SlideShare une entreprise Scribd logo
1  sur  23
Télécharger pour lire hors ligne
ስለ አዲሶቹ የጥራትና እውቅና ፍቃድ ኃላፊዎች ለለውጡ ደጋፊዎች እና
የለውጥ ሞተር ወይስ እንደቀድሞው ስረአት የእድገት አደናቃፊና ለራሳቸው
ጥቅም ሲሉ ስትራቴጂውን የሚጥሱ
……………………………………………………………………………………..
ገና በውድድር ካሸነፍን እርዳታውን ለምናገኘው ምቀኝነቱ በዛ፡፡ መስራት
ሀጢያት የሆነበት ሀገር፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በጠሩት የምክክር
መድረክና የእርዳታ ልገሳ የተገለሉ ሕብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ
ያወጡትን ጨረታ ለመወዳደር የተጀመረ ስራ ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት በሚል
ስራ ሳላቋርጥ በመስራቴ የመንግስት አሰሪ የተባሉ አካላት ለምን ትሰራለህ
የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ለምን ትሰራለህ የሚለው ቃል መጀመሪያ የጀመረው
ከክፍለ ከተማ አብሮኝ የሚሰራ ባለሙያ ደረጃ ሲሆን፡፡ አብረን ከተቀጠርን
ጊዜ ጀምሮ መሆኑ በተለያየ ጊዜ የያዝኳቸው መረጃዎች ምስክር ናቸው፡፡
ይሻለዋል በሚል ጉዳዩን ንቄ ስተው ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜ ካለሁበት ክፍለ
ከተማ ለመቀየር ስሞክር ከቆየሁ በኋላ እነሆ አሁን ተሳክቶልኝ ለመቀየር
በቅቻለሁ፡፡ ይህ ሰራተኛ ገና ከጅምሩ ለቅጥር እኳን የማያሟላ ሲሆን ከዛን
ጊዜ ጀምሮ እንዴት አላሰራ እንዳለ በመረጃ ቋት ተቀምጦለታል፡፡ ሁል ጊዜ
በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ቢሮ እየገባ ለምን ይሰራል? በሚል
ስለሚያንሿክክላቸው የስራ እንቅፋት ነበር፡፡ በመቀጠል ይኽው የተሳሳተ
ሀሳብ በኃላፊዎች ደረጃ ነበር ሲንጸባረቅ የነበረው፡፡
ለምን ትሰራለህ? በሚል በዚህ ደረጃ የተነሳው በነበርኩበት ክፍለ ከተማ ደረጃ
ስልጠና፣ ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የማጣቀሻ መጽሀፍት
ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ስለጻፍኩኝ ነበር፡፡
ይህ አትስራ የሚለው ጉዳይ እንዳይቀጥል ሪፎርሙን ሲያስተዋውቁ ስብሰባ
ላይ ነበር ማጣቀሻ መጽሃፍን አስመልክቶ ጉዳዩን የእስታንዳርድ ጉዳይ
መሆኑን እንዲረዱት ያቀረብኩት፡፡
በስብሰባ ላይ ያቀረብኩት የሰልጣኝ ማጣቀሻ መጽሃፍ በየተቋሞች ላይ
ያለመኖር ስህተት መሆኑን በግልጽ ቃላት ነበር ያቀረብኩላቸው፡፡
የሚከፈለን ከዩኒቨርሲቲ ስንመረቅ በገባነው ቃለ መሀላ መሰረትና በሚከፈለን
ልክ ለማገልገል መሆኑን ነው፡፡ ነገርግን ባለሙያ ተብሎ የተመደበ አካል
የየጽዳት፣ የተላላኪና የጸሃፊ ወዘተ ደመወዝ የሚከፈለው ስላልሆነ በሚከፈለው
ልክ ነው መስራት ያለበት በሚል ነበር ሁልጊዜ የምነግራቸው፡፡
ነገርግን መልሰው እነዚሁ የክፍለ ከተማ ሰዎች በከተማ ደረጃ ለተቀመጡ
ሰዎች አሁንም ሕገወጥ ስራ እየሰራ ነው በሚል ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ
ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር አብሮ ለምን ይሰራል ብለው አሁን
የጀመርኩትን ሀገራዊ ስራ ስለአስተባበርኩኝ ጥቆማ ደርሶናል በሚል
የጠየቁኝ፡፡ በመሆኑም እነዚሁ በከተማ ደረጃ አዲሶቹ ኃላፊዎች ለምን ስብሰባ
ጠራህ በሚል የተናገሩኝ፡፡ በከተማ ደረጃ የተቀመጡት ኃላፊዎች ጭምር
የሚነገራቸውን ስህተት ይዘው እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡት፡፡ ይህ
የጀመርኩት ስራ በክፍለ ከተማ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ ደረጃ በአቅምና
በብቃት ይሰሩታል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የመስራት አቅም ቢኖራቸው ኖሮ
መሰራት ያለበት በከተማ ደረጃ ነበር የሚሰራው፡፡ ነገርግን የተሰገሰጉት
በዘመድ፣ በፖለቲካ ማንነትና በጓደኝነት በመሆኑ ነው በአቅም የማይሰሩት፡፡
እነሱ ህገወጥ ነው የሚሉት፤ ከሕዝብ ውስጥ ገብቶ ችግር ለመፍታት የሚሰራ
ካለም ማመስገን እና መሸለም ሲገባቸው ለማዋረድ የሚሞክሩት፡፡
ስልጠናንም አስመልክቶ እነሱ ይመጥናል ብለው ለስልጠና የሚያመጡት እና
የሚያሰለጥን አካል ሲያወናብድ ቁጭ ብለው አይተው በደንቡና በመመሪያው
መሰረት የተቋማት የክህሎት ክፍተት ሳይለዩ አሰለጠነ ለተባለው አካል ምሆነ
ከፍተኛ ክፍያ ሲከፍሉ የኖሩት፡፡ ለስልጠና የወጣውን ብር ዓላማውን
መምታቱና አለመምታቱ የወጪ ፋይዳ ግመታ ቢሰራ ህሌናቸውን
የሚያማቸው ከሆነ የጠፋው ብር ወንጀል ስለሆነ እራሳቸውን ከስራ ባሰናበቱ
ነበር፡፡ የፍላጎት ዳሰሳ መስራቴን እዚሁ ሶሻል-ሚዲ ያላይ መስቀሌ
ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት የምሰራው በንቀት ሳይሆን ስራዮን ጠንቅቄ
በማወቅ ነው፡፡ የማያቁትን ስራ እየሰሩ በእውቀት ልስራ ሲሏቸው አውቃለሁ
ይላል ብለው ክስ ያቀርባሉ፡፡
በመሆኑም በዚሁ አመት የገጠመኝ አመታዊ እቅዴን ሳቀርብ ምንአይነት
ስልጠና እንደምሰጥ ሌሎች ከፍተኛ አካላት ምንስልጠና እነደሚሰጡ በግዜ
ሰሌዳ ያስቀመጥኩት፡፡ ነገርግን በሚከፈላቸው ደረጃ በመስራት ለድጋፍና
ክትትል እንወጣለን ብለው የሚሰሩትን ስራ ጠንቅቀው የማያቁ በመሆናቸው
ተቋሞቹን እያደናገሩ ነው፡፡ እኔ የምሰራው በእውቀት ስሰራ ምንም
እንዳልሰራ ዝም ብዬ እንድቀመጥ ለማድረግ የሞከሩት፡፡
ስልጣና አዘጋጅተው በሌላ አካል ሲሰጥ የማስተማሪያ መጽሃፍ እንዲያሰለጥን
የተጠራው አሰልጣኝ የማሰልጠኛ ዘዴውን ግልጽ ሳያደርግ ስልጠናውን ጀምሮ
ሊያጠናቅቅ አንድቀን ቀርቶት የማጠቃለያ ሀሳብ ሲሰጥ እኔ ተነስቸሀሜት ሳይ
ሆን ፊትለፊት መሆን ያለበትን ለአሰልጠኞቹ የነገርኳቸው፡፡ ተግባራዊ
የማሰልጠኛ የመምህር መምሪያና seetion plan/lesson paln አዘጋጅተው
እንዲመጡ ተቋምም ላይ ስንመጣ ይንን ዕቅዳችሁን ማግኘት ያለብን፡፡
በሚል ያቀረብኩት ሃሳብ ለኃላፊ በክስ ምክንያት የቀረበው፡፡ እንደዚህ
በእውቀት መስራት ሲችሉ ከገበያው መውጣት የሊለባቸው ምሁራንና
ባለሀብቶች በግልጽ የሚታይ ብር አምጡ ያክል ከተጠየቁ በኋላ እንዲዘጉ
ተደረጉ፡፡ እነዚህ ምሁራንና ባለሀብቶች ከስራው እንዲባረሩ ብቻ ሳይ ሆን
የተደረጉት በስደት ሌላ ሀገር እንዲሰሩ ነው የተደረጉት፡፡
ወደ አሁኑ ክስም ስመለስ ያለምንም ክፍያ የተዳከሙትን ተቋሞቻችንን
እርዳታ እንዲያገኙ በማሰብ የጀመርኩት ስራ ነው፡፡ የጀመርኩት ስራ ሀገራዊ
ፋይዳ ያለው ሰለሆነ ለመስራት ስታጭ የሰራሁበትን ስራ ስለማልጥል
በጻፍኩት የእሴት ሰንሰለት በሴት እማ-ወራ አርሶ አደሮችን ህይወት ለመቀየር
በተግባር በሰራሁትና በጻፍኩት መጣጥፍ ነበር በፌደራል ቴክኒክና ሙያ
ደረጃ ተጠርቼ ስለነበር ስራውን በቅንጅት ለመስራት ከግልና መያድ ጋር
ስራውን በእቅድ ደረጃ በድጋሚ አዲስ አበባና ከከተማው ወጣ ብሎ ባሉ
አርሶአደሮች ላይ ተጠቃሚዎችን ለማፍራት ያስጀመርኩት፡፡
ስራውን በእቅድና ቅንጅት ሳስጀምር ስልጣን ፈልጌ ሳይሆን በኃላፊነት
የሚሰሩ ተቋማትን ኃላፊነትን ለመስጠት ነው፡፡ በቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት እና
ቢሮ ደረጃ አሰራሬን የሚቃወም ወረራ አካሄደብኝ፡፡ ይህ ግለሰብ ና ውጣ
አይነት ግልምጫ በተደጋጋሚ ያሳየኝ ሲሆን፡፡ የጠራኋቸው ተቋማት
ችግሮችን ለመፍታት ሰብስቤያቸው በነበረበት ወቅት የተሰባሰብንበት ቦታ
በመምጣት ለመሳተፍ ፈልጎ ወንበር ስቦ ከተቀመጠ በኋላ ስብሰባውን እረግጦ
መውጣት ብቻ ሳይሆን ቢሮ ውስጥ ከቆየ በኋላ ሲወጣና ሲገባ ሲገላምጠን
የነበረው፡፡ ይህ በጎ ስራ እንዳልተዋጠለት የተረዳሁት በከተማ ደረጃ ሄዶ
መወንጀሉ ነው፡፡ በዚህ የምቀኝነት ስራው ለድጋፍና ክትትል በምንወጣበት
ጊዜ አቋሙን ተቋሞቹም እራሳቸው ጠንቅቀው የሚያቁት ሰው ነው፡፡
ለማሳያነት አብሬው ለድጋፍና ክትትል ተቋሞቹ ላይ በሄድኩበት ወቅት
በተደጋጋሚ ባለስልጣን ለመምሰል የሚያደርገውን አክት እኔ ያየሁበት ብቻ
ሳይሆን ተቋሞቹም ጭምር የሚያረጋግጡት ነው፡፡
ለስብሰባ የጠራኋቸውን ይሁን ለድጋፍና ክትትል የሄድኩባቸውን ተቋማት
አከብራቸዋለሁ እግዚአብሔር ይመስገን እነሱም ያከብሩኛል፡፡ የምሰራውም
በእውቀት እንጂ በንቀት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም በሚባል መልኩ
ምሁራን ስለሆኑ፡፡ ምንአለ በጽ/ቤት ደረጃ ብቻ ሳይሆን የባለሙያዋችን የስራ
አፈጻጸምና ስነምግባር እነዚሁ ሕጋዊ ስራቸው የገዘፈና ብቁ የሆኑ ተቋማት
ቢመዝኑና ውጤት ቢሰጡ ጥሩ ነበር፡፡ ለምሰራው የድጋፍ ስራ ብር
ካላመጣችሁ አልሰራም አላልኩም፡፡ ይህ የሚያንጓጥጥ አካል እስኪ ይናገር፡፡
እስኪ የደንበኞች የእርካታ መለኪያ የሰራውን ያሳይ፡፡ በዛሬው እለት
የገጠመኝ እና ውጣልኝ በሚል በግልምጫ ሀሳቡን ሲገልጽ ኃላፊ ቢሮ
የነበርኩኝ ሲሆን፡፡ በወቅቱ ስላናደደኝ ስህተቱን ልነግረው የወጣሁት፡፡ እኔ
ሁልጊዜ ተማሪ መሆኔን ነው የማውቀው፡፡ ይህ የሚኮፈስ አካል ኮንፒውተር
ላይ መጻፍ የማይችል ብቻ ሳይሆን እስካሁን የመጣበት መንገድ የኔን እቅድ
በመውሰድ እሰራለሁ ሲልና የሰራሁትን ፕሮፖዛል ምንም ሳያሻሽል ወስዶ
ከመንግስት ክፍያ የተቀበለበት፡፡ እንደዚህ ያለሰው ነው ተቋምን ለመደገፍ
የሚሄደው፡፡ ተቋማቱ ትክክለኛ ቅጥር እንዳያደርጉ የከሰመን ተቋም
የአሰልጣኞችን ፕሮፋይል እያወጣ ለተቋሞች ሲሸጥ ሀያባይ ያጣው፡፡
ባጠቃላይ ኃላፊ ተብለው የሚመደቡ አካላት እንደዚህ critical thinking በሆነ
እሳቤ አጥፊውን የሚገስጽ አይደሉም፡፡
ንትርኩ የጀመረው በፊት ሲሆን በራሴ ፍላጎት ከክፍለ ከተማው ከመቀየሬ
በፊት ዛሬ የጨረስኩትን ክሊራንስ ለመውሰድ በመጣሁበት ወቅት ውጣ ያለኝ
ሰውዬ በሰበሰብኩት ስብሰባ ላይ አባል ለመሆን ፈልጎ የሰበሰብኩት ስብሰባ ላይ
ከተቀመጠ በኋላ ተቋማቱን የጠራኋቸው በስሜ ስለሆነ የጻፍኩትን የጥሪ
ደብዳቤ በስሜ መሆኑን አይቶ በመበሳጨት ወዲያውኑ ተነስቶ ሲወጣ ያሳየኝ
ፊት በጣም መጥፎ ቢሆንም በወቅቱ ስብሰባው እንደይደናቀፍ የማቀው ምቀኛ
ሰው በመሆኑ ምንም አላልኩትም ነበር፡፡ ነገርግን እኔ የመረጥኳቸው ተቋማት
በአቅምና ብቃት መስራት የሚችሉ የማሰልጠኛ ተቋማትና የግል
አማካሪዎችና የመንግስት አካላት ስለሆኑ ነው ስራውን ያስጀመርኩት፡፡ ይህ
ያለአቅሙ የገባ የስራ ባልደረባ እንደዚህ አይነት ትልቅ ሀገራዊ ስራ
የመስራት አሻራ የሌለው ሲሆን በማደናቀፍና እኔ የሰራሁትን ስራ ነገርግን
ብር ያልጠየቅኩበትን ስራ ወስዶ ከመንግስት ብር ተቀብሏበታል፡፡ የሚጠይቅ
አካል ካለ መረጃውን በሰነድ መስጠት ይቻላል፡፡ ይህም ለማሳያነት ተግባራዊ
እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑበት ለአካባቢው ሕዝብ ስለሌለ በሚል የሕዝብ
ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ በአዲሱ ገበያ አካባቢ በግብረሰናይ ድርጅት
የተገነባው የበላይ ዘለቀ ት/ቤት ነው፡፡
ይህው አሁንም የጀመርኩት ስራ አወዳዳሪዎች የሚሰጡት ድጋፍ ሀገራዊ
ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ነበር በመረጡትኩት ቅንጅታዊ አሰራር ከተቋሞቹ
ጋራ ለመስራት ያቀድኩትና ወደውሳኔ የደረስኩት ፡፡
በቢሯችን በተደጋጋሚ ከኦ አይሲኢ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም
(Opportunity Industrilization Center Ethiopia (OICE TVET institute)
መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (መያድ) በየአመቱ ከለጋሾች የሚደረግለት
የእርዳታ ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው የተቀነሱ ሰራተኞች እየመጡ አቤቱታ
ሲያቀርቡ፣ ሲያለቅሱ ከቅነሳው የተረፉትም የደመወዝ እድገት ሳይሆን ቅናሽ
በማድረግ በፍቃደኝነት እየሰሩ እያየሁ ዝም አልልም፡፡ እኔም እንደነሱ
በትርፍ ሰአቴ ለምሰራው ስራ ክፍያ ሳልጠይቅ የሀብት ማሰባሰብ ስራን
ለመስራትና የተቀነሱትን ሰራተኞች ለማስመለስና ክፍያቸውም እንዲስተካከል
የወሰንኩት፡፡ ከማንም ተቋም ለምሰራው ስራ ብር ሳልጠይቅ እጄ በስራ ጫና
እስኪፈነዳ እና እግሬም ከመቀመጥ ብዛት እየደነዘዘ ነው በትጋት እየሰራሁ
ያለሁት፡፡ ከላይ እንዳስቀመጥኩት ከስራ ተባረው ለሚያለቅሱ ሰዎች
በመቆርቆር ስለሰራሁ ነው ስብሰባ መጥራት ፍቃድ ስለሌለህ ለምን ስብሰባ
ጠራህ የሚሉት፡፡ የትምህርትና ስልጠና ስራን የሚሰራን ሰራተኛ ከፖለቲካ
ጋር ማገናኘት ስህተትና ወንጀልም ጭምር ነው፡፡ ሕግን አለማወቅም
ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በማሰብ የሚሰራን ሰው
ሞራል መስበር የገፉበት፡፡
በግልጽ በሚታይ መልኩ ለወደቀው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰራር ተጠያቂ
ስላልሆኑ ነው በኃላፊነት ለመቀጠል የሚፍጨረጨሩት፡፡ የሚሰራን ሰው
ማዋረድና የሚገባውን ክብር አለመስጠት ወንጀል መሆኑን አያውቁም፡፡ ሕግን
አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ አዲስ የተመረጡት ኃላፊ ተብዬዋች
ከዚህ በፊት ስራ ሲያበላሹ የነበሩ ሰዎችን እንዴት ሲያበላሹ እንደነበር
ተነግሯቸው ተነግሯቸው የገባቸው ቢመስሉም አሁንም እዛው ድንቁርናቸው
ላይ ናቸው፡፡
እምላቸው ለሀገሬ በደንብ ስለሰራሁ ምስጋናው ቀርቶብኝ በቅጡ በኮንነኝ
ነው፡፡ ልክ ሌባ እናት ልጇን እንደማታምነው ነው ሁሉ ለምን ትሰራለህ
የሚሉት፡፡ ኃላፊ ተብየዎች ተማርን አወቅን የሚሉ ከሆነ ለወገናቸውና
ለሀገራቸው ሕዝብ ችግር ተቋርቁረው ለሚሰራው ስራ ከበደኝ መስራት
አልችልም ሳይሉ በጽኑ አቋም በመስራት ችግር የሚፈታውን ሲያከብሩ ብቻ
ነው፡፡ ስራን መስራት መቻል በተግባር ነው እንጂ በየቦታው በተለቃቀመ
የትምህርት ማስረጃ አይደለም፡፡ ያኽውም ኃላፊ ተብዬዋች ተማርን የሚሉት
ከሚሰሩት ስራ ጋር በምንም አጋጣሚ የማይገናኝ ትምህርት ተምረው ስራን
እያበላሹ ያሉ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም በብቸኝነት ፐብሊክ ሰርቪስ በሚል
የሚሰጣቸው ቁንጽል ትምህርት በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ተብለው ለሚያጠፉት
ጊዜ ተጠያቂ ያልሆነ ዩኒቨርሲቲውም ሲቀበል ምንያህል ከስራቸው ጋር
እንደሚገናኝ ሳይጠይቅ በመቀበሉ ለከሸፈው ፕሮግራም ተጠያቂ አለመሆኑ
ነው ችግሩ እንዲቀጥል የሆነው፡፡ እነዚህ አካላት ተማርን ብለው ሳይሰሩ
ለተከፈላቸው ብር ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው ለመስራት የገቡትን ቃለመሃላ
በመዘንጋት ለራሳቸው ጥቅም ሲስገበገቡና ስራን ሲያበላሹ በመሆኖራቸው
ነው፡፡
ወቅታዊ የሀገር ጉዳይን አስመልክቶ "ሙያተኞች ከስራቸው ተፈናቃይ
ሆነዋል የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ ሙያተኞች ጠፋ፡፡ ሁሉም የመንግስትም፣
መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግልም ሰራተኞች ፖለቲከኞች ሆኑ በሚል
(ታዋቂዋ ልበ ብርሀኗ የትነበርሽ)" ያቀረበችው፡፡ በመጨረሻም ፖለቲካውን
እስኪ ለፖለቲከኞች እንተው አለች"፡፡ ለኔ የእርሷ አባባል ትክክለኛ ነው ባይ
ነኝ፡፡ ስለሆነም ምስጋና ለታላቋ ልበ ብርሀኗ ምኁር የትነበርሽ፡፡ ባለፈው
አመትም በዚህ ጊዜ እኔም ፖለቲካ በቃ ወደስራ ብዬ ስራየጀመርኩት፡፡
ሀገራችን ስግብግብ በዝቶ እንዲህ አሳዛኝ በሆነ መልኩ ስለተገለጸች ስራችንን
መስራት ነው እንጂ ከስራችን መፈናቀል የለብንም ባይ ነኝ፡፡ ስራ ስንሰራ
የምታከላክሉ የመንግስት አካላት ሁሉ ከድርጊቱ ካልተቆጠባችሁ እናንተ
ከስራችሁ ተፈናቅላችሁ የምታላምጡት ስራችሁን ሳይሆን ፖለቲካውን ስለሆነ
ለምትተራመሰው ሀገራችን ተጠያቂ ናችሁ፡፡ ባልደረባችሁም እንዳይሰራ
በማድረግ ከስራ ስላፈናቀላችሁ በሕግም ተጠያቂ ናችሁ፡፡
ሳይሰሩ ውጤታማ ነኝ ማለትና ሳይሰሩ የስራ አፈጻጸም ውጤትን ለራስ ቆልሎ
በመስጠት ማንንም ማታለል አይቻልም፡፡ የቅርብ ኃላፊ በምታየኝ
የተንሸዋረረ መነጽር ልክ ነው የስራ ውጤቴ አፈጻጸም የሰጠችኝ፡፡
ነገርግን ከሰራኋቸው ተጨባጭ ስራውች በቅድሙያ በተጨባጭ
የሚያስደስተኝና መረጃ ማቅረብ የምችለው ከለጋሾች አካላት (ከወርልድ
ቪዢን ኮርያ) አውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት B+1 (basement plass one) በ
November 2015 ተጠናቆ የተመረቀው የሽሮ ሜዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ
ተቋም ነው፡፡ ሊዘጋ የነበረ የአውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት የህንጻ ግንባታ
የተመደበ በጀት የብር ድጋፍ ማስገኘቴ ነው፡፡ በወቅቱ ባለመሰራቱ ብሩ
ሊመለስ ሁለት ወር ብቻ ሲቀረው ነበር ለስራ የታጨሁት፡፡ ስራውን ስጀምር
ከወርልድ ቪዚን የመጡት ኃላፊ መግለጫ ከሰጡ በኋላ ስጋታቸውን
ሲያስቀምጡ መስራት ያላስቻላቸው የተወሳሰበው ቢሮክራሲ ውሳኔ ስለሆነ
እስካሁን ያልተሰራ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይሰራል የሚል እምነት
እንደሌላቸው የደመደሙት፡፡ በመሆኑም ይህ ስራ ካልተሳካ ይዘዋት
የመጡትን ኢንጂነር እንደሚያሰናብቱ ማብራሪያ የሰጡት፡፡ ኢንጂነሯን
እንደሚያባርሩ ሲገልጹ የተቀጠረችው ይህንኑ ፕሮጀክት ሰርታ ታጠናቅቃለች
በሚል ነበር ካሉ በኋላ፡፡ የተመደበው የግንባታ ባጀት የሚዘጋበት ጊዜ ደርሶ
ወደሌላ ክፍለ ከተማ ለማዘዋወር ወርልድ ቪዢን እያቀደ ባለበት ጊዜ ነው፡፡
በመሆኑም ለስራው የታጨሁትና እንዳይዘዋወርና ትባረራለች የተባለችውን
ኢንጂነር እንዳትባረር ያደረኩት፡፡ በተቃራኒው ይህ ታላቅ ስራ እንዲጠናቀቅ
አብረውን የደከሙ ኢንጂነሮች እንዲባረሩ መደረጋቸው ነበር ደስ ያላለኝ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ከ9 ያላነሱ ኢንጂነሮች የያዝነውን ስራ ካጠናቀቅን በኋላ
እንዲባረሩ ያደረጉት፡፡ በኋላ ላይ በፍርድ ቤት ተከራክረው እንዲመለሱ
ተፈርዶላቸው ስራቸውን የጀመሩት፡፡ ይህ ከስራ ያባረራቸው ኃላፊ
የሚሰራውን ስራ ያለቢሮክራሲ መስራት እንዳለብን ይህም የሚሆነው
የኢንጂነሮቹንም ጥቅም ማስከበር ይኖርብናል በሚል ሀሳቡ ሳቀርብለት ጥቅም
የምትለውን ቃል በክራይ ሰብሳቢነት የፈረጃት፡፡ ትክክል አለመሆኑን ነው
የነገርኩት ይህውም በሌላው አለምም ሰራተኛን ከ8 ሰአት በላይ ማሰራት
አትችልም፡፡ በሰሩት ልክ ሊከፈላቸው የሚገባውን ክፍያ በዋናነት አንተ
እራስህ በመቀጠል ስራውን የሚያ ሰራው አካል ለትርፍ ሰአት መክፈል
ያለባችሁ ያልኩት፡፡ ስራው ባጭር ጊዜ መጠናቀቅ ስላለበት በእኛ ቢሮክራሲ
ቢንጓተት እና ብሩ ተመላሽ ቦሆንና ቀልጣፋ ክፍለ ከተሞች ሚወስዱት ከሆነ
ተያቂ የምንሆ ነው ኃላፊነት ላይ የተቀመጥን አካል ነን ብዮ ያሳሰብኩት፡፡
ሰውየው የሚሰማ አይደለም የሳይት ጉብኝት ስራ ጋር በተያያዘ መኪና
ከመመደብ ጀምሮ እስከ ባለሙያ አበል በሚፈቅድልን መልኩ እንከፍላለን
የሚለው አላግባባንም ነበር፡፡ ከኃላፊው ጋር ባልግባባም በሌላ ቀን ምክትሉ
ጋር ገብቼ በጥሞና ካዳመጠኝ በኋላ ደብዳቤ ለመጻፍ ፍቃደኛ በመሆን
እነዚሁ ኢንጅነሮች ከሶይል ቴስት ጀምሮ እስከ አርክቴክቱ ስራ በአጭር ጊዜ
ተጠናቆ ወደስራ የተገባው፡፡
በመሆኑም ስራውን ሳስጀምር ያጋጠመኝ ተግዳሮት የአፈር ምርመራ 15 ቀን
የሚወስድ የነበረ ሲሆን አርክቴክቱም እንደዚሁ እረዥም ጊዜ ስለሚወስድና
የክፍለ ከተማ ኢንጂነሮች በአመቱ እቅዳቸው በስራ ተወጥረው ስለነበር ነው፡፡
በመሆኑም ከቢሮክራቶች ጋር አንገት ላንገት ተናንቄ መጨረሻ ላይ
የተመደበውን በጀት ያስለቀቅኩትና አውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት እንዲገነባ
ብቻ ሳይይሆን ያደረኩት የውስጥ ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው ጭምር ነው፡፡
ሲጀመር ለሕንጻው ተይዞ የነበረ በጀት 6ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን ተጨማሪ
ስራና የውስት ቁሳቁስ ሲሟላ ከ 28 ሚሊዮን ብር በገቢ ደረጃ እንዲገኝ
ያደረኩት፡፡
ለምን ስራችንን በእውቀት አንስራም? ሲሏቸው ፍቃድ የላችሁም ይላሉ፡፡
አሁንስ መረረኝ የት ሀገር ሄጄ ልስራ? ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ኃላፊነት
ላይ የተቀመጡ ሰዎች መስራት ስለማይችሉ ለምን ትሰራለህ ይላሉ፡፡ መማር
ማሰተማር ላይ ያልሰሩ እንዴት ባለስልጣን እንደሚያደርጓቸው ግልጽ
አይደለም፡፡ በመሆኑም እነዚህ ኃላፊዎች እያደናገሩ ስለሆነ ከዚህ እኩይ
ተግባራቸው መቆጠብ አለባቸው፡፡ እየተሰራ ያለው አሰራር በመመሪያ
የተደገፈ ሳይሆን እየተሰራበት ያለው አግባብ በዘር፣ በአካባቢ፣ በጓደኝነት፣
በፖለቲካ ወገንተኝነት አሰራር በመሆኑ ነው፡፡ እየሰሩ ያሉት በተቀመጠው
ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሕግጋት መሰረት ስለማይሰሩ ብዙውን የወጣ ትክክለኛ
ሕግ የሚሽሩት፡፡ በከተማ ደረጃ ያሉ በየጊዜው የፈተና ስርቆት የሚከሰተው
በዚህ መልኩ የተዛባ አመዳደብ ስላለ ነው፡፡
በግልጽ ለሚራበው፣ ከስራ ለሚባረረው፣ ለሚሰደደውና ለሚሞተው ወገናቸው
በኃላፊነት የሚጨነቁ አመራሮች አለመኖራቸው አሳሳቢ በመሆኑ ነው፡፡
እውነተኛ አመራር የሚሰራ ሰውን ያበረታታል እንጂ እንደመሰናክል
አያደናቅፍም፡፡ ስለቴክኒክና ሙያ ምንም እውቀት የሌላቸውና በተመሳሳይ
ስራ occupation ያላስተማሩ (መማር ማስተማርን ምንም የማያውቁ አካላት)
ናቸው ስልጣን ላይ የተቀመጡት:: አሁንም በእነዚሁ ካላት ጥቆማ ወደስልጣን
እንዲመጡ ያደረጓቸው አካላት በመሆናቸው ነው የአሰራር ብልሽት
እንዲቀጥል ያደረጉት፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት ሲያበላሹ የነበሩ ሳይሰሩ
ውጤት አፈጻጸማቸውን በራሳቸው እጅ ሲሞሉ የኖሩ ናቸው፡፡ እኔ ስልጣን
ለማግኘት ብዮ እንደተማሪ የስራ አፈጻጸም ውጤቴ ዝቅተኛ ነው የተሰጠኝ
በሚል ጨምሩልኝ ወይም አስተካክሉልኝ አልልም፡፡ አሁንም ቦታው ላይ
በኃላፊነት የተቀመጡት በስራ አፈጻጸም እራሳቸውን የላቀ አድርገው የሞሉ
ናቸው ቦታው እንዲሰጣቸው የተደረገው፡፡
በያዝነው አመት የቴክኒክና ሙያ አዲስ ሪፎርም መሰራቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራትና
እውቅና ፍቃድ፣ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን አደረጃጀት በአዲስ
መልክ መሰራቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም መመደብ የፈለኩበትም ቦታ
ስላልተመደብኩኝ ቅሬታዬን ሳስገባ ቅሬታ ሰሚዎቹ መልስ የሰጡኝ ሌሎቹ
በስራ አፈጻጸም አንተን የሚበልጡህ ስላሉ ከተማ መግባት አትችልም
የተባልኩት፡፡ እውን እነዚህ ሀገራዊ ስራን መስራት የማይችሉ አካላት ናቸው
እኔን መአከል ላይ በኃላፊነት ሳይሆን በባለሙያነት ለመመደብ በስራ
አፈጻጸም የሚበልጡኝ? የሚሰራው በትክክለኛ የስራ አፈጻጸም ሳይሆን
በጓደኝነትና ከዚህ በፊት በክራይ ስብሰባ አማካኝነት የጣሱትን ስትራቴጂ
እንዳልጠይቃቸው ነው፡፡ መዳቢና ቅሬታ ሰሚ የሆኑትና ይህ ግለሰብ ወደኛ
እንዳይመጣ ያሉትና ተግባራዊ ያደረጉት፡፡ እኔን በስራ አፈጻጸም ውጤት
የሚበልጡኝ ለጥቅማቸው የሚስገበገቡ ናቸው እንጂ በስራ አይደለም፡፡
በእርግጠኝነት እጄ ላይ ያለው መረጃ በእውቀት ደረጃ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ
ባለሙያዎች ናቸው እኔን በተዛባ የስራ አፈጻጸም ውጤት የሚበልጡኝ፡፡ ክስ
በማሰብሰብ ከተቋሞች በአግባቡ የሚሰሩ ሳይሆን አሸባሪና ብር አምጡ እያሉ
እደጠየቋቸው እውቅና የተሰጣቸው ባለሙያዎች ናቸው እኔን በስራ አፈጻጸም
የሚበልጡኝ፡፡
ለዚህ ማሳያ እንዲሆን በቅርቡ በከተማ ደረጃ ያሉ ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን
ባደረጉት መሰረት የሰጡት ግብረመልስ ባብዛኛው ስህተት የሆነ ግብረመልስ
ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ እነዚህ ከከተማ የመጡ ኢንስፔክሽን አድራጊ አካል
ብቻቸውን ተቋማትን ኢንስፔክት ሲያደርጉ በሰጡት ግብረመልስና ተቋሞቹ
ባቀረቡት ቅሬታ በግልጽ ስህተት እመንዳለባቸው ታይቷል፡፡ ቴክኒክና ሙያ
ማሰልጠኛ ተቋም ለመክፈት እውቅና ፍቃድ ሲሰጥ አካልጉዳተኞችን ያማከለ
እንዲሆን ስታንዳርዱ ከፍተኛ ነጥብ የሚያሰጠው compauond ከሆነ ነው
ይላል፡፡ ነገርግን እነዚህን ተቋማትን ኢንስፔክት ሲያደርጉ ዝቅተኛ ውጤት
የተሰጡት ኢንስፔክተሮቹ ብር እንዲከፍሎቸው ጠይቀው እንቢተኝነታቸውን
ስላሳዮቸው ነው፡፡ እነዚሁ ከከተማ ለኢንስፔክሽን የመጡ አካላት እራሳቸው
ለኮሌጆች እውቅና ፈቃድ ሲሰጡ 7፣8፣9 ወይም 10 ኛ ፎቅ ላይ ፈቃድ
እንዲያገኙ ሲሰጡ የሚገመግማቸው አካል ስለሌለ ነው፡፡ በዚህ ባልተገባ
ግምገማዎች ነው ብቁ የሆኑ ተቋማት ከገበያ እንዲወጡ ተደርገው
እስከወዲያኛው የተዘጉት፡፡ በመሆኑም መስራት የሚችሉ ተቋማት ለስደትና
ለስራ አጥነት የተዳረጉት፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ምዘናው ትክክል ባልሆነ ፍረጃ
እንደፈለጉት የሚጎትቱት በከለር (ቀይ፣ ፈዛዛ ቀይ፣ ቢጫ እና አረንጓዴ)
የታጀበው፡፡ ይህ አሰራር በማስረጃ በተደገፈ መልኩ ስህተት እንዳለው
በተደጋጋሚ ስናገር ቆይቼለሁ፡፡ ሲሰጥ የነበረው በከለር ሲሆን ይህውም በስራ
ሂደቶቹ የሚፈለጉት ተቋማት ብቻ አንጓሎ የሚጥል ሆኖ ነው የሚታየው፡፡
በግልጽ ሊሰራበት የሚገባው ቀጥሎ በማቀርበው መስፈርትና ክራይቴሪያ
በማውጣት ነው ይህውም የማያሳማ በዚህ መልኩ Accordingly, the criteria and
standards for evaluating TVET institutes have been set down as follows;
1. The capacity of raising enrolment (15%) out of this the institute got 15%
2. Minimizing dropout (15%)---15%
3. Cooperative training (15%)--10%
4. Conducting training by certified professionals (15%)----15%
5. Presenting trainees to center of competency assessment and certification
(CoCAC) for evaluation (25%)---25%
6. Submitting monthly report in due time (10%)---10%
7. Taking part in bezzras (income generating activity) (5%)-----0
Invention and Innovation____________ (additional criteria) 100% ---0%
etc……… እና እያንዳንዷ መስፈርት መጀመሪያ በቁጥር ተቀምጦ
በኋላላይ ወደፐርሰንት ተቀይሮ ነው መቅረብ ያለበት በመሆኑም
ውጤታቸው ሲገለጽ ፡- We have attached here with the result obtained by
conducting the evaluation carried out on the basses of the criteria stated
above. Based on this, the result of ………… TVET institution is now
ranked 1st
, 2nd, or
3rd
from ……….TVET Institutes under …….. Sub City
TVET institutions and the office highly recommend that this extraordinary
(Excellency) work should keep it up or amand your problem and ceased!
ነገርግን ስንቱ ሀቀኛ ተቋም ለምዘና ምቹ ተብለው COC ሳይቀር
ተቋሙ ለምዘና እውቅና የተሰጣቸው የመመዘኛን መስፈርት አሟልተው
ነው የተሰጣቸው ስታንዳርዱ በወረደ አሰራርና ምቀኝነት እንዲዘጉ
ተደረገ፡፡ ሀይ ባይ ይጥፋ?
የኔን ስራዎች በተግባር ማግኘት የሚፈልግ ካለ
http://www.slideshare.net berhanu tadesse uploads ብሎ በማግኘት
እማኝ ስራዎቼን ማየት ይችላል፡፡ የፈለኩት ስልጣን ሳይሆን በባለሙያነት
መአከል ስገባ እነሱ ያበላሹትን ስትራቴጂ ለማስተካከል ነበር የፈለኩት፡፡
በባለሙያነት ለመመደብ ባቀረብኩት ቅሬታ መሰረት ይበልጡሃል የተባሉት
ባለሙያዎች ከፈለጉ ከኔ ጋር በኔት ወርልድ ሚዛን ላይ ብንቀመጥ ምንም
ስራ እደሌላቸው ማሳየት እችላለሁ፡፡ ይህንን አድሎዊ የስራ ውጤት አፈጻጸም
ከበፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሲሰሩ የነበሩ ኃላፊ ተብዬዋች አሰራራቸው
ትከክልኛ አለመሆኑን ሁልጊዜ እነግራቸዋለሁ፡፡ በመሆኑም እነዚሁ አድሎ
ፈጻሚዎች ጊዜያቸውን ጠብቀው እየከሰሙ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው፡፡
እውቀቱ ሳይኖራቸው ብር ካላመጣችሁ በሚል የሚዘጉ የግል ማሰልጠኛ
ተቋሞች ብዙ ናቸው፡፡ እኔ በእውነተኛና በእውቀት ላይ ተመስርተው ለሚሰሩ
የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ምቀኛ አልሆንም ወይም አይደለሁም፡፡ በዚህ ዙሪያ
በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ሰፊ ንባብ ይዤ እወጣለሁ፡፡
ይኽቺ ሀገር መቼ ነው እውነተኛ ስራ ወዳድ ትውልድ የምታፈራውና
የደከመውንና ዜጎችን ከስራ ጋር በማገናኘት ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥርውን
የምትደግፈውና ያለመድሎ የምታደንቀው?
ከሰው ምንም አይነት ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት ስላልተቻለ እግዚያብሔር
የኔንና መሰሎቼን በሁሉም ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ይዚህችን ምስኪን
ሀገር ይጎብኘን! አሜን!
Yalem Fikir ሁሉንም አነበብሁት በብሶት እና በማዘን ከልብ የተጻፈ መሆኑን
ከዓረፍተ ነገሮች መረዳት ይቻላል። አሁን ላይ በየመስሪያ ቤቱ ብዙ
ጉድኝቶች ተፈጥረዋል።
፩/ #የአለቃና_እወደድ_ባይ( ቅቤ ጠባሾች) ጉድኝት።
ይህ በስራ እና በብቃታቸው የማይተማመኑ ሰራተኞች ለአለቃቸው አቤት
አቤት በማለት የአለቃቸውን ችሮታ የሚለማመጡ ጆሮ ጠቢዎች እና
አሸርጋጆችን ያካትታል። ዋና ስራቸው የሚሰሩትን ሰዎች ስህተት ብቻ
እየተከታተሉ ለአለቃ በማቀበል ለመስሪያ ቤቱ ምንም እሴት የማይጨምሩ
እንቅፋት የሆኑ ሸክሞች ናቸው።
፪/ #የዘር_ወይም_የአካባቢያዊ_ጉድኝት
ይሄኛው መስሪያ ቤቱ ውስጥ ለሚመጡ ጥቅማጥቅሞችም ሆነ የስራ እድገት
በማታውቀው እና ባልጠበቅኸው መንገድ እጁን ይዘህ ስልጠና የሰጠኸውና
መስሪያ ቤቱን ጠንቅቆ ያላወቀ ሰራተኛ ሃላፊህ ሆኖ ከች የሚልበት የዘር
ተዋረድ የሚነግስበት እና ዘላለምህን ታዛቢ ሆነህ የምትኖርበትን ያካትታል።
ጎረቢት ሆነው ሳይተዋወቁ የኖሩ ሰዎች በስራ ላይ እጅና ጓንት ሆነው
ሌሎችን በማውረድ እራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ሲታትሩ ታገኛቸዋለህ።
ጥረትህን ሳላደንቅ አላልፍም። የማይሰራ ሰው ሴረኛ ነውና
እንደምትጠነቀቃቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ሀገራችን ውስጥ ላለው ከፍተኛ
የስራ አጥ መብዛት ትልቁ ተጠያቂ #የትምህርት_ተቋማት በተለይ የቴክኒካል
ክፍሉ እና #መንግስት ናቸው። ትምህርታችን ፈጠራን እና የተግባር
ልምምድን ያማከለ ሳይሆን የወረቀት ብቻ መሆኑ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።
ለዚህ ደግሞ ግብዓቶቹ በችሎታ ሳይሆን በችሮታ የተቋማት ሀላፊዎች
መብዛታቸው ለሚገዙ የላብራቶሪ እቃዎች ባለመፈረም ለሚቀጠሩ መምህራን
ቁጥርና ችሎታ ማነቆ ሆነው እንደካሮት ቁልቁል አንደርድረው አሾቁትና
አረፉ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ እየታገልህ ስለሆነ በርታ ማለት እዎዳለሁ።
የጥቂቶች የሀሳብ ልዕልና የብዙዎችን የወደፊት እጣ ፈንታ ይወስናል ያንተም
የግል ጥረት ለብዙዎች ተስፋ ይሆናል እንዳልከው እግዚአብሔር ካንተ ጋር
ይሁን።
Yalem Fikir ለመልካም አስተያየትህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ! አሁን
ሰሞኑን የሪፎርም ስብሰባ ሰኔ ውስጥ 2011 ዓ.ም ኢሊሊ ሆቴል ላይ አ.አ.
መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ያአሁኑ ባለስልጣን የሙያብቃትንና
ትምህርት ጥራን ተከትሎ ሪፖርት ሲያቀርብ የወረደ ነበር የሆነብኝ፡፡ በዚህ
የተነሳ ትምህርት ጥራት ያቀረበችውንና በሆላ ላይ የሲኦሲ (CoC) ምዘና
ያቀረቡትን ሪፖርት ፐሮፌሽናል በሆነ መልኩ ያቀረቡ በመሆኑ አመስግኜ
የቴክኒክና ሙያን በግልጽ ተቃውሜ ነበር አስተያየት ላይ የቀረብኩት፡፡
ምክንያቱም ያመሰገንናቸው ሁለቱም ያቀረቡት በስታንዳርዱ መሰረት ሲሆን
ይህንን አሰራራቸውን ሙሉ አዳራሹ ተሰብሳቢዎች ነበር የታዘቡት፡፡ መደነቅ
ያለባቸውን ያደነቅነውና መታየት ያለባቸውን አስረግጬ ያቀረብኩት፡፡
ስብሰባው ላይ በግል ለተቃውሞ ያነሳሳኝ የቴክኒክና ሙያ ተወካዩ የአሁኑ
ተሿሚ ሪፖርት ሲያቀርብ ሜቴክ የገነባቸውን ተቋማትን ሲናገር
ያበላሻቸውንና የተዘረፈውን የዘለላቸው፡፡ ሪፖርቱ ሲቀርብ ስታንዳርድም ላይ
ምንም ሳይናገር ነበር የዘለለው፡፡ አንድም ከቁጥር ጋር የተገናኘ ሪፖርት
ሳያቀርብ አለፈ፡፡ በእርግጥ ሁሉም የግንባታ ጫራታዋች ወጥቶባቸው በግልጽ
ጨረታ የግል ተቋራጮች ተወዳድረውበት የተሰራ ቢሆን አያሳማውም ነበር፡፡
ነገርግን ሁሉንም ግንባታዎች በራሱ ነበር ሲሰራ የነበረው፡፡ ሜቴክንም
የማቀው ግን መገንባቱ መልካም ቢሆንም ያጠፋቸውና መስራት የሌለበት
ደግሞ ብዙ በመሆኑ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እንደሚከተለው አቀርባለሁ
በስፔስፌኬሽኑ መሰረት የክትትልና ግምገማ ሪፖርት የቀረበ ካለመኖሩ
ጀምሮ፣ ስቦርቅ ያደኩበትን የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኳስ ሜዳ ባልጠፋ
ቦታ የስፖርት ማዘውተሪያ ውስጥ ግንባታ ማካሄዱ ብቻ ሳይሆን የግል
ድርጅቶች ሳይወዳደሩ ከሁለት እስከ ሶስት መቶ ሺ ብር የማይፈጅ የመግቢያ
በር ግንባታ ከሶስት ሚሊዮን ብር ክፍያ የሁሉንም ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች
ግንባታ በማካሄድ ዘረፋ መካሄዱ ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡
እኔው እራሴ ባስተዋወቅኩላቸው መሰረት አ.አ መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ
የእውቅና ፍቃድ ባለስልጣን መካድ የማይችሉትና በመረጃ ላጋልጣቸው
የምወደው የስራ መስኩ ከፍተኛ የሰው ኃይል ይፈልጋል ተብሎ ስልጠና
የተጀመረባቸው መስኮች housholed service, domestic help and care
giving ላይ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ተቋማቱን በእውቅና ፈቃድ ወቅትም ይሁን
ፍቃድ ተሰጥቷቸው ከጀመሩም በኃላ እየተፈጠረ ያለውን ችግር በስልጠና
ሊፈታ ይቅርና እራሱ በቴክኔክና ሙያ ሕጎችና አሰራር ላይ ችግር እየፈጠረ
ነው፡፡ እየተሰራበት ያለው አግባብም ትክክል አለመሆኑን በሰኔው ስብሰባ ላይ
አቅርቤያሉ፡፡ ይህውም CoC የሙያ ደረጃ የወጣላቸውን የምዘና ቱል
ባለማውጣቱ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እስካሁን ባለመፈተናቸው መጉላላታቸው፡፡
ነገርግን አሰራሩ በሀገር አቀፍ በስትራቴጂው እንዲሁም በአለም ዓቀፍ ደረጃ
ፍቃድ የተሰጣቸውን TVETs Declaration መጣስ ነው (የሰውልጅ የመማር
መብት)፡፡ ይህውም CoC ኃላፊዎች በሰርኩላር ደብዳቤ ሲበትኑ ከስምንተኛ
ከፍል በታች መሰልጠን አይችሉም ተብሎ የወጣው ሕግን የጣሱት፡፡
የጠቀስኳቸው የስልጠና መስኮች housholed service and domestic help
የማቃቸው የተማርኳቸውና ሆም ኢኮኖሚክስና / home economics and
በኋላላይ hotel service ሲባል ሰልጥኜ ያስተማረኩት ትምህርት ብቻ ሳይሆን
አሁንም አብረውኝ የተማሩት በኮሌጅ ደረጃ የሚያስተምሩት ከዚህ በፊት
አብረውኝ የተማሩት ጓደኞቼ ናቸው፡፡ በመሆኑም አዲስ የውጭ ሀገር የስራ
ስምሪት የወሰዱ ተቋማትን ለመመዘን ከመሄዳችን በፊት ብዥታችንን
በጠረጼዛ ዙሬያ መቅረፍ ነበረብን፡፡ ሁለቱም የስልጠና መስኮች የማሰልጠኛ
ሞጁሎች ዝግጅት የጎላ ልዩነት ባይኖራቸውም ሞጁሎቹ ግልጸኝነት
እነዲኖራቸው የማጣቀሻ መጽሀፍ የጎደላቸውን ስታንዳርዶች በማካተት
በመስራት ላይ ነኝ፡፡
በdomestic help የሚሰጠው የስልጠና መስክ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው
ለሀገር ውስጥ የቤት ውስጥ ሰራተኞች ማሰልጠን ማለት ነው፡፡ የከተማው
ኢንስፔክተሮች ስህተታቸውን ለማረጋገጫ በበተኑት ግብረመልሶች ማረጋገጥ
የሚቻል መሆኑን የእውቀት ክፍተት መኖሩን መረዳት ይቻላል፡፡ ባለማወቅ
በከተማ ደረጃ የተቋቋመው እና ተግባራዊ ያደረገው የኢንስፔክሽን ቡድን
የሰጡት ግብረመልሶች እንዲህ ባለማወቅ የተሰጡ በመሆናቸው ያሳፍራሉ፡፡
በራሳቸው ስህተት የተባረሩም ተቋማት እንዳሉ በየክፍለከተማው መረጃው
አለ፡፡ በመሆኑም ይህ ስልጠና የሚሰጠው ለውጭ ሀገር ተጓዦች ብቻ ሳይሆን
ለሀግር ውስጥም የሰለጠነ የቤት ሰራተኛ ለማፍራት ነው፡፡ የሀገር ሰው
የሰለጠና የቤት ሰራተኛ አይወድለትም ያለው ማነው? ወይስ ወገኖቻችን
ሄደው ለሚሰቃዩበት የውጭ ሀገር ተጎዥን ለማብዛት ብቻ ነው መሰራት
ያለበት? አሰራሩ ውጡልኝ ብቻን የሚያበረታታ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የእስካሁኑ ማነቆ የሆነው የዚሁ ዘርፍ አሰራር
ለኃላፊዎች ከሰው አዘዋዋሪዎች የሚሰጥ ድጎማ ከፍተኛ ስለሆነ ነው አሰራሩ
እንዲበላሽ ተደረገው፡፡ በተግባር እንደታየው አሰራሩ ስትራቴጂውን መጣሱን
የሚያመለክተው ከስምንተኛ ክፍል በታች ቴክኒክና ሙያ እንዳይሰለጥኑ
መከልከላችን የሰልጣኝ ሰበአዊ መብትን መጣስ ነው፡፡ በስህተት የተሰሩ
መሻሻል ያለባቸውን እጅግ በጣም በርካታ የአሰራር ማነቆ ሳይፈታ
ለክትትልና ግምገማ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ላይ መላካችን ስህተት
ነው፡፡ ተቀይሬ እየሰራሁበት ባለው ክፍለ ከተማ ከነበርኩበት ክፍለከተማ ጋር
ተደምሮ ክፍተቱን ስር የሰደደ ስለሚያደርገው አሁን የሚካሄደው ድጋፍና
ክትትል ወደፍረጃ ከመግባታችን በፊት ችግሮቹን ለመፍታት በጠረጼዛ ዙሪያ
ቁጭ ብለን በውይይት መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ላይ ለስብሰባ
የጠሩት ኃላፊውችን ብቻ ሲን ምንመክረው ምን እንደሚያሻሽሉ
አይታወቅም፡፡
Aysheshim Tilahun ብሬ፣
የሚሰሩትን አላሰራ ማለት እኮ አዲስ አይደለም። አሁን አንተ disappointed
መሆንህ ለጠቀስከው አይነት ሰው የመጀመርያ ስኬቱ ነው። እውቀት ነክ የሆነ
ነገር ላይ ሰርተህ ብትከብር ደስ ሊለው ሲገባ በአስተሳሰብ ክፍተቱ በመጣ
አግላይ እና አውሬ አመለካከቱ አንተ ተሰፋ ባለመቁረጥ ለውጥ በመምጣት
አሳየው እንጂ ንዴትህን አታሳየው።
I know your capacity. Working on knowledge and technology transfer
and getting a fortune out of it is the antithesis of collecting money
on expense of the desperate. please use those guys as reason to
go forward. Focus on your job. Do those things with people who are
positively energized.
Berhanu Taye Maza • Aysheshim Tilahun thank you my adviser! I
respect and accept your recommendations. Since you gave me constructive advice
now and then, I'll apply it properly. If your advice is correct. But what I would like
to tell you is I never quite if the ting is goes in the wrong direction. I will fight until
the situation become right. Straggling is the real meanings of life but get the better
of (Prevail over) in the hands of Good indeed! I never and ever quite my fight
based one facet and truth event. thanks to God! Good news for us is I published
three reference books for TVET trainees with conceltancy. Brother Ayshe you are
the one who work with me Addis Ababa University and me also publised in
elctronics media hence, we'll publish our books together besed on your progress
after September by the will of God. I started the draft you'll update it as you and
your colleagues want. Respectfully yours!
• Aysheshim Tilahun anytime brother!

 Berhanu Taye Maza አይሽዬ የሚከሰቱትን ነገሮች እንደተራ ነገር ነው
የምቆጥረው። ማስታወሻ ለመያዝ ያክል ነው። አንጂ ለነዚህ በንፋስ ብቻ
የሚጠፉ አቧራዎች አልጨነቅም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በከፋ ለረዥም ጊዜ
ወያኔ በገባሁበት በመግባት ያለምንም መረጃ ከስራ እያባረረኝ የምበላው
አጥቼ ቤተሰቤ ሲበተን አይቻዋለሁ፡፡ ይህ ግፍ በኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም
ንጹሃን ላይ እንዳይቀጥል በማሰብ ነው ሰላማዊትግሌን የቀጠልኩት፡፡
ውጤቶቹም ለሰራተኞች የስራ አፈጻጸም በማዛባት
ኃላፊ መሆን የማይገባቸው ለሰራተኞች የስራ አፈጻጸም የሚሰጡት በስራና
በመመሪያ ሳይሆን ባልተገባ ተግባቦት ብቻ የስራ አፈጻጸም ውጤት ሲያዛቡ
ይስተዋላሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ስራና ሰራተኞች ሲበደሉ ይስተዋላል፡፡ አሁንም
እንደዚህ ከፍተኛ ጥፋት አጥፍተውና ስራን አበላሽተው ለራሳቸው ከፍተኛ
ውጤት ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም ለራሳቸው የሰጡት በአዲሱ ምደባ ላይ
ተጽእኖ እንደሚፈጥርና እነዚሁ ስራ የሚያበላሹ ሰዎች የኃላፊነት ቦታውን
ተመድበው አሁንም ስራ እንዳያበላሹ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡ ይህ ስጋት
በመጨረሻ ላይ እውን ሆኗል፡፡
የሚታይ ስራ መስራት ነው የሚያስፈልገው "አቧራ ሳይሆን አሻራ ለመሆን
የተሰራ ስራ"
አንደ መንፈሳዊ ፈረንሳዊት ኦሮቪል ፍልስፍና ከሆነ በደራሲ ተከስተ ብርሃን
ገ/ኪዳን በማብራራት እንደተፃፈው ክሆነ "ለመሞት ከመኖር ለመኖር መሞት
ይሻላል" ብለዋል፡፡ ያ ያሉት ትልቅ ቁምነገር ያዘለ አነጋገርም ደርሶኛል፡፡
ዕውነት ነው፤ መጀመሪያ እግዚአብሔር ያደለው እንጂ ማንም ሰው ለዘላለም
የማይሞት ሥራ መስራት አይችልም፡፡ ስለዚህ ሰው ወደዚህ ዓለም መጥቶ
ምንም ሳይሰራ ከሚሞት ለዘለዓለም ስሙን የሚያስጠራ ስራ ለመስራት
መታደል ታላቅነት ነው፡፡ ቢሆንም ይኽ አነጋገር በጣም ከበድ ያለና በብዙ
መልኩ ሊተረጎም የሚችል መሆኑን አስተውያለሁ፡፡
በኃላፊነት ተመድቤ ስራቸውን ስከታተል የነበሩት ኢንጂነሮች ስራቸው
ከአጀማመራቸው ሕያው ሊሆንላቸው እንደሚችል መመረቂያ ጽሁፌን ስጽፍ
በጽሁፍ አስቀምጬላቸው ነበር፡፡ እነዚሁ ኢንጂነሮች ሳይንጠራሩ ትልቅ
ቴክኖሎጂ በአንድ ጊዜ ለመፍጠር ሳይሆን የአካባቢያቸውን ሕዝብ የአኗኗር
ደረጃ በማየት ለመስራት የሄዱበት እርቀት እጅግ በጣም ነው ያስደመመኝና
እኔም በትልቅ ኢንዱስትሪ ላይ ከምሰራ መነዚሁ ልጆች መስራት
የመረጥኩት፡፡ በአካቢያቸው የሚኖረው ሲሰራበት የነበረው ከጉድጓድ ውስጥ
አውጥተው ለጤናቸው አስቸጋሪ በሆነ መልኩ የሚሰራን ሸማ ስራን ወደተሻለ
አሰራር ቀይረዋል፡፡ የምርታማነት ሰአታቸውንም አሻሸለውላቸዋል፡፡ በዚህም
ረገድ በርካታ የተሻሉ ማሽኖችን በመስራታቸው ተሸላሚ የሆኑት፡፡ ኤቲኤም
ኢንጂነሪግና ዶቤ ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዲስትሪ እድገታቸው
የሚያስደስት ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ እድገታቸው እኔንም የሚያስደስተኝ ነው
ምክንያቱም የመመረቂያ ጽሁፌን በመቀየር በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ
በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ የመመረቂያ ጽኁፉም ለቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች
በካይዘን ፍልስፍና በማገናኘት እነሱ ከሰሩት ታላቅ የፈጠራ ስራ በተጨማሪ
በኔ እየደከምኩላቸው ያለሁት ስማቸው በመማሪያነት ማጣቀሻ መጽሃፍነት
እንዲውል ማድረግ ነው፡፡ ማለትም አቧራ ሳይሆኑ አሻራ እንዲሆኑ በመስራት
ላይ ነኝ፡፡ በሁሉም የመማሪያ ሞጁሎች ላይ ማለትም ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5
ከ 5 ኤሰ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የካይዘን አስተዳደር የሀገር ልጆች ስኬት
የማቀርብበት ነው፡፡ የሁለቱም ኢንዲስትሪዎች እድገት እናንተን ብቻ ሳይሆን
እኔንም ስትጀምሩ የነበራችሁበት ቦታ አብሬችሁ የነበርኩትን ጭምር
የሚያኮራኝ ነው፡፡
አይሽዪ ተቆርቋሪዬ
በርቱልኝ ከዚህ በላይ ከፍ ያድርግልኝ!......
 Aysheshim Tilahun Thank you so much. And we Have to meet. I will
call.

Contenu connexe

Plus de berhanu taye

Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...
Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...
Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...berhanu taye
 
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdf
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdfበአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdf
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdfberhanu taye
 
T7 Curriculum Development.ppt
T7 Curriculum Development.pptT7 Curriculum Development.ppt
T7 Curriculum Development.pptberhanu taye
 
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdfEMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdfberhanu taye
 
Domestic Works Help It is known that the official.docx
Domestic Works Help It is known that the official.docxDomestic Works Help It is known that the official.docx
Domestic Works Help It is known that the official.docxberhanu taye
 
Management, leadership and Synergy.pdf
Management, leadership and Synergy.pdfManagement, leadership and Synergy.pdf
Management, leadership and Synergy.pdfberhanu taye
 
Yeka TVET Institiute information .pdf
Yeka TVET Institiute information .pdfYeka TVET Institiute information .pdf
Yeka TVET Institiute information .pdfberhanu taye
 
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdf
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdfየካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdf
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdfberhanu taye
 
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docx
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docxComparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docx
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docxberhanu taye
 
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdfEducation and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdfberhanu taye
 
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]berhanu taye
 
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...berhanu taye
 
Belaye zeleke new tvet ngo capital budget berhanu tadesse taye
Belaye zeleke new tvet  ngo capital budget berhanu tadesse taye Belaye zeleke new tvet  ngo capital budget berhanu tadesse taye
Belaye zeleke new tvet ngo capital budget berhanu tadesse taye berhanu taye
 
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutes
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutesSifa skills initiative for africa project and meeting minutes
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutesberhanu taye
 
Kaizen berhanu tadess taye edited
Kaizen berhanu tadess taye editedKaizen berhanu tadess taye edited
Kaizen berhanu tadess taye editedberhanu taye
 
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...berhanu taye
 
2013 berhanu training need assessment presentationi
2013 berhanu training need assessment presentationi2013 berhanu training need assessment presentationi
2013 berhanu training need assessment presentationiberhanu taye
 
Presentation tvet 2 edited
Presentation tvet 2 editedPresentation tvet 2 edited
Presentation tvet 2 editedberhanu taye
 
Best practice presented by berhanu tadesse
Best practice presented by berhanu tadesseBest practice presented by berhanu tadesse
Best practice presented by berhanu tadesseberhanu taye
 
Tvet strategy presentation
Tvet strategy presentationTvet strategy presentation
Tvet strategy presentationberhanu taye
 

Plus de berhanu taye (20)

Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...
Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...
Final Edited Post Accreditation Feedback በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ...
 
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdf
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdfበአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdf
በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር.pdf
 
T7 Curriculum Development.ppt
T7 Curriculum Development.pptT7 Curriculum Development.ppt
T7 Curriculum Development.ppt
 
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdfEMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
 
Domestic Works Help It is known that the official.docx
Domestic Works Help It is known that the official.docxDomestic Works Help It is known that the official.docx
Domestic Works Help It is known that the official.docx
 
Management, leadership and Synergy.pdf
Management, leadership and Synergy.pdfManagement, leadership and Synergy.pdf
Management, leadership and Synergy.pdf
 
Yeka TVET Institiute information .pdf
Yeka TVET Institiute information .pdfYeka TVET Institiute information .pdf
Yeka TVET Institiute information .pdf
 
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdf
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdfየካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdf
የካ ቅርንጫፍ ሚገኙ ተቋማት መረጃ New Microsoft Excel Worksheet (2).pdf
 
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docx
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docxComparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docx
Comparative study of UK Leadership with Africa Countries Leadership.docx
 
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdfEducation and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
 
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
 
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...
The debate over jonas and the debate over his acceptance of the article on hi...
 
Belaye zeleke new tvet ngo capital budget berhanu tadesse taye
Belaye zeleke new tvet  ngo capital budget berhanu tadesse taye Belaye zeleke new tvet  ngo capital budget berhanu tadesse taye
Belaye zeleke new tvet ngo capital budget berhanu tadesse taye
 
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutes
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutesSifa skills initiative for africa project and meeting minutes
Sifa skills initiative for africa project and meeting minutes
 
Kaizen berhanu tadess taye edited
Kaizen berhanu tadess taye editedKaizen berhanu tadess taye edited
Kaizen berhanu tadess taye edited
 
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...
Book review and bast practice in tvet institution yeka branch amharic edited ...
 
2013 berhanu training need assessment presentationi
2013 berhanu training need assessment presentationi2013 berhanu training need assessment presentationi
2013 berhanu training need assessment presentationi
 
Presentation tvet 2 edited
Presentation tvet 2 editedPresentation tvet 2 edited
Presentation tvet 2 edited
 
Best practice presented by berhanu tadesse
Best practice presented by berhanu tadesseBest practice presented by berhanu tadesse
Best practice presented by berhanu tadesse
 
Tvet strategy presentation
Tvet strategy presentationTvet strategy presentation
Tvet strategy presentation
 

The new doc of quality and regulatory autority1

  • 1. ስለ አዲሶቹ የጥራትና እውቅና ፍቃድ ኃላፊዎች ለለውጡ ደጋፊዎች እና የለውጥ ሞተር ወይስ እንደቀድሞው ስረአት የእድገት አደናቃፊና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ስትራቴጂውን የሚጥሱ …………………………………………………………………………………….. ገና በውድድር ካሸነፍን እርዳታውን ለምናገኘው ምቀኝነቱ በዛ፡፡ መስራት ሀጢያት የሆነበት ሀገር፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በጠሩት የምክክር መድረክና የእርዳታ ልገሳ የተገለሉ ሕብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ያወጡትን ጨረታ ለመወዳደር የተጀመረ ስራ ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት በሚል ስራ ሳላቋርጥ በመስራቴ የመንግስት አሰሪ የተባሉ አካላት ለምን ትሰራለህ የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ለምን ትሰራለህ የሚለው ቃል መጀመሪያ የጀመረው ከክፍለ ከተማ አብሮኝ የሚሰራ ባለሙያ ደረጃ ሲሆን፡፡ አብረን ከተቀጠርን ጊዜ ጀምሮ መሆኑ በተለያየ ጊዜ የያዝኳቸው መረጃዎች ምስክር ናቸው፡፡ ይሻለዋል በሚል ጉዳዩን ንቄ ስተው ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜ ካለሁበት ክፍለ ከተማ ለመቀየር ስሞክር ከቆየሁ በኋላ እነሆ አሁን ተሳክቶልኝ ለመቀየር በቅቻለሁ፡፡ ይህ ሰራተኛ ገና ከጅምሩ ለቅጥር እኳን የማያሟላ ሲሆን ከዛን ጊዜ ጀምሮ እንዴት አላሰራ እንዳለ በመረጃ ቋት ተቀምጦለታል፡፡ ሁል ጊዜ በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ቢሮ እየገባ ለምን ይሰራል? በሚል ስለሚያንሿክክላቸው የስራ እንቅፋት ነበር፡፡ በመቀጠል ይኽው የተሳሳተ ሀሳብ በኃላፊዎች ደረጃ ነበር ሲንጸባረቅ የነበረው፡፡ ለምን ትሰራለህ? በሚል በዚህ ደረጃ የተነሳው በነበርኩበት ክፍለ ከተማ ደረጃ ስልጠና፣ ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የማጣቀሻ መጽሀፍት ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ስለጻፍኩኝ ነበር፡፡
  • 2. ይህ አትስራ የሚለው ጉዳይ እንዳይቀጥል ሪፎርሙን ሲያስተዋውቁ ስብሰባ ላይ ነበር ማጣቀሻ መጽሃፍን አስመልክቶ ጉዳዩን የእስታንዳርድ ጉዳይ መሆኑን እንዲረዱት ያቀረብኩት፡፡ በስብሰባ ላይ ያቀረብኩት የሰልጣኝ ማጣቀሻ መጽሃፍ በየተቋሞች ላይ ያለመኖር ስህተት መሆኑን በግልጽ ቃላት ነበር ያቀረብኩላቸው፡፡ የሚከፈለን ከዩኒቨርሲቲ ስንመረቅ በገባነው ቃለ መሀላ መሰረትና በሚከፈለን ልክ ለማገልገል መሆኑን ነው፡፡ ነገርግን ባለሙያ ተብሎ የተመደበ አካል የየጽዳት፣ የተላላኪና የጸሃፊ ወዘተ ደመወዝ የሚከፈለው ስላልሆነ በሚከፈለው ልክ ነው መስራት ያለበት በሚል ነበር ሁልጊዜ የምነግራቸው፡፡ ነገርግን መልሰው እነዚሁ የክፍለ ከተማ ሰዎች በከተማ ደረጃ ለተቀመጡ ሰዎች አሁንም ሕገወጥ ስራ እየሰራ ነው በሚል ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር አብሮ ለምን ይሰራል ብለው አሁን የጀመርኩትን ሀገራዊ ስራ ስለአስተባበርኩኝ ጥቆማ ደርሶናል በሚል የጠየቁኝ፡፡ በመሆኑም እነዚሁ በከተማ ደረጃ አዲሶቹ ኃላፊዎች ለምን ስብሰባ ጠራህ በሚል የተናገሩኝ፡፡ በከተማ ደረጃ የተቀመጡት ኃላፊዎች ጭምር የሚነገራቸውን ስህተት ይዘው እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡት፡፡ ይህ የጀመርኩት ስራ በክፍለ ከተማ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ ደረጃ በአቅምና በብቃት ይሰሩታል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የመስራት አቅም ቢኖራቸው ኖሮ መሰራት ያለበት በከተማ ደረጃ ነበር የሚሰራው፡፡ ነገርግን የተሰገሰጉት በዘመድ፣ በፖለቲካ ማንነትና በጓደኝነት በመሆኑ ነው በአቅም የማይሰሩት፡፡
  • 3. እነሱ ህገወጥ ነው የሚሉት፤ ከሕዝብ ውስጥ ገብቶ ችግር ለመፍታት የሚሰራ ካለም ማመስገን እና መሸለም ሲገባቸው ለማዋረድ የሚሞክሩት፡፡ ስልጠናንም አስመልክቶ እነሱ ይመጥናል ብለው ለስልጠና የሚያመጡት እና የሚያሰለጥን አካል ሲያወናብድ ቁጭ ብለው አይተው በደንቡና በመመሪያው መሰረት የተቋማት የክህሎት ክፍተት ሳይለዩ አሰለጠነ ለተባለው አካል ምሆነ ከፍተኛ ክፍያ ሲከፍሉ የኖሩት፡፡ ለስልጠና የወጣውን ብር ዓላማውን መምታቱና አለመምታቱ የወጪ ፋይዳ ግመታ ቢሰራ ህሌናቸውን የሚያማቸው ከሆነ የጠፋው ብር ወንጀል ስለሆነ እራሳቸውን ከስራ ባሰናበቱ ነበር፡፡ የፍላጎት ዳሰሳ መስራቴን እዚሁ ሶሻል-ሚዲ ያላይ መስቀሌ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት የምሰራው በንቀት ሳይሆን ስራዮን ጠንቅቄ በማወቅ ነው፡፡ የማያቁትን ስራ እየሰሩ በእውቀት ልስራ ሲሏቸው አውቃለሁ ይላል ብለው ክስ ያቀርባሉ፡፡ በመሆኑም በዚሁ አመት የገጠመኝ አመታዊ እቅዴን ሳቀርብ ምንአይነት ስልጠና እንደምሰጥ ሌሎች ከፍተኛ አካላት ምንስልጠና እነደሚሰጡ በግዜ ሰሌዳ ያስቀመጥኩት፡፡ ነገርግን በሚከፈላቸው ደረጃ በመስራት ለድጋፍና ክትትል እንወጣለን ብለው የሚሰሩትን ስራ ጠንቅቀው የማያቁ በመሆናቸው ተቋሞቹን እያደናገሩ ነው፡፡ እኔ የምሰራው በእውቀት ስሰራ ምንም እንዳልሰራ ዝም ብዬ እንድቀመጥ ለማድረግ የሞከሩት፡፡ ስልጣና አዘጋጅተው በሌላ አካል ሲሰጥ የማስተማሪያ መጽሃፍ እንዲያሰለጥን የተጠራው አሰልጣኝ የማሰልጠኛ ዘዴውን ግልጽ ሳያደርግ ስልጠናውን ጀምሮ ሊያጠናቅቅ አንድቀን ቀርቶት የማጠቃለያ ሀሳብ ሲሰጥ እኔ ተነስቸሀሜት ሳይ ሆን ፊትለፊት መሆን ያለበትን ለአሰልጠኞቹ የነገርኳቸው፡፡ ተግባራዊ የማሰልጠኛ የመምህር መምሪያና seetion plan/lesson paln አዘጋጅተው እንዲመጡ ተቋምም ላይ ስንመጣ ይንን ዕቅዳችሁን ማግኘት ያለብን፡፡
  • 4. በሚል ያቀረብኩት ሃሳብ ለኃላፊ በክስ ምክንያት የቀረበው፡፡ እንደዚህ በእውቀት መስራት ሲችሉ ከገበያው መውጣት የሊለባቸው ምሁራንና ባለሀብቶች በግልጽ የሚታይ ብር አምጡ ያክል ከተጠየቁ በኋላ እንዲዘጉ ተደረጉ፡፡ እነዚህ ምሁራንና ባለሀብቶች ከስራው እንዲባረሩ ብቻ ሳይ ሆን የተደረጉት በስደት ሌላ ሀገር እንዲሰሩ ነው የተደረጉት፡፡ ወደ አሁኑ ክስም ስመለስ ያለምንም ክፍያ የተዳከሙትን ተቋሞቻችንን እርዳታ እንዲያገኙ በማሰብ የጀመርኩት ስራ ነው፡፡ የጀመርኩት ስራ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ሰለሆነ ለመስራት ስታጭ የሰራሁበትን ስራ ስለማልጥል በጻፍኩት የእሴት ሰንሰለት በሴት እማ-ወራ አርሶ አደሮችን ህይወት ለመቀየር በተግባር በሰራሁትና በጻፍኩት መጣጥፍ ነበር በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ደረጃ ተጠርቼ ስለነበር ስራውን በቅንጅት ለመስራት ከግልና መያድ ጋር ስራውን በእቅድ ደረጃ በድጋሚ አዲስ አበባና ከከተማው ወጣ ብሎ ባሉ አርሶአደሮች ላይ ተጠቃሚዎችን ለማፍራት ያስጀመርኩት፡፡ ስራውን በእቅድና ቅንጅት ሳስጀምር ስልጣን ፈልጌ ሳይሆን በኃላፊነት የሚሰሩ ተቋማትን ኃላፊነትን ለመስጠት ነው፡፡ በቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት እና ቢሮ ደረጃ አሰራሬን የሚቃወም ወረራ አካሄደብኝ፡፡ ይህ ግለሰብ ና ውጣ አይነት ግልምጫ በተደጋጋሚ ያሳየኝ ሲሆን፡፡ የጠራኋቸው ተቋማት ችግሮችን ለመፍታት ሰብስቤያቸው በነበረበት ወቅት የተሰባሰብንበት ቦታ በመምጣት ለመሳተፍ ፈልጎ ወንበር ስቦ ከተቀመጠ በኋላ ስብሰባውን እረግጦ መውጣት ብቻ ሳይሆን ቢሮ ውስጥ ከቆየ በኋላ ሲወጣና ሲገባ ሲገላምጠን የነበረው፡፡ ይህ በጎ ስራ እንዳልተዋጠለት የተረዳሁት በከተማ ደረጃ ሄዶ መወንጀሉ ነው፡፡ በዚህ የምቀኝነት ስራው ለድጋፍና ክትትል በምንወጣበት
  • 5. ጊዜ አቋሙን ተቋሞቹም እራሳቸው ጠንቅቀው የሚያቁት ሰው ነው፡፡ ለማሳያነት አብሬው ለድጋፍና ክትትል ተቋሞቹ ላይ በሄድኩበት ወቅት በተደጋጋሚ ባለስልጣን ለመምሰል የሚያደርገውን አክት እኔ ያየሁበት ብቻ ሳይሆን ተቋሞቹም ጭምር የሚያረጋግጡት ነው፡፡ ለስብሰባ የጠራኋቸውን ይሁን ለድጋፍና ክትትል የሄድኩባቸውን ተቋማት አከብራቸዋለሁ እግዚአብሔር ይመስገን እነሱም ያከብሩኛል፡፡ የምሰራውም በእውቀት እንጂ በንቀት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም በሚባል መልኩ ምሁራን ስለሆኑ፡፡ ምንአለ በጽ/ቤት ደረጃ ብቻ ሳይሆን የባለሙያዋችን የስራ አፈጻጸምና ስነምግባር እነዚሁ ሕጋዊ ስራቸው የገዘፈና ብቁ የሆኑ ተቋማት ቢመዝኑና ውጤት ቢሰጡ ጥሩ ነበር፡፡ ለምሰራው የድጋፍ ስራ ብር ካላመጣችሁ አልሰራም አላልኩም፡፡ ይህ የሚያንጓጥጥ አካል እስኪ ይናገር፡፡ እስኪ የደንበኞች የእርካታ መለኪያ የሰራውን ያሳይ፡፡ በዛሬው እለት የገጠመኝ እና ውጣልኝ በሚል በግልምጫ ሀሳቡን ሲገልጽ ኃላፊ ቢሮ የነበርኩኝ ሲሆን፡፡ በወቅቱ ስላናደደኝ ስህተቱን ልነግረው የወጣሁት፡፡ እኔ ሁልጊዜ ተማሪ መሆኔን ነው የማውቀው፡፡ ይህ የሚኮፈስ አካል ኮንፒውተር ላይ መጻፍ የማይችል ብቻ ሳይሆን እስካሁን የመጣበት መንገድ የኔን እቅድ በመውሰድ እሰራለሁ ሲልና የሰራሁትን ፕሮፖዛል ምንም ሳያሻሽል ወስዶ ከመንግስት ክፍያ የተቀበለበት፡፡ እንደዚህ ያለሰው ነው ተቋምን ለመደገፍ የሚሄደው፡፡ ተቋማቱ ትክክለኛ ቅጥር እንዳያደርጉ የከሰመን ተቋም የአሰልጣኞችን ፕሮፋይል እያወጣ ለተቋሞች ሲሸጥ ሀያባይ ያጣው፡፡ ባጠቃላይ ኃላፊ ተብለው የሚመደቡ አካላት እንደዚህ critical thinking በሆነ እሳቤ አጥፊውን የሚገስጽ አይደሉም፡፡ ንትርኩ የጀመረው በፊት ሲሆን በራሴ ፍላጎት ከክፍለ ከተማው ከመቀየሬ
  • 6. በፊት ዛሬ የጨረስኩትን ክሊራንስ ለመውሰድ በመጣሁበት ወቅት ውጣ ያለኝ ሰውዬ በሰበሰብኩት ስብሰባ ላይ አባል ለመሆን ፈልጎ የሰበሰብኩት ስብሰባ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ተቋማቱን የጠራኋቸው በስሜ ስለሆነ የጻፍኩትን የጥሪ ደብዳቤ በስሜ መሆኑን አይቶ በመበሳጨት ወዲያውኑ ተነስቶ ሲወጣ ያሳየኝ ፊት በጣም መጥፎ ቢሆንም በወቅቱ ስብሰባው እንደይደናቀፍ የማቀው ምቀኛ ሰው በመሆኑ ምንም አላልኩትም ነበር፡፡ ነገርግን እኔ የመረጥኳቸው ተቋማት በአቅምና ብቃት መስራት የሚችሉ የማሰልጠኛ ተቋማትና የግል አማካሪዎችና የመንግስት አካላት ስለሆኑ ነው ስራውን ያስጀመርኩት፡፡ ይህ ያለአቅሙ የገባ የስራ ባልደረባ እንደዚህ አይነት ትልቅ ሀገራዊ ስራ የመስራት አሻራ የሌለው ሲሆን በማደናቀፍና እኔ የሰራሁትን ስራ ነገርግን ብር ያልጠየቅኩበትን ስራ ወስዶ ከመንግስት ብር ተቀብሏበታል፡፡ የሚጠይቅ አካል ካለ መረጃውን በሰነድ መስጠት ይቻላል፡፡ ይህም ለማሳያነት ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑበት ለአካባቢው ሕዝብ ስለሌለ በሚል የሕዝብ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ በአዲሱ ገበያ አካባቢ በግብረሰናይ ድርጅት የተገነባው የበላይ ዘለቀ ት/ቤት ነው፡፡ ይህው አሁንም የጀመርኩት ስራ አወዳዳሪዎች የሚሰጡት ድጋፍ ሀገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ነበር በመረጡትኩት ቅንጅታዊ አሰራር ከተቋሞቹ ጋራ ለመስራት ያቀድኩትና ወደውሳኔ የደረስኩት ፡፡ በቢሯችን በተደጋጋሚ ከኦ አይሲኢ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም (Opportunity Industrilization Center Ethiopia (OICE TVET institute) መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (መያድ) በየአመቱ ከለጋሾች የሚደረግለት የእርዳታ ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው የተቀነሱ ሰራተኞች እየመጡ አቤቱታ ሲያቀርቡ፣ ሲያለቅሱ ከቅነሳው የተረፉትም የደመወዝ እድገት ሳይሆን ቅናሽ
  • 7. በማድረግ በፍቃደኝነት እየሰሩ እያየሁ ዝም አልልም፡፡ እኔም እንደነሱ በትርፍ ሰአቴ ለምሰራው ስራ ክፍያ ሳልጠይቅ የሀብት ማሰባሰብ ስራን ለመስራትና የተቀነሱትን ሰራተኞች ለማስመለስና ክፍያቸውም እንዲስተካከል የወሰንኩት፡፡ ከማንም ተቋም ለምሰራው ስራ ብር ሳልጠይቅ እጄ በስራ ጫና እስኪፈነዳ እና እግሬም ከመቀመጥ ብዛት እየደነዘዘ ነው በትጋት እየሰራሁ ያለሁት፡፡ ከላይ እንዳስቀመጥኩት ከስራ ተባረው ለሚያለቅሱ ሰዎች በመቆርቆር ስለሰራሁ ነው ስብሰባ መጥራት ፍቃድ ስለሌለህ ለምን ስብሰባ ጠራህ የሚሉት፡፡ የትምህርትና ስልጠና ስራን የሚሰራን ሰራተኛ ከፖለቲካ ጋር ማገናኘት ስህተትና ወንጀልም ጭምር ነው፡፡ ሕግን አለማወቅም ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በማሰብ የሚሰራን ሰው ሞራል መስበር የገፉበት፡፡ በግልጽ በሚታይ መልኩ ለወደቀው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰራር ተጠያቂ ስላልሆኑ ነው በኃላፊነት ለመቀጠል የሚፍጨረጨሩት፡፡ የሚሰራን ሰው ማዋረድና የሚገባውን ክብር አለመስጠት ወንጀል መሆኑን አያውቁም፡፡ ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ አዲስ የተመረጡት ኃላፊ ተብዬዋች ከዚህ በፊት ስራ ሲያበላሹ የነበሩ ሰዎችን እንዴት ሲያበላሹ እንደነበር ተነግሯቸው ተነግሯቸው የገባቸው ቢመስሉም አሁንም እዛው ድንቁርናቸው ላይ ናቸው፡፡ እምላቸው ለሀገሬ በደንብ ስለሰራሁ ምስጋናው ቀርቶብኝ በቅጡ በኮንነኝ ነው፡፡ ልክ ሌባ እናት ልጇን እንደማታምነው ነው ሁሉ ለምን ትሰራለህ የሚሉት፡፡ ኃላፊ ተብየዎች ተማርን አወቅን የሚሉ ከሆነ ለወገናቸውና ለሀገራቸው ሕዝብ ችግር ተቋርቁረው ለሚሰራው ስራ ከበደኝ መስራት አልችልም ሳይሉ በጽኑ አቋም በመስራት ችግር የሚፈታውን ሲያከብሩ ብቻ
  • 8. ነው፡፡ ስራን መስራት መቻል በተግባር ነው እንጂ በየቦታው በተለቃቀመ የትምህርት ማስረጃ አይደለም፡፡ ያኽውም ኃላፊ ተብዬዋች ተማርን የሚሉት ከሚሰሩት ስራ ጋር በምንም አጋጣሚ የማይገናኝ ትምህርት ተምረው ስራን እያበላሹ ያሉ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም በብቸኝነት ፐብሊክ ሰርቪስ በሚል የሚሰጣቸው ቁንጽል ትምህርት በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ተብለው ለሚያጠፉት ጊዜ ተጠያቂ ያልሆነ ዩኒቨርሲቲውም ሲቀበል ምንያህል ከስራቸው ጋር እንደሚገናኝ ሳይጠይቅ በመቀበሉ ለከሸፈው ፕሮግራም ተጠያቂ አለመሆኑ ነው ችግሩ እንዲቀጥል የሆነው፡፡ እነዚህ አካላት ተማርን ብለው ሳይሰሩ ለተከፈላቸው ብር ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው ለመስራት የገቡትን ቃለመሃላ በመዘንጋት ለራሳቸው ጥቅም ሲስገበገቡና ስራን ሲያበላሹ በመሆኖራቸው ነው፡፡ ወቅታዊ የሀገር ጉዳይን አስመልክቶ "ሙያተኞች ከስራቸው ተፈናቃይ ሆነዋል የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ ሙያተኞች ጠፋ፡፡ ሁሉም የመንግስትም፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግልም ሰራተኞች ፖለቲከኞች ሆኑ በሚል (ታዋቂዋ ልበ ብርሀኗ የትነበርሽ)" ያቀረበችው፡፡ በመጨረሻም ፖለቲካውን እስኪ ለፖለቲከኞች እንተው አለች"፡፡ ለኔ የእርሷ አባባል ትክክለኛ ነው ባይ ነኝ፡፡ ስለሆነም ምስጋና ለታላቋ ልበ ብርሀኗ ምኁር የትነበርሽ፡፡ ባለፈው አመትም በዚህ ጊዜ እኔም ፖለቲካ በቃ ወደስራ ብዬ ስራየጀመርኩት፡፡ ሀገራችን ስግብግብ በዝቶ እንዲህ አሳዛኝ በሆነ መልኩ ስለተገለጸች ስራችንን መስራት ነው እንጂ ከስራችን መፈናቀል የለብንም ባይ ነኝ፡፡ ስራ ስንሰራ የምታከላክሉ የመንግስት አካላት ሁሉ ከድርጊቱ ካልተቆጠባችሁ እናንተ ከስራችሁ ተፈናቅላችሁ የምታላምጡት ስራችሁን ሳይሆን ፖለቲካውን ስለሆነ
  • 9. ለምትተራመሰው ሀገራችን ተጠያቂ ናችሁ፡፡ ባልደረባችሁም እንዳይሰራ በማድረግ ከስራ ስላፈናቀላችሁ በሕግም ተጠያቂ ናችሁ፡፡ ሳይሰሩ ውጤታማ ነኝ ማለትና ሳይሰሩ የስራ አፈጻጸም ውጤትን ለራስ ቆልሎ በመስጠት ማንንም ማታለል አይቻልም፡፡ የቅርብ ኃላፊ በምታየኝ የተንሸዋረረ መነጽር ልክ ነው የስራ ውጤቴ አፈጻጸም የሰጠችኝ፡፡ ነገርግን ከሰራኋቸው ተጨባጭ ስራውች በቅድሙያ በተጨባጭ የሚያስደስተኝና መረጃ ማቅረብ የምችለው ከለጋሾች አካላት (ከወርልድ ቪዢን ኮርያ) አውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት B+1 (basement plass one) በ November 2015 ተጠናቆ የተመረቀው የሽሮ ሜዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ነው፡፡ ሊዘጋ የነበረ የአውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት የህንጻ ግንባታ የተመደበ በጀት የብር ድጋፍ ማስገኘቴ ነው፡፡ በወቅቱ ባለመሰራቱ ብሩ ሊመለስ ሁለት ወር ብቻ ሲቀረው ነበር ለስራ የታጨሁት፡፡ ስራውን ስጀምር ከወርልድ ቪዚን የመጡት ኃላፊ መግለጫ ከሰጡ በኋላ ስጋታቸውን ሲያስቀምጡ መስራት ያላስቻላቸው የተወሳሰበው ቢሮክራሲ ውሳኔ ስለሆነ እስካሁን ያልተሰራ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይሰራል የሚል እምነት እንደሌላቸው የደመደሙት፡፡ በመሆኑም ይህ ስራ ካልተሳካ ይዘዋት የመጡትን ኢንጂነር እንደሚያሰናብቱ ማብራሪያ የሰጡት፡፡ ኢንጂነሯን እንደሚያባርሩ ሲገልጹ የተቀጠረችው ይህንኑ ፕሮጀክት ሰርታ ታጠናቅቃለች በሚል ነበር ካሉ በኋላ፡፡ የተመደበው የግንባታ ባጀት የሚዘጋበት ጊዜ ደርሶ ወደሌላ ክፍለ ከተማ ለማዘዋወር ወርልድ ቪዢን እያቀደ ባለበት ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ለስራው የታጨሁትና እንዳይዘዋወርና ትባረራለች የተባለችውን ኢንጂነር እንዳትባረር ያደረኩት፡፡ በተቃራኒው ይህ ታላቅ ስራ እንዲጠናቀቅ
  • 10. አብረውን የደከሙ ኢንጂነሮች እንዲባረሩ መደረጋቸው ነበር ደስ ያላለኝ፡፡ የቢሮው ኃላፊ ከ9 ያላነሱ ኢንጂነሮች የያዝነውን ስራ ካጠናቀቅን በኋላ እንዲባረሩ ያደረጉት፡፡ በኋላ ላይ በፍርድ ቤት ተከራክረው እንዲመለሱ ተፈርዶላቸው ስራቸውን የጀመሩት፡፡ ይህ ከስራ ያባረራቸው ኃላፊ የሚሰራውን ስራ ያለቢሮክራሲ መስራት እንዳለብን ይህም የሚሆነው የኢንጂነሮቹንም ጥቅም ማስከበር ይኖርብናል በሚል ሀሳቡ ሳቀርብለት ጥቅም የምትለውን ቃል በክራይ ሰብሳቢነት የፈረጃት፡፡ ትክክል አለመሆኑን ነው የነገርኩት ይህውም በሌላው አለምም ሰራተኛን ከ8 ሰአት በላይ ማሰራት አትችልም፡፡ በሰሩት ልክ ሊከፈላቸው የሚገባውን ክፍያ በዋናነት አንተ እራስህ በመቀጠል ስራውን የሚያ ሰራው አካል ለትርፍ ሰአት መክፈል ያለባችሁ ያልኩት፡፡ ስራው ባጭር ጊዜ መጠናቀቅ ስላለበት በእኛ ቢሮክራሲ ቢንጓተት እና ብሩ ተመላሽ ቦሆንና ቀልጣፋ ክፍለ ከተሞች ሚወስዱት ከሆነ ተያቂ የምንሆ ነው ኃላፊነት ላይ የተቀመጥን አካል ነን ብዮ ያሳሰብኩት፡፡ ሰውየው የሚሰማ አይደለም የሳይት ጉብኝት ስራ ጋር በተያያዘ መኪና ከመመደብ ጀምሮ እስከ ባለሙያ አበል በሚፈቅድልን መልኩ እንከፍላለን የሚለው አላግባባንም ነበር፡፡ ከኃላፊው ጋር ባልግባባም በሌላ ቀን ምክትሉ ጋር ገብቼ በጥሞና ካዳመጠኝ በኋላ ደብዳቤ ለመጻፍ ፍቃደኛ በመሆን እነዚሁ ኢንጅነሮች ከሶይል ቴስት ጀምሮ እስከ አርክቴክቱ ስራ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደስራ የተገባው፡፡ በመሆኑም ስራውን ሳስጀምር ያጋጠመኝ ተግዳሮት የአፈር ምርመራ 15 ቀን የሚወስድ የነበረ ሲሆን አርክቴክቱም እንደዚሁ እረዥም ጊዜ ስለሚወስድና የክፍለ ከተማ ኢንጂነሮች በአመቱ እቅዳቸው በስራ ተወጥረው ስለነበር ነው፡፡ በመሆኑም ከቢሮክራቶች ጋር አንገት ላንገት ተናንቄ መጨረሻ ላይ የተመደበውን በጀት ያስለቀቅኩትና አውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት እንዲገነባ
  • 11. ብቻ ሳይይሆን ያደረኩት የውስጥ ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው ጭምር ነው፡፡ ሲጀመር ለሕንጻው ተይዞ የነበረ በጀት 6ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን ተጨማሪ ስራና የውስት ቁሳቁስ ሲሟላ ከ 28 ሚሊዮን ብር በገቢ ደረጃ እንዲገኝ ያደረኩት፡፡ ለምን ስራችንን በእውቀት አንስራም? ሲሏቸው ፍቃድ የላችሁም ይላሉ፡፡ አሁንስ መረረኝ የት ሀገር ሄጄ ልስራ? ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ሰዎች መስራት ስለማይችሉ ለምን ትሰራለህ ይላሉ፡፡ መማር ማሰተማር ላይ ያልሰሩ እንዴት ባለስልጣን እንደሚያደርጓቸው ግልጽ አይደለም፡፡ በመሆኑም እነዚህ ኃላፊዎች እያደናገሩ ስለሆነ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው መቆጠብ አለባቸው፡፡ እየተሰራ ያለው አሰራር በመመሪያ የተደገፈ ሳይሆን እየተሰራበት ያለው አግባብ በዘር፣ በአካባቢ፣ በጓደኝነት፣ በፖለቲካ ወገንተኝነት አሰራር በመሆኑ ነው፡፡ እየሰሩ ያሉት በተቀመጠው ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሕግጋት መሰረት ስለማይሰሩ ብዙውን የወጣ ትክክለኛ ሕግ የሚሽሩት፡፡ በከተማ ደረጃ ያሉ በየጊዜው የፈተና ስርቆት የሚከሰተው በዚህ መልኩ የተዛባ አመዳደብ ስላለ ነው፡፡ በግልጽ ለሚራበው፣ ከስራ ለሚባረረው፣ ለሚሰደደውና ለሚሞተው ወገናቸው በኃላፊነት የሚጨነቁ አመራሮች አለመኖራቸው አሳሳቢ በመሆኑ ነው፡፡ እውነተኛ አመራር የሚሰራ ሰውን ያበረታታል እንጂ እንደመሰናክል አያደናቅፍም፡፡ ስለቴክኒክና ሙያ ምንም እውቀት የሌላቸውና በተመሳሳይ ስራ occupation ያላስተማሩ (መማር ማስተማርን ምንም የማያውቁ አካላት) ናቸው ስልጣን ላይ የተቀመጡት:: አሁንም በእነዚሁ ካላት ጥቆማ ወደስልጣን እንዲመጡ ያደረጓቸው አካላት በመሆናቸው ነው የአሰራር ብልሽት
  • 12. እንዲቀጥል ያደረጉት፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት ሲያበላሹ የነበሩ ሳይሰሩ ውጤት አፈጻጸማቸውን በራሳቸው እጅ ሲሞሉ የኖሩ ናቸው፡፡ እኔ ስልጣን ለማግኘት ብዮ እንደተማሪ የስራ አፈጻጸም ውጤቴ ዝቅተኛ ነው የተሰጠኝ በሚል ጨምሩልኝ ወይም አስተካክሉልኝ አልልም፡፡ አሁንም ቦታው ላይ በኃላፊነት የተቀመጡት በስራ አፈጻጸም እራሳቸውን የላቀ አድርገው የሞሉ ናቸው ቦታው እንዲሰጣቸው የተደረገው፡፡ በያዝነው አመት የቴክኒክና ሙያ አዲስ ሪፎርም መሰራቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራትና እውቅና ፍቃድ፣ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን አደረጃጀት በአዲስ መልክ መሰራቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም መመደብ የፈለኩበትም ቦታ ስላልተመደብኩኝ ቅሬታዬን ሳስገባ ቅሬታ ሰሚዎቹ መልስ የሰጡኝ ሌሎቹ በስራ አፈጻጸም አንተን የሚበልጡህ ስላሉ ከተማ መግባት አትችልም የተባልኩት፡፡ እውን እነዚህ ሀገራዊ ስራን መስራት የማይችሉ አካላት ናቸው እኔን መአከል ላይ በኃላፊነት ሳይሆን በባለሙያነት ለመመደብ በስራ አፈጻጸም የሚበልጡኝ? የሚሰራው በትክክለኛ የስራ አፈጻጸም ሳይሆን በጓደኝነትና ከዚህ በፊት በክራይ ስብሰባ አማካኝነት የጣሱትን ስትራቴጂ እንዳልጠይቃቸው ነው፡፡ መዳቢና ቅሬታ ሰሚ የሆኑትና ይህ ግለሰብ ወደኛ እንዳይመጣ ያሉትና ተግባራዊ ያደረጉት፡፡ እኔን በስራ አፈጻጸም ውጤት የሚበልጡኝ ለጥቅማቸው የሚስገበገቡ ናቸው እንጂ በስራ አይደለም፡፡ በእርግጠኝነት እጄ ላይ ያለው መረጃ በእውቀት ደረጃ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ናቸው እኔን በተዛባ የስራ አፈጻጸም ውጤት የሚበልጡኝ፡፡ ክስ በማሰብሰብ ከተቋሞች በአግባቡ የሚሰሩ ሳይሆን አሸባሪና ብር አምጡ እያሉ እደጠየቋቸው እውቅና የተሰጣቸው ባለሙያዎች ናቸው እኔን በስራ አፈጻጸም የሚበልጡኝ፡፡
  • 13. ለዚህ ማሳያ እንዲሆን በቅርቡ በከተማ ደረጃ ያሉ ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን ባደረጉት መሰረት የሰጡት ግብረመልስ ባብዛኛው ስህተት የሆነ ግብረመልስ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ እነዚህ ከከተማ የመጡ ኢንስፔክሽን አድራጊ አካል ብቻቸውን ተቋማትን ኢንስፔክት ሲያደርጉ በሰጡት ግብረመልስና ተቋሞቹ ባቀረቡት ቅሬታ በግልጽ ስህተት እመንዳለባቸው ታይቷል፡፡ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ለመክፈት እውቅና ፍቃድ ሲሰጥ አካልጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን ስታንዳርዱ ከፍተኛ ነጥብ የሚያሰጠው compauond ከሆነ ነው ይላል፡፡ ነገርግን እነዚህን ተቋማትን ኢንስፔክት ሲያደርጉ ዝቅተኛ ውጤት የተሰጡት ኢንስፔክተሮቹ ብር እንዲከፍሎቸው ጠይቀው እንቢተኝነታቸውን ስላሳዮቸው ነው፡፡ እነዚሁ ከከተማ ለኢንስፔክሽን የመጡ አካላት እራሳቸው ለኮሌጆች እውቅና ፈቃድ ሲሰጡ 7፣8፣9 ወይም 10 ኛ ፎቅ ላይ ፈቃድ እንዲያገኙ ሲሰጡ የሚገመግማቸው አካል ስለሌለ ነው፡፡ በዚህ ባልተገባ ግምገማዎች ነው ብቁ የሆኑ ተቋማት ከገበያ እንዲወጡ ተደርገው እስከወዲያኛው የተዘጉት፡፡ በመሆኑም መስራት የሚችሉ ተቋማት ለስደትና ለስራ አጥነት የተዳረጉት፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ምዘናው ትክክል ባልሆነ ፍረጃ እንደፈለጉት የሚጎትቱት በከለር (ቀይ፣ ፈዛዛ ቀይ፣ ቢጫ እና አረንጓዴ) የታጀበው፡፡ ይህ አሰራር በማስረጃ በተደገፈ መልኩ ስህተት እንዳለው በተደጋጋሚ ስናገር ቆይቼለሁ፡፡ ሲሰጥ የነበረው በከለር ሲሆን ይህውም በስራ ሂደቶቹ የሚፈለጉት ተቋማት ብቻ አንጓሎ የሚጥል ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ በግልጽ ሊሰራበት የሚገባው ቀጥሎ በማቀርበው መስፈርትና ክራይቴሪያ በማውጣት ነው ይህውም የማያሳማ በዚህ መልኩ Accordingly, the criteria and standards for evaluating TVET institutes have been set down as follows; 1. The capacity of raising enrolment (15%) out of this the institute got 15% 2. Minimizing dropout (15%)---15% 3. Cooperative training (15%)--10%
  • 14. 4. Conducting training by certified professionals (15%)----15% 5. Presenting trainees to center of competency assessment and certification (CoCAC) for evaluation (25%)---25% 6. Submitting monthly report in due time (10%)---10% 7. Taking part in bezzras (income generating activity) (5%)-----0 Invention and Innovation____________ (additional criteria) 100% ---0% etc……… እና እያንዳንዷ መስፈርት መጀመሪያ በቁጥር ተቀምጦ በኋላላይ ወደፐርሰንት ተቀይሮ ነው መቅረብ ያለበት በመሆኑም ውጤታቸው ሲገለጽ ፡- We have attached here with the result obtained by conducting the evaluation carried out on the basses of the criteria stated above. Based on this, the result of ………… TVET institution is now ranked 1st , 2nd, or 3rd from ……….TVET Institutes under …….. Sub City TVET institutions and the office highly recommend that this extraordinary (Excellency) work should keep it up or amand your problem and ceased! ነገርግን ስንቱ ሀቀኛ ተቋም ለምዘና ምቹ ተብለው COC ሳይቀር ተቋሙ ለምዘና እውቅና የተሰጣቸው የመመዘኛን መስፈርት አሟልተው ነው የተሰጣቸው ስታንዳርዱ በወረደ አሰራርና ምቀኝነት እንዲዘጉ ተደረገ፡፡ ሀይ ባይ ይጥፋ? የኔን ስራዎች በተግባር ማግኘት የሚፈልግ ካለ http://www.slideshare.net berhanu tadesse uploads ብሎ በማግኘት እማኝ ስራዎቼን ማየት ይችላል፡፡ የፈለኩት ስልጣን ሳይሆን በባለሙያነት መአከል ስገባ እነሱ ያበላሹትን ስትራቴጂ ለማስተካከል ነበር የፈለኩት፡፡ በባለሙያነት ለመመደብ ባቀረብኩት ቅሬታ መሰረት ይበልጡሃል የተባሉት ባለሙያዎች ከፈለጉ ከኔ ጋር በኔት ወርልድ ሚዛን ላይ ብንቀመጥ ምንም
  • 15. ስራ እደሌላቸው ማሳየት እችላለሁ፡፡ ይህንን አድሎዊ የስራ ውጤት አፈጻጸም ከበፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሲሰሩ የነበሩ ኃላፊ ተብዬዋች አሰራራቸው ትከክልኛ አለመሆኑን ሁልጊዜ እነግራቸዋለሁ፡፡ በመሆኑም እነዚሁ አድሎ ፈጻሚዎች ጊዜያቸውን ጠብቀው እየከሰሙ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው፡፡ እውቀቱ ሳይኖራቸው ብር ካላመጣችሁ በሚል የሚዘጉ የግል ማሰልጠኛ ተቋሞች ብዙ ናቸው፡፡ እኔ በእውነተኛና በእውቀት ላይ ተመስርተው ለሚሰሩ የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ምቀኛ አልሆንም ወይም አይደለሁም፡፡ በዚህ ዙሪያ በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ሰፊ ንባብ ይዤ እወጣለሁ፡፡ ይኽቺ ሀገር መቼ ነው እውነተኛ ስራ ወዳድ ትውልድ የምታፈራውና የደከመውንና ዜጎችን ከስራ ጋር በማገናኘት ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥርውን የምትደግፈውና ያለመድሎ የምታደንቀው? ከሰው ምንም አይነት ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት ስላልተቻለ እግዚያብሔር የኔንና መሰሎቼን በሁሉም ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ይዚህችን ምስኪን ሀገር ይጎብኘን! አሜን! Yalem Fikir ሁሉንም አነበብሁት በብሶት እና በማዘን ከልብ የተጻፈ መሆኑን ከዓረፍተ ነገሮች መረዳት ይቻላል። አሁን ላይ በየመስሪያ ቤቱ ብዙ ጉድኝቶች ተፈጥረዋል። ፩/ #የአለቃና_እወደድ_ባይ( ቅቤ ጠባሾች) ጉድኝት። ይህ በስራ እና በብቃታቸው የማይተማመኑ ሰራተኞች ለአለቃቸው አቤት አቤት በማለት የአለቃቸውን ችሮታ የሚለማመጡ ጆሮ ጠቢዎች እና አሸርጋጆችን ያካትታል። ዋና ስራቸው የሚሰሩትን ሰዎች ስህተት ብቻ እየተከታተሉ ለአለቃ በማቀበል ለመስሪያ ቤቱ ምንም እሴት የማይጨምሩ እንቅፋት የሆኑ ሸክሞች ናቸው።
  • 16. ፪/ #የዘር_ወይም_የአካባቢያዊ_ጉድኝት ይሄኛው መስሪያ ቤቱ ውስጥ ለሚመጡ ጥቅማጥቅሞችም ሆነ የስራ እድገት በማታውቀው እና ባልጠበቅኸው መንገድ እጁን ይዘህ ስልጠና የሰጠኸውና መስሪያ ቤቱን ጠንቅቆ ያላወቀ ሰራተኛ ሃላፊህ ሆኖ ከች የሚልበት የዘር ተዋረድ የሚነግስበት እና ዘላለምህን ታዛቢ ሆነህ የምትኖርበትን ያካትታል። ጎረቢት ሆነው ሳይተዋወቁ የኖሩ ሰዎች በስራ ላይ እጅና ጓንት ሆነው ሌሎችን በማውረድ እራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ሲታትሩ ታገኛቸዋለህ። ጥረትህን ሳላደንቅ አላልፍም። የማይሰራ ሰው ሴረኛ ነውና እንደምትጠነቀቃቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ሀገራችን ውስጥ ላለው ከፍተኛ የስራ አጥ መብዛት ትልቁ ተጠያቂ #የትምህርት_ተቋማት በተለይ የቴክኒካል ክፍሉ እና #መንግስት ናቸው። ትምህርታችን ፈጠራን እና የተግባር ልምምድን ያማከለ ሳይሆን የወረቀት ብቻ መሆኑ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ግብዓቶቹ በችሎታ ሳይሆን በችሮታ የተቋማት ሀላፊዎች መብዛታቸው ለሚገዙ የላብራቶሪ እቃዎች ባለመፈረም ለሚቀጠሩ መምህራን ቁጥርና ችሎታ ማነቆ ሆነው እንደካሮት ቁልቁል አንደርድረው አሾቁትና አረፉ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ እየታገልህ ስለሆነ በርታ ማለት እዎዳለሁ። የጥቂቶች የሀሳብ ልዕልና የብዙዎችን የወደፊት እጣ ፈንታ ይወስናል ያንተም የግል ጥረት ለብዙዎች ተስፋ ይሆናል እንዳልከው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን። Yalem Fikir ለመልካም አስተያየትህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ! አሁን ሰሞኑን የሪፎርም ስብሰባ ሰኔ ውስጥ 2011 ዓ.ም ኢሊሊ ሆቴል ላይ አ.አ. መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ያአሁኑ ባለስልጣን የሙያብቃትንና ትምህርት ጥራን ተከትሎ ሪፖርት ሲያቀርብ የወረደ ነበር የሆነብኝ፡፡ በዚህ
  • 17. የተነሳ ትምህርት ጥራት ያቀረበችውንና በሆላ ላይ የሲኦሲ (CoC) ምዘና ያቀረቡትን ሪፖርት ፐሮፌሽናል በሆነ መልኩ ያቀረቡ በመሆኑ አመስግኜ የቴክኒክና ሙያን በግልጽ ተቃውሜ ነበር አስተያየት ላይ የቀረብኩት፡፡ ምክንያቱም ያመሰገንናቸው ሁለቱም ያቀረቡት በስታንዳርዱ መሰረት ሲሆን ይህንን አሰራራቸውን ሙሉ አዳራሹ ተሰብሳቢዎች ነበር የታዘቡት፡፡ መደነቅ ያለባቸውን ያደነቅነውና መታየት ያለባቸውን አስረግጬ ያቀረብኩት፡፡ ስብሰባው ላይ በግል ለተቃውሞ ያነሳሳኝ የቴክኒክና ሙያ ተወካዩ የአሁኑ ተሿሚ ሪፖርት ሲያቀርብ ሜቴክ የገነባቸውን ተቋማትን ሲናገር ያበላሻቸውንና የተዘረፈውን የዘለላቸው፡፡ ሪፖርቱ ሲቀርብ ስታንዳርድም ላይ ምንም ሳይናገር ነበር የዘለለው፡፡ አንድም ከቁጥር ጋር የተገናኘ ሪፖርት ሳያቀርብ አለፈ፡፡ በእርግጥ ሁሉም የግንባታ ጫራታዋች ወጥቶባቸው በግልጽ ጨረታ የግል ተቋራጮች ተወዳድረውበት የተሰራ ቢሆን አያሳማውም ነበር፡፡ ነገርግን ሁሉንም ግንባታዎች በራሱ ነበር ሲሰራ የነበረው፡፡ ሜቴክንም የማቀው ግን መገንባቱ መልካም ቢሆንም ያጠፋቸውና መስራት የሌለበት ደግሞ ብዙ በመሆኑ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እንደሚከተለው አቀርባለሁ በስፔስፌኬሽኑ መሰረት የክትትልና ግምገማ ሪፖርት የቀረበ ካለመኖሩ ጀምሮ፣ ስቦርቅ ያደኩበትን የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኳስ ሜዳ ባልጠፋ ቦታ የስፖርት ማዘውተሪያ ውስጥ ግንባታ ማካሄዱ ብቻ ሳይሆን የግል ድርጅቶች ሳይወዳደሩ ከሁለት እስከ ሶስት መቶ ሺ ብር የማይፈጅ የመግቢያ በር ግንባታ ከሶስት ሚሊዮን ብር ክፍያ የሁሉንም ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ግንባታ በማካሄድ ዘረፋ መካሄዱ ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡ እኔው እራሴ ባስተዋወቅኩላቸው መሰረት አ.አ መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ የእውቅና ፍቃድ ባለስልጣን መካድ የማይችሉትና በመረጃ ላጋልጣቸው የምወደው የስራ መስኩ ከፍተኛ የሰው ኃይል ይፈልጋል ተብሎ ስልጠና
  • 18. የተጀመረባቸው መስኮች housholed service, domestic help and care giving ላይ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ተቋማቱን በእውቅና ፈቃድ ወቅትም ይሁን ፍቃድ ተሰጥቷቸው ከጀመሩም በኃላ እየተፈጠረ ያለውን ችግር በስልጠና ሊፈታ ይቅርና እራሱ በቴክኔክና ሙያ ሕጎችና አሰራር ላይ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ እየተሰራበት ያለው አግባብም ትክክል አለመሆኑን በሰኔው ስብሰባ ላይ አቅርቤያሉ፡፡ ይህውም CoC የሙያ ደረጃ የወጣላቸውን የምዘና ቱል ባለማውጣቱ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እስካሁን ባለመፈተናቸው መጉላላታቸው፡፡ ነገርግን አሰራሩ በሀገር አቀፍ በስትራቴጂው እንዲሁም በአለም ዓቀፍ ደረጃ ፍቃድ የተሰጣቸውን TVETs Declaration መጣስ ነው (የሰውልጅ የመማር መብት)፡፡ ይህውም CoC ኃላፊዎች በሰርኩላር ደብዳቤ ሲበትኑ ከስምንተኛ ከፍል በታች መሰልጠን አይችሉም ተብሎ የወጣው ሕግን የጣሱት፡፡ የጠቀስኳቸው የስልጠና መስኮች housholed service and domestic help የማቃቸው የተማርኳቸውና ሆም ኢኮኖሚክስና / home economics and በኋላላይ hotel service ሲባል ሰልጥኜ ያስተማረኩት ትምህርት ብቻ ሳይሆን አሁንም አብረውኝ የተማሩት በኮሌጅ ደረጃ የሚያስተምሩት ከዚህ በፊት አብረውኝ የተማሩት ጓደኞቼ ናቸው፡፡ በመሆኑም አዲስ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት የወሰዱ ተቋማትን ለመመዘን ከመሄዳችን በፊት ብዥታችንን በጠረጼዛ ዙሬያ መቅረፍ ነበረብን፡፡ ሁለቱም የስልጠና መስኮች የማሰልጠኛ ሞጁሎች ዝግጅት የጎላ ልዩነት ባይኖራቸውም ሞጁሎቹ ግልጸኝነት እነዲኖራቸው የማጣቀሻ መጽሀፍ የጎደላቸውን ስታንዳርዶች በማካተት በመስራት ላይ ነኝ፡፡ በdomestic help የሚሰጠው የስልጠና መስክ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ለሀገር ውስጥ የቤት ውስጥ ሰራተኞች ማሰልጠን ማለት ነው፡፡ የከተማው
  • 19. ኢንስፔክተሮች ስህተታቸውን ለማረጋገጫ በበተኑት ግብረመልሶች ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን የእውቀት ክፍተት መኖሩን መረዳት ይቻላል፡፡ ባለማወቅ በከተማ ደረጃ የተቋቋመው እና ተግባራዊ ያደረገው የኢንስፔክሽን ቡድን የሰጡት ግብረመልሶች እንዲህ ባለማወቅ የተሰጡ በመሆናቸው ያሳፍራሉ፡፡ በራሳቸው ስህተት የተባረሩም ተቋማት እንዳሉ በየክፍለከተማው መረጃው አለ፡፡ በመሆኑም ይህ ስልጠና የሚሰጠው ለውጭ ሀገር ተጓዦች ብቻ ሳይሆን ለሀግር ውስጥም የሰለጠነ የቤት ሰራተኛ ለማፍራት ነው፡፡ የሀገር ሰው የሰለጠና የቤት ሰራተኛ አይወድለትም ያለው ማነው? ወይስ ወገኖቻችን ሄደው ለሚሰቃዩበት የውጭ ሀገር ተጎዥን ለማብዛት ብቻ ነው መሰራት ያለበት? አሰራሩ ውጡልኝ ብቻን የሚያበረታታ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የእስካሁኑ ማነቆ የሆነው የዚሁ ዘርፍ አሰራር ለኃላፊዎች ከሰው አዘዋዋሪዎች የሚሰጥ ድጎማ ከፍተኛ ስለሆነ ነው አሰራሩ እንዲበላሽ ተደረገው፡፡ በተግባር እንደታየው አሰራሩ ስትራቴጂውን መጣሱን የሚያመለክተው ከስምንተኛ ክፍል በታች ቴክኒክና ሙያ እንዳይሰለጥኑ መከልከላችን የሰልጣኝ ሰበአዊ መብትን መጣስ ነው፡፡ በስህተት የተሰሩ መሻሻል ያለባቸውን እጅግ በጣም በርካታ የአሰራር ማነቆ ሳይፈታ ለክትትልና ግምገማ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ላይ መላካችን ስህተት ነው፡፡ ተቀይሬ እየሰራሁበት ባለው ክፍለ ከተማ ከነበርኩበት ክፍለከተማ ጋር ተደምሮ ክፍተቱን ስር የሰደደ ስለሚያደርገው አሁን የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል ወደፍረጃ ከመግባታችን በፊት ችግሮቹን ለመፍታት በጠረጼዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን በውይይት መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ላይ ለስብሰባ የጠሩት ኃላፊውችን ብቻ ሲን ምንመክረው ምን እንደሚያሻሽሉ አይታወቅም፡፡
  • 20. Aysheshim Tilahun ብሬ፣ የሚሰሩትን አላሰራ ማለት እኮ አዲስ አይደለም። አሁን አንተ disappointed መሆንህ ለጠቀስከው አይነት ሰው የመጀመርያ ስኬቱ ነው። እውቀት ነክ የሆነ ነገር ላይ ሰርተህ ብትከብር ደስ ሊለው ሲገባ በአስተሳሰብ ክፍተቱ በመጣ አግላይ እና አውሬ አመለካከቱ አንተ ተሰፋ ባለመቁረጥ ለውጥ በመምጣት አሳየው እንጂ ንዴትህን አታሳየው። I know your capacity. Working on knowledge and technology transfer and getting a fortune out of it is the antithesis of collecting money on expense of the desperate. please use those guys as reason to go forward. Focus on your job. Do those things with people who are positively energized. Berhanu Taye Maza • Aysheshim Tilahun thank you my adviser! I respect and accept your recommendations. Since you gave me constructive advice now and then, I'll apply it properly. If your advice is correct. But what I would like to tell you is I never quite if the ting is goes in the wrong direction. I will fight until the situation become right. Straggling is the real meanings of life but get the better of (Prevail over) in the hands of Good indeed! I never and ever quite my fight based one facet and truth event. thanks to God! Good news for us is I published three reference books for TVET trainees with conceltancy. Brother Ayshe you are the one who work with me Addis Ababa University and me also publised in elctronics media hence, we'll publish our books together besed on your progress after September by the will of God. I started the draft you'll update it as you and your colleagues want. Respectfully yours! • Aysheshim Tilahun anytime brother!
  • 21.   Berhanu Taye Maza አይሽዬ የሚከሰቱትን ነገሮች እንደተራ ነገር ነው የምቆጥረው። ማስታወሻ ለመያዝ ያክል ነው። አንጂ ለነዚህ በንፋስ ብቻ የሚጠፉ አቧራዎች አልጨነቅም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በከፋ ለረዥም ጊዜ ወያኔ በገባሁበት በመግባት ያለምንም መረጃ ከስራ እያባረረኝ የምበላው አጥቼ ቤተሰቤ ሲበተን አይቻዋለሁ፡፡ ይህ ግፍ በኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ንጹሃን ላይ እንዳይቀጥል በማሰብ ነው ሰላማዊትግሌን የቀጠልኩት፡፡ ውጤቶቹም ለሰራተኞች የስራ አፈጻጸም በማዛባት ኃላፊ መሆን የማይገባቸው ለሰራተኞች የስራ አፈጻጸም የሚሰጡት በስራና በመመሪያ ሳይሆን ባልተገባ ተግባቦት ብቻ የስራ አፈጻጸም ውጤት ሲያዛቡ ይስተዋላሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ስራና ሰራተኞች ሲበደሉ ይስተዋላል፡፡ አሁንም እንደዚህ ከፍተኛ ጥፋት አጥፍተውና ስራን አበላሽተው ለራሳቸው ከፍተኛ ውጤት ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም ለራሳቸው የሰጡት በአዲሱ ምደባ ላይ ተጽእኖ እንደሚፈጥርና እነዚሁ ስራ የሚያበላሹ ሰዎች የኃላፊነት ቦታውን ተመድበው አሁንም ስራ እንዳያበላሹ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡ ይህ ስጋት በመጨረሻ ላይ እውን ሆኗል፡፡ የሚታይ ስራ መስራት ነው የሚያስፈልገው "አቧራ ሳይሆን አሻራ ለመሆን የተሰራ ስራ" አንደ መንፈሳዊ ፈረንሳዊት ኦሮቪል ፍልስፍና ከሆነ በደራሲ ተከስተ ብርሃን ገ/ኪዳን በማብራራት እንደተፃፈው ክሆነ "ለመሞት ከመኖር ለመኖር መሞት ይሻላል" ብለዋል፡፡ ያ ያሉት ትልቅ ቁምነገር ያዘለ አነጋገርም ደርሶኛል፡፡ ዕውነት ነው፤ መጀመሪያ እግዚአብሔር ያደለው እንጂ ማንም ሰው ለዘላለም
  • 22. የማይሞት ሥራ መስራት አይችልም፡፡ ስለዚህ ሰው ወደዚህ ዓለም መጥቶ ምንም ሳይሰራ ከሚሞት ለዘለዓለም ስሙን የሚያስጠራ ስራ ለመስራት መታደል ታላቅነት ነው፡፡ ቢሆንም ይኽ አነጋገር በጣም ከበድ ያለና በብዙ መልኩ ሊተረጎም የሚችል መሆኑን አስተውያለሁ፡፡ በኃላፊነት ተመድቤ ስራቸውን ስከታተል የነበሩት ኢንጂነሮች ስራቸው ከአጀማመራቸው ሕያው ሊሆንላቸው እንደሚችል መመረቂያ ጽሁፌን ስጽፍ በጽሁፍ አስቀምጬላቸው ነበር፡፡ እነዚሁ ኢንጂነሮች ሳይንጠራሩ ትልቅ ቴክኖሎጂ በአንድ ጊዜ ለመፍጠር ሳይሆን የአካባቢያቸውን ሕዝብ የአኗኗር ደረጃ በማየት ለመስራት የሄዱበት እርቀት እጅግ በጣም ነው ያስደመመኝና እኔም በትልቅ ኢንዱስትሪ ላይ ከምሰራ መነዚሁ ልጆች መስራት የመረጥኩት፡፡ በአካቢያቸው የሚኖረው ሲሰራበት የነበረው ከጉድጓድ ውስጥ አውጥተው ለጤናቸው አስቸጋሪ በሆነ መልኩ የሚሰራን ሸማ ስራን ወደተሻለ አሰራር ቀይረዋል፡፡ የምርታማነት ሰአታቸውንም አሻሸለውላቸዋል፡፡ በዚህም ረገድ በርካታ የተሻሉ ማሽኖችን በመስራታቸው ተሸላሚ የሆኑት፡፡ ኤቲኤም ኢንጂነሪግና ዶቤ ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዲስትሪ እድገታቸው የሚያስደስት ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ እድገታቸው እኔንም የሚያስደስተኝ ነው ምክንያቱም የመመረቂያ ጽሁፌን በመቀየር በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ የመመረቂያ ጽኁፉም ለቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች በካይዘን ፍልስፍና በማገናኘት እነሱ ከሰሩት ታላቅ የፈጠራ ስራ በተጨማሪ በኔ እየደከምኩላቸው ያለሁት ስማቸው በመማሪያነት ማጣቀሻ መጽሃፍነት እንዲውል ማድረግ ነው፡፡ ማለትም አቧራ ሳይሆኑ አሻራ እንዲሆኑ በመስራት ላይ ነኝ፡፡ በሁሉም የመማሪያ ሞጁሎች ላይ ማለትም ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 ከ 5 ኤሰ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የካይዘን አስተዳደር የሀገር ልጆች ስኬት
  • 23. የማቀርብበት ነው፡፡ የሁለቱም ኢንዲስትሪዎች እድገት እናንተን ብቻ ሳይሆን እኔንም ስትጀምሩ የነበራችሁበት ቦታ አብሬችሁ የነበርኩትን ጭምር የሚያኮራኝ ነው፡፡ አይሽዪ ተቆርቋሪዬ በርቱልኝ ከዚህ በላይ ከፍ ያድርግልኝ!......  Aysheshim Tilahun Thank you so much. And we Have to meet. I will call.