Publicité
Publicité

Contenu connexe

Publicité
Publicité

Training need assessment tot

  1. ለተቋማት ቴ/ሙያ ት/ስልጠና ጽ/ቤቶች ለአሰልጣኝና ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ሽሮ ሜዳ ቴ/ሙያ ት/ስልጠና ተቋም 2010 የስልጠና ፍላጐት ዳሰሳና የሥልጠና ዝግጅት 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  2.  የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ማካሄድ ይችላሉ፡፡  የሥልጠና ኘሮግራም ያካሂዳሉ ፡፡  የተለያዩ ማሰልጠኛ ዘዴዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡  የሥልጠና ግምገማ ያካሂዳሉ ፡፡  የሥልጠና ሪፖርት ያዘጋጁሉ፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  3. ምዕራፍ 1. የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳና ሥልጠና ዝርጀት፣ ምዕራፍ 2. የማሰልጠኛ ዘዴዎች አመርራጥ ፣አጠቃቀምና የአሰልጣኝ ክህሎቶች ፣ ምዕራፍ 3. የሥልጠና ግመገማና ሪፖርት አቀራረብ፣ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  4. የምዕራፋ ዓላማዎች ሰልጣኞች ይህን ምራዕፍ ሲያጠናቅቁ፤ የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ምንነትና አስፈላጊነትን ይገልፃሉ፡፡ የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ያካሂዳሉ፡፡ የሥልጠና ፍላጐቶችን በቅደም ተከተል ያስቀምጣሉ፡፡ የሥልጠና እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  5. 1. የሥልጠና ፍላጐት ምን ማለት ነው? 2. የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ምን ማለት ነው? 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  6. ቴ/ሙያ ት/ስልጠና ተቋማት ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች ወይም መ/ቤቶች ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የቆሙላቸውን አላማዎች ለማሳካት አሰልጣኝ / ሠራተኛው የሚጠበቅበትን እውቀት አና ክህሎት ተጠቅሞ በተግባር እየፈፀሙት ያለው የሥራ አፈፃፀም ውጤት መሆን ከሚገባው አንሶ የታየ የአፈፃፀም ልዩነት የስራ አፈፃፀም ችግር ወይም ፍላጐት ይባላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  7. የስልጠና ፍላጐት ዳሰሳ  አሰልጣኞችና ሰራተኞች በሥራቸው የሚያጋጥሟቸውን የሥራ አፈፃፀም ችግሮችን ለመረዳትና ለመለየት የሚያደርጉት የዳሰሳ ሂደት ነው፡፡  ይህ ሂደት በማሰልጠኛ ተቋማት ወይም ማንኝውም መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄደውን የሥራ ሂደት በመከታተልና መረጃ በመሰብሰብ የሚደረግ ዳሰሳ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  8. ሀ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም ማንኝውም መ/ቤት የሚጠብቀውን የሥራ አፈፃፀም ውጤት በመፈተሽ መለየት፣ ለ/ እየተተገበረ ያለው የሥራ አፈፃፀም ውጤት በመፈተሽ መለየት ፣ ሐ/ አስተያየቶችን ማዳመጥ እና በአግባቡ መዝግቦ መያዝ፣ መ/ ምክንያቶችን በየወቅቱ መለየት ፣ ሠ/ መፍትሔዎችን በጊዜው መለየት ፣2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  9. ተቋማት ወይም መ/ቤቶች የቆሙላቸውን አላማዎች ለማሳካት አሰልጣኝና ሠራተኛው የሚጠበቅበትን እውቀት፡ ክህሎት፡ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወዘተ… ተጠቅሞ በመሥራት ሊፈጽመው የሚጠበቅበት ውጤት ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  10. ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም ማንኝውም መ/ቤቶች የቆሙላቸውን አላማዎች ለማሳካት ሠራተኛው የሚጠበቅበትን እውቀት እና ክህሎት ተጠቅሞ በተግባር እየፈፀሙት ያለው የሥራ አፈፃፀም ውጤት መሆን ከሚገባው አንሶ የታየ የአፈፃፀም ልዩነት የስራ አፈፃፀም ችግር ወይም ፍላጐት ይባላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  11. የእውቀት፡ የክህሎትና የአመለካከት ችግሮች፡ የቴክኖሎጂ ፡የቁሳቁስና የመሳሪያዎች ችግሮች፡ የአሰራር ሂደት ችግሮች ፡ ወዘተ… ናቸው የሥራ አፈፃፀም ችግር ወይም ፍላጐት የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  12. የእውቀት የክህሎትና የአመለካከት ችግሮች በሥልጠና ሊወገዱ የሚችሉ ሲሆኑ የተቀሩት የሚጐድለውን በማሟላት ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሐ/ አስተያየቶችን ማዳመጥ ይህ ሂደት በአንድ መ/ቤት ውስጥ የታዩ የስራ አፈፃፀም ችግሮችንና የተጀመረ አዲስ ቴክኖሎጂ ካለ ሠራተኞችን የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎችን በችግሩ ዙሪያ ያላቸው አስተያየት በማዳመጥ መረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  13.  ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም በአንድ መ/ቤት ውስጥ በአሰራር ለታዩ ችግሮች ምክንያታቸውን ማወቅ የችግሩን ምንጭ ለመለየትና መፍትሄውን ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ሠ/ መፍትሄዎችን መለየት መፍትሄ የተፈጠሩትን የስራ አፈፃፀም ውጤት ችግሮች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማስወገድ የሚያስችል ክንውን ነው፡፡ o እንደየችግሩ ባህሪ የተለያዩ መፈትሄዎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የቁሳቁስ ፣የክህሎትና የአመለካከት ችግሮች በስልጠና ማስወገድ ወይም መቀነስ የቁሳቁስና የመሳሪያዎች እጥረቶች ደግሞ እጥረቶችን በማሟላት ችግሩ ሊፈታ ይችላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  14. 1ኛ. ችግሩ መኖሩን ማለየት 2ኛ. የችግሩን ምንጭ መለየት 3ኛ. የችግሩን መፍትሄ መለየት 3.1. በስልጠና የማይፈቱ ችግሮች 3.2. በሥልጠና የሚፈቱ ችግሮች በአጭሩ የስልጠና ዳሰሳ ሂደት በሚከተለው ሁኔታ መግለጽ ይቻላል 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  15. የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ አስፈላጊነት ምንድነው ? በ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም መስራቤት ስልጠና ከማካሄዳችሁ በፊት የስልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ታካሂዳላችሁ? የስልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ሳይካሄድ ስልጠና መስጠት የሚያስከትላቸው ችግሮች ምን ምን ናቸው? 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  16.  ሥልጠና በርካታ ገንዘብ፣ ቁሳቁስና የሰለጠ የሰው ሃይል የሚያስፈለገው ውድ ተግባር በመሆኑ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም መ/ቤቶች ደግሞ ያላቸው ሃብት ውስን በመሆኑ ይህንን ውስን ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም በመ/ቤቱ ውስጥ በተጨባጭ ያለውን ችግር በማጠናትና ችግሩን ለመፍታት ምን አይነት ስልጠና መሰጠት አንዳለበት ለመለየት የተለያዩ ስልጠናዎች ካላቸው ጠቀሜታና ካለው ውስን ሃብት አኳያ በቅደም ተከተል በማስቀመጥ ለመተግበር የስልጠና ፈላጐት ደሰሳ ማድረግ ወሳኝነት አለው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  17. የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ አስፈላጊነት ከዚህ በታች ያሉትን መከተል ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ ሥልጠና ለመስጠት ጠቀሜታ አለው 1. የስልጠና ፍላጐት መለየት፤ 2. ሥልጠና መሰጠት ለማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኝ ወይም ለማንኝውም ድርጅቱና ለሰራተኞች ጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ፤ 3. የሥልጠና ፍላጐቶች ካላቸው ጠቀሜታና ከወጪ አኳያ በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ፤ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  18.  በዚህ የዳሰሳ ሂደት ውስጥ በአሰልጣኝና ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም ችግሮች ላይ የአቅም ማነስ እንደ ዋነኛ ችግር ሆኖ ከተለየና ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኝ ወይም በማንኝውም መሥሪያ ቤት ውስጥ ሠራተኞች ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመፈፀም ሥልጠና እንደሚያሰፈለጋቸው ፈላጐት ካሳዩ ሥልጠና አንደዋነኛ መፈትሔ ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ይህ ሂደት የሥልጠና ፍላጐት ዳሰሳ ይባላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  19. የሥልጠና ፍላጐት የአንድን መሥሪያ ቤቱ ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ 1. የአጭር ጊዜ 2. የረጅም ጊዜ ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  20. ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም መ/ቤት እየተገበራቸው ያሉት ተግባራትና ያስቀመጠቸጣቸው ግቦች ከማሳካት አኳያ የአፈፃፀም ችግሮች ሲሆኑ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች በሥልጠና መፈታት ሲቻል ነው ለምሳሌ ፡- በርካታ ተማሪዎች ባሉበት ክፍል ውስጥ ተማሪን ማእከል ያደረገ የማስተማር ዘዴ በመተግበር ረገድ የሚቸገር አስተማሪ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  21. ማሰልጠኛ ተቋም ወይም በማንኝውም አንድ መ/ቤት •በስራው የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ •የፖሊሲ የቴክኖሎጂ እና የአደረጃጀት ለውጥ ለማድረግ ቢያስብ •በቀጣይ በቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም መ/ቤት ያለውን የስራ ባሕሉን ለመለወጥ ቢፈልግ አሰልጣኝ ወይም ሰራተኛው ወደ አዲሱ የአሰራር ሂደትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለመሸጋገር የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመቅረፍ እንደሚቻል ከተረጋገጠ ከረጅም ጊዜ አኳያ የስልጠና ፍላጐት ይባላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  22. 1.3 የስልጠና ፍላጐት ዳሰሳ በተለያዩ ደረጃዎች 1.3.1 በቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም የመስሪያ ቤት የሥልጠና ፍላጐት 1.3.2 የአሰልጣኝና የሰራተኛ የሥልጠና ፍላጐት 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  23. የስልጠና ፍላጐት ስርዓት ባለው መንገድ ከመንጩ ለማሰባሰብ የሚከተሉትን መሳሪያዎች መጠቀም ይቻላል ሀ. ቃለ መጠይቅ፣ ለ. ምልከታ ማካሄድ፣ ሐ. የቡድን ውይይት፣ መ. የጽሑፍ መጠይቅ፣ ሰ. በድጋፍና ክትትል ወቅት ቼክሊስት / መጠይቅ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  24.  አሰልጣኙም ይሁን ሰራተኞች በሚሰሩት የስራ ዘርፍ ውስጥ የሚያጋጥማቸው ችግሮችንና የሚያስፈለጓቸውን የስልጠናዎች ፈላጐቶችን ለማሳባሰብ ከሰራተኞች ስርናት ባለው መንገድ በመመረጥ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ፍላጐታቸውን ማጠናት የመንችልበት ዘዴ ነው፡፡  ቃለ መጠይቅ እንደሁኔታው በአካል፡ በቴሌፎንና በኢሜይል ወዘተ… ማካሄድ ይቻላል፡፡ ሀ. ቃለ መጠይቅ፣ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  25.  መረጃ ሰብሳቢው ሰራተኞች በሚገኙበት ቦታ በመሄድ ስራቸውን ሲያከናውኑ በመመልከት የስራተኞችን የሥራ አፈፃፀም ሁኔታና የሚታዩ ችግሮችን የሚከታተልበት ሂደት ነው፡፡ ይህ ማለት የላቀ የስራ አፈፃፀም ያላቸውን፡መካከለኛ የስራ አፈፃፀም ያላቸውን አና በስራ አፈፃፀማቸው ችግር ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት የተለያዩ የስራ አፈፃፀም አንዲኖር ያደረገበትን ምክንያት በመለየት መረጃ መሰብሰብ ያስፈለጋል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  26.  ሶስት ወይም ከዛ በላይ በመሆን በጋራ ተሰብስበው ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ በቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኝ ወይም በማንኝውም መ/ቤ ከሰራተኛው የሚጠበቀው ውጤት፣ አሰልጣኛች ወይም ሰራተኞች በተግባር እየፈፀሙት ያሉው የስራ አፈፃፀም ውጤት ፣ ለተፈጠረው የስራ አፈፃፀም ውጤት ምክንያቶቹ አና ወዘተ… ጉዳዩችን በማየት የስልጠና ፈላጐትን ለመዳሰስ አንደ አንድ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  27. በቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች ወይም በማንኝውም መስሪያቤት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች በስራቸው ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሟቸው ችግሮችና ችግሮችን ለመፈታት የሚያስፈልጓቸው የስልጠና አይነቶችን የጽሑፍ መጠይቅ በማዘጋጃት የስልጠና ፈላጐቶችን ለመለየት የመንጠቀምበት ሌላኛው መሳሪያ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  28. በድጋፍና ክትትል ወቅት ቼክሊስት / መጠይቅ በማዘጋጀት የስራ ውጤት በየደረጃው ለይቶ መያዝና ውጤቱን በሪፖርት መልክ ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ እንደሚታወቀው በግል፣ በመንግስትና በመያድ ቴ/ሙ/ማ/ ተቋሞቻችን ቼክሊስት በማዘጋጀት በየዓመቱ ሲጎበኙ የማሰልጠኛ ማቴሪያል ለሰልጣኝም ይሁን አሰልጣኙ እራሱ በተሟላ መልኩ እንደሌለ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑም ልየታው ያካተተው 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  29. 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  30.  በቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ወይም በማንኝውም መ/ቤት ያለው ሃብት ከተለዩት የሥልጠና ፍላጐቶች ጋር ሲነፃፀር ውሱን ሊሆን ስለሚችል ሁሉንም የሥልጠና ፍላጐቶች በአንድ ግዜ ለማካሄድ ስለማይቻል ማሰልጠኛ ተቋማት የሥልጠና ፍላጐቶችን በቅደም ተከተል በማስቀመጥ አቅድ አውጥቶ መፈፀም ያስፈለገዋል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  31. ለምሳሌ ፡- የመማሪያና ማስተማሪያ ማቴሪያል (TTLM) ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ማዘጋጀት፣ ከቴክኖሎጂው ጋር ለማላመድ አጫጭር ስልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኞች አማረኛ ቋንቋን መኮምፒውተርላይ እንዲጽፉ ማስቻልና ለደረጃ አሰልጣኞች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ት ጥራት ለማሻሻል መምህራን የአጭር ሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ቅድሚያ ሰጥቶ በመፈፀም ሌላው የረጅም ግዜ አቅድ በማውጣት በሂደት መፈፀም ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም የቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት የስልጠና ፍላጐቶችን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ መስፈርቶችን በመለየት የሚፈጽመው ይሆናል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  32.  የቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ዓላማ ከማሳካት አኳያ ከፍተኛ እንቅፋት የሆኑትን፣  ባለው ሃብት የሰው ሃይለና ቴክኖሎጁ በቀላሉ ሊፈፀሙ የሚችሉትን፣  ከጊዜ አኳያ በአጭር ጊዜ ቢተገበር የቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት ዓላማዎች ለማሳካት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ፣  ሥልጠው ሲካሄድ የቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማት እንቅስቀሴ ከማስተጓጓል አኳያ ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውን፣ ወዘተ … የሚያሟሉትን ቅድሚያ በመሰጠት በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ይቻላል፡፡2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  33.  የስልጠና ፈላጐት ከተለየ በኋላ ቀጣዩ ሂደት የሥልጠና እቅድ ማዘጋጀት ይሆኖል፡፡ የእቅዱ ይዘትም  የስልጠናውን አላማ መወሰን፣  የስልጠና ይዘት መወሰን ፣  ለሰልጣኞች የሚሆኑ ጽሑፎችና ሌሎች ግብአቶች ማዘጋጀት ፣  የስልጠና ዘዴዎችን መመረጥ ፣  የስልጠናው ኘሮግራም አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ፣  የስልጠና ክትትልና ግምገማ ማካሄድ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  34. የምእራፍ ዓላማዎች የማሰልጠኛ ዘዴዎች መምረጫ መስፈርቶችን ይገነዘባሉ፡፡ የተለያዩ የማሰልጠኛ ዘደዎችን ይለያሉ፡፡ በየሥልጠኛ ኘሮግራናሞች ተስማሚ የማሰልጠኛ ዘዴዎችን በመለየት ይጠቀማሉ፡፡ የአሰልጣኝ ክህሎቶችን በሥልጠና ላይ መጠቀም ይችላሉ፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  35.  የአንድን የሥልጠና ኘሮግራም ውጤታማነት ከሚወስኑት ዋና ጉዳዩች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡  ስልጠና ገና ሲታቀድ ጀምሮ ስለማሰልጠኛ ዘዴው አብሮ ማሰብ መጀመር በጣም አስፈላጊ ነው መክንያቱም የማሰለጠኛ ዘዴ  ከሥልጠናው ዓላማ፣  የስልጠናው ይዘት ፣  የስልጠናው አይነት፣  ለማሰልጠኛ ገንዘብና ጊዜና ፋሲሊቲ  ከአሰልጣኞች ዓይነት ወዘተ…ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  36. 1. ሰብአዊ ሁኔታዎች፣ 2. የሥልጠናው ዓላማ፣ 3. የስልጠናው ይዘት ወይም የት/ቱ አይነት፣ 4. ለማሰልጠኛ የተሰጠው ጊዜ ገንዘብና ማቴሪያል …ናቸው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  37. ሀ. የአሰልጣኞች አይነት፣ ለ. የሰልጣኞች አይነት፣ ሐ. የሰልጣኞች ማሕበራዊና ባሕላዊ አካባቢ 2. የስልጠናው አላማ አብዛኛውን ጊዜ የስልጠና ዓላማዎች በሶስት ነገሮች ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይችላል፡፡ እነዚህም -  እውትን ማስጨበጥ(Knowledge) የክህሎት(Skill training) የአመለካከት(attitude training) ናቸው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  38. የተለያዩ የሥልጠና ይዘቶች ወይም የሙያ ዓይነቶች እንደየ ባሕሪያቸው የተለያዩ የአሰለጣጠን ዘዴወች ያስፈለጋሉ ፡፡ የማሰልጠኛ ግብዓቶች 1. ጊዜ 2. የማሰልጠኛ ገንዘብ 3. የማሰልጠኛ ፋሲሊቲዎች 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  39. ከበርካታዎቹ የማሰልጠኛ ዘዴዎች በቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ዘርፍ የሚገኙ አሰልጣኝና ባለሙያዎች ለማሰልጠን የምንጠቀምባቸው የማሰልጠኛ ዘዴዎች ዋና ዋናዎቹ 1. የቃል ገለፃ 2. የቡድን የስልጠና ዘዴ 3. የጭብጥ ጥናት የማሰልጠኛ ዘዴ 4. በተግባር የማሰልጠኛ ዘዴ 5. የኘሮጀክት ሥራ በማለማመድ የማሠልጠን ዘዴ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  40.  አንድ ስልጠና ግቡን እንዲመታና ከታለመለት ዓላማ ላይ አንዲደርስ የስልጠና ሂደቱን ከሚመራው አሰለጣኝ ብዙ የሚጠበቁ የስልጠና አመራር ችሎታዎች ሊኖሩ ይገባል  በአጠቃላይ ሲታይ አንድ አሰለጣኝ ሶስት ብቃቶችን (Competence) እንዲኖሩት ያስፈለጋል፡፡ 1. የውይይት ርእስና ይዘትን ማወቅ 2. የውይይት አቀራረብ ዘዴን መቅረጽ 3. የግል ባሕሪያዊ ስሜትን ማስተዋል 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  41.  በስልጠና ጊዜ ተሳታፊዎች በሚቀርበው ርአስ ሃሳባቸውን አንዲያቀርቡ ወይም እንዲተገብሩ የሚከተሉትን አራት የማሰልጠን ክህሎቶች መጠቀም ጠቃሚ ነው፡፡ 1. ጥያቄዎች ማቅረብ 2. የተባለን ሃሳብ በሌላ መንገድ መድገም 3. ሃሳቦችን ማጠቃለል 4. ማበረታታት 5. በሥልጠና ጊዜ የማነቃቂያ አይነቶችና አጠቃቀም 6. ዓይን ገላጭ 7. በስልጠናው መካከል የሚደረግ ማነቃቂያ 8. ወደ ዋናው ስልጠናና ትመህርት ይዘት የመሳብ ዘዴ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  42. ከዚህ ምእራፍ ፍፃሜ በኋላ  የሥልጠና ግምገማ ዓይነቶችን ይዘረዝራሉ የሥልጠና ግምገማ የትኩረት ነጥቦችን ይለያሉ የሥልጠና ሪፖርት በጥራት ያዘጋጃሉ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  43. በየቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ተቋማችሁ የሥልጠና ግመገማ የሚካሄደው በምን አይነት መንገድ ነው ገምጋሚው አካል ማን ነው የግመገማው ተከታታይነትስ ምን ይመስላል 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  44.  ስልጠና በእቅድ የሚመራና ከዓላማ አንፃር የሚካሄድ በመሆኑ የሚፈለገውን ውጤት ስለማምጣቱ መገምገም አንዱ የሥልጠና ሂደት አካል ነው፡  በመሆኑም አሰለጣኞች ከስልጠና በፊት በስልጠና ጊዜ የስልጠና ኘሮግራምና አንዲሁም ከስልጠና በኋላ ሰለጣኞች ወደ ስራ ከተመለሱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በስራቸው ላይ ያሳዩትን ለውጥ ሊገመገም ይገባል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  45. የቅድመ ስልጠና ግምገማ የሚካሄደው ሰልጣኞች ያላቸውን ክህሎትና ልምድ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ተመሳሳየነት ስልጠና መውሰዳቸውና አለመውሰዳቸውን ለማወቅ አሰልጣኞች የሚሰጡት ስልጠና፣ ከስራ ሃላፊነታቸውና ከትመህርት ደረጃቸወ ጋር የሚመጣጠን ሥልጠና ለማዘጋጀት አንዲረዳ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  46. ይህ ስልጠና ለሚሰጠው የስልጠና ሂደት የቦታው የአቀራረቡ የማቴሪያል አቅርቦት ወዘተ ጉድለቶች ካሉ በየቁኑ እየተከታተሉ ለማስተካከል ከተሳታፊወች በወረቀት በቃል ሃሳባቸውን አንዲገለፁ በማድረግ የሚካሄድ ነው፡1 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  47. ይህ ግምገማ የስልጠናው ኘሮግራም በሚያበቃበት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊ ወች በተካሄደው ሥልጠና ላይ ያገኙትን አውቀት ክህሎት ልምድና የእርካታቸውን መጠን የሚገልፁበትና ለወደፊቱ መደረግ የሚገባውን የማሻሻያ ሃሳብ የሚያቀርቡበት ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  48.  ስልጠና የወሰዱ አካላት ተፈላጊውን አውቀት፣ ክህሎትና የአስተሳሰብ ለውጥ አግኝተው ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ በሚሰጡት አገለግሎት መሻሻል / ለውጥ ማመጣታቸውን የምንከታተልበት ሂደት ነው፡፡  የተሰጠው ስልጠና የሚያስገኙው መሻሻል ለውጥ Impact ዓይነተ የተለያየ በመሆኑ በአጭር በመካከለኛ ጊዜና በረዥም ጊዜ መገመገም የቻላል  የግመገማው ሂደትም ተከታተይነት ያለው ሊሆን የገባል፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  49. የስልጠና ሪፖርት ስልጠናው ካበቃ በኋላ ስልጠናው ከመጀመሪያ አስከ መጨረሻው አንዴት አንደተካሄደ የሚገልጽ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  50.  የሥልጠና ዓይነት  የስልጠናው ዓላማ  የሥልጣኞች ዓይነትና ብዛት  የሥልጣኞች ብዛትና የመጡበት ቦታ  የሥልጠናው ይዘት የአመራር ይዘቱ አሰልጣኝና ፍፃሜው  የሥልጠና ጊዜና ቦታ  ሥልጠናውን ያዘጋጀው አካል  የሥልጠናው ዘደዎች  የተሳታፊዎች የግመገማ ውጤት  በመጨረሻም ሪፖርቱ ላይ በገንዘብም ሆነ በማቴሪያል አገዛ ላደረጉ አካላት አንዲደርስ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  51. 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  52. 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
  53. አመሰግናለሁ 2/19/2018Berhanu Tadesse Taye
Publicité