ይህ ስልጠና ከበይነመረብ እና ዓለም ዓቀፍ ድር አሳሽ ጋር የተያያዙ መሰረታዊ የኮምፒውተር ቃላትን ያብራራል። በይነመረብ ስለሚያቀርባቸው የተለያዩ የመገናኛ መገልገያዎች እና በዓለም ዓቀፍ ድር ላይ መረጃ የማግኛ ዘዴዎችን ይገልፃል። ይህ ስልጠና ስለ ኢ-ኮሜርስ (e-commerce) ጽንሰ ሃሳብም ያብራራል።