በኣንድ ትንሽ ገበያ ተቻብኩ በዚህች ሽያጭ አንጂ ገዢ ብዙውም የለም። ሁታው ለማረጋገጥ
ወደ ሽያጮች ጠጋ ብየ ለምን ይህ ሁለ እንስሳ ገበያ ወረደ አሁን የመኸረ ጊዜ ነው። ረሃብ የለም። የበቆሎና የጥራጥሬ እሸትአለ ብየ
ጠየቅሁ። የሰጡኝ ምላሽ እኛ በአሁኑ ጊዜ በአንደ በኩል የደደቢት ብድርና ቁጠባ(የደደቢት ማይክሮፋይናንስ)፣ በሌላ በኩል የፓኬጅ
በተጨማሪም የመዳበርያ ገዢ ብድር ክፈሉ ካለመለዝያ ንብረታሁንና ሰብላችሁን ይወረሳል ስለ ተባለ ተደናግጠን በአሁኑ ጊዜ እኮ ሁሉ
የትግራይ ህዝብ አርሶአደሩና አንስተኛ ነጋዴ ብያንስ ከ5 ዓመት በላይ ውዝፍ እዳ አለው። አብዛኛ ህዝብ እዳ መክፈል ተስኖት በኖ
ጠፍተዋል ብለውኛል።
የእንስሳ ዋጋ እንዴት ነው ስላቸው ገበያው ረክሷል ምክንያቱም ገዢ የለም ሁሉም ሸያጭ ነው አንድ አንድ የስጋ ቤት የሚገዙ ቢኒሩም
በዝቅተኛ ዋጋ ልንሸጥላቸው ነው የሚፈልጉ። የሚጠይቁን ያሉ ዋጋ ከገዛንበት 40% በታች እንባቸው እየፈሰሰ ቀንሷል ይሉ።ብድሩ የስንት
ዓመት ነበር ፣ የ5፣ የ2፣ የ1 ዓመት በር አሁን ክፈሉ እያሉ እያስገደዱን ስላሉ እንጂ ለክሳራ ተዳርገናል። የምንሰደድበት ሃገር አጥተን እንጂ
ተሰደው እንደጠፉ በጠፋን ነበር ይላሉ። በዚህ ዓይነት ትዝብቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ ከገበያ ውጭ ባሉ ዜጎች ቀስ ብየ መጠየቅ ጀመርኩ።
የሰጡኝ መልስ በደደቢት ብድርና ቁጠባ የተጠቀመ ሰው ጥቂት መሆኑ አብዛኛውህዝብ በደደቢትና በፓኬጅ በመደበርያ ግዢብድር
የታቀፈ ብድርና ውዝፍ(ወለድ) ተጨምሮ ተበዳሪው ሊከፍለው የማችለው ሁኔታ እንዳለ ደደቢት ብድርና ቁጠባ ያበደረው ገንዘብ በህዝብ
ጫንቃ ላይ በቢልዮን የሚቆጠር ብር መኖሩ የውስጥ አዋቂዎች ነገሩን። እኔም በትእዝብቴ ተጨባጭ ለማረጋገጫ ለማያዝ ኣራት ጎጦች
እያንዳዳቸው 25 ኣባ ወራዎች ያላቸው መንደሮች በራሴ ሰዎች ኣጠናሁ ።
የሚገርመው ነገር በ3ቱ ጎጦች ያሉ ገበሬዎች 100% እዳ ኣላቸው ። በኣንድ ጎጥ 3 ሰዎች ብቻ ዕዳ የለላቸው ኣገኜሁ ። ይህ
የሚያረጋግጠው ሁሉ የትግራይ ህዝብ በዕዳ የተያዘ ግን ደግሞ ዕዳው ለመክፈልስ ይቅር ለምግብ ማስትና የሌለው ህዝብ ሁኖ
ኣግኝችውኣሉሁ። የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን 4.3 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ኣንጡራ ሃብት ወደ እጃቸው ለማስገባት ብለው ያቋቋሙት
የደደቢት ፍትሃዊ ብድርና ቁጠባ ባንክ ፍትሃዊ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ግብኣተ መሬት ያስገባ እና ህዝብ ኣባትና ልጅ ባልና ሚስት
የበታተነ የህ.ወ.ሃ.ት የንግድ ድርጅት ነው ።
በተጨባጭ ራሴ እንዳራጋገጥኩትም ከ18 ዓመት እድሜ በላይ የትግራይ ህዝብ ምንም ጥናት ያልተደረገለት የስራ መስክ ለተበዳሪውም
ምንም ትርፍማ ባልሆነ ስራ እያወቁ ገንዘብ ያበድራሉ። ሰው ሲጨንቀው ንብረቱ ሽጦ ይከፍላቸዋል ንብረት የሌለው ቢጠፋም ምናቸው
ሁኖ ። እነሱ የሚፈልጉ የህዝብ ንብረት በሃራጅ ሽጦው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ኪስ ሞሙላት ነው ።የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቢታመሙ ከነ
ልጆቻቸው ዘር መንዘራቸው በታይዋን ፤በደቡብ ኣፍሪካ ፤በኢሜሪካ ፤ጀርመን ወዘተ እየሄዱ ይታከምበታል ። ለልጆቻቸው ኣውሮፓ እና
ኣሜሪካ እንዲሁም ቻይና ያስተሙሩበታል ።
ደደቢት ብድርና ቁጠባ እንዶ ለሎች ስራዎች በዝባዥ ኣሰራሩ እንደ ተመኩሮ ለባኣዴን ፤ለኦሆዴድ ለደቡቦች ፤ለዓፋር ፤ለሱማሌ ወዘተ
በመስተላለፍ ይገኛል ። መጥፎ ኣሰራሩ በኣማራ ፤በኦሮሞ በሌሎች ብሔረሰዎች እንደወረሽኝ በሽታ እያስተላለፈ ነው ። በኣጠቃላይ ጥናት
በጎደሎው የደደቢት ብድርና ቁጠባ በፈጠረው ችግር የቀንድ ከብቶች እና ሌሎች እንስሳት ዋጋ በመውረዱ የትግራይ ኣርሶ ኣደር ኣነስተኛ
ነጋዴዎች በከባድ የድህነት ኣረንቋ ገብተዋል ምህረቱን ይስጣቸው ።
በትእዝብቴን ያየሁት
በትግራይና ሴሜን ጎንደር ደጋማ ቦታዎች የባቄላና የኣተር ሰብል በዋግና ትል ተበልቶ ጠፍተዋል
በኣሁኑ ግዜ የክልሎች ይሁን የሃገራችን መንግስት እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ፤የእርሻ ባለሙያዎች ሰልጠና ግንባር ቀደምት ኣትኩሮት
ተሰጥቶት በኣስር ሺ የሚቆጠሩ የእርሻ ባለሙያዎች ሰልጥነው በቀበሌው ተሰማርተው በሙያቸው እንደመስራት ፈንታ የኣቤታዊ
ዲሞክራሲ ኣስተሳሰብ (ኣይዶሎጂ )በማሰረፅ ቀዳሞት ለፖለቲካ ዘመቻ በመስጠት ሲሰሩ ይታያል ። እኔ ሰሞኑን በተንቀሳቀስኩባቸው
ቀበሌዎች ወረዳዎች እንደታዘብኩት ግን በተለይ በትግራይ ክልል በደጋማ ቦታዎችና በሰሜን ጎንደር ወረዳዎች በጃን ኣሞራ ፤በቦዳ ፤
ሰላምጌ ፀለምት ፤በላምት በ40%ከዛ በላይ ምርት የሚዘው በቀላ በትግራይ ቃንቃ ዋግ (ሕሞዲያ) በኣማርኛ በሚባለው 100% ተቃጥላል
በሌላ በኩል ኣተር የሚባል ሰብል በነዛ የተጠቀሱ ደጋማ ወረዳዎች የሚበቅል ወሳኝ ሰብል በማይታወቅ ትል ተበልታል ይህ ሰብልም
ከ10% እስከ 15% ምርት የሚዘው በትል ተበልታል ። ኣርሶ ኣደር ክረምቱን ሙሉ እየተንከባከቡየቆዩውና ቅጣሉን ኣይቶ ተስፋ ኣድርጎ
የቆየው የትግራይና የሰሜን ጎንደር ደጋማ ነዋሪ ህዝብ የባቄላና ኣተር ምርት ሊያፍስ በተስፋ ሲጠብቅ የከረመው በመጨረሻ መስከረም ወር
ሰብሉ በእሳት እንዳተቃጠለ ገለባ ተቃጥሎ ቀረ ኣርሶ ኣደር ቅጠል ሲያይ ኮርሞ በመኸር ወቅት ውሃ ዘግኖ ቀረ ። ታድያ የዘመናችን
የኢ.ህኣድግ ባለ ስልጣናት ይህን ያህል ሚሊዮን ኩንታል ምርት እናገኛለን ሲሉን እንሰማለን ፤የክልላችን የእርሻ ባለሙያዎች ይህን የስብል
5
በሽታ ከለተከለከሉ ስራቸው ምንድነው ።በበኩሌ የግብርና ባለሙያዎች በየገጠሩ ተበታትነው ቢነሩም ለሚሰሩት ስራ የሰብል በሽታ
መከላከያ (ለማከም) የሚያስችል የመድሃኒት ግብኣት እንዳማያገኝ በሚገባ ኣረጋግጫለሁ ።
የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ቢተውና ተከተዮቻቸው የሚናገርት ባዶ ዲስኩርመሆኑም ኣረጋግጫለሁ። ይህ ሃቅ የሆነ
ተቆርቃሪ ዜጋ ሄደ ሊያጣራ ይችላል ። በኣርሶ ኣደሮች ድረስ ያለ አዳጊ ግልፅ ሆኖ ያገኜዋል ።በሰሜን ጎንደር ተራራዎች ባቄላ ኣተር፤ገብስና
፤ስንዴ በትል እየተበላ ኣጋር ኣጥተው ወደ ስደት እንደፈሰሱ ከኣሁን በፊት በፍትህ ጋዜጣ የጨለማን ኑሮ የተለየው ህዝብ ብየ ጠቁሜ ነበር
።
የኣባይ ግድብ መስርያ ለሁለተኛ ጊዜ ገንዘብ ኣውጡ መባሉ የመንግስት ሰራተኛ ደስተኛ ኣይደለም
የጠቅላይ ሚኒስቲር ህልፈት ተከትሎ ለሁሉ የመንግስት ሰራተኛና ሌሎች ህብተሰብ የመለስን ጅምሮች ለመፈፀም ቃል ኪዳን ያለገባ
የህ.ወ.ሃት ኢ.ህኣደግ ኣባል ያልሆነ ዜጋና ሰራተኛ ኣገር ወዳጅ እንዳለሆነ ብዙ የህ.ወ.ሃት ኢ.ህኣደግ ከድሬዎች እያነፀ በርቀት እንደሰነበቱ
የሚታወስ ነው። በትግራይ ክልልና በዘኖች ፤ ወረዳዎች ቢሮዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በየ ኣካባቢው ከሚደረገው የሰነበተ
ስብሰባ ተያይዞ ለተሰብሳቢዎች የመለስ ረኣይ ልንከተል የተወሰነ መመሪያ ለመፈፀም በቃለ መሃላ ኣረጋግጥ እየተባለ እጅ ለእጅ ተያያዙና
ተማማሉ እየተባለ ከተማለ ብኃላ ኣስከትሎ የኣባይን ድጋፍ ለመወሰን ፈርም እንዱሞላና እንድፈርም ይገደዳል ። ሰራተኛው ግን ባለስጋት
ምክንያት ሳያምንበት ይፈርማል የማይናቅ ቁጥር ያላቸውም ኣንፈርምን እያሉ ኣሉ።
ለነዚህ ኣንፈርምን ባሉ ሰዎችም ብዙ ሃሜትና ጥላቻ በመሰንዘር የሚገልፅ ውንጀላ ኣለ። በሌላ በኩል እነዚ ንከፍላለን ብለው የፈረሙ
ዜጎችም ተመልሰው ሲራገሙ ይታያሉ የሆነ ሆኖ የኣባይ ግድብ የሚቃወም ሰው ባይኖር ይደረግ ያለ በተፅእኖ ካለው የንሮ ውድነት የወር
ደሞዝ ክፈል ማለት ግን ፍትሃዊ እንዳልሆነ ግን ይነገራሉ ። ሌላ ቀርቶ ታማኝ የህ.ወ.ሃት ካድሬዎችም ቤት ዘግተው እያሙ ይገኛሉ ።
ስለሆነ የኣባይን መዋጮ በኣሁኑ ጊዜ ሁሉ የመንግስት ሰራተኛ ደስተኛ እንዳልሆነ ነው ትእዝብቴን ። ስጋት ግን እስከመቼ ነው ለመሆኑ
ስጋት ፈጣሪ ማነው ስጋት የሚፈጠርበትስ ማነው ሁሉም ዜጎች ኣይደሉም ። ዜጎች የህሊና ነፃነት ክሌላቸው ምን ስብእና ኣላቸው ይባላል
ኣሳዛኝ ነገር።
ኣሁን በዘመነ ስልጣን ሃይለማርያም ደሳለኝ ትግራይ ሞሞከርያ እየሆነች ነው
በዘመነ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ሁሉም ነገር በትግራይ ከተሞከረ ብኃላ ወደ ሌሎች ክልሎች እንደሰርቶ ማሳያ (ዲሞንስትረሽን)
ተጠቅመው ምንም ሳይለውጡ በየ ክልላቸው ይተገብሩት እንደነበሩ መላው የኢትዮጽያ ህዝብ የሚያውቀው የቅርብ ትዝታ ነው።
ይህ ኣሰራር በዘመነ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠናክሮ መጀመር ጀመርዋል ይህ ያልኩት ምክንያት በ2004ዓ.ም የግብርና
ቀረፅ ገቢመሰብሰብ በትግራይ ክልል በ2003 ዓ.ም ከተሰበሰበው ግብር በብዙ እጥፍ እንደተሰበሰበ የገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን
ትግራይ ቅርንጣፍ ራሳቸው ሲናገሩት ከርመዋል ። እንደሉትም ግብር በትግራይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከፍሎ የማያውቅ በዘንድሮ
በቢሊዮን የሚቆጠር ግብርና ከእቅድ እጥፍ እጥፍ ተሰብስባል ተብሏል። ስለሚወራም ኣግራሞትም ፈጥራል ። ይህ ግብር ኣሰባሰብ ግን
በትግራይ ባለሃብት ነጋዴ ያፈናቀለ ለስደት ያደረገ እጅግ ብዙ ንግድ ቤቶች ቢዘጉ ያደረገ ወራር የግብር ኣሰባሰብ ነበር።
ለዚሁ ሃቅ ለመረጋገጥ ካሁን በፊትም ደጋግመን እንደተረጋገጠ ነው። በትግራይ የነበሩ የህንፃ ተቃራጭ ኮንትራክቶሮች ጭራሽ ክልሉ
ለቀው ኣዲስ ኣበባ ደቡብ ሰሜን ሸሽተዋል ። ከስረው ስራቸው የዘጉም ኣሉ። የንግድ ኣስመጪዎች የችርቻሮ ነጋዴዎች ንግዳቸው ዘግተው
ጠፍተዋል ፤ በኣስር ሽዎች የሚቆጠሩ የጥቃቅንና ኣነስተኛ ተቋማት ከሰመዋል፤ ከነ ንብረታቸው የታሸጉ ንግድቤቶችም ኣሉ፤ ለቀሩ
ነጋዴዎችም ጥዋት ጥዋት በሚቀየሮው መመሪያ እየተናጡ በጭንቀት ተውጣል ፤ የነበረ የንግድ የሞቀ ስራ ኣሁን ፍፅም ቀዝቅዟል ፤
ኣስመጭና ነጋዴዎች ስለ ሸሹ የሸቀጥ እቃዎች ንረዋል ፤ በኣጠቃላል በትግራይ ፍትሃዊ የግብር ኣካፋፈል ስለቤ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች
በመሸሻቸው የነበረው እንቅስቃሴ እየቀዘቀዘ ይገኛል፡፡
ሁኔታው እንደዚህ እያለ በኣቶ መልኣኩ ፋንታየ የኢትዮፕያ ገቢዎች ግምሩክ ዳሪክተር የታመኑ ከሁሉም ክልሎች የተወጣው የገቢዎችና
ጉሙሩክ ሰራተኛ ባለስልጣኖች እንደ ተለመደው መፈተኛ የሆነው የትግራይ ግብር ኣሳባሰብ ተሞክሮ ለመቅሰም ተብሎ በየ ክልላቸው
በኣየር ትራንስፖርት ተጉዞው በመቀሌ ሃወልት ሰማእታት ተሰብስበው ነጋዴ እንዴት ታቀዋለህ የሚል ልምድ ሲቀስም ሰንብተው ፤
ህዝባቸው ለመሮቐስ የህ.ወ.ሃት የቀሰማቸው የማፈኛና ሚሞሪ ተሞልተው ተስማርተዋል። ይህም የህ.ወ.ሃት ኣስተሳሰብ የሆነ ኣንባ ገነኑ
ኣቤታዊ ዲሞክራሲ ከህ.ወ.ሃት መንደር ኣመንጭቶ የ80 ሚሊዮን ተላላፊ የወረርሽን በሽታ እንዳዳረገው ሁሉ ይህ ነጋዴ ገዳይ የሆነው
የግብር ኣሰባሰብም የኸው ከትግራይ ወደ 80 ሚሊዮን ህዝብ ሊሰራጭ ከመቀሌ ሃወልት ሰማእታት ኣዳራሽ ተልኮልቸዋል።
የተከበራችሁ ኣንባብያን ፤እኔ እምለውያለሁ ግብር ቀረፅ መክፈል የለበትም ኣደለም እያልኩ ያለሁት ፤ ግበር መክፈል የዜግነት ግዴታ ነው፤
መክፈል ኣለበት ፤ እኔ እምለው ያለሁ በጥናት የተመሰረተና በፍትሃዊ መሆን ኣለበት ነውያለሁኝ ያለሁት በትግራይ ክልል ያለው የግብር
ኣከፋፈል ግን ኣስፈሪና የነጋዴ ህብረተሰብ የነቀለ ለኛ ህብርተሰብ ወደ ውደቀት ያስገባ ነው እላለሁ።
እናንተ የህ.ወ.ሃት የግብር ኣስተሳሰብ ልምድና ተሞኩሮ ቀስማችሁ ሄዳችሁ ያላችሁም ይህ የኣፈና ልምድ በህዝቦች ጫንቃ ከተገበራችሁ
ከጥቅሙ ኣደጋው ነው የሚያመዝነው።
የፅንብላ መይል ቀበሌ ኣርሶ ኣደሮች በግድ እየተፈናቀሉ ናቸው
6
በዚህ ጉዳይ በትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን በኣስገደ ፅንብላ ወረዳ በመይል ቀበሌና ኣካባቢዋ የሚኖሩ በሺ የሚቆጠሩ ኣርሶ ኣደሮች ከ
60 ኣመት በላይ የኖረበት ቦታ በኢፈርት ትእምት ሱር የሚገኘው ኢዛና ወርቅ ማኣድን ድርጅት የወርቅ ቁፋሮ ካንፓኒ ስለሚቆፈርበት ለነሱ
ተብለው፡፡ ለዘለቄታ ምን ይሆናሉ የሚል በቂ ግምት ሳይሰጣቸው ከመኖርያ ቆያቸው ተነሱ ተብለው በትልቅ ጭንቀትና ችግር እየተናጡ
ናቸው፡፡
እዚ ላይ እኔ የምለው በዛ ቦታ መኣድን መቆፈር የለበትም ኣይደለም የምለው ያለሁ የመኣድን ቁፋሮ መካሄዱ ኣልቃወምም፡፡
ነገር ግን መይል የሚባል ቦታ ብዙ ኣርሶ ኣደር የሚኖርበት ለቀንድ ከብት ማራባት ለእርሻ ሰብል ተሰማሚ ነው በመሆኑ ብዙ ገበሬዎች
ኣቅፎ ነበር እኔ የሚታዩኝ ኣርሶ ኣደሮች ከመፈናቀላቸው በፊት ብዙ ዝግጅቶች ያስፈልጋል፡፡ ከ ዝግጅቶች ለመጥቀስ ለንሮኣቸው ኣመች
ይሆነ ለእርሻ እንስሳ ማርባት የተመች ቦታ መስጠት ኣለበት የተመቻቸ መኖርያ ሊሰራላቸው ይገባል 60 ኣመት የኖረበት ቤት ንብረት
ወድመባቸው ስላለ ይሄ ማቃቃምያ ማግኘት ኣለባቸው ለፈረሰው ቤታቸው ያለሙት መሬት ግምት መስጠት ኣለበት የሚሰጣቸው ግምት
ለዘለቂታው እንዲሰጣቸው፡፡
ለልጆቻቸው በማኣድን ቁፋሮ ስራ ኣንዲፈጠረላቸው ካልሆነ ዝም ብሎ ህዝብ መፈናቀል ኣይገባም፡፡
ግልፅነት ባለው ለህዝብ በማሳመን መሆን ኣለበት ይህ ተግባር በመደባይ ታብር የሚገኝ በኢፈርትና በቻይና የሚቃቃም ያለው የማኣደን
ቁፋሮም በሺ የሚቆጠሩ ገበሬዎች የተፈናቀሉ ስላሉ ይህም መታየት ያለበት ነው፡፡
በመይል ያለው የህዝብ ቁጣ መንግስት በግልፅና ከህዝቡ በማግባባት ካልፈታው በኔ ትእዝብት ችግር ይፈጥራል፡፡
ማጠቃለያ
በዚህ ፅሁፍ በትግራይ በኣገራችን ያሉችግሮች በልማት በዲሞክራሲ በፍትህና የዜጎች ነፃነት መንጠቅ የህ.ወ.ሃት ኢ.ህ.ኣደግ ዲሞክራሲ
የኣፈና ፖሊሲዎች ፤በትግራይ ሰለማዊ ተየቃዋሚ ፓለቲካዊ ፓርቲ መንቀሳቀስ ፍፅም ተቀምጦልያል ብታምንም ያጠብብና ብሎም
ተቃዋሚዎች እንዲ ከሰሙ እሚያደርግ የስለላ ነትወርክ መስራት ፤ለዚሁ ኣፋኝ ኣላማ ለማስተግበር መሞቶ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ
የሚያባክን ኣሰራር፤ በጠቅላይ ሚኒስቴር ሞት በመሳሰብ 40(50)ኣመት መመርያ የሚያሰራ መመርያ ተቀምጧል ያስ ብታምንም
ባታምንም ተግባር ብሎ ሳይወዱ በግድ ፎርም እንዲሞላ ማድረጉ ።
ከኛ ሌላ ኣታምልክ የሚል የህሊናውያን መርሕ በመያዝ ዜጎች ማስገደድ ፤ለሃገራችንም ለናንተም ኣይጠቅምም። ከሂትራልና ሞስሎኒ
ኣፋይኝና ፋሽሽታዊ ተግባር ኣለምን ያንቀጠቀጠ ኣልነበረም።ግን ውሸታሞች ነበሩ በርሊን በ360 ድግሪ ተክባ ሊገድል ትንሽ ግዜ ሲቀረው
ሚድያዋችን ተቆጣጥሮ ድልን እየተገናፀፍኩ ነኝ እያለ ይደነፍ ነበር ግን ምፅኣተ ኣለም ደረሰች በቃ ህዝቡ ኣሸነፈ። ደርግም ሁሉም ነገር
ማጥጦና ኣፍኖ በመያዝ ኢትጵያን በራሻ ኣጃቢ የሰለጠኑ ባንዳሰላዮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ በማሰልጠን ህዝቡ እንዳይናገር እንዳይ ሰማ
ቆርኖ ይዘት ነበር። በሌላ በኩል ሁሉ ህዝብ ያለፍላጎቱ ኢሰፖ ኣባል መሆን ኣለበት በማለት ኣስገድዶ ኣባል ያድርግ ነበር ።
ለሁሉም ነገር በጥይት በድህንነት መዋቅር በማስፈራራት ኣምነዋል ፤ገድለዋል ፤ኣስረዋል ፤ሁሉም በቁጥጥር እንዲሆን ኣድርገዋል። ውስጡ
በሰበሰ እያለ ኣለሁ አፋኝ እማይሞላ ወንበዴዎች ነገ በእጃቸው ይዘቸለሁ እያለ ህዝብ ያታል ነበር። ግን ኣልሆነም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ
ወታደሮች ሰላዮች የኢሰፓ ኣባል ይዞ ተቸነፈ። ምክንያቱም 70 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ተገዶኣለሁ ይለው ነበር እንጂ በውስጡ ደርግ
የሚወድቅበት ብልሃት ይቆፈር ነበር። ለደርግ ህ.ወ.ሃት ብቻውን ኣልነበረም የነበረ ቢረክራሲ ፤ሙሁራኖች ፤መላው ህዝብ ነው የተፉት
ግን ከዛ ከሸነፈው ደርግ ተምሮ ለህዝብ ታማኝ ሆኖ እንደመገኘት ፈንታ የደርግን ውሸት በመድገም 80 ሚሊዮን ህዝብ በኔ ሳንባ ብቻ
ካልተነፈሰ ብሎ ህገመንግስት ኣክብረው ለሚታገሉት ፖለቲካ ፖሪቲዎች ለማክሰም 100 % ህዝብ ኣባል ህ.ወ.ሃት ይሁን ማለቱ
ውድቀቱን መጥራት ነው ስለ ሆነ ህዝብ በወታደር በታንክ በእሳትና ኤሌክትሪክ ቢከበብም ኣይሸነፍም ህ.ወ.ሃት ከራስህ ልምድ ተማር ።
ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል
መቀሌ

ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
November 27, 2012
7

Contenu connexe

Tendances (9)

Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capitalAddis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
 
Weyane violates own_constitution
Weyane violates own_constitutionWeyane violates own_constitution
Weyane violates own_constitution
 
News 03-04-2014
News 03-04-2014News 03-04-2014
News 03-04-2014
 
33
3333
33
 
Joint statement on_the_election
Joint statement on_the_electionJoint statement on_the_election
Joint statement on_the_election
 
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
 
News eda-eritrea
News eda-eritreaNews eda-eritrea
News eda-eritrea
 
Abiy ahmed vs hailemariam desalegn
Abiy ahmed vs hailemariam desalegnAbiy ahmed vs hailemariam desalegn
Abiy ahmed vs hailemariam desalegn
 
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
 

Similaire à Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.

Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptx
Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptxIndigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptx
Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptxTagelWondimu
 
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs  Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Aeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharicAeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharictsehaydemeke
 
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesMuhammad Shamsaddin Megalommatis
 

Similaire à Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run. (8)

Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a countryEnde hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
 
Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptx
Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptxIndigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptx
Indigeneous Conflict Resolution for MoP Final.pptx
 
33
3333
33
 
33
3333
33
 
የትግራይ ህዝብ
የትግራይ ህዝብየትግራይ ህዝብ
የትግራይ ህዝብ
 
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs  Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
 
Aeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharicAeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharic
 
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
 

Plus de Ethio-Afric News en Views Media!!

VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethio-Afric News en Views Media!!
 

Plus de Ethio-Afric News en Views Media!! (20)

History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in AmharicHistory of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
 
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
 
Thanks/ Misgana
Thanks/ MisganaThanks/ Misgana
Thanks/ Misgana
 
The ark of the covenant
The ark of the covenant The ark of the covenant
The ark of the covenant
 
Arkofthecovenent
ArkofthecovenentArkofthecovenent
Arkofthecovenent
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
 
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
Coment on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  melesComent on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  meles
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
 
Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
 
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
 
King of kings yohannes 2.
King of kings yohannes 2.King of kings yohannes 2.
King of kings yohannes 2.
 
King of kings yohannes & Ethiopian unity
King of kings yohannes &  Ethiopian unityKing of kings yohannes &  Ethiopian unity
King of kings yohannes & Ethiopian unity
 

Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.

  • 1. ትዝብቴን ብገልፅ (ቁጥር 2) የህወሐት ኢህአዴግ የፖለቲካ ጭንቀት ከአስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል (መቀሌ) ከጠቅላይ ሚንስተር ህመምና ህልፈተ ህይወት ተያይዞ ሃገራችን በወሬና በስብሰባ እየተናጠች እንደ ከረመች ሁሉም ዜጎች የሚያስታውሱት ነው። ለነበሩ ስብሰባዎችም ብዙ ገንዘብ እንደተጠየቀ የቅርብ ትዝብታችን ነው። ያ አልበቃም ብሎ አሁንም ለአንድ ፓርቲ ህወሐት ኢህአዴግ ለማጠናከር ተብሎ 80 ሚልዮን ህዝባችን፣ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ፣ የህወሃት ኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና የአጋር ፓርቲዎች አባላት፣ የከተማ የገጠር ህዝቦች በስብሰባ ተጠምደው እየተናጡ ይገኛሉ። ለዚሁ ለማስረጃነት ያህል ባለፈው ሳምንታት ከ11/02/05 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል በትግራይ ዘኖች ወረዳዎች ከተሞች ተንቀሳቅሼ ነበር። በተንቀሳቀስኩባቸው ቦታዎች ያየሁትና የታዘብኩት ቢኖር በዚህ ፅሑፌ አንድ በአንድ አርእስት በመስጠት ለአንባብያን እንዲደርስ አድርጌላሁ። የትግራይ ህዝብ 100% በግድ የህወሐት ኢህአዴግ አባል ፓርቲ እንዲሆን እየተገደደ ይገኛል።አሁን ግዜው የመኸር ወቅት ሁኖ የገጠር ህዝብ የዘራውን ሰብል ለማጨድና ለመውቃት ሌት ተቀን የሚረባረብበት ሰዓት ነበር። ነገር ግን ከጠቅላይ ሚንስተር መለስ ሞት ጀምሮ ያልተረጋጉ የህወሐት መሪዎች የገጠሩ ህዝብ በየፆታው፣ በየዕድሜው እየለያዩ ሴቶች ለብቻ በቀን 30 ብር፣ ለወንዶች ለብቻቸው 35 ብር አበል በመስጠት በየአቅራብያቸው በሚገኙ የወረዳና የዞን ከተሞች ጠርተው በመሰብሰብ የልማት ስልጠና በሚል ሽፋን፣ ሁሉም ሰው የህወሐት ፓርት አባላት መሆን አለበት በማለት ከ4 እስከ 7 ቀናት በመሰብሰብ የኔትዎርክ አደረጃጀት እያደረጉ ይገኛሉ። የአደረጃጀቱ ጥበብም ሴቶች ለብቻቸው ያነሰ ህዋስ(ዋህዮ) 1/5 (1/6)፣ ከፍተኛው ኔትዎርክ (ዋህዮ) በአንድ ሁኖው በ4 ለ30 ሴቶች ይደራጃሉ። ሁሉም ሴቶች በዓመት የህወሐት አባልነት 12 ብር፣ የወይን ጋዜጣ 3 ብር፣ ለሴቶች ማኅበር 6 ብር፣ ለቀይ መስቀል 3 ብር፣ ድምር 24 ብር እንዲያዋጡ ይገደዳሉ። እነዚህ የገጠር ሴቶች ሁሉም የህወሐት የ40 (የ50) ዓመት የመለስ እቅድ (መመርያዎች) ሊተገበሩ ከሆኑ ከውስጣቸው ከህወሐት ኢህአዴግ እምነቶች ውጭ የሌላ ፖለቲካ እምነቶች እነዳይሰራጩ በጥብቅ እንዲኮንኑዋቸውና ከተገኙ እንዲለቅሙዋቸው በስልጠናው ተናግረዋል። ሌላ የተሰጣቸው ስልጠና መለስ የተወልን ለ50 ዓመት እቅድና መመርያ የማይተገብር ማነኛውም ዜጋ እንደ ጠላት እንደሚታይና ክትትል እነዲደረግለት በጥብቅ ተነግረዋል።በዘንድሮው በ2005 ዓ.ም የመስኖ ስራ ከ49 ሚልዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ማፈስ ስላለብን እቅድ ግብ እንዲመታ ሴቶች ወሳኝ ሚና ስላላቸው ለመስኖ የሚሆን መሬት ይኑራቸው አይኑራቸው መዳበርያ በግድ እንዲወስዱ ተደርጓል። በሌላ በኩል ወንዶች አርሶ አደሮች ልክ እንደሴቶች በ1/5 እና 4 ለ30 ተደራጅተው የመለስ በትግርኛ ሕንፃፃት(እቅድና መመርያ እምነቶች) እነዲተገበሩ ከህወሐት አስተሳሰብ ውጭ እንዳያስቡ እንዳይተነፍሱ በሚል ለ4(5) ቀን በ35 ብር አበል ሰልጥነዋል። የሴቶችና የወንዶች አርሶ አደሮች ከላይ እንደገለፅኩት ከመደራጀት አልፈው በየጐጡ ያሉ አባወራዎች ቤት ቁጥር ኣስር ቤት በአንድ ኔትዎርክ አንድ ለ10 ሲደራጅ በነብስ ወከፍ የአባወራ ቤት ኣባወራና እማወራ ከነ ልጆቻቸው እንዲደራጁ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት በሚልዮን የሚቆጠር ብር ከ4 ቀናት በላይ ለአንድ ፓርቲ ዕድሜ ማራዘምያ ተብሎ በስብሰባ ወጭ ማድረግ በብዙ ሚልዮን ብር የሚቆጠር አበል፣ ትራንስፖርት በመክፈል የመንግስት ገንዘብ ማባከን ምን ያህል ስህተት መሆኑ በሌላ በኩል ህዝብ በስብሰባ ሲናጥ የእርሻ ሰብል ደርቆ መታጨድ የሚገባው እያለ ዝናም ዘንቦ ሰብሉን እያበላሸው የመንግስት ባለስለጣናት፣ የግብርና ባለሙያዎች ስለሚበላሸው ያለው ሰብል ብዙ ሲቆረቆሩ አይታዩም። የመንግስት ሰራተኞችም ልክ እንደ አርሶ አደሩ የመንግስት ገንዘብ ከ91 እስከ 220 ብር በቀን አበል እየተሰጣቸው ከ7 ቀን በላይ ተሰብስበው በአንድ ለአምስት ኔትዎርክ በመደረራጀት ሁሉም አባል ህወሐት እንዲሆኑ ሲገደዱ ለዚሁ ለመተማመኛ ለአባይ ግድብ የአንድ ወር ደሞዝ እንዲከፍሉ ፎርም እንዲሞሉ ወረቀት ይሰጣቸዋል። በዝያች ፎርም ሞልቶ ያልፈረሙ የመለስን እምነቶችና እቅዶች የማይተገብር የካደ ተብሎ ይፈረጃሉ። አረ ስንት ነገር አለ ተፅፎ የማያልቅ። በሁሉም ት/ ቤት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በህወሐት ፓርቲ እንዲደራጅ ግድ ይላል።በአሁኑ ጊዜ እንስሳ ዘቤት ካልሆነ በስተቀር በህወሐት ፓርቲ ያልተደራጀ አንባገነን የአብዮታዊ ዲሞክራስያዊ አስተሳሰብ ያልተከተለ በዚህች መሬት አይኖራትም ወይ ዳግም በትግርኛ ቋንቋ ኳኵቶ (በአማርኛ አቃቅማ እሾህ) ማለት ነው ተብለዋል። በአቶ አባይ ወልዱ ተሰይሞ ተመርቆ የተሰጠ ስም የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ህወሐት ኢህአዴግ 80 ሚልዮን ህዝብ እኛ የተነፈስንበት ካልተነፈስክ አትኖራትም። በማለት በአሁኑ ጊዜ ፍትሃዊና ታማኝ ዲሞክራሲ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ እንዴት ይታመናል።ይህ የአፈናና የፈላጭ ቆራጭ አደረጃጀት በትግራይ ብቻ ታጥሮ የሚቀር ቢሆን አይከፋም ነበር። ትልቁ መርዛም ነገር ካሁን በፊት እነደተለመደው በትግራይ ተፈትኖ በህወሐት መሪዎች ብቁ ነው ፈተና አልፈዋል ተብሎ ከፀደቀ በኋላ ወደ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ከዛ በኋላም ወደ አጋር ድርጅቶች ተላልፎ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ይንጥ እንደነበረ ሁሉ 1
  • 2. አሁንም በትግራይ ተጀምሮ ፈተና አልፈዋል ተብሎ በትግራይ የሚደረገው ያለው አፈና በሁሉም ክልሎች መተግበር ጀምሮ አርሶ አደሮችና ምሁራኖች፣ ተማሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች በስብሰባና በቃል ኪዳን መሃላ እየተናጡ እናያለን እየማሉ እናያለን። ይህ አሰራር የመድብለ ፓርት መኖር አምናለሁ የሚለው የህወሐት ኢህአዴግ ፓርትና መንግስት አሁን በሚከተለው ያለው አፋኝ አደረጃጀትና የዜጎችን ነፃነት መንጠቅ ዜጎች ተሸማቅቀውና ፈርተው፣ ሰግተው እንዲኖሩ ማድረግ በ2002 ዓም የነበራ ሃገራዊ ምርጫ 99.6% ተመረጥኩ ያለበት የተጭበረበረ ምርጫ ለመጪው 2007 ለሁሉም በሰላማዊ መንገድ ፓርላማ ተወዳድረው ለአንባገነኑ ህወሐት ኢህአዴግ በህዝብ ዳኝነት በምርጫ አሸንፈን ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንመሰርታለን ለሚሉ ፓርቲዎች ከወዲሁ አስወግዶ 100% ወንበር ለመያዝ ብቻው ለብቻው በአንድ እጅ እያጨበጨበ በ2007 ዓም ተወዳድሮ ለቀጣይ አምስት ዓመት አንባገነኑ ስርዓቱ ለማራመድ ስለፈለገ ነው። ለዚህ የህወሐት ኢህአዴግ ርካሽ ፍላጎት በሃገራችን ያሉ ሰላማዊ ትግል አምነው የሚታገሉ የምርጫ ኃይሎች በመተባበር አንድነት በመፍጠር ህወሐት ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በነፃ የመንቀሳቀስ እድላቸው ለማፈን የሚከተለው ያለ በህዝብ ላይ ተፅዕኖ መጭው ውድድር የውድድር ዲሞክራስያዊ መጫወቻ ሜዳው እነዲሰፋ ጠንክረው መታገል አለባቸው። የህወሐት ኢህአዴግ ተስፈኞች የሆኑ ገልበጥበጥ የሚሉ ተወላዋይ ፓርቲዎችም ህወሐት ኢህአዴግ ለግዜው ተጠቅሞ የሚጥላቸው መሆኑ አውቀው ወደ ትክክለኛ የተቃውሞ ሃይል ጐራ ቢደባለቁ ወይ በግልፅ ህወሐት ኢህአዴግ ጐራ ወግነው ቢታገሉ፣ ካለበለዝያ ገልበጥበጥ እያሉ ለኢትዮጵያ ሃቀኛ ዲሞክራስያዊ ሃይሎች ባያምሱ ይሻላል። በተጨማሪ ምሁራኖች፣ ባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች፣ መላው የሃገራችን አርሶ አደሮች፣ ሰራተኞች፣ የመንግስተ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች ህወሃት ኢህአዴግ እሚፈፅመው ያለ አስገዳድ የአፈና አደረጃጀት፣ ነፃነታችሁና ስብእናችሁ የመነጠቀ ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለመጭው ትውልድም ጠንቅ ስለሆነ የዜግነት ግዳጃችሁን ብትወጡ ለሃገራችን ጥቅም በዜጎችም የተረጋጋ ኑሮና ሰላም ይፈጠራል። በውሸት የልማት አዋጅ ስልጣን ማራዘም አይቻልም የ ህወሐት መሪዎችና ካድሬዎች ከጠ/ሚንስተር ግብአተ መሬት በኋላ በብዙ ጨለምተኝነት አስተሳሰብ ላይና ታች እያሉ ቆይተው፣ ጠ/ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝና ምክትላቸው ደመቀ መኮነን ስለጣን ከተረከቡ በኋላ የህወሐት መሪዎች እንደተለመደ ሰርቶ ማሳያ ፕሮጀክታቸውን ሰርተው በሞዴልነታቸው ለሃገራችን ክልሎች ለማበርከት በክልልና በዞን ከተሞች በመከፋፈል በዓይን ሊታይ በማችል ፣ የማይቀመስ የማይዳሰስ የማይሰማ የሃሰት ልማትን አስመልክተው የመንግስተ ብዙሃን መገናኛ በመቆጠቀጠር በየነ መኩሩ በሽሬ በሑሞራ፣ አባይ ወልዱ በአኩሱም፣ ቴድሮስ ሓጎስ በመቀሌ ሓወልት ሰማዕታትና አኩሱም ሂቴል፣ ኪሮስ ቢተው ለእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሰራተኞች፣ ሌሎች መሪዎችም እየዞሩ ሲደስኩሩ ሰንብተዋል። በሁሉም ቦታ የነበሩ አጀንዳዎች 1)ከላይ የዘረዘርኩት አፋኝና አስገዳጅ አደረጃጀት በስፋትና በጥልቀት በመቀስቀስ የመለስን አደራ በቃል ኪዳን ታጥቀን ካልሰራን፣ የመለስ የአምሳ ዓመት የተወልን መመርያ በቆራጥነት ካልሰራን፣ ለእድገታችን እነቅፋት የሆኑ በታኞችና አድሃሪዎች፣ ኳኵቶ(አቃቅማ) እንዳይበቅሉ በመልቀም እንስራ ብለዋል። 2)በዘንድሮ 2005ዓ.ም የመስኖ ልማት 49 ሚልዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ እናፍሳለን በማለት በተለይ ደግሞ የትግራይ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊና የክልሉ መክትል ፕረዚደንት አቶ ኪሮስ ቢተው የተባሉ ለዚህ ሁሉ የእርሻና መአድን ተመራማሪ ያወረዱለት መመርያ ሙያ የጐደለው በግብታውነት የሰከረ(ኣፕሸሸ) አቀራረብ፣ በዘንድሮው የመስኖ ምርታችን 49 ሚልዮን በላይ ኩንታል ማፈስ አለበን። ይህን ምርት ለማፈስ ግን ሁሉ የግብርና ሰራተኛ የመለስን ራእይ በመከተል የህወሐት አባል በሆን አለበት ብለዋል። በዚሁ ግብታውነት የተሞላበት አነጋገርና የመመርያ አሰጣጥ ምሁራኖች በደስታ አልተቀበሉትም። ለምን ለሚለው ጥያቄ 49 ሚልዮን ኩንታል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለማፈስ የተመቻቸ ሁኔታ ስለሌለ፣ 50% የትግራይ ታራሽ መሬት በመስኖ አጠጥቶ ምርት ለማፈስ ውሃ የት አለ ስንት ግድብ አለ? የሚሰጠን ያለመመርያ በትግርኛ ቋንቋ ህንዱድነት(ግብታውነት ነው) አሉት። የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች በትግራይ ክልል ይቅርና የትግራይ ታራሽ መሬት 50% በመስኖ ለማጠጣትስ ይቅር ከመቀሌ ከተማ ጀምሮ የዞን የወረዳ ከተሞች ለህዝብ የሚጠጣ ውሃ የለም። በትግራይ ክልል ያሉ ግድቦች በቀድሞው የክልሉ አስተዳዳሪ የነበሩ አቶ ገብሩ አስራት የተሰሩ፣ በአኩሱም እንዳ ንጉስ በሚባል ግድብ በ3.8 ሚልዮን የተሰራ 100 አባወራ አርሶ አደር ያቀፈኘ፣ በሽሬ አውራጃ በዓዲ ዳዕሮ መስከበት በተባለ ወንዝ በ4 ሚልዮን ብር ግምት በሰው ሃይል የተሰራ 100 ሄክታር ማሳ መስኖ የሚያጠጣ፣ በሳምረ አከባቢ 150 ሄክታር መስኖ የሚያጠጡ ትናንሽ ግድቦች፣ በቤት ማራ የሚገኙ የወንዝ ጠለፋዎች ከ200 ሄክታር የማይበልጡ መስኖ የሚያጠጡ አሉ። ሌሎች ከጥንት ጀምረው የነበሩ በመኸር ወቅት ብቻ የሚሰሩ ምንጮች ነበሩ። በጋ ሙሉ የሚሰሩ የመንጭና ትናንሽ የጕድጓድ ውሃዎች አሉ። እነዚህ ምንጮች ሁሉ ተሰብስበው የሚሰጡት የመስኖ ምርት እጅጉን ትንሽ ናቸው። በሌላ በኩል በራያ የተቆፈሩ ጥልቅ ጕድጓዶች ከ200 በላይ አሉ ይባላል። እነዚህ ጥልቅ ጕድጓዶች እስከ አሁን ግልጋሎት አልሰጡም። ታድያ 6 መቶ ሺ 17 ሄክታር መሬት በየተኛው ውሃ መስኖ የሚያጠጣ የሚል ጥያቄ አቶ ኪሮስ ቢተው መልስ የላቸውም። ይህልም እንጀራ ከመሆን አልፎ ? 2
  • 3. አቶ ቴድሮስ ሃጎስም በአኩሱም ሆቴልና በሐወልት ሰማዕታት አዳራሽ ለምሁራኖች ያደረጉት ስብሰባ ተቀባይነት አላገኘም። አልተሳካላቸውም። በአጠቃላይ የህወሐት መሪዎች ታማኝነት ለማግኘት እየዞሩ የሚያደርጉት ስብሰባ ይቅርና አባል ፓርቲ ባልሆኑ ዜጎች በአባሎቻቸውና በካድሬዎቻቸውም ተቀባይነት አላገኙም።ሌላ ቀርቶ ለመስኖ ማዳበርያ ውሰድ የተባለ ገበሬውም አልተቀበለውም።እንደ አብነት ለመጥቀስ በ17/02/2005 ዓም በዓድዋ አውራጃ በሓሓይለ፣ በዓዲ አሕፈሮም ቀበሌዎች በካድሬዎች የቀረበላቸው የውሸት ልማት በመቃወም በመበተን ወደየስራቸው ሂደዋል። በሴቶችና በወንደች መካከል የነበረ የውሎ አበል አከፋፈል አድላዊ በመሆኑ ሴቶች አኩርፈዋል። በአጠቃላይ የህወሐት መሪዎች በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር የመንግስት ገንዘብ የመንግስት የስራ ሰዓት የተሰብሳቢ ኣርሶኣደር ሰብሉን እንዳይሰበስብ በስብሰባ መጠመዱ ኪሳራ በማባከን ለአንድ ፓርት ለማጠናከር ተብሎ በዘመቻ የተሰማሩበት ለህዝብ በሃይለኛ አፈናና የትግራይ ህዝብ እንደሚደርሰው 100% የደደቢት ብድርና ቁጠባ፣ ፓኬጅ፣ የመዳበርያ እዳ ስላለው ተሎ ክፈል ተብሎ እነዳይገደድ ነው እነጂ ይደረጋል የተባለው በስብሰባ መናጥ አልተቀበለውም። በአቶ አባይ ወልዱና በአቶ በየነ ሞኩሩ የተደረገው ቅስቀሳመ ነጋዴው ፣ ባለሃብቱ፣ ምሁራኑ አልተቀበሉትም። ምክንያቱም በተግባር የማይተገበር ይህልም እነጀራ ስለሆነ።እኔ እሚገርመኝ ሌሎች ዜጎችም እምያሳስባቸው ያለው ህወሐት ለ38 ዓመት ሙሉ የትግራይ ህዝብ ከህወሐት አስተሳሰብ(እምነት)ሌላ እንዳያመልክ ተደርጎ ቆይቷል። ይህ የትግራይ አፈናና ያለ ፍላጎቱ አምላኪ እንዲሆን ማድረጉ እንደተሳበ (ወረርሽኝ) በሽታ ወደ ሌሎች ብሄሮች ብሄረሰዎች እንዲዛመት ተደርጎ በብዙ ሚልዮን ዜጎች ለምጥ ፈጥሮ ቆይቷል።አሁንም እየቀጠለበት ይገኛል። ለመሆኑ መቋጫው ያት ነው? ህወሐት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በውስጡ የተለያዩ ሐሳብ ላነሱ ወገኖች በዲሞክራሲያዊ መድረክ በመወያየት ከቂም በቀል በፀዳ መንገድ ግርጭቶች ፈቶ እነደማያውቅ በእርግጠኝነት አውቃለሁ። ነገር ግን ያጊዜ የተዘባረቀ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነበረ እነበል። ግን ከ38 አመት በኋላ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ሊደረግ የማይገባው ማድረግ ለምን ያደርጋል? ከአመሪካና አውሮፓ ዲሞከራት አገሮች እኩል ባለስቀምጠውም በአፍሪካ ካሉት ዲሞክራቲክ አገሮች እነኳን ሊማር አይችልም? እኔ በዚች ዕድሜየ 4ኛ መንግስት የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ምናልባትም እግዚአብሔር ካለው ሁሉም አይሳነውምና 5ኛ መንግስትም የሚያይ ይምስለኛል። እዚህ ላይ ግን የ4ቱ መንግስታት በማነፃፀር ባህሪያቸው ጠቁሜ ልለፍ።ጃኖሆይ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በስብከት፣ በሃይማኖት፣ በከፋፍለህ ግዛ በአምልኮት ህዝብ ጨቁነው በመያዝ ለ40 ዓመት ገዝተውናል። መነግስቱ ሃይለማርያም መጀመርያ በውሸት አዋጆች የህልም ዲሞክራሲና እንጀራ በማብላት ኋላም የማይደበቅ ፋሽሽታዊ ወታደራዊ ባህርዩን በማጋለጥ በጠርሙስ ደም በሞምላት በአደባባዮች ደም በመርጨት በወቅቱ 60-70 ሚልዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ስጋትና ሽበራ በመፍጠር 17 ዓመት በፋሽሽታዊ አፈና ገዛን። የህውሓት ኢሃደግ መንግስት ሃይለማሪያም ለወታደራዊ መንግስቱ በወታደራዊ ሃይል በማስወገድ ስቢል መስለው ስልጣን ከያዙ በኋላ ቀስበቀስ ያ ወታደራዊ ባህርያቸው መጣና እንደ መንግስቱ ደም በአደባባይ ባይረጩም ማንም ሰው የፈንጅ ወረዳ ከጣሰ ያገኛታል በሚል አነጋገርና ስጋትና ሽብር ፈጣሪ ነበሩ።ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝም መደባዊ አመጣጣችው ንፁህ ስቢል ሰው ናቸው። ሆኖ ግን ከህወሐት ኢህአዴግ ወታደራዊ አመራር የወሰዱት ስልጠና ያለ ይመስለኛል። ተመሳሳይ አነጋገር እሳትን ከነካችሁ ትቃጠላላችሁ ዎዮላችሁ ማለት ጀምረዋል። በተግባርም በአሁኑ ጊዜ በትግራይ የተጀመረው ሁሉ ሰው የህወሐት አባል ካልሆነ ታማኝነት የለውም የሚል በሞላው የኢትዮጵያ ህዝብ በ80 ሚልዮን ህዝብ በውድም በግድም የኢህአዴግ አባል መሆን ኣለበት ተብሎ በስብሰባ ይናጣል ። የጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርምጃው ከመደገፍ ውጭ ኣይሆንም ። ኣንድ ኣንድ መጥፎ እርምጃ ሲወስዱም እናያለን ። ሌላ በዚህ ኣጭር ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣንም ወራትም ሰው በጥይት ሞሞት ጀምራል ለዚህ ኣብነት በደሴ በሙስሊም ህብረተሰብ የተጀመረ ግድያ ኣለ። የግድያ ተገቢ ነገር ኣልነበረም ኣይደለም የኔ ጥያቄ ዋና ነገር ግርጭት በመግደል ጥይት በመተኮስ መፈታት የለበትም ። በትግራይ የሚነገረው ያለው የስድብ ናዳም መቋጫ መኖር ኣለበት እላለሁ። ከስድብ በኃላ ወዴት ነው ጉዞው?ኣደገኛ ነገር ነው። ኣሁንም ትእዝብቴ መቋጫ የሌለው የኢሮፕ ብሄረሰብ ረሃብና የውሃ ጥም የኢሮብ ብሄረሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኝ ከኣድግራት ከተማ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሆም የኢሮብ ህዝብ ሲወሰድ ኢሮፕ ኢሮፕ እንዳልጌዳ ኢሮፕ መኩኔቶ ኢሮፕ ሓሳብለ የሚባሉ ዜጎች ናቸው የነዚህ ህዝብ ብዛት ከ38 ኣመት በፊት ብዛታቸው ከ100ሺ በላይ እንደ ነበር የኣከባቢው መሬት ትላልቅ ተራራዎች ይገኙበታል የኣከባቢ ኢሮፕ የተፈጥሮ ሃብት የኢሮፕ መልከኣ ምድር ከ38 ኣመት በፈት በጥድ በዌራ በበለስ ሌሎች እፅዋት የተሸፈነ ነበር ።በዚሁ ቦታ እንስሳ ዘቤት ንብ ነፍሰወከፍ ኣባወራ (ኣርሶ ኣደር) ከ30 ቆፎ በላይ ንብ ነበሩት ፍየል በግ በብዛት ነበሩ የቀንድ ከብትም ቢያንስ በኣንድ ኣባወራ ዝቅተኛ 3
  • 4. ከ20 በላይ ነበሩት በዚ የሚመረት የምግብ ኣይነት ገብስ የተለያዩ ስንዴ በቆሎ ፤በለስ ፤ማር ቅቤ ነበር ። በዚ ወቅት የኦሮፕ ህዝብ ድርቅ ረሃብ የሚባል ኣልነበረም ተረጅም ኣልነበረም። የኢሮፕ ብሄረተሰብ የኣሁኑ ገፅታው እንስሳ ዘቤት በሚመለከት ከብት ፍዮሎች ንብ ከ38 ኣመት በፊት ከነበረው ብዛት ከ2%በታች ይገኛል እፅዋት በሚመለከት በኣለም እጁጉን ቀንሳል ሌላ እፅዋት እንደ ጥድ ዌራ ሌሎች ለሙዜም የሚሆንም የሉም ሌላ ቀርቶ የኣሲንባ ተራራ የነበሩ እፅዋት ጠፍተዋል። የህዝብ ብዘት በሚመለከት ኢሮፕ ብሄረሰብ በዘመነ ህ.ወ.ሃ.ት ኢህኣደግ ስልጣን ወደ ሁለት ወረዳዎች ተከፍሏል እሱም ግማሹ ወደ ሳዕስዕፃዕዳ እምባ ወረዳ ዕዳጋ ሓሙስ ግማሹ ደግሞ ወረዳ ኢሮፕ ሆኖ ዋና ከተማው ደውሃን ነው። የኢሮፕ ህዝብ ከ100ሺ በላይ የነበረው በኣሁኑ ግዜ በኢሮፕ ወረዳ ያለ ህዝብ ከ16ሺ ኣይበልጥም የቀረው ህዝብ ኣብዛኛው በተለይ ሙሁር ህብረተሰብ ወደ ውጭ ኣገርተሰደዋል ፤ጥቂት የማይባልም የምድር በዳ ንሮ የመረረው በኣዲግራትና መቀሌ ይኖራል ወረዳ ኢሮፕ ድሮ የንብ የፍየል የከብት መንደር ብዙ ህዝብ የሚኖርበት የነበረች በኣሁኑ ጊዜ የወታደር መንደር ሆናለች የኢሮፕ ህዝብ ሻኣብያ ኣፍኖ የወሰዳቸው እስከ ኣሁን ያልተመለሱ በዛው የቀሩ ኣሉ ። የኢሮፕ ቋንቋ በትግርኛ ቋንቋ እየተዋጠ ለሙዚየም የማይገኝበት ሁኔታ ተፈጥራል። እንግዱህ ይህ ካልኩ ወደ ዋና ኣጀንዳየ በመምጣት የኢሮፕ ህዝብ ሃብት እየተመናመነ መጥቶ ድርቅና የዝናብ እጥረትተደምሮበት ባለፉት 21 ኣመታት የእርዳታ ጥገኛ ሆኖ ቢቆይም ግን ዳግም የማይናቅ የእርሻ ምርት ማር ወተት ወዘተ ያገኝ ነበር ኣሁን እንደ ታዘብኩት እንስሳውም ንቡ ከብት ፍየሉ የሉም ቢኖሩም የሚጠጣ ውሃ የለም የሚበላ መኖ ሰር የለም ይቅርና ለእንስሳ ለሰውም ውሃየለም የእርሻ ምርትም ጭራሽ ኣልገባም ዝናብ ባለ መዝነቡ ያለው ህዝብ በእርዳታ ነው የሚነረው ኣሁን ያ የበሰበሰ ስንዴም የለም ህዝቡም እጅጉን ጥቂት ነው የቀረው በደውሃንና ዓሊተና ያሉ ሰዎችም ከወታደሮች የተሳሰሩ ሴተኛ ኣዳሪና ነጋዴዎች ናቸው ያእርጅና ለኢሮፕ የለም ኣለ የሚባለው ህዝብ ከ21ሺ ኣይበልጥም። ለኢሮፕ ችግር መፍትሄ የምስራቃዊ ዞን መሪዎች ይሁኑ የክልሉ መንግስት ሲያግዙት ኣይታዩም ታድያ የኢሮፕ ችግር መቸ ይቃጫል ሁሉ ግዜ ጥያቄ ያስነሳል ያነሳበት የድርቅ ጉዳይ ካነሳሁ በኣሁኑ ግዜ በደቡብና ደቡባዊ ምስራቅ ትግራይ በራያ በመሁኒ መቸር ካለና ፤ዋጅራት በኣሰርሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተደጋጋሚ ግዜ በዝናብ እጥረት ለብዙ ኣመታት የእርሻ ምርት ያላስገቡ ። የውሃና የምግብችግር ያላቸው ሆነው በትግራይ መንግስት ለጉዳዩ ኣትኩረት ሰጥቶ እንዳጣ ገዛ ከላይ እንደዘረዘርኩት ስልጣኑ ለመረጋጋት ብቻ የሚረጠው ያለው የራያና የዋጅራት ህዝብም ኣጋር ከሚሆነው መንግስት ያሰፈልገዋል ኣደጋ ላይ ነው ያለው ። ኣደጋ ብቻ ሳይሆን በኣሁኑ ግዜ ሰውም እንስሳ የሚበላ ውሃ የሚጠጣው የለውም።የዚህ ችግረኛ ህዝብ ብዛት ቢያንስ ከ30.000 በላይ ነው፡፡ በከሮምና ኣላማጣ ያየሁት የዜጎችን መብት የሚነካ ኣሰራርተከስታል በጉዘዮ እንዳዩሁ በከሮምና በኣላማጣ ወረዳዎች እድሜ ደረሰና ነዋሪ ህዝብ መታወቅያ ሊሰጠውና ሊታደስለት ሲጠዩቅ ስደት ስለምትሄድ ኣይታደስላችውም እየተባሉ ይከለከላሉ ያመታወቅያ መስጠት የ ህገ መንግስታዊ የዘግነት መብታቸው እያለ እየተጉላሉ ይገኛሉ። የመታወቅያ ጥያቄ ጉዳይ በትግራይ ክልል መታወቅያ ለማግኘት ብዙ ቅድሜ ሁኔታ ሟሟላት ግድ ይላል ይህም ማንም ሰው መታወቅያ ለማግኜት የቀይ መስቀል የትግራይ ልማት ማህበር የወጣት ፤ የግብረ ማህበር ለወይን ጋዜጣ ፤ የህ.ወ.ሃ.ት ኣባልነት ገንዘብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ ይህ ኣሰራር በመላው የትግራይ ዜጎች ፤ ወረዳዎች ፤ቀበሌዎች የሚተገበር ኣሰራር ነው። ዋና ኣለማውደግም ሁሉ እንቅስቃሴ ገንዘብ የሚል በሽታ ይመስለኛል ። ለ ህ.ወ.ሃ.ት ለመጠናከር የሚጠፋ ያለው ገንዘብ ስንት ይሆናል ?በሞቶሺ ወይ በሚሊዮን በትግራይ ክልል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ህልፈት ተከትሎ በፓሪቲዎች በተፈጠረ ጭንቅንቅ 80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በስብሰባ ተጠምዶ እየተናጠ እንደከረመ በዚህ ትእዝብቴ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ስብሰባው እንደሞደልነት(መፈተኛ) በትግራይ ስለተፈተነ በነዚህ ስብሰባዎች በትግራይ ብቻ ለውሎ ኣበል ለትራንስፖርት ለተሰብሳቢዎች ገበሬዎች ሰብላቸው በሚሰበሱቡበትና በሚወቀበት ጊዜ ያባከነ ጉልበት በገንዘብ ሲታሰብ የመንግስት ሰራተኛ በመንግስት የስራ ስዓት ለህዝቡ ይሰጠው የነበረ ኣገልግሎት ገንዘብ ሰታሰብ የተገልጋይ ህዝብ ኣገልግሎት በማጣቱ የከሰረው ጊዜና ገንዘብ በገንዘብ ሲታመን ከኣንድ ፓርት ህ.ወ.ሃ.ት ለመጠናከርና ለመረጋጋት በሞቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ማባከን ምን ያህል ወንጀል መሆኑ ለህዝብ ግልፅ መሆን ኣለበት ። በትግራይ ያሉ 5 የሚሆኑ ትናንሽ ግድቦች በህዝብና በትንሽ የማሽነሪ ደጋፊ የተሰኑ ግድቦች ከ20 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ኣልፈጅም በነዚህ ግድቦች ከ1500 በላይ ኣባወራ ኣርሶ ኣዶሮች ተጠቃሚ ሆነዋል ፤ ኣሁን ለኣበልና ለትራንስፖርት ሌሎችም የባከነ ገንዘብ ሳንጨምር ለውሎ ኣበል ብቻ የወጣ ገንዘብ ሲተመን ፤ህ.ወ.ሃ.ት ኣንድ ሚሊዮን ኣባል ቢነረው በዝቅተኛ ውሉ ሌላ ኣሁን ኣባል ለማድረግ በስብሰባ ለ5 ቀን ተጠምዶ የሰነበተው ለኣንድ ሚሊዮን ህዝብ በቀን 35 ብር ሲታሰብ ለ 4ቀን ሲታሰብ የኩፍኛ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኛ 220 በቀን ሲዮን ከ100.000 ሰው ለ 7ቀን ውጪ ሲታሰብ ስንት ይሆናል ስንት መቶ ሚሊየን ኣንባብያን ልብ በሉት፡፡ በግዚዮው ባለ መሰብሰቡ የፈሰስ ስብል የመኸር ዝናብ ያባላሸው በገንዘብ ሲተመን እጅግ ብዙ ገንዘብ ነው ። ስለ ሆነ ሁኔታው ሲታዘብ ምን እያሉ እና እየሰሩ በማለት እኔም ይገርመኛል ። ህዝቡም የመንግስት ሰራተኛው ለሁኔታወ አግራሞት እየተሰማው ዝምታን መርጦ ተጨንቆ ይኖራል። በተለይ ሙሁር ክፍል የሚፈጸመው ያለ የመደናገር ስራ እያወቀ እንዳላወቀ ዝም ብሎ መለፍ ለራሱም ለሃገሩም ጎጂ እንጂ ጠቃሚ አለመሆኑ አውቆ አለመቃወሙ ለወደፊቱ ተወቃሽ እንደሚየደርገው ይታየኛል። 4
  • 5. የህወሐት ህአዴግ መሪች በአሁኑ ጊዜ የሚፈጽሙት ያሉት ስህተት ቆም ብለው አስበውበት የጥፋት መንገዱ አቁሞው ምን እየተባለ ነው ብለው ከምሁራኖችና ከከፍተኛ በለሞያዎች የሕግ፣የታሪክ አዋቂዎች የዕድሜ ባለፀጋዎች ቢያማክሩ በግብታውነት ተጉዘው ወደ ጨለማ ከመግባትያድናቸዋል። በኔ ትዝብት በሁሉም በትግራይ ከተሞች የፍየሎችና የቀንድ ከብት በሁሉም የእንስሳ ገበያ ረክሰዋል ለምን? በተንቀሳስኩባቸው ከተማዎች የአርሶአደሩ ፍየሎችና የቀንድ ከብቶች በብዛት ወደ ገበያ ሲሄዱ አየሁ። እኔም ይህ ሁታ ምንድነው ሿጭ ማነው ገዢውስ ማነው የሚል ጥያቄ አነሳሁ። በኣንድ ትንሽ ገበያ ተቻብኩ በዚህች ሽያጭ አንጂ ገዢ ብዙውም የለም። ሁታው ለማረጋገጥ ወደ ሽያጮች ጠጋ ብየ ለምን ይህ ሁለ እንስሳ ገበያ ወረደ አሁን የመኸረ ጊዜ ነው። ረሃብ የለም። የበቆሎና የጥራጥሬ እሸትአለ ብየ ጠየቅሁ። የሰጡኝ ምላሽ እኛ በአሁኑ ጊዜ በአንደ በኩል የደደቢት ብድርና ቁጠባ(የደደቢት ማይክሮፋይናንስ)፣ በሌላ በኩል የፓኬጅ በተጨማሪም የመዳበርያ ገዢ ብድር ክፈሉ ካለመለዝያ ንብረታሁንና ሰብላችሁን ይወረሳል ስለ ተባለ ተደናግጠን በአሁኑ ጊዜ እኮ ሁሉ የትግራይ ህዝብ አርሶአደሩና አንስተኛ ነጋዴ ብያንስ ከ5 ዓመት በላይ ውዝፍ እዳ አለው። አብዛኛ ህዝብ እዳ መክፈል ተስኖት በኖ ጠፍተዋል ብለውኛል። የእንስሳ ዋጋ እንዴት ነው ስላቸው ገበያው ረክሷል ምክንያቱም ገዢ የለም ሁሉም ሸያጭ ነው አንድ አንድ የስጋ ቤት የሚገዙ ቢኒሩም በዝቅተኛ ዋጋ ልንሸጥላቸው ነው የሚፈልጉ። የሚጠይቁን ያሉ ዋጋ ከገዛንበት 40% በታች እንባቸው እየፈሰሰ ቀንሷል ይሉ።ብድሩ የስንት ዓመት ነበር ፣ የ5፣ የ2፣ የ1 ዓመት በር አሁን ክፈሉ እያሉ እያስገደዱን ስላሉ እንጂ ለክሳራ ተዳርገናል። የምንሰደድበት ሃገር አጥተን እንጂ ተሰደው እንደጠፉ በጠፋን ነበር ይላሉ። በዚህ ዓይነት ትዝብቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ ከገበያ ውጭ ባሉ ዜጎች ቀስ ብየ መጠየቅ ጀመርኩ። የሰጡኝ መልስ በደደቢት ብድርና ቁጠባ የተጠቀመ ሰው ጥቂት መሆኑ አብዛኛውህዝብ በደደቢትና በፓኬጅ በመደበርያ ግዢብድር የታቀፈ ብድርና ውዝፍ(ወለድ) ተጨምሮ ተበዳሪው ሊከፍለው የማችለው ሁኔታ እንዳለ ደደቢት ብድርና ቁጠባ ያበደረው ገንዘብ በህዝብ ጫንቃ ላይ በቢልዮን የሚቆጠር ብር መኖሩ የውስጥ አዋቂዎች ነገሩን። እኔም በትእዝብቴ ተጨባጭ ለማረጋገጫ ለማያዝ ኣራት ጎጦች እያንዳዳቸው 25 ኣባ ወራዎች ያላቸው መንደሮች በራሴ ሰዎች ኣጠናሁ ። የሚገርመው ነገር በ3ቱ ጎጦች ያሉ ገበሬዎች 100% እዳ ኣላቸው ። በኣንድ ጎጥ 3 ሰዎች ብቻ ዕዳ የለላቸው ኣገኜሁ ። ይህ የሚያረጋግጠው ሁሉ የትግራይ ህዝብ በዕዳ የተያዘ ግን ደግሞ ዕዳው ለመክፈልስ ይቅር ለምግብ ማስትና የሌለው ህዝብ ሁኖ ኣግኝችውኣሉሁ። የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን 4.3 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ኣንጡራ ሃብት ወደ እጃቸው ለማስገባት ብለው ያቋቋሙት የደደቢት ፍትሃዊ ብድርና ቁጠባ ባንክ ፍትሃዊ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ግብኣተ መሬት ያስገባ እና ህዝብ ኣባትና ልጅ ባልና ሚስት የበታተነ የህ.ወ.ሃ.ት የንግድ ድርጅት ነው ። በተጨባጭ ራሴ እንዳራጋገጥኩትም ከ18 ዓመት እድሜ በላይ የትግራይ ህዝብ ምንም ጥናት ያልተደረገለት የስራ መስክ ለተበዳሪውም ምንም ትርፍማ ባልሆነ ስራ እያወቁ ገንዘብ ያበድራሉ። ሰው ሲጨንቀው ንብረቱ ሽጦ ይከፍላቸዋል ንብረት የሌለው ቢጠፋም ምናቸው ሁኖ ። እነሱ የሚፈልጉ የህዝብ ንብረት በሃራጅ ሽጦው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ኪስ ሞሙላት ነው ።የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቢታመሙ ከነ ልጆቻቸው ዘር መንዘራቸው በታይዋን ፤በደቡብ ኣፍሪካ ፤በኢሜሪካ ፤ጀርመን ወዘተ እየሄዱ ይታከምበታል ። ለልጆቻቸው ኣውሮፓ እና ኣሜሪካ እንዲሁም ቻይና ያስተሙሩበታል ። ደደቢት ብድርና ቁጠባ እንዶ ለሎች ስራዎች በዝባዥ ኣሰራሩ እንደ ተመኩሮ ለባኣዴን ፤ለኦሆዴድ ለደቡቦች ፤ለዓፋር ፤ለሱማሌ ወዘተ በመስተላለፍ ይገኛል ። መጥፎ ኣሰራሩ በኣማራ ፤በኦሮሞ በሌሎች ብሔረሰዎች እንደወረሽኝ በሽታ እያስተላለፈ ነው ። በኣጠቃላይ ጥናት በጎደሎው የደደቢት ብድርና ቁጠባ በፈጠረው ችግር የቀንድ ከብቶች እና ሌሎች እንስሳት ዋጋ በመውረዱ የትግራይ ኣርሶ ኣደር ኣነስተኛ ነጋዴዎች በከባድ የድህነት ኣረንቋ ገብተዋል ምህረቱን ይስጣቸው ። በትእዝብቴን ያየሁት በትግራይና ሴሜን ጎንደር ደጋማ ቦታዎች የባቄላና የኣተር ሰብል በዋግና ትል ተበልቶ ጠፍተዋል በኣሁኑ ግዜ የክልሎች ይሁን የሃገራችን መንግስት እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ፤የእርሻ ባለሙያዎች ሰልጠና ግንባር ቀደምት ኣትኩሮት ተሰጥቶት በኣስር ሺ የሚቆጠሩ የእርሻ ባለሙያዎች ሰልጥነው በቀበሌው ተሰማርተው በሙያቸው እንደመስራት ፈንታ የኣቤታዊ ዲሞክራሲ ኣስተሳሰብ (ኣይዶሎጂ )በማሰረፅ ቀዳሞት ለፖለቲካ ዘመቻ በመስጠት ሲሰሩ ይታያል ። እኔ ሰሞኑን በተንቀሳቀስኩባቸው ቀበሌዎች ወረዳዎች እንደታዘብኩት ግን በተለይ በትግራይ ክልል በደጋማ ቦታዎችና በሰሜን ጎንደር ወረዳዎች በጃን ኣሞራ ፤በቦዳ ፤ ሰላምጌ ፀለምት ፤በላምት በ40%ከዛ በላይ ምርት የሚዘው በቀላ በትግራይ ቃንቃ ዋግ (ሕሞዲያ) በኣማርኛ በሚባለው 100% ተቃጥላል በሌላ በኩል ኣተር የሚባል ሰብል በነዛ የተጠቀሱ ደጋማ ወረዳዎች የሚበቅል ወሳኝ ሰብል በማይታወቅ ትል ተበልታል ይህ ሰብልም ከ10% እስከ 15% ምርት የሚዘው በትል ተበልታል ። ኣርሶ ኣደር ክረምቱን ሙሉ እየተንከባከቡየቆዩውና ቅጣሉን ኣይቶ ተስፋ ኣድርጎ የቆየው የትግራይና የሰሜን ጎንደር ደጋማ ነዋሪ ህዝብ የባቄላና ኣተር ምርት ሊያፍስ በተስፋ ሲጠብቅ የከረመው በመጨረሻ መስከረም ወር ሰብሉ በእሳት እንዳተቃጠለ ገለባ ተቃጥሎ ቀረ ኣርሶ ኣደር ቅጠል ሲያይ ኮርሞ በመኸር ወቅት ውሃ ዘግኖ ቀረ ። ታድያ የዘመናችን የኢ.ህኣድግ ባለ ስልጣናት ይህን ያህል ሚሊዮን ኩንታል ምርት እናገኛለን ሲሉን እንሰማለን ፤የክልላችን የእርሻ ባለሙያዎች ይህን የስብል 5
  • 6. በሽታ ከለተከለከሉ ስራቸው ምንድነው ።በበኩሌ የግብርና ባለሙያዎች በየገጠሩ ተበታትነው ቢነሩም ለሚሰሩት ስራ የሰብል በሽታ መከላከያ (ለማከም) የሚያስችል የመድሃኒት ግብኣት እንዳማያገኝ በሚገባ ኣረጋግጫለሁ ። የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ቢተውና ተከተዮቻቸው የሚናገርት ባዶ ዲስኩርመሆኑም ኣረጋግጫለሁ። ይህ ሃቅ የሆነ ተቆርቃሪ ዜጋ ሄደ ሊያጣራ ይችላል ። በኣርሶ ኣደሮች ድረስ ያለ አዳጊ ግልፅ ሆኖ ያገኜዋል ።በሰሜን ጎንደር ተራራዎች ባቄላ ኣተር፤ገብስና ፤ስንዴ በትል እየተበላ ኣጋር ኣጥተው ወደ ስደት እንደፈሰሱ ከኣሁን በፊት በፍትህ ጋዜጣ የጨለማን ኑሮ የተለየው ህዝብ ብየ ጠቁሜ ነበር ። የኣባይ ግድብ መስርያ ለሁለተኛ ጊዜ ገንዘብ ኣውጡ መባሉ የመንግስት ሰራተኛ ደስተኛ ኣይደለም የጠቅላይ ሚኒስቲር ህልፈት ተከትሎ ለሁሉ የመንግስት ሰራተኛና ሌሎች ህብተሰብ የመለስን ጅምሮች ለመፈፀም ቃል ኪዳን ያለገባ የህ.ወ.ሃት ኢ.ህኣደግ ኣባል ያልሆነ ዜጋና ሰራተኛ ኣገር ወዳጅ እንዳለሆነ ብዙ የህ.ወ.ሃት ኢ.ህኣደግ ከድሬዎች እያነፀ በርቀት እንደሰነበቱ የሚታወስ ነው። በትግራይ ክልልና በዘኖች ፤ ወረዳዎች ቢሮዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በየ ኣካባቢው ከሚደረገው የሰነበተ ስብሰባ ተያይዞ ለተሰብሳቢዎች የመለስ ረኣይ ልንከተል የተወሰነ መመሪያ ለመፈፀም በቃለ መሃላ ኣረጋግጥ እየተባለ እጅ ለእጅ ተያያዙና ተማማሉ እየተባለ ከተማለ ብኃላ ኣስከትሎ የኣባይን ድጋፍ ለመወሰን ፈርም እንዱሞላና እንድፈርም ይገደዳል ። ሰራተኛው ግን ባለስጋት ምክንያት ሳያምንበት ይፈርማል የማይናቅ ቁጥር ያላቸውም ኣንፈርምን እያሉ ኣሉ። ለነዚህ ኣንፈርምን ባሉ ሰዎችም ብዙ ሃሜትና ጥላቻ በመሰንዘር የሚገልፅ ውንጀላ ኣለ። በሌላ በኩል እነዚ ንከፍላለን ብለው የፈረሙ ዜጎችም ተመልሰው ሲራገሙ ይታያሉ የሆነ ሆኖ የኣባይ ግድብ የሚቃወም ሰው ባይኖር ይደረግ ያለ በተፅእኖ ካለው የንሮ ውድነት የወር ደሞዝ ክፈል ማለት ግን ፍትሃዊ እንዳልሆነ ግን ይነገራሉ ። ሌላ ቀርቶ ታማኝ የህ.ወ.ሃት ካድሬዎችም ቤት ዘግተው እያሙ ይገኛሉ ። ስለሆነ የኣባይን መዋጮ በኣሁኑ ጊዜ ሁሉ የመንግስት ሰራተኛ ደስተኛ እንዳልሆነ ነው ትእዝብቴን ። ስጋት ግን እስከመቼ ነው ለመሆኑ ስጋት ፈጣሪ ማነው ስጋት የሚፈጠርበትስ ማነው ሁሉም ዜጎች ኣይደሉም ። ዜጎች የህሊና ነፃነት ክሌላቸው ምን ስብእና ኣላቸው ይባላል ኣሳዛኝ ነገር። ኣሁን በዘመነ ስልጣን ሃይለማርያም ደሳለኝ ትግራይ ሞሞከርያ እየሆነች ነው በዘመነ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ሁሉም ነገር በትግራይ ከተሞከረ ብኃላ ወደ ሌሎች ክልሎች እንደሰርቶ ማሳያ (ዲሞንስትረሽን) ተጠቅመው ምንም ሳይለውጡ በየ ክልላቸው ይተገብሩት እንደነበሩ መላው የኢትዮጽያ ህዝብ የሚያውቀው የቅርብ ትዝታ ነው። ይህ ኣሰራር በዘመነ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠናክሮ መጀመር ጀመርዋል ይህ ያልኩት ምክንያት በ2004ዓ.ም የግብርና ቀረፅ ገቢመሰብሰብ በትግራይ ክልል በ2003 ዓ.ም ከተሰበሰበው ግብር በብዙ እጥፍ እንደተሰበሰበ የገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን ትግራይ ቅርንጣፍ ራሳቸው ሲናገሩት ከርመዋል ። እንደሉትም ግብር በትግራይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከፍሎ የማያውቅ በዘንድሮ በቢሊዮን የሚቆጠር ግብርና ከእቅድ እጥፍ እጥፍ ተሰብስባል ተብሏል። ስለሚወራም ኣግራሞትም ፈጥራል ። ይህ ግብር ኣሰባሰብ ግን በትግራይ ባለሃብት ነጋዴ ያፈናቀለ ለስደት ያደረገ እጅግ ብዙ ንግድ ቤቶች ቢዘጉ ያደረገ ወራር የግብር ኣሰባሰብ ነበር። ለዚሁ ሃቅ ለመረጋገጥ ካሁን በፊትም ደጋግመን እንደተረጋገጠ ነው። በትግራይ የነበሩ የህንፃ ተቃራጭ ኮንትራክቶሮች ጭራሽ ክልሉ ለቀው ኣዲስ ኣበባ ደቡብ ሰሜን ሸሽተዋል ። ከስረው ስራቸው የዘጉም ኣሉ። የንግድ ኣስመጪዎች የችርቻሮ ነጋዴዎች ንግዳቸው ዘግተው ጠፍተዋል ፤ በኣስር ሽዎች የሚቆጠሩ የጥቃቅንና ኣነስተኛ ተቋማት ከሰመዋል፤ ከነ ንብረታቸው የታሸጉ ንግድቤቶችም ኣሉ፤ ለቀሩ ነጋዴዎችም ጥዋት ጥዋት በሚቀየሮው መመሪያ እየተናጡ በጭንቀት ተውጣል ፤ የነበረ የንግድ የሞቀ ስራ ኣሁን ፍፅም ቀዝቅዟል ፤ ኣስመጭና ነጋዴዎች ስለ ሸሹ የሸቀጥ እቃዎች ንረዋል ፤ በኣጠቃላል በትግራይ ፍትሃዊ የግብር ኣካፋፈል ስለቤ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች በመሸሻቸው የነበረው እንቅስቃሴ እየቀዘቀዘ ይገኛል፡፡ ሁኔታው እንደዚህ እያለ በኣቶ መልኣኩ ፋንታየ የኢትዮፕያ ገቢዎች ግምሩክ ዳሪክተር የታመኑ ከሁሉም ክልሎች የተወጣው የገቢዎችና ጉሙሩክ ሰራተኛ ባለስልጣኖች እንደ ተለመደው መፈተኛ የሆነው የትግራይ ግብር ኣሳባሰብ ተሞክሮ ለመቅሰም ተብሎ በየ ክልላቸው በኣየር ትራንስፖርት ተጉዞው በመቀሌ ሃወልት ሰማእታት ተሰብስበው ነጋዴ እንዴት ታቀዋለህ የሚል ልምድ ሲቀስም ሰንብተው ፤ ህዝባቸው ለመሮቐስ የህ.ወ.ሃት የቀሰማቸው የማፈኛና ሚሞሪ ተሞልተው ተስማርተዋል። ይህም የህ.ወ.ሃት ኣስተሳሰብ የሆነ ኣንባ ገነኑ ኣቤታዊ ዲሞክራሲ ከህ.ወ.ሃት መንደር ኣመንጭቶ የ80 ሚሊዮን ተላላፊ የወረርሽን በሽታ እንዳዳረገው ሁሉ ይህ ነጋዴ ገዳይ የሆነው የግብር ኣሰባሰብም የኸው ከትግራይ ወደ 80 ሚሊዮን ህዝብ ሊሰራጭ ከመቀሌ ሃወልት ሰማእታት ኣዳራሽ ተልኮልቸዋል። የተከበራችሁ ኣንባብያን ፤እኔ እምለውያለሁ ግብር ቀረፅ መክፈል የለበትም ኣደለም እያልኩ ያለሁት ፤ ግበር መክፈል የዜግነት ግዴታ ነው፤ መክፈል ኣለበት ፤ እኔ እምለው ያለሁ በጥናት የተመሰረተና በፍትሃዊ መሆን ኣለበት ነውያለሁኝ ያለሁት በትግራይ ክልል ያለው የግብር ኣከፋፈል ግን ኣስፈሪና የነጋዴ ህብረተሰብ የነቀለ ለኛ ህብርተሰብ ወደ ውደቀት ያስገባ ነው እላለሁ። እናንተ የህ.ወ.ሃት የግብር ኣስተሳሰብ ልምድና ተሞኩሮ ቀስማችሁ ሄዳችሁ ያላችሁም ይህ የኣፈና ልምድ በህዝቦች ጫንቃ ከተገበራችሁ ከጥቅሙ ኣደጋው ነው የሚያመዝነው። የፅንብላ መይል ቀበሌ ኣርሶ ኣደሮች በግድ እየተፈናቀሉ ናቸው 6
  • 7. በዚህ ጉዳይ በትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን በኣስገደ ፅንብላ ወረዳ በመይል ቀበሌና ኣካባቢዋ የሚኖሩ በሺ የሚቆጠሩ ኣርሶ ኣደሮች ከ 60 ኣመት በላይ የኖረበት ቦታ በኢፈርት ትእምት ሱር የሚገኘው ኢዛና ወርቅ ማኣድን ድርጅት የወርቅ ቁፋሮ ካንፓኒ ስለሚቆፈርበት ለነሱ ተብለው፡፡ ለዘለቄታ ምን ይሆናሉ የሚል በቂ ግምት ሳይሰጣቸው ከመኖርያ ቆያቸው ተነሱ ተብለው በትልቅ ጭንቀትና ችግር እየተናጡ ናቸው፡፡ እዚ ላይ እኔ የምለው በዛ ቦታ መኣድን መቆፈር የለበትም ኣይደለም የምለው ያለሁ የመኣድን ቁፋሮ መካሄዱ ኣልቃወምም፡፡ ነገር ግን መይል የሚባል ቦታ ብዙ ኣርሶ ኣደር የሚኖርበት ለቀንድ ከብት ማራባት ለእርሻ ሰብል ተሰማሚ ነው በመሆኑ ብዙ ገበሬዎች ኣቅፎ ነበር እኔ የሚታዩኝ ኣርሶ ኣደሮች ከመፈናቀላቸው በፊት ብዙ ዝግጅቶች ያስፈልጋል፡፡ ከ ዝግጅቶች ለመጥቀስ ለንሮኣቸው ኣመች ይሆነ ለእርሻ እንስሳ ማርባት የተመች ቦታ መስጠት ኣለበት የተመቻቸ መኖርያ ሊሰራላቸው ይገባል 60 ኣመት የኖረበት ቤት ንብረት ወድመባቸው ስላለ ይሄ ማቃቃምያ ማግኘት ኣለባቸው ለፈረሰው ቤታቸው ያለሙት መሬት ግምት መስጠት ኣለበት የሚሰጣቸው ግምት ለዘለቂታው እንዲሰጣቸው፡፡ ለልጆቻቸው በማኣድን ቁፋሮ ስራ ኣንዲፈጠረላቸው ካልሆነ ዝም ብሎ ህዝብ መፈናቀል ኣይገባም፡፡ ግልፅነት ባለው ለህዝብ በማሳመን መሆን ኣለበት ይህ ተግባር በመደባይ ታብር የሚገኝ በኢፈርትና በቻይና የሚቃቃም ያለው የማኣደን ቁፋሮም በሺ የሚቆጠሩ ገበሬዎች የተፈናቀሉ ስላሉ ይህም መታየት ያለበት ነው፡፡ በመይል ያለው የህዝብ ቁጣ መንግስት በግልፅና ከህዝቡ በማግባባት ካልፈታው በኔ ትእዝብት ችግር ይፈጥራል፡፡ ማጠቃለያ በዚህ ፅሁፍ በትግራይ በኣገራችን ያሉችግሮች በልማት በዲሞክራሲ በፍትህና የዜጎች ነፃነት መንጠቅ የህ.ወ.ሃት ኢ.ህ.ኣደግ ዲሞክራሲ የኣፈና ፖሊሲዎች ፤በትግራይ ሰለማዊ ተየቃዋሚ ፓለቲካዊ ፓርቲ መንቀሳቀስ ፍፅም ተቀምጦልያል ብታምንም ያጠብብና ብሎም ተቃዋሚዎች እንዲ ከሰሙ እሚያደርግ የስለላ ነትወርክ መስራት ፤ለዚሁ ኣፋኝ ኣላማ ለማስተግበር መሞቶ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያባክን ኣሰራር፤ በጠቅላይ ሚኒስቴር ሞት በመሳሰብ 40(50)ኣመት መመርያ የሚያሰራ መመርያ ተቀምጧል ያስ ብታምንም ባታምንም ተግባር ብሎ ሳይወዱ በግድ ፎርም እንዲሞላ ማድረጉ ። ከኛ ሌላ ኣታምልክ የሚል የህሊናውያን መርሕ በመያዝ ዜጎች ማስገደድ ፤ለሃገራችንም ለናንተም ኣይጠቅምም። ከሂትራልና ሞስሎኒ ኣፋይኝና ፋሽሽታዊ ተግባር ኣለምን ያንቀጠቀጠ ኣልነበረም።ግን ውሸታሞች ነበሩ በርሊን በ360 ድግሪ ተክባ ሊገድል ትንሽ ግዜ ሲቀረው ሚድያዋችን ተቆጣጥሮ ድልን እየተገናፀፍኩ ነኝ እያለ ይደነፍ ነበር ግን ምፅኣተ ኣለም ደረሰች በቃ ህዝቡ ኣሸነፈ። ደርግም ሁሉም ነገር ማጥጦና ኣፍኖ በመያዝ ኢትጵያን በራሻ ኣጃቢ የሰለጠኑ ባንዳሰላዮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ በማሰልጠን ህዝቡ እንዳይናገር እንዳይ ሰማ ቆርኖ ይዘት ነበር። በሌላ በኩል ሁሉ ህዝብ ያለፍላጎቱ ኢሰፖ ኣባል መሆን ኣለበት በማለት ኣስገድዶ ኣባል ያድርግ ነበር ። ለሁሉም ነገር በጥይት በድህንነት መዋቅር በማስፈራራት ኣምነዋል ፤ገድለዋል ፤ኣስረዋል ፤ሁሉም በቁጥጥር እንዲሆን ኣድርገዋል። ውስጡ በሰበሰ እያለ ኣለሁ አፋኝ እማይሞላ ወንበዴዎች ነገ በእጃቸው ይዘቸለሁ እያለ ህዝብ ያታል ነበር። ግን ኣልሆነም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወታደሮች ሰላዮች የኢሰፓ ኣባል ይዞ ተቸነፈ። ምክንያቱም 70 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ተገዶኣለሁ ይለው ነበር እንጂ በውስጡ ደርግ የሚወድቅበት ብልሃት ይቆፈር ነበር። ለደርግ ህ.ወ.ሃት ብቻውን ኣልነበረም የነበረ ቢረክራሲ ፤ሙሁራኖች ፤መላው ህዝብ ነው የተፉት ግን ከዛ ከሸነፈው ደርግ ተምሮ ለህዝብ ታማኝ ሆኖ እንደመገኘት ፈንታ የደርግን ውሸት በመድገም 80 ሚሊዮን ህዝብ በኔ ሳንባ ብቻ ካልተነፈሰ ብሎ ህገመንግስት ኣክብረው ለሚታገሉት ፖለቲካ ፖሪቲዎች ለማክሰም 100 % ህዝብ ኣባል ህ.ወ.ሃት ይሁን ማለቱ ውድቀቱን መጥራት ነው ስለ ሆነ ህዝብ በወታደር በታንክ በእሳትና ኤሌክትሪክ ቢከበብም ኣይሸነፍም ህ.ወ.ሃት ከራስህ ልምድ ተማር ። ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መቀሌ ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com November 27, 2012 7