SlideShare une entreprise Scribd logo
1  sur  33
Télécharger pour lire hors ligne
የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት




በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ዙርያ   የተደረገ
           ጥናት ሪፖርት




                      መጋቢት 2004
ማውጫ
ገጽ
1.ማጠቃለያ ................................................................................................................................................... 1
2.መግቢያ ...................................................................................................................................................... 4
3. ዓላማው .................................................................................................................................................... 5
4.የጥናቱ አስፈላጊነት.................................................................................................................................... 5
5.ዝርዝር ዳሰሳ.............................................................................................................................................. 6
     5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞን.............................................................................................................. 6
     5.2. ጅጅጋና አካባቢው.............................................................................................................................. 8
        5.2.1. ቶጎ ውጫሌ ............................................................................................................................... 9
ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳት ብዛትና
የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ.................................................................................10
        5.2.2. ሀርትሼክ.................................................................................................................................. 10
     5.3 አፋር ክልል...................................................................................................................................... 11
     5.4.ትግራይ ክልል................................................................................................................................... 12
        5.4.1. ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን) ............................................................................................12
     5.5.አማራ ክልል...................................................................................................................................... 13
ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ ክልል በኮንትሮባንድ (በህገ ወጥ መንገድ) ወደ
ሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳት ........................................................................................................ 14
     5.6.ሞያሌ ................................................................................................................................................15
6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች ..........................................................................................16
7.      ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች........................................................................................................... 17
8.      በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች .................................................................................................... 18
9.      ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች...........................................................................................19
10.የኳራንቲን አገልግሎት ..........................................................................................................................20
ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ
2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት ................................................................................................................... 1
ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ
2004) ............................................................................................................................................................ 2
ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብር ....................................................................................................... 3



                                              የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                                                                               Page ii
1.ማጠቃለያ


የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በአፋርና በትግራይ (ሁመራ) ክልሎች የጸረ ኮንትሮባንድ
ጥምር ኮሚቴ እስከታችኛው ቀበሌ እርከን ድረስ በተቀናጀ መልኩ ከአገር ሽማግሌዎችና መላው
ህብረተሰብ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ
በመወያየት የጋራ አቋም በመያዙና ወደ ተግባርም በመግባት ውጤታማ ሥራ በማከናወናቸው
የመቀነስ ዝንባሌ ያሳያል፡፡

በሱማሌ ክልል፤በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ
በተመለከተ ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ተመስርቶ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረገ
ቢገኝም የጥምር ኮሚቴው እንቅስቃሴ ተከታታይነት የሌለው በመሆኑ፤ህብረተሰቡ በህገ ወጥ የንግድ
እንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤

ከዚህም በተጨማሪ ካለው ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰንና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት
የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው፤ ህዝቡ በጎሳ፤በእምነት፤በባህል የተሳሰረ
መሆኑ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ያለ መስራት ችግሮች ምክንያት የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ
እንቅሰቃሴ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለምሳሌ በህርትሼክና በሀርሺም መካከል ባለው መውጫ በር በብዙ ቁጥር የሚገመት እንስሳት በተለይም
በጎችና ፍየሎች ወደ ሱማሌ ላንድ እየወጡ ሲሆን ግመሎችና የቀንድ ከብቶች እንደቀደም ተከተላቸው
በብዛት እንደሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በአማራ ክልል በሽንፋ አቅጣጫ ወደ ቲሃ የሚወጣ የቀንድ ከብት በቀን አስከ 300 እንደ ሚወጣ
መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ይህም ምን ያህል አሳሳቢና በዓመት ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ማስላትና
የችግሩ ስፋት መገንዘብ አያዳግትም፡፡

በሞያሌ በኩል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ በተመለከተ እንስሳቱ ያለ ምንም እገዳ
እና ቁጥጥር ሳይደረግባቸው ሙሉ በሙሉ በህገ ወጥ መልኩ በቀን በአማካይ እስከ 500 የቁም እንስሳት
እንስት ከብቶችን ጭምር በኮንትሮባንድ አጎራባች አገር ወደ ሆነችው ኬንያ ይወጣሉ፡፡

በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND MEAT)
በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናት እንደሚያመለክተው በ2007 ዓ.ም ሱማሌ በበርበራና በቦሳሶ ወደብ በኩል
3.05 ሚሊዮን በጎችና ፍየሎች 200000 የቀንድ ከብቶች ለወጪ ገበያ ያቀረበች ሲሆን ከዚህ ውስጥ
ግማሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ እንስሳት መሆናቸውን በመጥቀስ በ2005-06 እ.ኤ.አ በኮንተሮባንድ
ለወጪ የቀረቡ እንስሳት 328000 የቀንድ ከብቶችና 1.1 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንደሆኑና ይህም
አገራችን በህጋዊ መንገድ ለወጪ ንግድ ካቀረበችው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥ የጥናት ጽሁፉ
ይጠቁማል፡፡

ከጅጅጋ ኳራንቲን ባለሙያዎች በተገኘው መረጃ መሰረት በህገ ወጥ መልኩ ወደ ሱማሌ ላንድ
የሚወጡት እንስሳት መጠን 80 ከመቶ እንደሚሆንና በህጋዊ መልኩ የሚወጣው 20 ከመቶ መሆኑን
መረጃው ያሳያል፡፡
በሠንጠረዥ 1.ላይ እንደሚያሳየው   በ2003 ዓ.ም በጅጅጋ በቶጎ ውጫሌ በኩል በድምሩ 96416 የቁም
እንስሳት በህጋዊ መንገድ በመላክ   34 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ
ከሚወጣው የቁም እንስሳት 20      ከመቶ ድርሻ እንዳለውና ሌላው 80 ከመቶ የሚሆነው ግን
በኮንትሮባንድ መልክ እንደሚወጣና   ችግሩም ምንያህል አሳሳቢ እንደሆነ መረዳት የቻላል፡፡

በአብዛኛው የጠረፍ አካባቢ የሚገኙ አጎራባች አገሮች ህጋዊ ንግዱን ከማበረታታት ይልቅ
የሚያዳክሙ መሆናቸውና በተዘዋዋሪ መልኩ ህገ ወጡን ንግድ የሚያበረታቱ መሆኑን
መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለአብነትም በህጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድ
ከብት ብር 400 ቀረጥ  የሚያስከፍሉ ሲሆን በኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻ
ማስከፈላቸው ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡

ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በኮንትሮባንድ መልክ ወደ አጎራባች
አገሮች እንደሚወጡና አገሪቷ ከዘረፉ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ እያጣች መሆኑን ለመገንዘብ
ይቻላል፡፡ስለዚህ ይህ ለአመታት የቀየ ችግር አሳሳቢና ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

በቁም እንሳሰቱ ግብይት ከፍተኛ አቅም ያላችውና በዋናነት ስራዬ ነው ብለው ወደ ስራ የገቡ ነጋዴዎች
ባለመኖራቸው ህገወጡን በማዳከም ህጋዊ ንግዱ አሸንፎ እንዲወጣና ህገ ወጦቹ ወደ መስኩ እንዲመጡ
አለማድረጉ በአገሪቷ የሰፈነው የኮንትሮባንድ ንግድ ጉልህ ማሳያ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንስኤዎችና ችግሮች በተመለከተ አስተማማኝ የገበያ
ትስስር በየአካባቢው አለመኖር ያሉት የስጋና የስጋ ውጤቶች ማደራጃ ወይም ቄራዎች እንስሳቱ
በሚገኝበት አካባቢ ሳይሆን በመሃል አገር ላይ ማዕከል ማድረጋቸው እና በሙሉ አቅማቸው
አለመስራታቸው፤ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ
የሚያበረታቱ መሆኑ፤ዋንኛ መንስኤዎች ሲሆኑ

ከዚህም በተጨማሪ የጠረፍ አካባቢዎች ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው፤ረዥምና ሰፊ
የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች
መኖራቸው እና በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተ
የተሳሰሩ መሆናቸው ለችግሩ መባባስ መንስኤ መሆናቸውን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ንግድን ለመቆጣጠር እንዲቻል ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን
የቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረት
እንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳት ዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ፤

የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም በአንዳንድ
አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ
ቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ
የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና የግብይት ስርዓቱን
የሚከታተልና የሚመራ የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት
መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡

በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት ከአጎራባች አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ህገ ወጡን
እንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ ፤የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ

                 የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት              Page 2
ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚና በህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክ
የሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ፤

በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እንደ አካባቢው መልካምድር አቀማመጥ
አስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይል፤የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀ
መልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም
የሚገታበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የግድ ይላል፡፡

ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የኳራንቲንና ኢንስፔክሽን አገልግሎት አሰጣጥ ሲሆን በአጠቃላይ
ክልሎቹ እንደገለጹት መመሪያውን ባልተከተለ መልኩ በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደ
መሆኑን እና መስፈርቱን የማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸው
እንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላ ከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡ
እና የደሙ እንስሳት በህጋዊ መንገድ በአብዛኛው ቦታዎች (አማራ ክልል፤ጅጅጋ፤ሁመራ) ከብቶቹ
ሳይታዩ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

ደረጃውን የጠበቀ ኳራንቲን ባለመኖሩ በገልፍ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸውን የቦረና
የቀንድ ከብቶችና የሱማሌ በላክ ሄድ (ዋንኬ) በጎች ወደ ጅቡቲ ከገቡ በኋላ በጅቡቲ ኳራንቲን ቆይተው
በጅቡቲ ስም እየተላኩ ጅቡቲ ተጠቃሚ እየሆነች ትገኛለች፡፡ስለዚህ ጥናት ተደርጎ ደረጃቸውን የጠበቁ
ኳራንቲን መገንባትና ተከታታይነት ያለው የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ስርዓቱን የጠበቀ
የኳራንቲን ጣቢያ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡




                 የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት             Page 3
2.መግቢያ


የእንስሳት ዘርፍ ለአለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለግብርና ክ/ኢኮኖሚ ያበረከተው አስተዋጽኦ 30%
እና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ደግሞ 16% ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል(የጽ/ቤቱ ዶኩመንት 2003) ፡፡
ሀገራችን እንስሳትንና የእንስሳት ውጤቶችን ለውጪ ሀገር ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ
የማግኘት አቅም ያላት ሲሆን ለአብነትም ያህል በስጋና በቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ባለፈው የ2003
በጀት ዓመት 210 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል፡፡

ይህ እያደገ የመጣው የቁም እንሰሳት ንግድ ግምት ውስጥ በማስገባትና ሌሎች ነባር ሁኔታዎች
በመመልከት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የመጪው አምስት ዓመት ዕቅድ በእንስሳት ሀብት ልማት
ዘርፍ ሥጋ አሁን ካለበት 10ሺ ቶን ወደ 111ሺ ቶን፣ የቁም እንስሳት 334ሺ ወደ ከ2.5ሚሊየን
በማሳደግ በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎረሜሽን መጨረሻ ዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ
ምንዛሪ ለማግኘት ዕቅድ ተይዟል፡፡

ሆኖም ግን ህገወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሃገሪቷ በተለያዩ የጠረፍ አካባቢዎች ተንሰራፍቶ የሚገኝ
ሲሆን በተለያዩ ህገወጥ መውጫ በሮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት ወደ ጎረቤት ሃገሮች
ሶማሊያ፣ ኬንያና ጅቡቲ እና ሱዳን እንደሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ በዚህ ጥናት Analysis of the Ethio-Sudan cross-border cattle trade:
The case of Amhara Regional State በሚል ርዕስ IPMS/ILRI እኤአ 2007 የተደረገው ጥናት
ከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ወደ 24,000 ዳልጋ ከብቶች በዓመት እንደሚወጡ እና ይህም እኤአ 2006
ዓ ም በመተማ ዮሐንስ በኩል በህጋዊ መንገድ ወደሱዳን የተላኩት ዳልጋ ከብቶች 60% መሆኑ
ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እኤአ ግንቦት                     20 1997 ጥናት
(Livestock Marketing and Cross Border Trade in the Southeast of   Ethiopia) መሰረት
በሁለቱ የሶማሊያ ወደቦች (በርበራና ቦሳሶ) በዓመት 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር              ዋጋ ካላቸውና ወደ
ውጭ ከሚወጡት እንስሳት ውስጥ ሰማኒያ ከመቶ ወይም 96 ሚሊዮን የአሜርካን                    ዶላር ዋጋ ያላቸው
ምንጫቸው ከኢትዮጵያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንሰራፋት መንስኤዎችም የተለያዩ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው
እንስሳት በህገወጥ መንገድ ከሀገራችን በመውጣታቸው እነዚህ እንስሳት በህጋዊ መንገድ ለአለም ገበያ
ቢቀርቡ ሀገራችን ማግኘት የምትችለውን    በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር    በአመት
በማጣት ላይ እንደምትገኝ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

በዋቢነት ለመጥቀስም በእንስሳት ገበያ ባለሥልጣን በ1993 ዓ ም በተደረገው ጥናት በደቡብ፤ ደቡብ
ምስራቅና ምስራቅ አቅጣጫዎች ወደ ጎረቤት አገሮች በሚደረገው ህገወጥ ንግድ በዋናነት (የቁም
እንስሳት) በዓመት ከአንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ ታጣለች፡፡

ስለዚህ ይህንን ችግር ለመቀነስና ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ከፍ ለማድረግ እንዲቻል
እና እቅዱን ለማሳካት የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ከገቢዎችና ጉምሩክ

                      የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                         Page 4
ባለስልጣን፤ከግብርና ሚኒስቴር፤ከንግድ ሚኒስቴር፤ከቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበር እንዲሁም ከሌሎች
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሀገሪቱ በተለያዩ የጠረፍ
አካባቢዎች ምን ይመስላል፤ዋና ዋና መውጫ በሮች የመለየትና በምን መልክ መቆጣጠር እንደሚቻል
በተለያዩ የክልል ከተሞች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ያሉት ጭብጥ ሁኔታዎች በማየት ሀገሪቱ ከዘርፉ
ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማሳደግ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች በማቅረብ የሚመለከታቸው
ባለ ድርሻ አካላት መመሪያዎቻቸውን በማስተካከል የጥምር ኮሚቴዎችን በማጠናከር እቅዱን ማሳካት
ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ መሆኑን በማስገንዘብ ይህ አጭር ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡


3. ዓላማው
የህገወጥ ንግድ መንስኤዎች መለየትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሆኑትን አቅጣጫዎችን በመንደፍ ባለ
ድርሻ አካላት በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ


4.የጥናቱ አስፈላጊነት
በዋና ዋና መውጫ በሮች በኩል እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ የእንስሳት ንግድ ላይ ጥናት በማካሄድ
ህገወጥ ንግዱን ሊቀንሱ የሚችሉ ተግባራዊ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ የተጠቀምንበት ስልት

     በቀጥታ ከሚመለከታቸው በወጪ ንግድ ከተሰማሩ ነጋዴዎች፣           ከክልሉ የመንግስት አመራር
      አካላት እና ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች( ጥምር ኮሚቴ ጋር ውይይት ተደርጓል
     በወጪ ንግዱ ዙሪያ የሚደረጉ የግብይት ሂደትና ስርዓት እንዲሁም የጤና ጥራት ቁጥጥርን
      ቦታው ድረስ በመሄድ ዳሰሳ ተደርገዋል
     ክፍተኛ የእንስሳት አቅርቦት በምንጭነት የሚያገለግሉ ቦታዎች ዳሰሳ ተደርጓል
     የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻና መውጫ በሮችን መለየትና ለችግሩ መባባስ ምክንያት የሆኑ
      ጉዳዮችን መለየት ተችሏል፡፡
      በጎረቤት ሀገሮች ያሉትን የገበያ ማዕከላት በመመልከት ከህገወጥ ንግዱ ጋር ያላቸውን ቁርኝት
      ለማጤን ተችሏል፡፡




                    የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት               Page 5
5.ዝርዝር ዳሰሳ

5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞን
ድሬደዋ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ከፍተኛ ህገወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች
ዋንኛው ሲሆን ከተማው የህጋዊ ወጪ ንግድ መተላለፊያ መስመር ሆኖም ያገለግላል፡፡

ቡድኑ በአካባቢው ከተቋቋመው ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት በድሬደዋና አካባቢው
የህገ ወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ራቅ ካሉት አካባቢዎች ማለትም ባሌ ፤ ቦረና
፤ አርሲ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ወዘተ ስፍራዎች ከመሃል አገር ሳይቀር በርካታ ቁጥር ያላቸው
የቁም እንስሳት ብዙ መንገድ አቋርጠው በዚህ አካባቢ በማለፍ በተለያዩ ህገ ወጥ መንገድ በተለያዩ ህገ
ወጥ መውጫ በሮች በመጠቀም ወደ ጅቡቲ፤ሱማሌ ላንድ እንደ ሚወጡ ለመገንዘብ ችሏል ፡፡

ከሚወጡትም የቁም እንስሳት መካከል እንስት የቀንድ እንስሳት፤የቀንድ ከብቶች ፤ (ጥጃዎች ፤
ወይፈኖች ) ፤አልፎ አልፎም ፍየሎችና በጎች እንዲሁም ግመሎችንም ይጨምራል፡፡ ቀደም ሲል በቀን
እስከ 200 መኪና ያላነሰ በኮንትሮባንድ ይወጣ እንደነበረና ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እየቀየረ መጠኑ ከፍ
እያለ የመጣ ቢሆንም ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የአካባቢው የጸረ- ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ተቋቋሞ ከዞን
እስከ ቀበሌ በመደራጀት እንቅስቃሴ በማድረጉ ህገ ወጥ ንግዱ በተወሰነ መልኩ መቀነሱን ከተደረገው
ውይይት ለማወቅ ችሏል፡፡

በድሬደዋ እና አካባቢው ለህገ ወጥ የቁም እንስሳት በመነሻነት የሚያገለግሉ ገበያዎች የድሬደዋ
ገበያ፤የቢኬ ገበያ፤እና የባቢሌ ገበያ ናቸው፡፡

የባቢሌ የገበያ ማዕከል በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉት የግመል ገበያዎች ያቬሎ ከሚገኘው ሀሮበኬ ገበያ
ቀጥሎ በከፍተኛ መጠን የግመል እንሰሳት ገበያ የሚካሄድበት የገበያ ማዕከል ነው፡፡

ገበያ ማዕከሉ በሳምንት ሁለት ጊዜ ሰኞና ሀሙስ የሚካሄድ ሲሆን የሰኞ ገበያ ትልቁ ገበያ ነው፡፡ገበያው
በዋናነት የግመል ግዥና ሽያጭ የሚከናወንበት ቢሆንም በተጨማሪም የዳልጋ ከብት፤በግ፤ፍየልና
እንዲሁም የጋማ ከብት(አህያ) ግብይት ይካሄዳል፡፡

ከወረዳው የንግድና ኢንዱስትሪ የገበያ ጥናት ባለሙያ ባገኘነው መረጃ መሰረት በአማካይ በሰኞ ገበያ ቀን
እስከ 3000 ግመሎች እዚህ ገበያ ላይ ይቀርባሉ፡፡

እዚህ ገበያ የሚቀርቡት እንስሳት መነሻቸው በአብዛኛው ከምስራቅና ምእራብ ሐረርጌ ዞኖች ሲሆን
ከባሌ፤ከቦረና፤ከጎዴ፤ከጭረቲ እና ከሌሎች ርቀት ካላቸው አካባቢዎች ይቀርባሉ፡፡ በግብይቱም ሂደት
ተሳታፊዎች አርቢዎች፤ደላሎች፤ህጋዊ ነጋዴዎች፤እና የውጭ ሀገር ዜጎች መመልከት ችለናል፡፡

እነዚህም ከሱዳን ፤ከሱማሌ ላንድ ፤ከየመንና ከግብጽ የመጡ የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው በቀጥታ
ገበያው ውስጥ በመግባት በአካል ተገኝተው በደላላዎችና ፈቃድ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጋር
በመሆን ለአገር ውስጥ ዜጎች ብቻ የተፈቀደውን ንግድ ላይ በመሳተፍ ግዥ ሲያከናውኑንና ሲያስገዙ
ተመልክተናል፡፡ይህ ድርጊታቸው የገበያውን የግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸውንና ገበያውም
ህጋዊንና ህገ ወጥ ንግዱን እያስተናገደ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡የቁም እንስሳቶቹም የሚጓጓዙት
በአብዛኛው በነጂዎች አመካኝነት በእግር ነው፡፡


                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት              Page 6
ከእነዚህ የገበያ ማእከሎች ድሬደዋ፤ቤኪ እና ባቢሌ የሚገዙት የቁም እንስሳት በህገ ወጥ መንገድ
የሚጓጓዙበት እና የሚወጡበት አቅጣጫ

ከቢኬ     ሜቶ ጣቢያ           ሓሬ          ዲከል(ጅቡቲ)

ከቢኬ     ኡመር ጉልፍ          ዱርዱር           ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ     ሽንሌ     ጋድ           አዲጋላ        ኡመር ጉልፍ        ዱርዱር      ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ     ሽንሌ      ጋድ          ሜቶ        ሀሬ        ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ     አዲጋላ         ሐጂም             ዲከል(ጅቡቲ)

ባቢሌ    ፋፈም       ቆቦ ቦቃ        ጭናክሰን        ደንበል     አሻ       ሀጂም(ሱማሌ ላንድ)

ባቢሌ    ጭናክሰን      ቱሉጉሌት            ዶሮናጂ         ሱማሌላንድ

ባቢሌ     ጅጅጋ        ቶጎውጫሌ               ሱማሌ ላንድ(ህጋዊና ህገ ወጥ በሆነ መልኩ)

ቡድኑ ከድሬደዋ ገቢዎችና ጉምሩክ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ኃላፊ፤ከደሬደዋ ኳራንቲን ባለሙያዎች እና
የሽንሌ ዞን መስተዳድር ጋር በመሆን የቁም እንስሳት ህገ ወጥ እንስሳት እንቅስቃሴን መተመለከተ
ውይይት ተደርጓል፡፡

 ሽንሌ ዞን ከሱማሌ ክልል ዞኖች አንዱ ስትሆን በሰሜን ምስራቅ በኩል ትገኛለች፡፤ዞኑ ከጅቡቲ እና
ከሱማሌ ላንድ ጋር በድንበር ይገናኛል፡፡

የሽንሌ ዞን ከምስራቅ ሐረርጌ፤ከምእራብ ሐረርጌ፤ከአርሲና ከባሌ የሚመጡ ህገ ወጥ የእንስት እንስሳት
ጥጃዎች ማረፊያና ማስተላለፊያ በመሆን ወደ ጅቡቲና ሱማሌ ላንድ ለሚሄዱ ህገ ወጥ እንስሳት መነሻ
ሆና ታገለግላለች፡፡

እንስሳቶቹ ከሽንሌ ዞን በመነሳት ከዋናው መስመር ከ60-65 ኪ.ሜ በመራቅ በረሃውን ተከትለው
ስለሚሄዱ ለቁጥጥርና ክትትልም አመቺ አይደለም፡፡ ሌላው ከቤኪ፤መኢሶና አፍደም ላይ የግብይት
ስርአቱን ከአካሄዱ በኋላ ሳር እናበላለን በሚል ሰበብ ወደ ድንበሩ ከተጠጉ በኋላ በአዲጋላ በኩል ወደ
ጅቡቲ ያስወጣሉ፡፡

በዞኑ የዞኑ የቆዳ ስፋትና የእንስሳት ክምችን በአማከለ መልኩ የተሰሩ የገበያ ማዕከላት አለመኖሩ በዞኑ
ከሚታዩት አበይት ችግሮች አንዱና ዋንኛው ሲሆን ይህም ለህገ ወጡ ንግድ መንሰራፋት ምክንያት
ሆኖአል፡፡

ስለዚህ የዞኑን ቆዳ ስፋትና በረሃነት እንዲሁም የእንስሳት ክምችትን መሰረት ባደረገ መልኩ የግብይት
ማዕከላትን በማቋቋም ከላኪና ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ላኪዎችና ነጋዴዎች ጋር የግብይት ትስስርን
በመፍጠር ተግባራዊነቱን በመከታተል የእንስሳት ፍልሰቱን መቀነስ ይቻላል፡፡




                   የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                        Page 7
5.2. ጅጅጋና አካባቢው
ቡድኑ በጅጅጋ ለሚገኙት ለሚመለከታቸው መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች፤ ነጋዴዎችና ማህበራት ተወካዮች
ተልዕኮውን  በመግለጽ በህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ፤መንስኤዎችና ችግሮች እንዲሁም
የመፍትሄ ሀሳቦች ዙርያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት በአሁኑ
ወቅት በጠረፍ አካባቢዎች አባላትን በመመደብ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ እና ከጥምር
ኮሚቴ ጋር በቅንጅት መስራት በመጀመራችው በተወሰነ መልኩ ኮንትሮባንዱ እንቅስቃሴ የመቀነስ
አዝማሚያ ቢያሳይም ከአካባቢው ካለው ስፋት አንጻር ከአንዱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እና ከሌላው
መቆጣጠሪያ ጣቢያ መካከል ያለው ርቀት በጣም ሰፊ በመሆኑ አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው የቁም
እንስሳት በኮንትሮባንድ መንገድ ከሀርትሼክ እስከ ጋሻሞ ባሉት መውጫ በሮች ወደ ሱማሌ ላንድና
ፑንት ላንድ እየወጡ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታም የክልሉ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንደገለጹት በክልሉ የኮንትሮባንድ
ንግድ እንቅስቃሴ እየቀነሰ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ለዚህም በዋናነት ከመሃል አገር ወደ ጠረፉ አካባቢ
ስኳር፤ ዘይት እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶች መምጣት በመጀመራቸው እና በመንግስት 6
የሚሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ በመፍቀዱ ኮንትሮባነድ ንግዱ
በአንጻራዊነት እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ገልጸዋል፡፡

 አያይዘውም ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከዚህ በፊት ብቻውን ሲሰራ የነበረውን አሰራር በመቀየር
ከንግድና ትራንስፖርት፤ከአስተዳደር ም/ቤት፤ከአስተዳደርና ፍትህ፤ከፌደራል ፖሊስና መከላከያ ጋር
በቅንጅት የጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በየወሩ ወር በገባ በ25ኛው ቀን ላይ በመገናኘት የጋራ ውይይት
በማድረግ በሚከሰቱ በችግሮች ዙርያ በመወያያትና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማስቀመጥ በሂደት ችግሮችን
እየተፈቱ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡

የመውጫ በሮችንም በተመለከተ

        ከደገሀቡር በመነሳት በሀርሼንና በሀርትሼክ መካከል (አበከር) አድርጎ   ወደ ሱማሌ ላንድ
         ይገባል

        ከጨረቲ፤ከአፍዴር፤ከጎዴ፤ከቀብሪድሀር በመነሳት በሀርትሼክና በሀርሺን መካከል በመውጣት
         ወደ ሱማሌ ላንድ ይገባል

        ከባቢሌና ከፊቅ በመነሳት ጅጅጋን ወደ ግራ በመተው በቀብሪበያህ በኩል ሀርቲሼክን ወደ
         ቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል

        ከኮምቦልቻ ከሃረርና ጉርሱም በመነሳት በጭናክሰን አድርገው በተፈሪበርና ለፌሳ መካከል
         በማለፍ ቶጎ ውጫሌን ወደቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል

የሚወጡትም የቁም እንስሳት የዳልጋ ከብት፤በግናፍየል እንዲሁም ግመሎች ይገኙበታል፡፡




                   የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት              Page 8
ከሱዳን የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያ          ከሱማሌ ላንድ የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያ
ግብይት ላይ




5.2.1. ቶጎ ውጫሌ
ቶጎውጫሌ ከጅጅጋ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ከተማዋ የህጋዊ የቁም እንስሳት
የወጪ ንግድ መውጫ በር ሆና ታገለግላለች፡፡ ከኢትዮጵያ ድንበር በግምት 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
የምትገኘው ሱማሌላንድ ቶጎውጫሌ ላይ ሰፊ የቀንድ ከብት ግብይት ይካሄድባታል፡፡ በዚህ ገበያ ህጋዊና
ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሰፊው የሚካሄድበት ሲሆን ቡድኑ በ08/06/04 በገበያ ማዕከሉ
በመገኘት የገበያውን እንቅስቃሴ ለማየት ችሏል፡፡ በአማካይ ከ50 በላይ አይሱዙና ኤፍ.ኤስ.አር አይሱዙ
መኪናዎች በየቀኑ ወደ ገበያው ይመጣሉ ( በአረፋና በኢድ የሙስሊም በዓላት ወቅት የሚቀርበው
የቁም እንስሳት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻቅብ የአካባቢው ነጋዴዎች ይገልጻሉ)

 የቁም እንስሳቱም  የሚመጡት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሆን በዋናነትም      ከባሌ፤ ከቦረና፤
ከኢሉባቦር (ጨወቃ)፤ከጅማ፤ ከወለጋ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ለማየት
ተችሏል፡፡ከሚቀረቡትም እንስሳት በእድሜም ሆነ በክብደት በአብዛኛው ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር
በወጣ መመሪያ ከተፈቀደው 320 ኪ.ግ ወይም ከዚያ በላይ የሚለውን በመጣስ ዕድሜአቸው ከ 1
ዓመት ተኩል በታችና ክብደታቸው ደግሞ በአማካይ ከ150 ኪ.ግ በታች የሆኑ ጥጃዎች መሆናቸውን
ለማየት ተችሏል፡፡

     የቁም እንስሳት ጭነው ወደ ገበያው የሚገቡ መኪናዎች ለእያንዳንዳቸው          ብር     150
      እንደሚከፈልና ለተጨማሪ ወጪዎች መዳረጋቸውን ነጋዴዎቹ በምሬት ይናገራሉ፡፡

     ሌላው ከነጋዴዎቹ መገንዘብ የተቻለው የቁም እንስሳት ግብይቱ የሚካሄደው ከኢትዮጵያ ድንበር
      2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የሱማሌላንዷ ቶጎውጫሌ መሬት ላይ በመሆኑና ከአገር ውስጥ
      የወጣ የቁም እንስሳ ካልተሸጠ ወደ ሀገር ውስጥ መመለስ ስለማይችል እና እዚያም ለማቆየትም
      የመኖ ችግር በመኖሩ ነጋዴው እንስሳቱን አቆይቶ እና ተደራድሮ በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ እድል
      ስለማይኖራቸው በተገኘው ዋጋ በቅናሽ በመሸጥ ለኪሳራ ይዳረጋሉ ፡፡

     አንዳንድ ጊዜ ሽያጩ ከተካሄደ በኋላ ገንዘቡ ወዲያው ስለማይከፍሏቸው ነጋዴው ሱማሌላንድ
      ላይ ገንዘቡን ለማግኘት በሱማሌ ላንድ በሚደረገው ቆይታና መጉላላት ለከፍተኛ ወጪ ስለ
      ሚዳረጉ ኪሳራ ውስጥ በመግባት ከግብይቱም በመውጣት አልፎ አልፎም ወደ ህገ ወጡ ንግድ
      ለመቀላቀል ይገደዳሉ፡


                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                 Page 9
በቶጎ ውጫሌ ከኢትዮጵያ ወደ ሱማሌ ላንድ የሄዱና ለገበያ የቀረቡ ጥጃዎች ፎቶ ግራፍ




      ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳት
      ብዛትና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ
ተ.ቁ   ዝርዝር              መለኪያ      2000        2001        2002         2003           ምርመራ

1     የቀንድ ከብት          ቁጥር       15901       16579       33619        65619

2     ግመል               ፤         143         137         7646         13937

3     በግ                ፤         2767        10500                    8834

4     ፍየል               ፤         580                                  8026

      ድምር               ፤         19391       27216       41265        96416

      የተገኘው የውጭ ምንዛሪ    ዶላር       6,902,938   7,545,172   17,300,716   34,093,050

             ምንጭ፡-የጅጅጋ ኳራንቲን ጣቢ

      5.2.2. ሀርትሼክ
      በመጨረሻም ቡድኑ ከጅጅጋ 70 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሀርት ሼክ ገበያ ላይ በመገኘት የቁም
      እንስሳት ገበያውን ለማየት እና መረጃዎችን ለመሰብሰብ ችሏል፡፡ በአካባቢው በከፍተኛ ደረጃ የውሃ
      አቅርቦት ችግር በመኖሩ አንድ በርሜል ውሃ እስከ 80 ብር እንደሚሸጥ እና የገበያ ማዕከሉም ከፍተኛ
      የውሀ አቅርቦት ችግር እንዳለበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

      የገበያ ማዕከሉ የተገነባው በቮካ ኢትዮጵያ ሲሆን ገበያው ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው በጎችና ግመሎች
      ለግብይት የሚቀርቡበትና እንስሳቶቹም በሃርትሼክ     በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ
      እንደሚወጡ ከስፍራው ከነበሩ ነጋዴዎች እና ነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

      በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND
      MEAT) በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናታዊ ጽሁፍ እንደ ሚያመለክተው ሱማሌ ላንድ እኤአ በ2007
      ዓ.ም በኮንትሮባንድ መልክ በሀርትሼክና በለፌሳ በኩል በቶጎ ውጫሌ አድርጎ ሱማሌ ላንድ የገባ ከ1.5
      ሚሊዮን በላይ በግና ፍየል እንዲሁም 100,000 የሚገመት የቀንድ ከብት ለወጪ ገበያ አቅርባለች፡፡



                        የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                                Page 10
በአጠቃላይ የሱማሌ ክልል በእንስሳት ሀብት ክምችት በተለይም ግመል፤ፍየል እና በግ የሚታወቅ
ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱማሌ
ላንድ፤ፑንትላንድ፤እንዲሁም ወደ ጅቡቲ እንደሚወጡ ከዚያም በራሳቸው ስም ወደ አጎራባች አረብ
አገሮች እንደሚላኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ይህንንም ከላይ በፎቶግራፉ የሚታዩት በጎች እና ፍየሎች
መመልከት ይቻላል፡፡ አዚህም አካባቢ የሚታየው ዋንኛው ችግር የክልሉ የድንበር ስፋት በአማከለ
መልኩ የክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦት በበቂ ደረጃ
አለመኖር ፤ በሱማሌ ላንድና በኢትዮጵያ ሱማሌ መካከል ያለው የጠነከረ የጎሳ ትስስር እና የፍጆታ
ዕቃዎች በበቂ ሁኔታ ያለመድረስ ነው፡፡

   ከሀርት ሼክ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ ለመላክ የተዘጋጁ በጎች




5.3 አፋር ክልል
የአፋር ክልል ከኢትዮጵያ አርብቶ አደር ክልሎች አንዱ ሲሆን ክልሉ በዋናነት ግመል፤በግና ፍየል
እንዲሁም የቀንድ ከብት የሚረባበት አካባቢ ነው፡፡ክልሉ እንደ አጎራባቹ ሱማሌ ክልል ሰፊ የሆነ
የድንበር ወሰን ያለው ነው፡፡

ወደ ክልሉ እንስሳት ከተለያዩ አጎራባች ክልሎች የመገበያያ ቦታዎች ጎሊና(ወልዲያ)፤አለውሃ(ትግራይና
አማራ)፤ዳንዲ(ትግራይ )እና ከክልሉ ፤ጭፍራ እና ከመሳሰሉት ተገዝተው ወደ ክልሉ ትልቁ የገበያ
ማዕከል አሳይታ ይገቡና ግብይቱ ከተከናወነ በኋላ የቁም እንስሳቱ በህገ ወጥ መንገድ በአፋምቦ በኩል
ወደ ዳካ በመሻገር በእግር ወደ ጅቡቲ ይወጣሉ፡፡

ሌላው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መውጫ ከአካባቢው በመነሳት ከአዳይትና ገዳማይቱ በኩል አድርገው
በሽንሌ ዞን በኩል ወደ ጅቡቲ እንደሚገቡ ከክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ የተገኘው መረጃ
ያመለክታል፤፤




                 የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት            Page 11
ሆኖም በአሁኑ ወቅት ያለው የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የመቀነስ ሁኔታዎች
ይታያሉ፡፡  ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው በክልሉ ፕሬዝዳንት የሚመራ የጸረ-ኮንድሮባንድ ጥምር
ኮሚቴ ተቋቋሞ ህገ ወጡን ንግድ ለመቀነስና ብሎም ለመግታት የሚያስችለውን እቅድ ነድፎ እስከ
ታችኛው አስተዳደር እርከን በማውረድ ኮሚቴው በከፍተኛ ደረጃ በመንቀሳቀሱና በየሁለት ሳምንቱ
እተገናኘ የሚያጋጥሙትንና ያጋጠሙትን ችግር እየፈተሸ እና መፍትሄ እያስቀመጠ በቅንጅት እየሰራ
በመሆኑ ነው፤፤

ክልሉ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የጠራ የመከላከል አቋም እንዳለው ህዝቡን ከላይ እስከ ታች ግንዛቤ
በማስጨበጥ ፤የአካባቢው ሽማግሌዎችን በማሳተፍ በአገሪቷ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚያሳድረውን
ተጽዕኖ በዝርዝር በማስረዳት ህብረተሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲያገኝ በመደረጉ ነው፤፤

ይህም ለሌሎች ተመሳሳይ ክልሎች መልካም ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል ቡድኑ ያምንበታል፤፤

5.4.ትግራይ ክልል
የትግራይ ክልል የቁም እንስሳት   የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ ከሚካሄድባቸው ክልሎች አንዱ
ስትሆን በሰሜን በኩል ከኤርትራ እና በሰሜን ምእራብ በኩል ከሱዳን እንደምትዋሰንና የህገ ወጡ የቁም
እንስሳት መውጫም በሁመራ ደቡባዊ ምእራብ አቅጣጫ በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱዳን እንደ
ሚገቡ ቡድኑ የክልሉን የገቢዎችና ጉምሩክ፤ንግድ መምሪያ፤ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ክፍሎች
በማነጋገር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የሚወጡት የቁም እንስሳት የሚመጡትም ከተለያዩ ቦታዎች ሲሆን በዋናነትም
ደቡብ ትግራይ፤ ራያና ሰሜን ወሎ፤ሰሜን አርማጮ እና ቀፍታ ሁመራ ወረዳዎች መሆናቸውንና
የሚወጡትም እንስሳት በአብዛኛው የዳልጋ ከብትና ግመሎች ናቸው፡፡

5.4.1. ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን)
ቡድኑ ከመቀሌ ወደ ሁመራ በመጓዝ በአካባቢው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ለመቃኘት
ሞክሯል፡፡ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰብሳቢነት ፤የገቢዎችና ጉምሩክ የሁመራ መቅረጫ
ጣቢያ ሀላፊ፤ግብርና መምሪያ ሃላፊ፤አስተዳደርና ጸጥታ ሐላፊ፤ፌደራል ፖሊስ ፤የዞኑ ፖሊስ ፤ንግድና
እንዱስትሪ መምሪያ ሐላፊ፤ የፌደራል ኳራንቲን ተወካይ በተገኙበት ስለ ህገ ወጥ እንስሳት ንግድ
መነሻ እና ፤መውጫ በሮች፤መንስኤዎችና መፍትሄዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ በአካባቢው የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ተገልጾ ከሚያዚያ ወር 2003
ዓ.ም የዞኑ ጀምሮ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በጋራ በመሆን በቅንጅት በተጠናከረ መልኩ
መንቀሳቀስ በመጀመሩ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው መቀነሱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ጥምር ኮሚቴው በዞን ደረጃ በየወሩ ወር በገባ በ9ኛው ቀን በወረዳ ደረጃ በየ 15 ቀኑ እንዲሁም በቀበሌ
ደረጃ በየሳምንቱ እየተገናኙ አጠቃላይ ከጸጥታና ኮንትሮባንድ ንግድ ጋር በተያያዘ ግምገማ በማካሄድ
ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ በመወያየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን እየፈቱ በመሄዳቸው
የህገወጥ ንግዱ እንቅስቃሴ መቀነሱ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጻል፡፡ በዞኑ የግብይት ሁኔታዎች
በሚፈለገው ደረጃ ያልተመቻቹና በአግባብም ያልተሰራበት አንድም ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት ገበያ
ማዕከልናየእንስሳት ማቆያ የሌለበት መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት             Page 12
5.5.አማራ ክልል
በአማራ ክልል ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ከሌሎች ምርቶች ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፤ለዚህም
ዋናው ምክንያት ሰፊ የጠረፍ ድንበር መኖሩ ለክትትልና ቁጥጥር አስቸጋሪና ሁሉም ቦታዎች
ለመድረስና ለመሸፈን አለመቻል ሲሆን ሌላው ደግሞ የግብይቱ ስርአት አለመመቻቸት ነው፡፡ ይኸውም
ሱዳን አገር የቀንድ ከብት ዋጋ ከሀገር ውስጥ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር በሀገር ውስጥ የአንድ ቀንድ ከብት
ዋጋ ብር 2500-3000 የሚያወጣ ሲሆን ይህ የቀንድ ከብት ሱዳን ተሸግሮ የሚሸጠው እስከ 5000 ብር
ነው፡፡

ስለዚህ በዚህና በሌሎች ከታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ብዙ እንስሳት በኮንትሮባንድ መልኩ ይወጣሉ
፡ይህንን ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ቀደም ብሎ
ቢቋቋምም አንዴ ሞቅ አንዴ ላላ እያለ ነበር አሁን ግን የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ለሴክተር መ/ቤቶች
ኦርየንቴሽን በመስጠት ኮንትሮባንዱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምሯል ፡፡

ጥምር ኮሚቴው ስራውን በመገምገም ከህገ ወጥ ነጋዴው ጋር በመሆን በህገ ወጥ ንግዱ ተሳታፊ
የነበሩ የመዋቅር አካላት በማጋለጥ እና በማሰር እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠሉ የህገ ወጡ
እንቅስቃሴ በመተማ በኩል ቢቀንስም ህገ ወጥ ነጋዴዎቹ ስልታቸውን በመቀየር ወደ ሽንፋ አቅጣጫ
መዞራቸውንና በአካባቢው በተደረገ ክትትል በተለያዩ ግዚያት 200 ፤ 150 እና 50 በድምሩ 400
የቀንድ ከብት በዚህ በጀት ዓመት መያዛቸውን ከአካባቢው የተገኘ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በመተማ
ቁጥጥሩ ሲጠናከር ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ወደ ሺንፋ 53 ኪ.ሜ በመራቅ በቀን እስከ 300 ከብት በህገ
ወጥ መንገድ በአማካይ እየወጣ መሆኑን ገቢዎችና ጉምሩክ ገንደ ውሃ መቅረጫ ጣቢያ ሓላፊ ጋር
ከተደረገው ውይይት ለመገንዘብ ተችሎዋል፡፡

መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት 60 ከመቶ የሚሆነው የቁም እንሰሳ የሚወጣው በኮንትሮባንድ መልክ
መሆኑንና ከቆላማው አካባቢ ለኮንትሮባንዱ ንግድ 78 ከመቶ ድርሻ እንዳለው መረጃዎቹ ያመለክታሉ፡፡

 በምሳሌነት ለመጥቀስ Yacob Aklilu, “the most excessive taxation system on cattle in East
Africa” ን በመጥቀስ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND
MEAT)” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 በቀረበው የጥናት ጽሁፍ በተገለጸው መሰረት በህጋዊ
መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድ ከብት ብር 400 ቀረጥ                የሚያስከፍሉ ሲሆን
በኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻ ያስከፍላል ፡፡

ይህም የሚያሳየው በሱዳን በኩል የህጋዊ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴን የሚያዳክምና የህገ ወጡን
የቁም እንስሳት ንግድን የሚያበረታታ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይህንን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ለመቆጣጠር ካለው ሰፊ ሜዳና የድንበር ስፋት(ከመተማ ዮሀንስ ግራና
ቀኝ) አንጻር በገቢዎችና ጉምሩክ ኬላ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ያለውን የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦት
እና የሰው ሀይል ችግር ቢቀረፍና ጥናት ተደርጎ በሺንፋና ሳንጃ ላይ መቆጣጠሪያ ኬላ ቢቋቋም ችግሩ
ሊቀንስ እንደሚችል ከውውይቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻቸው በዋናነት ከሰሜን አርማጮ፤ ሰሜን ወሎ(ራያና
ቆቦ)፤ሰከላናመራዊ(ጎጃም) በአነስተኛም ደረጃም ቢሆን ከባሌ፤አዳማ፤ቦረና፤፤አርሲ ሲሆኑ ወደ ውጪም
የሚወጡት ከሱዳን ጋር ባለው ሰፊ ድንበር የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው

      በሳንጃ አድርጎ በአሴራ ወደ ሱዳንና


                      የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                        Page 13
   በመተማ ዮሃንስ 50ኪ.ሜ በስተደቡብ በኩል አድርጎ በሽንፋ ወደ ቲሃ (ሱዳን )

       በቁንዝላ ቋራ በመሄድ በሺንፋ በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) እንዲሁም

       ከነገደ ባህር ወደ ሽንፋ በመሄድ በይሙት በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) ይገባል፡፡

    በአካባቢው ለወጪ እንስሳት የሚደረገው የጤና አገልግሎት አሰጣጥንም በተመለከተ ሥርዓቱን
    የተከተለ ሳይሆን እንስሳቱ በሌሉበት እና ሳይታዩ ነጋዴው የእንስሳቱን ቁጥር ብቻ በመግለጽ የጤና
    ሰርትፍኬት ከጎንደርና ከሌሎች አካባቢዎች ይዘው ይመጣሉ፡፡ ይህም አሰራር ከመመሪያው ወጪ
    በመሆኑ ሊቆም ይገባዋል፡፡

    እንደሌሎቹ አካባቢዎች ሁሉ በአማራው ክልል ጠንካራ አቅም ያላቸው የቁም እንስሳት ላኪዎች
    ያልተሰማሩበትና ጥቂት በመስኩ የተሰማሩትም እንስሳትን በዱቤ በመሸጥ ገዥዎቹ ክፍያውን
    ሳይፈጽሙ ስለሚሰወሩ በርካታ ላኪዎች ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ስለዚህ የዱቤ አሰራርም ከወዲሁ
    ሊታሰብበትና መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል፡፡


ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ                        ክልል   በኮንትሮባንድ
(በህገ ወጥ መንገድ) ወደ ሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳት
ተ.ቁ         የእንስሳት ዓይነት             መለኪያ            መጠን     በገንዘብ

1           በሬ                      በቁጥር            896

2           ላም                                      453

3           ወይፈን                                    335

4           ጊደር                                     83

5           ጥጃ                                      214

6           ፍየል                                     326

7           አህያ                                     8

8           ግመል                                     1

9           በግ                                      147

ድምር                                                 2463    10395700

  (ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ) ከዚህ ሰንጠረዥ መገንዘብ የሚቻለው የቁም
እንስሳት ኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳያል፡፡




                     የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                      Page 14
5.6.ሞያሌ
ሞያሌ ወረዳ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሮሚ›ያ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን      እና በሱማሌ ክልላዊ
መንግስት በሊበን ዞን የሚገኝ ሲሆን ህብረተሰቡ በአብዛኛው አርብቶ         አደር ነው፡፡ የቀንድ
ከብት፤ግመል፤ፍየልና በግ በከፍተኛ ሁኔታ የሚረባበት አካባቢው ነው፡፡

በዚህም ዞን እንደሌሎች ክልሎች የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ይካሄድበታል፡፡ የገቢዎችና
ጉምሩክ የሞያሌ ቅርንጫፍ እንደገለጸው በዚህ ሞያሌ መውጫ በር በህጋዊ መልክ የሚወጣ የቁም
እንስሳት እንደሌለ እና ወደ ኬንያ የሚሄደው እንስሳ በሙሉ የሚጓዘው በህገ ወጥ መልኩ መሆኑን
ተገልጾዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በየ ቀኑ በኢትዮጵያ ሞያሌ በቦሌ በኩል በቀን በሺዎች
የሚቆጠሩ ከብቶች (እንስት በብዛት) ወደ ኬንያ እንደሚወጡ ታውቆአል፡፡የሚወጡትም እንስሳት
የተኮላሸ ከብት(ሰንጋ)ና፤ላሞች ናቸው፡፡የጥናት ቡድኑ ኬንያ የሚገኘውን የገበያ ማዕከል በመሄድ
ለማየትና ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

 ቡድኑ ድንበር ተሻግሮ በጥዋቱ የኬንያ ገበያ ለመመልከት በሄደበት ወቅት የኬንያው ጉምሩክ ባለሙያ
እንደገለጹልን ከሆን ገበያው ከመድረሳችን በፊት 20 መኪናዎች(500 ከብቶች) ጭነው ወደ ናይሮቢ
መሄዳቸውን የገለጹልን ሲሆን በገበያው ውስጥ የነበሩ ከብቶች ቁጥር በግምት 1500 እስከ 2000
ይደርሳል፡፡ባለሙያው እንደገለጹት ከብቶቹ በሙሉ የመጡት በኮንትሮባንድ ከኢትዮጵያ መሆኑንና
ኢትዮጵያ እነዚህን ከብቶች በህጋዊ መንገድ ወደ ኬንያ እንዲገባ ብታደርግልን ኬንያ ቀረጥ በመሰብሰብ
ተጠቃሚ ልትሆን ትችል ነበር ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የወጡ የቁም እንስሳት የግብይት ስነ ስርዓት በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ገበያ
ከተከናወነ በኋላ ወደ ናይሮቢ በመውሰድ ከፊሎቹን ራንች ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ አደልበው ወደ
ውጪ እንዲላኩ ይደረጋል፡፡መረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት ኬንያ ከምታቀርበው እንስሳት ከ25-30 ከመቶ
የሚሆነው ምንጫቸው ኢትዮጵያ መሆኑን ያመላክታል፡፡

ቡድኑ ቦታው ድረስ በሄደበት ወቅት ያየውን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ፍሰት ተመልክቶ ከገቢዎችና
ጉምሩክ ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውይይት በማድረግ ቡድኑ በገባበት ማግስት 20 ሰንጋዎች
መያዛቸውን ለመመልከት ችሏል፡፡

ያለውን ችግር መነሻ በማድረግ ቡድኑ ከዞኑ አስተዳዳሪ ጋር ባደረገው ውይይት የህገ ወጡ ንግድ
እንቅስቃሴ መኖሩን ና ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች

     የሞያሌ ከተማ እና አካባቢው በሁለት መስተዳድር መተዳደሩ ለቁጥጥር አመቺ አለመሆን

     በሁለቱ የጠረፍ ድንበር አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ በጎሳ በባህልና በልማድ የተሳሰረ በመሆኑ
      ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆኑ

     የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ   እንቅስቃሴ ያለመኖር

     የህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር እና እንደሌሎቹ ሁሉ የእንስሳት ግብይት ሁኔታዎች ያልተመቻቸ
      እና መሰረታዊ ለውጥ ያልታየበት መሆኑ ነው፡፡፡



                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት             Page 15
ክልሉ የአካባቢውን የእንስሳት ለመቀነስ በበጀት አመቱ አስር ከመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየተንቀሳቀስ
ቢሆንም በገበያ እጦት ምክንያት እቅዱን ለማሳካት እንደሚቸገር በመግለጽ ይህንን እቅድ ለማሳካት
በአስቸኳይ የገበያ ችግር መቅረፍ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

የእነዚህ እንስሳት መነሻ ቦታዎች ቦረና ዞን(ያቬሎ-ሀሮበኬ ገበያ፤ድብሉቅ፤) ስሩጳ እና ኮንሶ ሲሆኑ
በሜጋ በኩል በማድረግ በቦሌ(ሞያሌ) ወደ ኬንያ ይገባሉ፡፡

እንስት እንስሳትና በሬዎች ከሞያሌ (በቦሌ በኩል)       ከሞያሌ (በቦሌ በኩል) ወደ ኬንያ ሲጓዙ የተያዙ
ወደ ኬንያ ሲጓዙ




6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች
  1. አስተማማኝ ገበያ በየአካባቢው አለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤት አገሮች ዋጋ ጋር
     የሚወዳደር ወይም የተሻለ አለመሆን፤ በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆን የሚችል የግብይት
     ስርዓት አለመኖርና የግብይት መሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣
  2. ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ
     የሚያበረታቱ መሆኑ፤ይህም የሚገለጸው በህጋዊ መንገድ በሚገባ እንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ
     ከፍተኛ መሆንና በተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባ መሆኑ ነው፡፡
  3. የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊ አቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው
     ከዚያ ራቅ ካሉት እንደ ሱማሌ ቦረና እና አፋር አካባቢዎች ወደ መሃል የኤክስፖርት ገበያዎች
     ከማቅረብ ይልቅ የትራንስፖርት ወጪና የተሻለ ዋጋ ወደ አለው ጎረቤት አገሮች ማቅረቡ
     የተሻለ አማራጭ በመሆኑ፣
  4. ከመሃል አገር ለጠረፍ አካባቢዎች የሚቀርበው የፍጆታ ዕቃ አለመኖር ወይም አነስተኛ መሆንና
     በተቃራኒው   ከጎረቤት   አገሮች   በኩል   የየዕለት   የፍጆታ   ዕቃዎች   ለመጥቀስም   ያህል
     ስኳር፤የተፈበረኩ የምግብ ምርቶችና ለጠረፍ ሞቃት አካባቢዎች የሚስማሙ አልባሳት ከመሃል
     አገር በተሻለ ዋጋ የሚቀርብ በመሆኑ

                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                Page 16
5. ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግዱ ለብዙ ጊዜያት ሲካሄድ የቆየ በመሆኑ በልምድ፣ በፋይናንስ
  አቅርቦት፣ በመረጃ ልውውጥ የተጠናከረ ፣ በተሳታፊዎች በሚደረግለት ድጋፍ ከህጋዊ ንግዱው
  በተሻለ መልክ የተመቻቸና አዳዲስ ተሳታፊዎችን በበለጠ ሁኔታ መሳብ መቻሉ፣
6. ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ
  የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች መኖራቸው፣እነዚህንም መውጫ በሮችን ለመቆጣጠር በሰው
  ኃይልም ሆነ በሎጅስቲክ አለመጠናከራቸው፤
7. በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተ ከመተሳሰሩም
  ባሻገር   ለጠረፍ   አካባቢ   ነዋሪዎች   ለአብዛኛው   ህብረተሰብ    የኑሮ   ምሰሶአቸው   እንስሳትን
  በማርባትና    ከእንስሳት     ሽያጭ     የሚያገኙት   ገቢ      የሚጠቀሙ   በመሆናቸው     የበለጠ
  የሚያስተሳስራቸው በመሆኑ ይህ ግንኙነታቸው ለህገወጥ ንግዱ መጠንከር አስተዋፅኦ ማድረጉ፣



7. ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች
   1. የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም
      በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት
      በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት
      ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ
      እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት

   2. በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት በሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት
      ህገ ወጡን እንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ እና የሎጅስቲክና
      የተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር
      በማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም የሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት

   3. በሀገር ውስጥ በተለይም በጠረፍ አካባቢዎች አምራቹንና ነጋዴውን በማስተሳሰር በሃገር
      ውስጥ የተሻለ ዋጋ ለመፍጠር አካባቢዎቹ ላይ በሂደት በመንግስትና በግል ባለሀብቶች
      ኤክስፖርት ቄራዎችን ማቋቋምና እና የግብይቱን ስርአቱን የሚከታተልና የሚመራ
      የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች
      ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡

   4. በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የፍጆታ እቃዎችን ስኳር፤ዘይት፤አልባሳት…ወዘተ ከጎረቤት
      አገሮች ከሚገቡት ምርቶች ዋጋ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጠረፍ አካባቢዎች በጅንአድ
      ወይም ማህበራትን በማጠናከር በበቂ ደረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ ፤

   5. ህገ ወጡን ንግድ ለማዳከም ህጋዊ ነጋዴውና አስፈጻሚ አካላት በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ
      ስራዎችን በማከናወን ፤የነጋዴዎችን የገንዘብና(የካፒታል) የማስፈጸም አቅማቸውን
      በማሳደግ ፤ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች በማቅረብ ክትትልና ጠንካራ ቁጥጥር በማድረግ
      በግብይቱ ዙርያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሰፉና ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲመጡ ማድረግ፤


                 የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                    Page 17
6. በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እና እንደ አካባቢው
   መልካምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይልና የሎጅስቲክ አቅርበትና
   ተሻከርካሪ በማቅረብ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮችን
   በመቆጣጠር ህግን ማስከበር

7. በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የግብይት ማህበራትን በማደራጀትና በሁለንተናዊ
   መልኩ በማብቃት በእንስሳት ወጪ ንግድ እንዲሰማሩ ማድረግ ከዚህም በተጨማሪ
   በጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎችን በስነ ልቦና ሆነ ባህላዊ ትስስሩ ከመሃል አገር ጋር እንዲተሳሰር
   ተከታታይ የሆነ ትምህርት መስጠት፤


 8. በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች
1. በጠረፍ አካባቢዎች የሚገኙ ገበያዎች የሚገኙበት ቦታ ለጎረቤት አገሮች በጣም ቅርብ እና
   ደረጃቸው ተጠብቆ የተገነቡ አለመሆናቸው ለአብነትም የሞያሌ (40ሜትር) የሁመራና ና
   የመተማ ገበያ ቦታዎች የሚገኝበት ስፍራ ለጠረፍ በጣም የቀረበ እና በ15 ኪ.ሜ ክልል
   ውስጥ በመሆናቸው ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆናቸው

2. የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት በሀገሪቱ ስርዓቱ ገና ባለመጀመሩ ምክንያት
   የሚገድብ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ያለ ገደብ ስለሚንቀሳቀሱ በተለይም
   ለህገ ወጡ ንግድ ሁኔታዎች የተመቻቸ መሆናቸው

3. የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው እስከ መሀል አገር ዘልቆ በመግባት ለሀገር ውስጥ ዜጋ
   ብቻ የተፈቀደውን ገበያ ውስጥ በመግባት እንስሳትን በቀጥታ በመግዛትና መርጦ በማስገዛት
   የግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸው

4. ከንግድ ሚኒስቴር ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ ቀልጣፋ ባለመሆኑ ጊዜና
   ተጨማሪ ወጪ በመጠየቁ እና ሚጠይቀው ካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ነጋዴዎች ህጋዊ
   ፈቃድ አውጥተው ከመንቀሳቀስ ይልቅ ወደ ህገ ወጥ ንግድ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ

5. በአንዳንድ አካባቢዎች የጸረ ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ከክልል ጀምሮ በተዋረድ የህገ ወጡን ንግድ
   ለመቆጣጠርን ለህብረተሰቡ የህገ ወጡን ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን
   ተጽዕኖ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዙርያ በቅንጅት ያለመንቀሳቀስ ክፍተቶች ይታያሉ ለአብነት
   በቦረና እና በሊበን ዞኖች በተለይም ሞያሌ ወረዳ

6. እንስት እንስሳትና ጥጃ እንዲሁም የውጭ ዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥና እገዳ
   በተመለከተ ግልጽና የማያሻማ በጽሁፍ የተዘጋጀ መመሪያ ያለመኖር

7. የጠረፍ አካባቢ ህብረተሰብ ኮንትሮባንድ ንግድ በህገሪቱ ኢኮኖሚና ደህንነት እንዲሁም
   ማህበራዊ ኑሮ እና በህጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሰው ነጋዴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽኖ
   የግንዛቤ ችግር መኖሩና ለገበያ አማራጭና ለተሻለ ዋጋ በህገ ወጡ ንግድ መሳተፍና ተባባሪ
   መሆን



             የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት             Page 18
8. በሀገሪቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቁም እንስሳት ኳራንቲንና ኢንስፔክሽን እንዲሁም እንስሳት
     ቼክ ፖስቶች እንዲሁም የእንስሳት የማቆያ ቦታ ያለመኖር

  9. ለኤክስፖርት የተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና
     በተቆጣጣሪው አካል የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀርና የመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛ
     መሆኑ


   9. ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች
1. በሞያሌም ሆነ በሌሎች ጠረፍ አካባቢዎች የሚገነቡት የቁም እንስሳት መሰረተ ልማቶች (ገበያ
   ማዕከላት) ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ከጠረፍ አካባቢዎች ራቅ ብለው ምቹና የእንስሳት
   ክምችትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ማድረግ፡፡

2. ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን የቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችን
   ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳት
   ዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ

3. ለዜጎች የተፈቀደውን የአገር ውስጥ ገበያ የውጭ ዜጎች ገብተው የግብይት ስርዓቱን እንዳያዛቡ
   በሚል ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር የተላለፈው መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ አፈጻጸሙን
   መከታተል

4. በንግድ ሚኒስቴር ያለውን የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት በመፈተሸ
   ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ

5. የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴው ከክልል በተዋረድ እስከ ቀበሌ ያለው ተግባራዊ ሊሆኑ
   የሚችሉ የኮንትሮባንዱን ለመከላከል የሚያግዙ ተግባራትን በማቀድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል
   መስተዳድር አካላት (ከክልል እስከ ቀበሌ) ስራውን በሐላፊነት የእኔ ጉዳይ ነው ብሎ
   በቁርጠኝነት እንዲከታተልና እንዲመራው የጋራ የውይይት መድረክ በመፍጠር ተግባራዊ
   እንዲሆን ማድረግ

6. በእንስት የቀንድ ከብት ፤ጥጃ እና የወጭ ዝርያ       ያላቸው እንስሳት አወጣጥ ዙርያ ግልጽና
   የማያሻማ ገላጭ የሆነ መመሪያ እንዲኖር ማድረግ

7. የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚና
   በህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክ የሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ
   ያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ

8. ደረጃቸውን የጠበቁ የኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶች የእንስሳት አቅርቦትን ክልሉን በአማካለ
   መልኩ በተጠኑ ቦታዎች ላይ መገንባትና ማጠናከር

9. የወጪ እንስሳት የመለያ ቁጥር(ኢር ታግ) በሚስጢር ኮድ ተሰጥቶት በሀገር መከላከያ ሚ/ር
   ተዘጋጅቶ ለቁጥጥር በሚያመች መልኩ በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ



               የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት               Page 19
10.የኳራንቲን አገልግሎት


የግብርና ሚ/ር በአዋጅ ቁጥር 4/1987 በአንቀጽ 19/8 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ
የሚገቡትም ሆነ በሚወጡት እንስሳት እጽዋት እና የእንስሳት ውጤቶች ላይ ተገቢውን የኳራንቲንና
ኢንስፔክሽን እንዲያደርግ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ላይ እንደተገለጸው አንድ ህጋዊ ነጋዴ እንስሳትን ወደ ውጪ
ለመላክ የጤና ማረጋገጫ ወረቀት ከመጠየቁ በፊት እነዚህን ቅድመ ዝግጅቶች ማሟላት አለበት

     ክትባትና ሕክምና የሚያገኙበት ድርጅት/ጣቢያ

     የኳራንቲን ጊዚያቸውን የሚፈጽሙበት ጣቢያ

     ተፈላጊውን ክብደት እስኪያገኙ የሚቆዩበት ማደለቢያ ጣቢያ…..ወዘተ እንዲኖረው ያስፈልጋል
      ይላል፡፡

ሌላው በበመመሪያው የተገለጸው ደግሞ በቁም ወደ ውጪ ገበያ የሚቀርቡ የቀንድ ከብቶች
፤በጎች፤ፍየሎችና ግመሎች ተገቢውን ክትባትና ሕክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡በኳራንቲን ጣቢያ ቢበዛ
እስከ 30 ቀናት ሊቆዩ ይገባል፡፡የሚል ቢሆንም

ቡድኑ የተገነዘበው ነገር ቢኖር አሁን ያለው ኳራንቲን እየሰራ ያለው መመሪያውን ባልተከተለ መልኩ
መሆኑን ነው፡፡

 ነጋዴው ከብቶቹን    ከመግዛቱ   በፊት   የሚገዛውን     የከብት ቁጥር   ብቻ በመግለጽ   ሰርትፍኬት
  እንደሚዘጋጅለት

 መኪና ላይ እያሉ ምንም አይነት ክትባት ሳይሰጥና የማቆያ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ሰርትፊኬቱን
  እንዲያገኙ ማድረግ

 አንድ ነጋዴ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ዝግጅት ማሟላቱን ሳይጠየቅና ምንም ዝግጅት ሳይኖረው
  ፈቃድና ሰርትፍኬት እንዲያገኝ መደረጉ

በአጠቃላይ ክልሎቹ እንደገለጹት በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደ መሆኑን እና መስፈርቱን
የማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸው እንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላ
ከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡ እና የደሙ እንስሳት በህጋዊ
መንገድ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ህገ ወጥ አሰራር ምክንያቶች/መንስኤዎች

 የፌደራል ንግድ ሚንስቴር ለወጭ እንስሳት ፈቃድ ሲሰጥና ሲያድስ ነጋዴዎቹ ተገቢውን መስፈርት
  ማሟላታቸውን ከግብርና ሚ/ር ማረጋገጫ እንዲያመጡ ሳይጠይቅ ፈቃድ መስጠቱ

 በእንስሳት ንግዱ ዙርያ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ሆነ እንስሳት አርቢው ህብረተሰብ በድንበር ዘለል
  የእንስሳት በሽታዎች ዙርያ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆን

                   የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                 Page 20
 የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት የህግ ክፍተትና ጉድለት መኖሩ

 የየአካባቢው የእንስሳት በሽታዎች ስፋትና ስርጭት የሚያመላክቱ መረጃዎች ውስንነት እና ጉድለት

 መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም የስራ ኃላፊነትና የስራ ድርሻቸውን በተመለከተ በፌደራል
  ለተወከሉ ባለሙያዎችና ውክልና የተሰጣቸው ክልሎች በሚገባ እንዲያውቁት አለመደረጉ እና
  የክትትልና የቁጥጥር አለመኖር

 የእንስሳት ኳራንቲን የሥራ ክፍል በሥሩ በሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስትና ጣቢያዎች አሠራር
  ወጥ አለመሆን እና ለሥራ ክፍሉ ከዚህ በፊት የወጡ መመሪያዎችና ደንቦች በየጊዜው አለመሻሻል፣
 በሀገሪቱ የሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስት ጣቢያዎች ባለሙያዎችና በሥራው ዙሪያ የወጣውን
  መመሪያ ጠንቅቆ አለማወቅ /አለመረዳት/ እና ተግባራዊ አለማድረግ፣
 በእነዚህ ጣቢያዎች ካለው የሥራ /የኤክስፖርት/ ስፋት አንፃር እና መንግስት ካስቀመጠው እቅድ
  አንፃር ከግብ ለማድረስ ጣቢያዎቹ በሠው ኃይልና በሎጀስቲክስ ያልተሟላ መሆን፣
 ለኤክስፖርት ለተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና በተቆጣጣሪው አካል
  የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀየርና የመለወጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑ፣
 የኤክስፖርት ሥራውን ስፋት በአማከለ መልኩ የኳራንቲን ጣቢያና ሰርቪስ የሚሰጡ ጣቢያዎች
  በአገሪቱ   ማዕከላዊ   ቦታዎች   መደራጀት    /ለምሣሌ፡-   አዳማ፣ድሬዳዋ/   እና   በጠረፍ    አካባቢዎች
  አገልግሎቱ አለመኖር፣
 የመድሃኒትና የክትባት አቅርቦት አስተማማኝ አለመሆንና ከሚመለከታቸው አካላት ውጪ ደረጃውን
  ባልጠበቀ ሁኔታ መያዝ፣
 ለክልሎች የተሰጠው የሠርቲፍኬሽን ውክልና መመሪያና ደንብ የሌለውና ለክትትልም አስቸጋሪ
  መሆን፣
 በኳራንቲን የቼክ ፖስት ጣቢያዎች በሱፐርቪዥን እና የክትትል ሥራ ከዋናው መ/ቤት ክትትልና
  ድጋፍ ደካማ መሆን፣
 በኳራንቲን   ጣቢያዎች    ለሥራው     የሚመደቡ     ባለሙያዎች      ተከታታይ     የሆኑ    ስልጠናዎች፣
  በተደራጁት ኳራንቲን ቦታና /አዳማ፣ድሬዳዋ/ የልምድ ልውውጥ አለማግኘት፣
 በኤክስፖርት ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሀብቶች ስለ ሥራው /ስለ ኳራንቲን/ አዋጅ፣ ደንብና
  መመሪያ አሠራር በቂ ግንዛቤ አለመኖርና ለደንቡ መፈጸም ተነሳሽነት አለመኖር፣
 ለእንስሳት መጓጓዣነት የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ለዚሁ ተግባር ያልተዘጋጁ መሆናቸው በእንስሳው
  አካላዊ ጉዳት ማድረስ ማለትም ስብራትና ከፍተኛ ቁስለት ስለሚገጥማቸው /በተለይም ግመልና
  ከብት/ በተቀባይ አገራት ስለኢትዮጵያ እንስሳት ያላቸውን ፒክቸር / ስዕል/ የተበላሸ መሆን፣




                    የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                      Page 21
 በኳራንቲን ጣቢያዎች በጉዞ ላይ ለሚሞቱና ለሚጐዱ እንስሳት የአወጋገድ የማገገሚያ መመሪያና
    ደንብ አለመኖር፣ /የእንስሳት በሽታ ስርጭትን ማባባስ/
 የእንስሳት    ዝውውር       /ማለትም    ከክልል    ክልል/   ልቅ   መሆን       ለእንስሳት   በሽታ   ስርጭትና
    ለኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት መንስኤ መሆን፣
 በሰፋፊና     በዋና   ዋና   የእንስሳት   ገበያ    ማዕከላት   /ለምሣሌ፣   ያቤሎ፣ባቢሌ፣ገንዳውሃ፣ሁመራ../
    አቅራቢያ ለተገዙት እንስሳት ደረጃውን የተጠበቀ መጫኛ፣ ማራገፍያ፣ መመገቢያና ውሃ የሚገኝበት
    ቦታዎች አለመኖር፣
   የቄራዎች    የስጋና      የስጋ   ውጤቶች      ማደራጃ    አለመኖር፣     /   ያሉትም     በአጥጋቢ    ሁኔታ
    አለመሰራት/ጐንደር፣ባ/ዳር፣መልጌ ወንዶ/ ቄራዎች፣
 ከሁለት ዓመት በፊት በሱማሌ ክልል የኳራንቲን ቼክ ፖስት ላይ የተመደቡት ባለሙያዎች ወደ
    ሥራ አለመግባት ፣




                        የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                           Page 22
ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት


                                      የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም
                      መቀሌ              ድሬደዋ         ባህር ዳር              ጅጅጋ


                   የተያዙ                           የተያዙ             የተያዙ               ጠቅላላ ድምር
        የወጪ         የቁም           የተያዙ             የቁም              የቁም           የቁም
      ኮንትሮባንድ      እንስሳት           የቁም     በገንዘብ እንስሳት     በገንዘብ   እንስሳት በገንዘብ እንስሳት በገንዘብ
ተ.ቁ     ዓይነት  መለኪያ  ብዛት    በገንዘብ እንስሳት     ሲተመን    ብዛት    ሲተመን      ብዛት   ሲተመን ብዛት       ሲተመን
  1   ቀንድ ከብት በቁጥር     66 159,100     44   44,000  1,849 9,166,100     73 301,000   2032   9,670,200
  2   በግ      በቁጥር     42  33,600     56   27,900    147    88,200    667 319,060    912     468,760
  3   ፍየል     በቁጥር                   160   68,132    260   156,000    127  62,200    547     286,332
  4   ግመል     በቁጥር      7  57,000                      1    10,000                     8      67,000
  5   አህያ     በቁጥር      2   2,000                      8    15,000                    10      17,000

      ድምር              117 251,700   260 140,032   2,265 9,435,300    867 682,260   3,509   10,509,292


ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ
ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004)


ተ.ቁ                       የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም
                                                                                             ጠቅላላ
      የወጪ እንስሳት    መለኪያ   መቀሌ(ሁመራ) ድሬደዋ              ባህር ዳር       ጅጅጋ            አፋር(ጋላፊ)
                                                                                             ድምር
                                                     (ገንዳውሃ)

      ቀንድ ከብት      በቁጥር        10,199         459        60,871      67,168

      በግ           በቁጥር           556                                17,843

      ፍየል          በቁጥር         2,080       5,739                    10,177

      ግመል          በቁጥር        12,975       1,640                        4,025

      ድምር                      25,809       7,838        60,871      99,213        218,053    411,784

      በገንዘብ ሲተመን   ዶላር       9,856,380   1,236,705    24,351,420 31,005,943 መረጃ የለም 66,450,448

ምንጭ፡-ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን




                                          የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                          Page 2
ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብር
ተ.                                                                                                              የሚመለከታቸው




                                                                                                                              ሰሌዳ
                                                                                                                              የጊዜ
ቁ               መንሲኤዎችና ችግሮች                        መፍትሄዎች                         የሚከናወኑ ተግባሮች                   አካላት
                                                                       የአጭር                       የረጅም
                                           የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች                                              ንግድ ሚ/ር
                                           እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም                                              ፤ግብርና፤ህብረት
                                           በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች                                             ሥራ፤ባለሀብቶች፤
                                                                                                                የኢስወቴኢ
                                           ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት
                                                                       1.ነባር የግብይት ማዕከላትን የውስጥ                  ፤ክልሎች
                                           በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ    መሰረተ ልማቶችን በማሟላት
                                           የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት    ለግብይት ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ
        የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊ               ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ    2.ለህጋዊ ቁም እንስሳት ነጋዴዎች
        አቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ         የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ   የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ገበያዎችን
        በመሆናቸውአስተማማኝ ገበያ በየአካባቢው           እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና        በማመቻቸት ረገድ ወቅታዊ የግብይት      1.ጥናት ተደርጎ
        አለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤት        የግብይት ስርዓቱን የሚከታተልና የሚመራ    መረጃዎችን በመስጠት የግብይት         በጅጅጋ፤በደጋሀቡር
                                                                       ትስስሮች እንዲኖር ማድረግ           ላይ መንግስትና
        አገሮች ዋጋ ጋር የሚወዳደር ወይም የተሻለ         የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር
                                                                       3.የግብይት ህብረት ስራ ማህበራትን     በግል ባለሃብቶች
        አለመሆንና በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆን        ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት     በማደራጀት የማስፈጸምን የገንዘብ       የኤክስፖርት
        የሚችል የግብይት ስርዓት አለመኖርና የግብይት       መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ        አቅማቸውን በማጠናከር እንስሳትን       ቄራዎች መገንባት
1       መሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣             ማድረግ፡፡                      ለውጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻል       2.የግዥ ጣቢያዎች
                                                                                                  ማቋቋም
                                           በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት                                             የፌደራል
                                           በሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች      1.ከዚህ ቀደም ከጎረቤት አገሮች ጋር                  ጉዳዮች፤ገቢዎችና
                                           መሰረት ህገ ወጡን እንቅስቃሴ          የተደረጉ ስምምነቶች እንዲከበሩ የጋራ                  ጉምሩክ፤ክልሎች፤
        ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል      የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ     ውይይት በመፍጠር ዲፕሎማሳዊ
                                                                       ስራዎችን መስራት
        ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታቱ      እና የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን
                                                                       2.የነበሩት ስምምነቶች ከወቅቱ ጋር
        መሆኑ፤የህም የሚገለጸው በሀጋዊ መንገድ በሚገባ      በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት     በማገናዘብ እንዲሻሸል ማድረግ
        እንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከፍተኛ መሆንና        ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ     3.አስፈላጊ የሚሆኑ አቅርቦቶቹን
        በተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባ   ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም         በማሟት በተቀናጀ መልኩ ጠንከር ያለ
    2   መሆኑ ነው፡፡                           የሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት        ክትትልና ቁጥጥር ምድረግ




                                                                  የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት                       Page 3
147 (repaired)(1)
147 (repaired)(1)
147 (repaired)(1)
147 (repaired)(1)
147 (repaired)(1)
147 (repaired)(1)

Contenu connexe

Tendances

Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey Consultants
Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey ConsultantsBusiness Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey Consultants
Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey ConsultantsAurelien Domont, MBA
 
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case Study
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case StudyOperational Discipline - Deepwater Horizon Case Study
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case StudyWilson Perumal and Company
 
Lean Accounting
Lean AccountingLean Accounting
Lean AccountingPeter Klym
 
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001lancedafric.org
 
Management in the Digital Age - Vistage Presentation
Management in the Digital Age - Vistage PresentationManagement in the Digital Age - Vistage Presentation
Management in the Digital Age - Vistage PresentationRESULTS.com
 
Quality management strategy prince2
Quality management strategy prince2Quality management strategy prince2
Quality management strategy prince2selinasimpson2601
 
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocio
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocioMapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocio
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocioIsrael Rey
 
full assignment answer for BIS
 full assignment answer for BIS full assignment answer for BIS
full assignment answer for BISmarine9090
 
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...Rehan Elbedwehy
 
Histoire des SI
Histoire des SIHistoire des SI
Histoire des SIG Ramis
 
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark Report
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark ReportAberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark Report
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark ReportAnybill
 
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...PECB
 
Information systems in global business today in Management information system...
Information systems in global business today in Management information system...Information systems in global business today in Management information system...
Information systems in global business today in Management information system...Tonmoy zahid Rishad
 

Tendances (16)

Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey Consultants
Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey ConsultantsBusiness Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey Consultants
Business Process Management Training | By ex-Deloitte & McKinsey Consultants
 
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case Study
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case StudyOperational Discipline - Deepwater Horizon Case Study
Operational Discipline - Deepwater Horizon Case Study
 
Lean Accounting
Lean AccountingLean Accounting
Lean Accounting
 
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001
MANAGEMENT DES SYSTMES DE MANAGEMENT: L'APPORT DE ISO 27001
 
Management in the Digital Age - Vistage Presentation
Management in the Digital Age - Vistage PresentationManagement in the Digital Age - Vistage Presentation
Management in the Digital Age - Vistage Presentation
 
Quality management strategy prince2
Quality management strategy prince2Quality management strategy prince2
Quality management strategy prince2
 
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocio
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocioMapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocio
Mapas cognitivos y Mapas causales para comprender el proceso de negocio
 
full assignment answer for BIS
 full assignment answer for BIS full assignment answer for BIS
full assignment answer for BIS
 
Business Process
Business ProcessBusiness Process
Business Process
 
類神經網路
類神經網路類神經網路
類神經網路
 
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...
( إتحاف المهرة فى جمع العشرة للشيخ قدرى بن محمد بن عبد الوهاب حفظه الله ( سور...
 
Histoire des SI
Histoire des SIHistoire des SI
Histoire des SI
 
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark Report
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark ReportAberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark Report
Aberdeen Group: Invoice Reconciliation & Payment Benchmark Report
 
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...
Risk Based thinking - une nouvelle démarche pour un système de management de ...
 
Information systems in global business today in Management information system...
Information systems in global business today in Management information system...Information systems in global business today in Management information system...
Information systems in global business today in Management information system...
 
Business Process Management Training session 2
Business Process Management Training session 2Business Process Management Training session 2
Business Process Management Training session 2
 

147 (repaired)(1)

  • 1. የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ዙርያ የተደረገ ጥናት ሪፖርት መጋቢት 2004
  • 2. ማውጫ ገጽ 1.ማጠቃለያ ................................................................................................................................................... 1 2.መግቢያ ...................................................................................................................................................... 4 3. ዓላማው .................................................................................................................................................... 5 4.የጥናቱ አስፈላጊነት.................................................................................................................................... 5 5.ዝርዝር ዳሰሳ.............................................................................................................................................. 6 5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞን.............................................................................................................. 6 5.2. ጅጅጋና አካባቢው.............................................................................................................................. 8 5.2.1. ቶጎ ውጫሌ ............................................................................................................................... 9 ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳት ብዛትና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ.................................................................................10 5.2.2. ሀርትሼክ.................................................................................................................................. 10 5.3 አፋር ክልል...................................................................................................................................... 11 5.4.ትግራይ ክልል................................................................................................................................... 12 5.4.1. ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን) ............................................................................................12 5.5.አማራ ክልል...................................................................................................................................... 13 ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ ክልል በኮንትሮባንድ (በህገ ወጥ መንገድ) ወደ ሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳት ........................................................................................................ 14 5.6.ሞያሌ ................................................................................................................................................15 6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች ..........................................................................................16 7. ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች........................................................................................................... 17 8. በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች .................................................................................................... 18 9. ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች...........................................................................................19 10.የኳራንቲን አገልግሎት ..........................................................................................................................20 ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት ................................................................................................................... 1 ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ............................................................................................................................................................ 2 ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብር ....................................................................................................... 3 የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page ii
  • 3. 1.ማጠቃለያ የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በአፋርና በትግራይ (ሁመራ) ክልሎች የጸረ ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ እስከታችኛው ቀበሌ እርከን ድረስ በተቀናጀ መልኩ ከአገር ሽማግሌዎችና መላው ህብረተሰብ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ በመወያየት የጋራ አቋም በመያዙና ወደ ተግባርም በመግባት ውጤታማ ሥራ በማከናወናቸው የመቀነስ ዝንባሌ ያሳያል፡፡ በሱማሌ ክልል፤በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ በተመለከተ ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ተመስርቶ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረገ ቢገኝም የጥምር ኮሚቴው እንቅስቃሴ ተከታታይነት የሌለው በመሆኑ፤ህብረተሰቡ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ ካለው ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰንና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው፤ ህዝቡ በጎሳ፤በእምነት፤በባህል የተሳሰረ መሆኑ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ያለ መስራት ችግሮች ምክንያት የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅሰቃሴ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በህርትሼክና በሀርሺም መካከል ባለው መውጫ በር በብዙ ቁጥር የሚገመት እንስሳት በተለይም በጎችና ፍየሎች ወደ ሱማሌ ላንድ እየወጡ ሲሆን ግመሎችና የቀንድ ከብቶች እንደቀደም ተከተላቸው በብዛት እንደሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በአማራ ክልል በሽንፋ አቅጣጫ ወደ ቲሃ የሚወጣ የቀንድ ከብት በቀን አስከ 300 እንደ ሚወጣ መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ይህም ምን ያህል አሳሳቢና በዓመት ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ማስላትና የችግሩ ስፋት መገንዘብ አያዳግትም፡፡ በሞያሌ በኩል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ በተመለከተ እንስሳቱ ያለ ምንም እገዳ እና ቁጥጥር ሳይደረግባቸው ሙሉ በሙሉ በህገ ወጥ መልኩ በቀን በአማካይ እስከ 500 የቁም እንስሳት እንስት ከብቶችን ጭምር በኮንትሮባንድ አጎራባች አገር ወደ ሆነችው ኬንያ ይወጣሉ፡፡ በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND MEAT) በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናት እንደሚያመለክተው በ2007 ዓ.ም ሱማሌ በበርበራና በቦሳሶ ወደብ በኩል 3.05 ሚሊዮን በጎችና ፍየሎች 200000 የቀንድ ከብቶች ለወጪ ገበያ ያቀረበች ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ እንስሳት መሆናቸውን በመጥቀስ በ2005-06 እ.ኤ.አ በኮንተሮባንድ ለወጪ የቀረቡ እንስሳት 328000 የቀንድ ከብቶችና 1.1 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንደሆኑና ይህም አገራችን በህጋዊ መንገድ ለወጪ ንግድ ካቀረበችው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥ የጥናት ጽሁፉ ይጠቁማል፡፡ ከጅጅጋ ኳራንቲን ባለሙያዎች በተገኘው መረጃ መሰረት በህገ ወጥ መልኩ ወደ ሱማሌ ላንድ የሚወጡት እንስሳት መጠን 80 ከመቶ እንደሚሆንና በህጋዊ መልኩ የሚወጣው 20 ከመቶ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡
  • 4. በሠንጠረዥ 1.ላይ እንደሚያሳየው በ2003 ዓ.ም በጅጅጋ በቶጎ ውጫሌ በኩል በድምሩ 96416 የቁም እንስሳት በህጋዊ መንገድ በመላክ 34 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ ከሚወጣው የቁም እንስሳት 20 ከመቶ ድርሻ እንዳለውና ሌላው 80 ከመቶ የሚሆነው ግን በኮንትሮባንድ መልክ እንደሚወጣና ችግሩም ምንያህል አሳሳቢ እንደሆነ መረዳት የቻላል፡፡ በአብዛኛው የጠረፍ አካባቢ የሚገኙ አጎራባች አገሮች ህጋዊ ንግዱን ከማበረታታት ይልቅ የሚያዳክሙ መሆናቸውና በተዘዋዋሪ መልኩ ህገ ወጡን ንግድ የሚያበረታቱ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለአብነትም በህጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድ ከብት ብር 400 ቀረጥ የሚያስከፍሉ ሲሆን በኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻ ማስከፈላቸው ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በኮንትሮባንድ መልክ ወደ አጎራባች አገሮች እንደሚወጡና አገሪቷ ከዘረፉ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ እያጣች መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ስለዚህ ይህ ለአመታት የቀየ ችግር አሳሳቢና ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በቁም እንሳሰቱ ግብይት ከፍተኛ አቅም ያላችውና በዋናነት ስራዬ ነው ብለው ወደ ስራ የገቡ ነጋዴዎች ባለመኖራቸው ህገወጡን በማዳከም ህጋዊ ንግዱ አሸንፎ እንዲወጣና ህገ ወጦቹ ወደ መስኩ እንዲመጡ አለማድረጉ በአገሪቷ የሰፈነው የኮንትሮባንድ ንግድ ጉልህ ማሳያ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንስኤዎችና ችግሮች በተመለከተ አስተማማኝ የገበያ ትስስር በየአካባቢው አለመኖር ያሉት የስጋና የስጋ ውጤቶች ማደራጃ ወይም ቄራዎች እንስሳቱ በሚገኝበት አካባቢ ሳይሆን በመሃል አገር ላይ ማዕከል ማድረጋቸው እና በሙሉ አቅማቸው አለመስራታቸው፤ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታቱ መሆኑ፤ዋንኛ መንስኤዎች ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ የጠረፍ አካባቢዎች ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው፤ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች መኖራቸው እና በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተ የተሳሰሩ መሆናቸው ለችግሩ መባባስ መንስኤ መሆናቸውን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ንግድን ለመቆጣጠር እንዲቻል ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን የቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳት ዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ፤ የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና የግብይት ስርዓቱን የሚከታተልና የሚመራ የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡ በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት ከአጎራባች አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ህገ ወጡን እንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ ፤የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 2
  • 5. ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚና በህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክ የሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ፤ በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እንደ አካባቢው መልካምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይል፤የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም የሚገታበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የግድ ይላል፡፡ ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የኳራንቲንና ኢንስፔክሽን አገልግሎት አሰጣጥ ሲሆን በአጠቃላይ ክልሎቹ እንደገለጹት መመሪያውን ባልተከተለ መልኩ በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደ መሆኑን እና መስፈርቱን የማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸው እንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላ ከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡ እና የደሙ እንስሳት በህጋዊ መንገድ በአብዛኛው ቦታዎች (አማራ ክልል፤ጅጅጋ፤ሁመራ) ከብቶቹ ሳይታዩ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ኳራንቲን ባለመኖሩ በገልፍ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸውን የቦረና የቀንድ ከብቶችና የሱማሌ በላክ ሄድ (ዋንኬ) በጎች ወደ ጅቡቲ ከገቡ በኋላ በጅቡቲ ኳራንቲን ቆይተው በጅቡቲ ስም እየተላኩ ጅቡቲ ተጠቃሚ እየሆነች ትገኛለች፡፡ስለዚህ ጥናት ተደርጎ ደረጃቸውን የጠበቁ ኳራንቲን መገንባትና ተከታታይነት ያለው የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ስርዓቱን የጠበቀ የኳራንቲን ጣቢያ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 3
  • 6. 2.መግቢያ የእንስሳት ዘርፍ ለአለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለግብርና ክ/ኢኮኖሚ ያበረከተው አስተዋጽኦ 30% እና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ደግሞ 16% ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል(የጽ/ቤቱ ዶኩመንት 2003) ፡፡ ሀገራችን እንስሳትንና የእንስሳት ውጤቶችን ለውጪ ሀገር ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅም ያላት ሲሆን ለአብነትም ያህል በስጋና በቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ባለፈው የ2003 በጀት ዓመት 210 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል፡፡ ይህ እያደገ የመጣው የቁም እንሰሳት ንግድ ግምት ውስጥ በማስገባትና ሌሎች ነባር ሁኔታዎች በመመልከት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የመጪው አምስት ዓመት ዕቅድ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ሥጋ አሁን ካለበት 10ሺ ቶን ወደ 111ሺ ቶን፣ የቁም እንስሳት 334ሺ ወደ ከ2.5ሚሊየን በማሳደግ በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎረሜሽን መጨረሻ ዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ዕቅድ ተይዟል፡፡ ሆኖም ግን ህገወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሃገሪቷ በተለያዩ የጠረፍ አካባቢዎች ተንሰራፍቶ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ ህገወጥ መውጫ በሮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት ወደ ጎረቤት ሃገሮች ሶማሊያ፣ ኬንያና ጅቡቲ እና ሱዳን እንደሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ በዚህ ጥናት Analysis of the Ethio-Sudan cross-border cattle trade: The case of Amhara Regional State በሚል ርዕስ IPMS/ILRI እኤአ 2007 የተደረገው ጥናት ከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ወደ 24,000 ዳልጋ ከብቶች በዓመት እንደሚወጡ እና ይህም እኤአ 2006 ዓ ም በመተማ ዮሐንስ በኩል በህጋዊ መንገድ ወደሱዳን የተላኩት ዳልጋ ከብቶች 60% መሆኑ ተመልክቷል፡፡ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እኤአ ግንቦት 20 1997 ጥናት (Livestock Marketing and Cross Border Trade in the Southeast of Ethiopia) መሰረት በሁለቱ የሶማሊያ ወደቦች (በርበራና ቦሳሶ) በዓመት 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ካላቸውና ወደ ውጭ ከሚወጡት እንስሳት ውስጥ ሰማኒያ ከመቶ ወይም 96 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምንጫቸው ከኢትዮጵያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንሰራፋት መንስኤዎችም የተለያዩ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በህገወጥ መንገድ ከሀገራችን በመውጣታቸው እነዚህ እንስሳት በህጋዊ መንገድ ለአለም ገበያ ቢቀርቡ ሀገራችን ማግኘት የምትችለውን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር በአመት በማጣት ላይ እንደምትገኝ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በዋቢነት ለመጥቀስም በእንስሳት ገበያ ባለሥልጣን በ1993 ዓ ም በተደረገው ጥናት በደቡብ፤ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ አቅጣጫዎች ወደ ጎረቤት አገሮች በሚደረገው ህገወጥ ንግድ በዋናነት (የቁም እንስሳት) በዓመት ከአንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ ታጣለች፡፡ ስለዚህ ይህንን ችግር ለመቀነስና ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ከፍ ለማድረግ እንዲቻል እና እቅዱን ለማሳካት የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ከገቢዎችና ጉምሩክ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 4
  • 7. ባለስልጣን፤ከግብርና ሚኒስቴር፤ከንግድ ሚኒስቴር፤ከቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበር እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሀገሪቱ በተለያዩ የጠረፍ አካባቢዎች ምን ይመስላል፤ዋና ዋና መውጫ በሮች የመለየትና በምን መልክ መቆጣጠር እንደሚቻል በተለያዩ የክልል ከተሞች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ያሉት ጭብጥ ሁኔታዎች በማየት ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማሳደግ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች በማቅረብ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት መመሪያዎቻቸውን በማስተካከል የጥምር ኮሚቴዎችን በማጠናከር እቅዱን ማሳካት ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ መሆኑን በማስገንዘብ ይህ አጭር ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡ 3. ዓላማው የህገወጥ ንግድ መንስኤዎች መለየትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሆኑትን አቅጣጫዎችን በመንደፍ ባለ ድርሻ አካላት በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ 4.የጥናቱ አስፈላጊነት በዋና ዋና መውጫ በሮች በኩል እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ የእንስሳት ንግድ ላይ ጥናት በማካሄድ ህገወጥ ንግዱን ሊቀንሱ የሚችሉ ተግባራዊ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ የተጠቀምንበት ስልት  በቀጥታ ከሚመለከታቸው በወጪ ንግድ ከተሰማሩ ነጋዴዎች፣ ከክልሉ የመንግስት አመራር አካላት እና ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች( ጥምር ኮሚቴ ጋር ውይይት ተደርጓል  በወጪ ንግዱ ዙሪያ የሚደረጉ የግብይት ሂደትና ስርዓት እንዲሁም የጤና ጥራት ቁጥጥርን ቦታው ድረስ በመሄድ ዳሰሳ ተደርገዋል  ክፍተኛ የእንስሳት አቅርቦት በምንጭነት የሚያገለግሉ ቦታዎች ዳሰሳ ተደርጓል  የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻና መውጫ በሮችን መለየትና ለችግሩ መባባስ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን መለየት ተችሏል፡፡ በጎረቤት ሀገሮች ያሉትን የገበያ ማዕከላት በመመልከት ከህገወጥ ንግዱ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጤን ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 5
  • 8. 5.ዝርዝር ዳሰሳ 5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞን ድሬደዋ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ከፍተኛ ህገወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ዋንኛው ሲሆን ከተማው የህጋዊ ወጪ ንግድ መተላለፊያ መስመር ሆኖም ያገለግላል፡፡ ቡድኑ በአካባቢው ከተቋቋመው ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት በድሬደዋና አካባቢው የህገ ወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ራቅ ካሉት አካባቢዎች ማለትም ባሌ ፤ ቦረና ፤ አርሲ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ወዘተ ስፍራዎች ከመሃል አገር ሳይቀር በርካታ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት ብዙ መንገድ አቋርጠው በዚህ አካባቢ በማለፍ በተለያዩ ህገ ወጥ መንገድ በተለያዩ ህገ ወጥ መውጫ በሮች በመጠቀም ወደ ጅቡቲ፤ሱማሌ ላንድ እንደ ሚወጡ ለመገንዘብ ችሏል ፡፡ ከሚወጡትም የቁም እንስሳት መካከል እንስት የቀንድ እንስሳት፤የቀንድ ከብቶች ፤ (ጥጃዎች ፤ ወይፈኖች ) ፤አልፎ አልፎም ፍየሎችና በጎች እንዲሁም ግመሎችንም ይጨምራል፡፡ ቀደም ሲል በቀን እስከ 200 መኪና ያላነሰ በኮንትሮባንድ ይወጣ እንደነበረና ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እየቀየረ መጠኑ ከፍ እያለ የመጣ ቢሆንም ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የአካባቢው የጸረ- ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ተቋቋሞ ከዞን እስከ ቀበሌ በመደራጀት እንቅስቃሴ በማድረጉ ህገ ወጥ ንግዱ በተወሰነ መልኩ መቀነሱን ከተደረገው ውይይት ለማወቅ ችሏል፡፡ በድሬደዋ እና አካባቢው ለህገ ወጥ የቁም እንስሳት በመነሻነት የሚያገለግሉ ገበያዎች የድሬደዋ ገበያ፤የቢኬ ገበያ፤እና የባቢሌ ገበያ ናቸው፡፡ የባቢሌ የገበያ ማዕከል በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉት የግመል ገበያዎች ያቬሎ ከሚገኘው ሀሮበኬ ገበያ ቀጥሎ በከፍተኛ መጠን የግመል እንሰሳት ገበያ የሚካሄድበት የገበያ ማዕከል ነው፡፡ ገበያ ማዕከሉ በሳምንት ሁለት ጊዜ ሰኞና ሀሙስ የሚካሄድ ሲሆን የሰኞ ገበያ ትልቁ ገበያ ነው፡፡ገበያው በዋናነት የግመል ግዥና ሽያጭ የሚከናወንበት ቢሆንም በተጨማሪም የዳልጋ ከብት፤በግ፤ፍየልና እንዲሁም የጋማ ከብት(አህያ) ግብይት ይካሄዳል፡፡ ከወረዳው የንግድና ኢንዱስትሪ የገበያ ጥናት ባለሙያ ባገኘነው መረጃ መሰረት በአማካይ በሰኞ ገበያ ቀን እስከ 3000 ግመሎች እዚህ ገበያ ላይ ይቀርባሉ፡፡ እዚህ ገበያ የሚቀርቡት እንስሳት መነሻቸው በአብዛኛው ከምስራቅና ምእራብ ሐረርጌ ዞኖች ሲሆን ከባሌ፤ከቦረና፤ከጎዴ፤ከጭረቲ እና ከሌሎች ርቀት ካላቸው አካባቢዎች ይቀርባሉ፡፡ በግብይቱም ሂደት ተሳታፊዎች አርቢዎች፤ደላሎች፤ህጋዊ ነጋዴዎች፤እና የውጭ ሀገር ዜጎች መመልከት ችለናል፡፡ እነዚህም ከሱዳን ፤ከሱማሌ ላንድ ፤ከየመንና ከግብጽ የመጡ የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው በቀጥታ ገበያው ውስጥ በመግባት በአካል ተገኝተው በደላላዎችና ፈቃድ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጋር በመሆን ለአገር ውስጥ ዜጎች ብቻ የተፈቀደውን ንግድ ላይ በመሳተፍ ግዥ ሲያከናውኑንና ሲያስገዙ ተመልክተናል፡፡ይህ ድርጊታቸው የገበያውን የግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸውንና ገበያውም ህጋዊንና ህገ ወጥ ንግዱን እያስተናገደ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡የቁም እንስሳቶቹም የሚጓጓዙት በአብዛኛው በነጂዎች አመካኝነት በእግር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 6
  • 9. ከእነዚህ የገበያ ማእከሎች ድሬደዋ፤ቤኪ እና ባቢሌ የሚገዙት የቁም እንስሳት በህገ ወጥ መንገድ የሚጓጓዙበት እና የሚወጡበት አቅጣጫ ከቢኬ ሜቶ ጣቢያ ሓሬ ዲከል(ጅቡቲ) ከቢኬ ኡመር ጉልፍ ዱርዱር ዲከል(ጅቡቲ) ድሬደዋ ሽንሌ ጋድ አዲጋላ ኡመር ጉልፍ ዱርዱር ዲከል(ጅቡቲ) ድሬደዋ ሽንሌ ጋድ ሜቶ ሀሬ ዲከል(ጅቡቲ) ድሬደዋ አዲጋላ ሐጂም ዲከል(ጅቡቲ) ባቢሌ ፋፈም ቆቦ ቦቃ ጭናክሰን ደንበል አሻ ሀጂም(ሱማሌ ላንድ) ባቢሌ ጭናክሰን ቱሉጉሌት ዶሮናጂ ሱማሌላንድ ባቢሌ ጅጅጋ ቶጎውጫሌ ሱማሌ ላንድ(ህጋዊና ህገ ወጥ በሆነ መልኩ) ቡድኑ ከድሬደዋ ገቢዎችና ጉምሩክ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ኃላፊ፤ከደሬደዋ ኳራንቲን ባለሙያዎች እና የሽንሌ ዞን መስተዳድር ጋር በመሆን የቁም እንስሳት ህገ ወጥ እንስሳት እንቅስቃሴን መተመለከተ ውይይት ተደርጓል፡፡ ሽንሌ ዞን ከሱማሌ ክልል ዞኖች አንዱ ስትሆን በሰሜን ምስራቅ በኩል ትገኛለች፡፤ዞኑ ከጅቡቲ እና ከሱማሌ ላንድ ጋር በድንበር ይገናኛል፡፡ የሽንሌ ዞን ከምስራቅ ሐረርጌ፤ከምእራብ ሐረርጌ፤ከአርሲና ከባሌ የሚመጡ ህገ ወጥ የእንስት እንስሳት ጥጃዎች ማረፊያና ማስተላለፊያ በመሆን ወደ ጅቡቲና ሱማሌ ላንድ ለሚሄዱ ህገ ወጥ እንስሳት መነሻ ሆና ታገለግላለች፡፡ እንስሳቶቹ ከሽንሌ ዞን በመነሳት ከዋናው መስመር ከ60-65 ኪ.ሜ በመራቅ በረሃውን ተከትለው ስለሚሄዱ ለቁጥጥርና ክትትልም አመቺ አይደለም፡፡ ሌላው ከቤኪ፤መኢሶና አፍደም ላይ የግብይት ስርአቱን ከአካሄዱ በኋላ ሳር እናበላለን በሚል ሰበብ ወደ ድንበሩ ከተጠጉ በኋላ በአዲጋላ በኩል ወደ ጅቡቲ ያስወጣሉ፡፡ በዞኑ የዞኑ የቆዳ ስፋትና የእንስሳት ክምችን በአማከለ መልኩ የተሰሩ የገበያ ማዕከላት አለመኖሩ በዞኑ ከሚታዩት አበይት ችግሮች አንዱና ዋንኛው ሲሆን ይህም ለህገ ወጡ ንግድ መንሰራፋት ምክንያት ሆኖአል፡፡ ስለዚህ የዞኑን ቆዳ ስፋትና በረሃነት እንዲሁም የእንስሳት ክምችትን መሰረት ባደረገ መልኩ የግብይት ማዕከላትን በማቋቋም ከላኪና ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ላኪዎችና ነጋዴዎች ጋር የግብይት ትስስርን በመፍጠር ተግባራዊነቱን በመከታተል የእንስሳት ፍልሰቱን መቀነስ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 7
  • 10. 5.2. ጅጅጋና አካባቢው ቡድኑ በጅጅጋ ለሚገኙት ለሚመለከታቸው መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች፤ ነጋዴዎችና ማህበራት ተወካዮች ተልዕኮውን በመግለጽ በህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ፤መንስኤዎችና ችግሮች እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦች ዙርያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት በአሁኑ ወቅት በጠረፍ አካባቢዎች አባላትን በመመደብ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ እና ከጥምር ኮሚቴ ጋር በቅንጅት መስራት በመጀመራችው በተወሰነ መልኩ ኮንትሮባንዱ እንቅስቃሴ የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም ከአካባቢው ካለው ስፋት አንጻር ከአንዱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እና ከሌላው መቆጣጠሪያ ጣቢያ መካከል ያለው ርቀት በጣም ሰፊ በመሆኑ አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት በኮንትሮባንድ መንገድ ከሀርትሼክ እስከ ጋሻሞ ባሉት መውጫ በሮች ወደ ሱማሌ ላንድና ፑንት ላንድ እየወጡ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም የክልሉ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንደገለጹት በክልሉ የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ እየቀነሰ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ለዚህም በዋናነት ከመሃል አገር ወደ ጠረፉ አካባቢ ስኳር፤ ዘይት እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶች መምጣት በመጀመራቸው እና በመንግስት 6 የሚሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ በመፍቀዱ ኮንትሮባነድ ንግዱ በአንጻራዊነት እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከዚህ በፊት ብቻውን ሲሰራ የነበረውን አሰራር በመቀየር ከንግድና ትራንስፖርት፤ከአስተዳደር ም/ቤት፤ከአስተዳደርና ፍትህ፤ከፌደራል ፖሊስና መከላከያ ጋር በቅንጅት የጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በየወሩ ወር በገባ በ25ኛው ቀን ላይ በመገናኘት የጋራ ውይይት በማድረግ በሚከሰቱ በችግሮች ዙርያ በመወያያትና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማስቀመጥ በሂደት ችግሮችን እየተፈቱ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡ የመውጫ በሮችንም በተመለከተ  ከደገሀቡር በመነሳት በሀርሼንና በሀርትሼክ መካከል (አበከር) አድርጎ ወደ ሱማሌ ላንድ ይገባል  ከጨረቲ፤ከአፍዴር፤ከጎዴ፤ከቀብሪድሀር በመነሳት በሀርትሼክና በሀርሺን መካከል በመውጣት ወደ ሱማሌ ላንድ ይገባል  ከባቢሌና ከፊቅ በመነሳት ጅጅጋን ወደ ግራ በመተው በቀብሪበያህ በኩል ሀርቲሼክን ወደ ቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል  ከኮምቦልቻ ከሃረርና ጉርሱም በመነሳት በጭናክሰን አድርገው በተፈሪበርና ለፌሳ መካከል በማለፍ ቶጎ ውጫሌን ወደቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል የሚወጡትም የቁም እንስሳት የዳልጋ ከብት፤በግናፍየል እንዲሁም ግመሎች ይገኙበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 8
  • 11. ከሱዳን የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያ ከሱማሌ ላንድ የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያ ግብይት ላይ 5.2.1. ቶጎ ውጫሌ ቶጎውጫሌ ከጅጅጋ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ከተማዋ የህጋዊ የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ መውጫ በር ሆና ታገለግላለች፡፡ ከኢትዮጵያ ድንበር በግምት 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ሱማሌላንድ ቶጎውጫሌ ላይ ሰፊ የቀንድ ከብት ግብይት ይካሄድባታል፡፡ በዚህ ገበያ ህጋዊና ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሰፊው የሚካሄድበት ሲሆን ቡድኑ በ08/06/04 በገበያ ማዕከሉ በመገኘት የገበያውን እንቅስቃሴ ለማየት ችሏል፡፡ በአማካይ ከ50 በላይ አይሱዙና ኤፍ.ኤስ.አር አይሱዙ መኪናዎች በየቀኑ ወደ ገበያው ይመጣሉ ( በአረፋና በኢድ የሙስሊም በዓላት ወቅት የሚቀርበው የቁም እንስሳት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻቅብ የአካባቢው ነጋዴዎች ይገልጻሉ) የቁም እንስሳቱም የሚመጡት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሆን በዋናነትም ከባሌ፤ ከቦረና፤ ከኢሉባቦር (ጨወቃ)፤ከጅማ፤ ከወለጋ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ለማየት ተችሏል፡፡ከሚቀረቡትም እንስሳት በእድሜም ሆነ በክብደት በአብዛኛው ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር በወጣ መመሪያ ከተፈቀደው 320 ኪ.ግ ወይም ከዚያ በላይ የሚለውን በመጣስ ዕድሜአቸው ከ 1 ዓመት ተኩል በታችና ክብደታቸው ደግሞ በአማካይ ከ150 ኪ.ግ በታች የሆኑ ጥጃዎች መሆናቸውን ለማየት ተችሏል፡፡  የቁም እንስሳት ጭነው ወደ ገበያው የሚገቡ መኪናዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 150 እንደሚከፈልና ለተጨማሪ ወጪዎች መዳረጋቸውን ነጋዴዎቹ በምሬት ይናገራሉ፡፡  ሌላው ከነጋዴዎቹ መገንዘብ የተቻለው የቁም እንስሳት ግብይቱ የሚካሄደው ከኢትዮጵያ ድንበር 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የሱማሌላንዷ ቶጎውጫሌ መሬት ላይ በመሆኑና ከአገር ውስጥ የወጣ የቁም እንስሳ ካልተሸጠ ወደ ሀገር ውስጥ መመለስ ስለማይችል እና እዚያም ለማቆየትም የመኖ ችግር በመኖሩ ነጋዴው እንስሳቱን አቆይቶ እና ተደራድሮ በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ እድል ስለማይኖራቸው በተገኘው ዋጋ በቅናሽ በመሸጥ ለኪሳራ ይዳረጋሉ ፡፡  አንዳንድ ጊዜ ሽያጩ ከተካሄደ በኋላ ገንዘቡ ወዲያው ስለማይከፍሏቸው ነጋዴው ሱማሌላንድ ላይ ገንዘቡን ለማግኘት በሱማሌ ላንድ በሚደረገው ቆይታና መጉላላት ለከፍተኛ ወጪ ስለ ሚዳረጉ ኪሳራ ውስጥ በመግባት ከግብይቱም በመውጣት አልፎ አልፎም ወደ ህገ ወጡ ንግድ ለመቀላቀል ይገደዳሉ፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 9
  • 12. በቶጎ ውጫሌ ከኢትዮጵያ ወደ ሱማሌ ላንድ የሄዱና ለገበያ የቀረቡ ጥጃዎች ፎቶ ግራፍ ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳት ብዛትና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ ተ.ቁ ዝርዝር መለኪያ 2000 2001 2002 2003 ምርመራ 1 የቀንድ ከብት ቁጥር 15901 16579 33619 65619 2 ግመል ፤ 143 137 7646 13937 3 በግ ፤ 2767 10500 8834 4 ፍየል ፤ 580 8026 ድምር ፤ 19391 27216 41265 96416 የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ዶላር 6,902,938 7,545,172 17,300,716 34,093,050 ምንጭ፡-የጅጅጋ ኳራንቲን ጣቢ 5.2.2. ሀርትሼክ በመጨረሻም ቡድኑ ከጅጅጋ 70 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሀርት ሼክ ገበያ ላይ በመገኘት የቁም እንስሳት ገበያውን ለማየት እና መረጃዎችን ለመሰብሰብ ችሏል፡፡ በአካባቢው በከፍተኛ ደረጃ የውሃ አቅርቦት ችግር በመኖሩ አንድ በርሜል ውሃ እስከ 80 ብር እንደሚሸጥ እና የገበያ ማዕከሉም ከፍተኛ የውሀ አቅርቦት ችግር እንዳለበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የገበያ ማዕከሉ የተገነባው በቮካ ኢትዮጵያ ሲሆን ገበያው ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው በጎችና ግመሎች ለግብይት የሚቀርቡበትና እንስሳቶቹም በሃርትሼክ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ እንደሚወጡ ከስፍራው ከነበሩ ነጋዴዎች እና ነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡ በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND MEAT) በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናታዊ ጽሁፍ እንደ ሚያመለክተው ሱማሌ ላንድ እኤአ በ2007 ዓ.ም በኮንትሮባንድ መልክ በሀርትሼክና በለፌሳ በኩል በቶጎ ውጫሌ አድርጎ ሱማሌ ላንድ የገባ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ በግና ፍየል እንዲሁም 100,000 የሚገመት የቀንድ ከብት ለወጪ ገበያ አቅርባለች፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 10
  • 13. በአጠቃላይ የሱማሌ ክልል በእንስሳት ሀብት ክምችት በተለይም ግመል፤ፍየል እና በግ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱማሌ ላንድ፤ፑንትላንድ፤እንዲሁም ወደ ጅቡቲ እንደሚወጡ ከዚያም በራሳቸው ስም ወደ አጎራባች አረብ አገሮች እንደሚላኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ይህንንም ከላይ በፎቶግራፉ የሚታዩት በጎች እና ፍየሎች መመልከት ይቻላል፡፡ አዚህም አካባቢ የሚታየው ዋንኛው ችግር የክልሉ የድንበር ስፋት በአማከለ መልኩ የክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦት በበቂ ደረጃ አለመኖር ፤ በሱማሌ ላንድና በኢትዮጵያ ሱማሌ መካከል ያለው የጠነከረ የጎሳ ትስስር እና የፍጆታ ዕቃዎች በበቂ ሁኔታ ያለመድረስ ነው፡፡ ከሀርት ሼክ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ ለመላክ የተዘጋጁ በጎች 5.3 አፋር ክልል የአፋር ክልል ከኢትዮጵያ አርብቶ አደር ክልሎች አንዱ ሲሆን ክልሉ በዋናነት ግመል፤በግና ፍየል እንዲሁም የቀንድ ከብት የሚረባበት አካባቢ ነው፡፡ክልሉ እንደ አጎራባቹ ሱማሌ ክልል ሰፊ የሆነ የድንበር ወሰን ያለው ነው፡፡ ወደ ክልሉ እንስሳት ከተለያዩ አጎራባች ክልሎች የመገበያያ ቦታዎች ጎሊና(ወልዲያ)፤አለውሃ(ትግራይና አማራ)፤ዳንዲ(ትግራይ )እና ከክልሉ ፤ጭፍራ እና ከመሳሰሉት ተገዝተው ወደ ክልሉ ትልቁ የገበያ ማዕከል አሳይታ ይገቡና ግብይቱ ከተከናወነ በኋላ የቁም እንስሳቱ በህገ ወጥ መንገድ በአፋምቦ በኩል ወደ ዳካ በመሻገር በእግር ወደ ጅቡቲ ይወጣሉ፡፡ ሌላው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መውጫ ከአካባቢው በመነሳት ከአዳይትና ገዳማይቱ በኩል አድርገው በሽንሌ ዞን በኩል ወደ ጅቡቲ እንደሚገቡ ከክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፤፤ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 11
  • 14. ሆኖም በአሁኑ ወቅት ያለው የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የመቀነስ ሁኔታዎች ይታያሉ፡፡ ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው በክልሉ ፕሬዝዳንት የሚመራ የጸረ-ኮንድሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ተቋቋሞ ህገ ወጡን ንግድ ለመቀነስና ብሎም ለመግታት የሚያስችለውን እቅድ ነድፎ እስከ ታችኛው አስተዳደር እርከን በማውረድ ኮሚቴው በከፍተኛ ደረጃ በመንቀሳቀሱና በየሁለት ሳምንቱ እተገናኘ የሚያጋጥሙትንና ያጋጠሙትን ችግር እየፈተሸ እና መፍትሄ እያስቀመጠ በቅንጅት እየሰራ በመሆኑ ነው፤፤ ክልሉ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የጠራ የመከላከል አቋም እንዳለው ህዝቡን ከላይ እስከ ታች ግንዛቤ በማስጨበጥ ፤የአካባቢው ሽማግሌዎችን በማሳተፍ በአገሪቷ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በዝርዝር በማስረዳት ህብረተሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲያገኝ በመደረጉ ነው፤፤ ይህም ለሌሎች ተመሳሳይ ክልሎች መልካም ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል ቡድኑ ያምንበታል፤፤ 5.4.ትግራይ ክልል የትግራይ ክልል የቁም እንስሳት የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ ከሚካሄድባቸው ክልሎች አንዱ ስትሆን በሰሜን በኩል ከኤርትራ እና በሰሜን ምእራብ በኩል ከሱዳን እንደምትዋሰንና የህገ ወጡ የቁም እንስሳት መውጫም በሁመራ ደቡባዊ ምእራብ አቅጣጫ በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱዳን እንደ ሚገቡ ቡድኑ የክልሉን የገቢዎችና ጉምሩክ፤ንግድ መምሪያ፤ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ክፍሎች በማነጋገር ለመረዳት ተችሏል፡፡ በህገ ወጥ መንገድ የሚወጡት የቁም እንስሳት የሚመጡትም ከተለያዩ ቦታዎች ሲሆን በዋናነትም ደቡብ ትግራይ፤ ራያና ሰሜን ወሎ፤ሰሜን አርማጮ እና ቀፍታ ሁመራ ወረዳዎች መሆናቸውንና የሚወጡትም እንስሳት በአብዛኛው የዳልጋ ከብትና ግመሎች ናቸው፡፡ 5.4.1. ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን) ቡድኑ ከመቀሌ ወደ ሁመራ በመጓዝ በአካባቢው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ለመቃኘት ሞክሯል፡፡ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰብሳቢነት ፤የገቢዎችና ጉምሩክ የሁመራ መቅረጫ ጣቢያ ሀላፊ፤ግብርና መምሪያ ሃላፊ፤አስተዳደርና ጸጥታ ሐላፊ፤ፌደራል ፖሊስ ፤የዞኑ ፖሊስ ፤ንግድና እንዱስትሪ መምሪያ ሐላፊ፤ የፌደራል ኳራንቲን ተወካይ በተገኙበት ስለ ህገ ወጥ እንስሳት ንግድ መነሻ እና ፤መውጫ በሮች፤መንስኤዎችና መፍትሄዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ በአካባቢው የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ተገልጾ ከሚያዚያ ወር 2003 ዓ.ም የዞኑ ጀምሮ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በጋራ በመሆን በቅንጅት በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ በመጀመሩ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው መቀነሱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ጥምር ኮሚቴው በዞን ደረጃ በየወሩ ወር በገባ በ9ኛው ቀን በወረዳ ደረጃ በየ 15 ቀኑ እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ በየሳምንቱ እየተገናኙ አጠቃላይ ከጸጥታና ኮንትሮባንድ ንግድ ጋር በተያያዘ ግምገማ በማካሄድ ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ በመወያየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን እየፈቱ በመሄዳቸው የህገወጥ ንግዱ እንቅስቃሴ መቀነሱ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጻል፡፡ በዞኑ የግብይት ሁኔታዎች በሚፈለገው ደረጃ ያልተመቻቹና በአግባብም ያልተሰራበት አንድም ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት ገበያ ማዕከልናየእንስሳት ማቆያ የሌለበት መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 12
  • 15. 5.5.አማራ ክልል በአማራ ክልል ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ከሌሎች ምርቶች ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፤ለዚህም ዋናው ምክንያት ሰፊ የጠረፍ ድንበር መኖሩ ለክትትልና ቁጥጥር አስቸጋሪና ሁሉም ቦታዎች ለመድረስና ለመሸፈን አለመቻል ሲሆን ሌላው ደግሞ የግብይቱ ስርአት አለመመቻቸት ነው፡፡ ይኸውም ሱዳን አገር የቀንድ ከብት ዋጋ ከሀገር ውስጥ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር በሀገር ውስጥ የአንድ ቀንድ ከብት ዋጋ ብር 2500-3000 የሚያወጣ ሲሆን ይህ የቀንድ ከብት ሱዳን ተሸግሮ የሚሸጠው እስከ 5000 ብር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህና በሌሎች ከታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ብዙ እንስሳት በኮንትሮባንድ መልኩ ይወጣሉ ፡ይህንን ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ቀደም ብሎ ቢቋቋምም አንዴ ሞቅ አንዴ ላላ እያለ ነበር አሁን ግን የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ኦርየንቴሽን በመስጠት ኮንትሮባንዱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምሯል ፡፡ ጥምር ኮሚቴው ስራውን በመገምገም ከህገ ወጥ ነጋዴው ጋር በመሆን በህገ ወጥ ንግዱ ተሳታፊ የነበሩ የመዋቅር አካላት በማጋለጥ እና በማሰር እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠሉ የህገ ወጡ እንቅስቃሴ በመተማ በኩል ቢቀንስም ህገ ወጥ ነጋዴዎቹ ስልታቸውን በመቀየር ወደ ሽንፋ አቅጣጫ መዞራቸውንና በአካባቢው በተደረገ ክትትል በተለያዩ ግዚያት 200 ፤ 150 እና 50 በድምሩ 400 የቀንድ ከብት በዚህ በጀት ዓመት መያዛቸውን ከአካባቢው የተገኘ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በመተማ ቁጥጥሩ ሲጠናከር ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ወደ ሺንፋ 53 ኪ.ሜ በመራቅ በቀን እስከ 300 ከብት በህገ ወጥ መንገድ በአማካይ እየወጣ መሆኑን ገቢዎችና ጉምሩክ ገንደ ውሃ መቅረጫ ጣቢያ ሓላፊ ጋር ከተደረገው ውይይት ለመገንዘብ ተችሎዋል፡፡ መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት 60 ከመቶ የሚሆነው የቁም እንሰሳ የሚወጣው በኮንትሮባንድ መልክ መሆኑንና ከቆላማው አካባቢ ለኮንትሮባንዱ ንግድ 78 ከመቶ ድርሻ እንዳለው መረጃዎቹ ያመለክታሉ፡፡ በምሳሌነት ለመጥቀስ Yacob Aklilu, “the most excessive taxation system on cattle in East Africa” ን በመጥቀስ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND MEAT)” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 በቀረበው የጥናት ጽሁፍ በተገለጸው መሰረት በህጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድ ከብት ብር 400 ቀረጥ የሚያስከፍሉ ሲሆን በኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻ ያስከፍላል ፡፡ ይህም የሚያሳየው በሱዳን በኩል የህጋዊ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴን የሚያዳክምና የህገ ወጡን የቁም እንስሳት ንግድን የሚያበረታታ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህንን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ለመቆጣጠር ካለው ሰፊ ሜዳና የድንበር ስፋት(ከመተማ ዮሀንስ ግራና ቀኝ) አንጻር በገቢዎችና ጉምሩክ ኬላ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ያለውን የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦት እና የሰው ሀይል ችግር ቢቀረፍና ጥናት ተደርጎ በሺንፋና ሳንጃ ላይ መቆጣጠሪያ ኬላ ቢቋቋም ችግሩ ሊቀንስ እንደሚችል ከውውይቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻቸው በዋናነት ከሰሜን አርማጮ፤ ሰሜን ወሎ(ራያና ቆቦ)፤ሰከላናመራዊ(ጎጃም) በአነስተኛም ደረጃም ቢሆን ከባሌ፤አዳማ፤ቦረና፤፤አርሲ ሲሆኑ ወደ ውጪም የሚወጡት ከሱዳን ጋር ባለው ሰፊ ድንበር የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው  በሳንጃ አድርጎ በአሴራ ወደ ሱዳንና የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 13
  • 16. በመተማ ዮሃንስ 50ኪ.ሜ በስተደቡብ በኩል አድርጎ በሽንፋ ወደ ቲሃ (ሱዳን )  በቁንዝላ ቋራ በመሄድ በሺንፋ በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) እንዲሁም  ከነገደ ባህር ወደ ሽንፋ በመሄድ በይሙት በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) ይገባል፡፡ በአካባቢው ለወጪ እንስሳት የሚደረገው የጤና አገልግሎት አሰጣጥንም በተመለከተ ሥርዓቱን የተከተለ ሳይሆን እንስሳቱ በሌሉበት እና ሳይታዩ ነጋዴው የእንስሳቱን ቁጥር ብቻ በመግለጽ የጤና ሰርትፍኬት ከጎንደርና ከሌሎች አካባቢዎች ይዘው ይመጣሉ፡፡ ይህም አሰራር ከመመሪያው ወጪ በመሆኑ ሊቆም ይገባዋል፡፡ እንደሌሎቹ አካባቢዎች ሁሉ በአማራው ክልል ጠንካራ አቅም ያላቸው የቁም እንስሳት ላኪዎች ያልተሰማሩበትና ጥቂት በመስኩ የተሰማሩትም እንስሳትን በዱቤ በመሸጥ ገዥዎቹ ክፍያውን ሳይፈጽሙ ስለሚሰወሩ በርካታ ላኪዎች ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ስለዚህ የዱቤ አሰራርም ከወዲሁ ሊታሰብበትና መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ ክልል በኮንትሮባንድ (በህገ ወጥ መንገድ) ወደ ሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳት ተ.ቁ የእንስሳት ዓይነት መለኪያ መጠን በገንዘብ 1 በሬ በቁጥር 896 2 ላም 453 3 ወይፈን 335 4 ጊደር 83 5 ጥጃ 214 6 ፍየል 326 7 አህያ 8 8 ግመል 1 9 በግ 147 ድምር 2463 10395700 (ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ) ከዚህ ሰንጠረዥ መገንዘብ የሚቻለው የቁም እንስሳት ኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 14
  • 17. 5.6.ሞያሌ ሞያሌ ወረዳ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሮሚ›ያ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን እና በሱማሌ ክልላዊ መንግስት በሊበን ዞን የሚገኝ ሲሆን ህብረተሰቡ በአብዛኛው አርብቶ አደር ነው፡፡ የቀንድ ከብት፤ግመል፤ፍየልና በግ በከፍተኛ ሁኔታ የሚረባበት አካባቢው ነው፡፡ በዚህም ዞን እንደሌሎች ክልሎች የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ይካሄድበታል፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ የሞያሌ ቅርንጫፍ እንደገለጸው በዚህ ሞያሌ መውጫ በር በህጋዊ መልክ የሚወጣ የቁም እንስሳት እንደሌለ እና ወደ ኬንያ የሚሄደው እንስሳ በሙሉ የሚጓዘው በህገ ወጥ መልኩ መሆኑን ተገልጾዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በየ ቀኑ በኢትዮጵያ ሞያሌ በቦሌ በኩል በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች (እንስት በብዛት) ወደ ኬንያ እንደሚወጡ ታውቆአል፡፡የሚወጡትም እንስሳት የተኮላሸ ከብት(ሰንጋ)ና፤ላሞች ናቸው፡፡የጥናት ቡድኑ ኬንያ የሚገኘውን የገበያ ማዕከል በመሄድ ለማየትና ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ቡድኑ ድንበር ተሻግሮ በጥዋቱ የኬንያ ገበያ ለመመልከት በሄደበት ወቅት የኬንያው ጉምሩክ ባለሙያ እንደገለጹልን ከሆን ገበያው ከመድረሳችን በፊት 20 መኪናዎች(500 ከብቶች) ጭነው ወደ ናይሮቢ መሄዳቸውን የገለጹልን ሲሆን በገበያው ውስጥ የነበሩ ከብቶች ቁጥር በግምት 1500 እስከ 2000 ይደርሳል፡፡ባለሙያው እንደገለጹት ከብቶቹ በሙሉ የመጡት በኮንትሮባንድ ከኢትዮጵያ መሆኑንና ኢትዮጵያ እነዚህን ከብቶች በህጋዊ መንገድ ወደ ኬንያ እንዲገባ ብታደርግልን ኬንያ ቀረጥ በመሰብሰብ ተጠቃሚ ልትሆን ትችል ነበር ብለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የወጡ የቁም እንስሳት የግብይት ስነ ስርዓት በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ገበያ ከተከናወነ በኋላ ወደ ናይሮቢ በመውሰድ ከፊሎቹን ራንች ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ አደልበው ወደ ውጪ እንዲላኩ ይደረጋል፡፡መረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት ኬንያ ከምታቀርበው እንስሳት ከ25-30 ከመቶ የሚሆነው ምንጫቸው ኢትዮጵያ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ቡድኑ ቦታው ድረስ በሄደበት ወቅት ያየውን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ፍሰት ተመልክቶ ከገቢዎችና ጉምሩክ ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውይይት በማድረግ ቡድኑ በገባበት ማግስት 20 ሰንጋዎች መያዛቸውን ለመመልከት ችሏል፡፡ ያለውን ችግር መነሻ በማድረግ ቡድኑ ከዞኑ አስተዳዳሪ ጋር ባደረገው ውይይት የህገ ወጡ ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ና ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች  የሞያሌ ከተማ እና አካባቢው በሁለት መስተዳድር መተዳደሩ ለቁጥጥር አመቺ አለመሆን  በሁለቱ የጠረፍ ድንበር አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ በጎሳ በባህልና በልማድ የተሳሰረ በመሆኑ ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆኑ  የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ እንቅስቃሴ ያለመኖር  የህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር እና እንደሌሎቹ ሁሉ የእንስሳት ግብይት ሁኔታዎች ያልተመቻቸ እና መሰረታዊ ለውጥ ያልታየበት መሆኑ ነው፡፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 15
  • 18. ክልሉ የአካባቢውን የእንስሳት ለመቀነስ በበጀት አመቱ አስር ከመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየተንቀሳቀስ ቢሆንም በገበያ እጦት ምክንያት እቅዱን ለማሳካት እንደሚቸገር በመግለጽ ይህንን እቅድ ለማሳካት በአስቸኳይ የገበያ ችግር መቅረፍ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡ የእነዚህ እንስሳት መነሻ ቦታዎች ቦረና ዞን(ያቬሎ-ሀሮበኬ ገበያ፤ድብሉቅ፤) ስሩጳ እና ኮንሶ ሲሆኑ በሜጋ በኩል በማድረግ በቦሌ(ሞያሌ) ወደ ኬንያ ይገባሉ፡፡ እንስት እንስሳትና በሬዎች ከሞያሌ (በቦሌ በኩል) ከሞያሌ (በቦሌ በኩል) ወደ ኬንያ ሲጓዙ የተያዙ ወደ ኬንያ ሲጓዙ 6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች 1. አስተማማኝ ገበያ በየአካባቢው አለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤት አገሮች ዋጋ ጋር የሚወዳደር ወይም የተሻለ አለመሆን፤ በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆን የሚችል የግብይት ስርዓት አለመኖርና የግብይት መሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣ 2. ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታቱ መሆኑ፤ይህም የሚገለጸው በህጋዊ መንገድ በሚገባ እንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከፍተኛ መሆንና በተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባ መሆኑ ነው፡፡ 3. የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊ አቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው ከዚያ ራቅ ካሉት እንደ ሱማሌ ቦረና እና አፋር አካባቢዎች ወደ መሃል የኤክስፖርት ገበያዎች ከማቅረብ ይልቅ የትራንስፖርት ወጪና የተሻለ ዋጋ ወደ አለው ጎረቤት አገሮች ማቅረቡ የተሻለ አማራጭ በመሆኑ፣ 4. ከመሃል አገር ለጠረፍ አካባቢዎች የሚቀርበው የፍጆታ ዕቃ አለመኖር ወይም አነስተኛ መሆንና በተቃራኒው ከጎረቤት አገሮች በኩል የየዕለት የፍጆታ ዕቃዎች ለመጥቀስም ያህል ስኳር፤የተፈበረኩ የምግብ ምርቶችና ለጠረፍ ሞቃት አካባቢዎች የሚስማሙ አልባሳት ከመሃል አገር በተሻለ ዋጋ የሚቀርብ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 16
  • 19. 5. ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግዱ ለብዙ ጊዜያት ሲካሄድ የቆየ በመሆኑ በልምድ፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ በመረጃ ልውውጥ የተጠናከረ ፣ በተሳታፊዎች በሚደረግለት ድጋፍ ከህጋዊ ንግዱው በተሻለ መልክ የተመቻቸና አዳዲስ ተሳታፊዎችን በበለጠ ሁኔታ መሳብ መቻሉ፣ 6. ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች መኖራቸው፣እነዚህንም መውጫ በሮችን ለመቆጣጠር በሰው ኃይልም ሆነ በሎጅስቲክ አለመጠናከራቸው፤ 7. በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተ ከመተሳሰሩም ባሻገር ለጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብዛኛው ህብረተሰብ የኑሮ ምሰሶአቸው እንስሳትን በማርባትና ከእንስሳት ሽያጭ የሚያገኙት ገቢ የሚጠቀሙ በመሆናቸው የበለጠ የሚያስተሳስራቸው በመሆኑ ይህ ግንኙነታቸው ለህገወጥ ንግዱ መጠንከር አስተዋፅኦ ማድረጉ፣ 7. ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች 1. የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት 2. በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት በሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ህገ ወጡን እንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ እና የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም የሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት 3. በሀገር ውስጥ በተለይም በጠረፍ አካባቢዎች አምራቹንና ነጋዴውን በማስተሳሰር በሃገር ውስጥ የተሻለ ዋጋ ለመፍጠር አካባቢዎቹ ላይ በሂደት በመንግስትና በግል ባለሀብቶች ኤክስፖርት ቄራዎችን ማቋቋምና እና የግብይቱን ስርአቱን የሚከታተልና የሚመራ የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡ 4. በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የፍጆታ እቃዎችን ስኳር፤ዘይት፤አልባሳት…ወዘተ ከጎረቤት አገሮች ከሚገቡት ምርቶች ዋጋ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጠረፍ አካባቢዎች በጅንአድ ወይም ማህበራትን በማጠናከር በበቂ ደረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ ፤ 5. ህገ ወጡን ንግድ ለማዳከም ህጋዊ ነጋዴውና አስፈጻሚ አካላት በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ ስራዎችን በማከናወን ፤የነጋዴዎችን የገንዘብና(የካፒታል) የማስፈጸም አቅማቸውን በማሳደግ ፤ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች በማቅረብ ክትትልና ጠንካራ ቁጥጥር በማድረግ በግብይቱ ዙርያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሰፉና ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲመጡ ማድረግ፤ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 17
  • 20. 6. በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እና እንደ አካባቢው መልካምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይልና የሎጅስቲክ አቅርበትና ተሻከርካሪ በማቅረብ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮችን በመቆጣጠር ህግን ማስከበር 7. በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የግብይት ማህበራትን በማደራጀትና በሁለንተናዊ መልኩ በማብቃት በእንስሳት ወጪ ንግድ እንዲሰማሩ ማድረግ ከዚህም በተጨማሪ በጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎችን በስነ ልቦና ሆነ ባህላዊ ትስስሩ ከመሃል አገር ጋር እንዲተሳሰር ተከታታይ የሆነ ትምህርት መስጠት፤ 8. በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች 1. በጠረፍ አካባቢዎች የሚገኙ ገበያዎች የሚገኙበት ቦታ ለጎረቤት አገሮች በጣም ቅርብ እና ደረጃቸው ተጠብቆ የተገነቡ አለመሆናቸው ለአብነትም የሞያሌ (40ሜትር) የሁመራና ና የመተማ ገበያ ቦታዎች የሚገኝበት ስፍራ ለጠረፍ በጣም የቀረበ እና በ15 ኪ.ሜ ክልል ውስጥ በመሆናቸው ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆናቸው 2. የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት በሀገሪቱ ስርዓቱ ገና ባለመጀመሩ ምክንያት የሚገድብ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ያለ ገደብ ስለሚንቀሳቀሱ በተለይም ለህገ ወጡ ንግድ ሁኔታዎች የተመቻቸ መሆናቸው 3. የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው እስከ መሀል አገር ዘልቆ በመግባት ለሀገር ውስጥ ዜጋ ብቻ የተፈቀደውን ገበያ ውስጥ በመግባት እንስሳትን በቀጥታ በመግዛትና መርጦ በማስገዛት የግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸው 4. ከንግድ ሚኒስቴር ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ ቀልጣፋ ባለመሆኑ ጊዜና ተጨማሪ ወጪ በመጠየቁ እና ሚጠይቀው ካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ነጋዴዎች ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው ከመንቀሳቀስ ይልቅ ወደ ህገ ወጥ ንግድ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ 5. በአንዳንድ አካባቢዎች የጸረ ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ከክልል ጀምሮ በተዋረድ የህገ ወጡን ንግድ ለመቆጣጠርን ለህብረተሰቡ የህገ ወጡን ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዙርያ በቅንጅት ያለመንቀሳቀስ ክፍተቶች ይታያሉ ለአብነት በቦረና እና በሊበን ዞኖች በተለይም ሞያሌ ወረዳ 6. እንስት እንስሳትና ጥጃ እንዲሁም የውጭ ዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥና እገዳ በተመለከተ ግልጽና የማያሻማ በጽሁፍ የተዘጋጀ መመሪያ ያለመኖር 7. የጠረፍ አካባቢ ህብረተሰብ ኮንትሮባንድ ንግድ በህገሪቱ ኢኮኖሚና ደህንነት እንዲሁም ማህበራዊ ኑሮ እና በህጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሰው ነጋዴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽኖ የግንዛቤ ችግር መኖሩና ለገበያ አማራጭና ለተሻለ ዋጋ በህገ ወጡ ንግድ መሳተፍና ተባባሪ መሆን የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 18
  • 21. 8. በሀገሪቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቁም እንስሳት ኳራንቲንና ኢንስፔክሽን እንዲሁም እንስሳት ቼክ ፖስቶች እንዲሁም የእንስሳት የማቆያ ቦታ ያለመኖር 9. ለኤክስፖርት የተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና በተቆጣጣሪው አካል የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀርና የመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ 9. ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች 1. በሞያሌም ሆነ በሌሎች ጠረፍ አካባቢዎች የሚገነቡት የቁም እንስሳት መሰረተ ልማቶች (ገበያ ማዕከላት) ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ከጠረፍ አካባቢዎች ራቅ ብለው ምቹና የእንስሳት ክምችትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ማድረግ፡፡ 2. ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን የቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳት ዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ 3. ለዜጎች የተፈቀደውን የአገር ውስጥ ገበያ የውጭ ዜጎች ገብተው የግብይት ስርዓቱን እንዳያዛቡ በሚል ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር የተላለፈው መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ አፈጻጸሙን መከታተል 4. በንግድ ሚኒስቴር ያለውን የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት በመፈተሸ ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ 5. የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴው ከክልል በተዋረድ እስከ ቀበሌ ያለው ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የኮንትሮባንዱን ለመከላከል የሚያግዙ ተግባራትን በማቀድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስተዳድር አካላት (ከክልል እስከ ቀበሌ) ስራውን በሐላፊነት የእኔ ጉዳይ ነው ብሎ በቁርጠኝነት እንዲከታተልና እንዲመራው የጋራ የውይይት መድረክ በመፍጠር ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ 6. በእንስት የቀንድ ከብት ፤ጥጃ እና የወጭ ዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥ ዙርያ ግልጽና የማያሻማ ገላጭ የሆነ መመሪያ እንዲኖር ማድረግ 7. የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚና በህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክ የሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ 8. ደረጃቸውን የጠበቁ የኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶች የእንስሳት አቅርቦትን ክልሉን በአማካለ መልኩ በተጠኑ ቦታዎች ላይ መገንባትና ማጠናከር 9. የወጪ እንስሳት የመለያ ቁጥር(ኢር ታግ) በሚስጢር ኮድ ተሰጥቶት በሀገር መከላከያ ሚ/ር ተዘጋጅቶ ለቁጥጥር በሚያመች መልኩ በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 19
  • 22. 10.የኳራንቲን አገልግሎት የግብርና ሚ/ር በአዋጅ ቁጥር 4/1987 በአንቀጽ 19/8 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትም ሆነ በሚወጡት እንስሳት እጽዋት እና የእንስሳት ውጤቶች ላይ ተገቢውን የኳራንቲንና ኢንስፔክሽን እንዲያደርግ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ላይ እንደተገለጸው አንድ ህጋዊ ነጋዴ እንስሳትን ወደ ውጪ ለመላክ የጤና ማረጋገጫ ወረቀት ከመጠየቁ በፊት እነዚህን ቅድመ ዝግጅቶች ማሟላት አለበት  ክትባትና ሕክምና የሚያገኙበት ድርጅት/ጣቢያ  የኳራንቲን ጊዚያቸውን የሚፈጽሙበት ጣቢያ  ተፈላጊውን ክብደት እስኪያገኙ የሚቆዩበት ማደለቢያ ጣቢያ…..ወዘተ እንዲኖረው ያስፈልጋል ይላል፡፡ ሌላው በበመመሪያው የተገለጸው ደግሞ በቁም ወደ ውጪ ገበያ የሚቀርቡ የቀንድ ከብቶች ፤በጎች፤ፍየሎችና ግመሎች ተገቢውን ክትባትና ሕክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡በኳራንቲን ጣቢያ ቢበዛ እስከ 30 ቀናት ሊቆዩ ይገባል፡፡የሚል ቢሆንም ቡድኑ የተገነዘበው ነገር ቢኖር አሁን ያለው ኳራንቲን እየሰራ ያለው መመሪያውን ባልተከተለ መልኩ መሆኑን ነው፡፡  ነጋዴው ከብቶቹን ከመግዛቱ በፊት የሚገዛውን የከብት ቁጥር ብቻ በመግለጽ ሰርትፍኬት እንደሚዘጋጅለት  መኪና ላይ እያሉ ምንም አይነት ክትባት ሳይሰጥና የማቆያ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ሰርትፊኬቱን እንዲያገኙ ማድረግ  አንድ ነጋዴ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ዝግጅት ማሟላቱን ሳይጠየቅና ምንም ዝግጅት ሳይኖረው ፈቃድና ሰርትፍኬት እንዲያገኝ መደረጉ በአጠቃላይ ክልሎቹ እንደገለጹት በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደ መሆኑን እና መስፈርቱን የማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸው እንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላ ከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡ እና የደሙ እንስሳት በህጋዊ መንገድ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ህገ ወጥ አሰራር ምክንያቶች/መንስኤዎች  የፌደራል ንግድ ሚንስቴር ለወጭ እንስሳት ፈቃድ ሲሰጥና ሲያድስ ነጋዴዎቹ ተገቢውን መስፈርት ማሟላታቸውን ከግብርና ሚ/ር ማረጋገጫ እንዲያመጡ ሳይጠይቅ ፈቃድ መስጠቱ  በእንስሳት ንግዱ ዙርያ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ሆነ እንስሳት አርቢው ህብረተሰብ በድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎች ዙርያ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆን የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 20
  • 23.  የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት የህግ ክፍተትና ጉድለት መኖሩ  የየአካባቢው የእንስሳት በሽታዎች ስፋትና ስርጭት የሚያመላክቱ መረጃዎች ውስንነት እና ጉድለት  መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም የስራ ኃላፊነትና የስራ ድርሻቸውን በተመለከተ በፌደራል ለተወከሉ ባለሙያዎችና ውክልና የተሰጣቸው ክልሎች በሚገባ እንዲያውቁት አለመደረጉ እና የክትትልና የቁጥጥር አለመኖር  የእንስሳት ኳራንቲን የሥራ ክፍል በሥሩ በሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስትና ጣቢያዎች አሠራር ወጥ አለመሆን እና ለሥራ ክፍሉ ከዚህ በፊት የወጡ መመሪያዎችና ደንቦች በየጊዜው አለመሻሻል፣  በሀገሪቱ የሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስት ጣቢያዎች ባለሙያዎችና በሥራው ዙሪያ የወጣውን መመሪያ ጠንቅቆ አለማወቅ /አለመረዳት/ እና ተግባራዊ አለማድረግ፣  በእነዚህ ጣቢያዎች ካለው የሥራ /የኤክስፖርት/ ስፋት አንፃር እና መንግስት ካስቀመጠው እቅድ አንፃር ከግብ ለማድረስ ጣቢያዎቹ በሠው ኃይልና በሎጀስቲክስ ያልተሟላ መሆን፣  ለኤክስፖርት ለተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና በተቆጣጣሪው አካል የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀየርና የመለወጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑ፣  የኤክስፖርት ሥራውን ስፋት በአማከለ መልኩ የኳራንቲን ጣቢያና ሰርቪስ የሚሰጡ ጣቢያዎች በአገሪቱ ማዕከላዊ ቦታዎች መደራጀት /ለምሣሌ፡- አዳማ፣ድሬዳዋ/ እና በጠረፍ አካባቢዎች አገልግሎቱ አለመኖር፣  የመድሃኒትና የክትባት አቅርቦት አስተማማኝ አለመሆንና ከሚመለከታቸው አካላት ውጪ ደረጃውን ባልጠበቀ ሁኔታ መያዝ፣  ለክልሎች የተሰጠው የሠርቲፍኬሽን ውክልና መመሪያና ደንብ የሌለውና ለክትትልም አስቸጋሪ መሆን፣  በኳራንቲን የቼክ ፖስት ጣቢያዎች በሱፐርቪዥን እና የክትትል ሥራ ከዋናው መ/ቤት ክትትልና ድጋፍ ደካማ መሆን፣  በኳራንቲን ጣቢያዎች ለሥራው የሚመደቡ ባለሙያዎች ተከታታይ የሆኑ ስልጠናዎች፣ በተደራጁት ኳራንቲን ቦታና /አዳማ፣ድሬዳዋ/ የልምድ ልውውጥ አለማግኘት፣  በኤክስፖርት ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሀብቶች ስለ ሥራው /ስለ ኳራንቲን/ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ አሠራር በቂ ግንዛቤ አለመኖርና ለደንቡ መፈጸም ተነሳሽነት አለመኖር፣  ለእንስሳት መጓጓዣነት የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ለዚሁ ተግባር ያልተዘጋጁ መሆናቸው በእንስሳው አካላዊ ጉዳት ማድረስ ማለትም ስብራትና ከፍተኛ ቁስለት ስለሚገጥማቸው /በተለይም ግመልና ከብት/ በተቀባይ አገራት ስለኢትዮጵያ እንስሳት ያላቸውን ፒክቸር / ስዕል/ የተበላሸ መሆን፣ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 21
  • 24.  በኳራንቲን ጣቢያዎች በጉዞ ላይ ለሚሞቱና ለሚጐዱ እንስሳት የአወጋገድ የማገገሚያ መመሪያና ደንብ አለመኖር፣ /የእንስሳት በሽታ ስርጭትን ማባባስ/  የእንስሳት ዝውውር /ማለትም ከክልል ክልል/ ልቅ መሆን ለእንስሳት በሽታ ስርጭትና ለኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት መንስኤ መሆን፣  በሰፋፊና በዋና ዋና የእንስሳት ገበያ ማዕከላት /ለምሣሌ፣ ያቤሎ፣ባቢሌ፣ገንዳውሃ፣ሁመራ../ አቅራቢያ ለተገዙት እንስሳት ደረጃውን የተጠበቀ መጫኛ፣ ማራገፍያ፣ መመገቢያና ውሃ የሚገኝበት ቦታዎች አለመኖር፣  የቄራዎች የስጋና የስጋ ውጤቶች ማደራጃ አለመኖር፣ / ያሉትም በአጥጋቢ ሁኔታ አለመሰራት/ጐንደር፣ባ/ዳር፣መልጌ ወንዶ/ ቄራዎች፣  ከሁለት ዓመት በፊት በሱማሌ ክልል የኳራንቲን ቼክ ፖስት ላይ የተመደቡት ባለሙያዎች ወደ ሥራ አለመግባት ፣ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 22
  • 25. ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም መቀሌ ድሬደዋ ባህር ዳር ጅጅጋ የተያዙ የተያዙ የተያዙ ጠቅላላ ድምር የወጪ የቁም የተያዙ የቁም የቁም የቁም ኮንትሮባንድ እንስሳት የቁም በገንዘብ እንስሳት በገንዘብ እንስሳት በገንዘብ እንስሳት በገንዘብ ተ.ቁ ዓይነት መለኪያ ብዛት በገንዘብ እንስሳት ሲተመን ብዛት ሲተመን ብዛት ሲተመን ብዛት ሲተመን 1 ቀንድ ከብት በቁጥር 66 159,100 44 44,000 1,849 9,166,100 73 301,000 2032 9,670,200 2 በግ በቁጥር 42 33,600 56 27,900 147 88,200 667 319,060 912 468,760 3 ፍየል በቁጥር 160 68,132 260 156,000 127 62,200 547 286,332 4 ግመል በቁጥር 7 57,000 1 10,000 8 67,000 5 አህያ በቁጥር 2 2,000 8 15,000 10 17,000 ድምር 117 251,700 260 140,032 2,265 9,435,300 867 682,260 3,509 10,509,292 ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ
  • 26. ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ተ.ቁ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ጠቅላላ የወጪ እንስሳት መለኪያ መቀሌ(ሁመራ) ድሬደዋ ባህር ዳር ጅጅጋ አፋር(ጋላፊ) ድምር (ገንዳውሃ) ቀንድ ከብት በቁጥር 10,199 459 60,871 67,168 በግ በቁጥር 556 17,843 ፍየል በቁጥር 2,080 5,739 10,177 ግመል በቁጥር 12,975 1,640 4,025 ድምር 25,809 7,838 60,871 99,213 218,053 411,784 በገንዘብ ሲተመን ዶላር 9,856,380 1,236,705 24,351,420 31,005,943 መረጃ የለም 66,450,448 ምንጭ፡-ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 2
  • 27. ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብር ተ. የሚመለከታቸው ሰሌዳ የጊዜ ቁ መንሲኤዎችና ችግሮች መፍትሄዎች የሚከናወኑ ተግባሮች አካላት የአጭር የረጅም የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች ንግድ ሚ/ር እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም ፤ግብርና፤ህብረት በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ሥራ፤ባለሀብቶች፤ የኢስወቴኢ ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት 1.ነባር የግብይት ማዕከላትን የውስጥ ፤ክልሎች በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት ለግብይት ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊ ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ 2.ለህጋዊ ቁም እንስሳት ነጋዴዎች አቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ገበያዎችን በመሆናቸውአስተማማኝ ገበያ በየአካባቢው እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና በማመቻቸት ረገድ ወቅታዊ የግብይት 1.ጥናት ተደርጎ አለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤት የግብይት ስርዓቱን የሚከታተልና የሚመራ መረጃዎችን በመስጠት የግብይት በጅጅጋ፤በደጋሀቡር ትስስሮች እንዲኖር ማድረግ ላይ መንግስትና አገሮች ዋጋ ጋር የሚወዳደር ወይም የተሻለ የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር 3.የግብይት ህብረት ስራ ማህበራትን በግል ባለሃብቶች አለመሆንና በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆን ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት በማደራጀት የማስፈጸምን የገንዘብ የኤክስፖርት የሚችል የግብይት ስርዓት አለመኖርና የግብይት መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ አቅማቸውን በማጠናከር እንስሳትን ቄራዎች መገንባት 1 መሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣ ማድረግ፡፡ ለውጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻል 2.የግዥ ጣቢያዎች ማቋቋም በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት የፌደራል በሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች 1.ከዚህ ቀደም ከጎረቤት አገሮች ጋር ጉዳዮች፤ገቢዎችና መሰረት ህገ ወጡን እንቅስቃሴ የተደረጉ ስምምነቶች እንዲከበሩ የጋራ ጉምሩክ፤ክልሎች፤ ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ ውይይት በመፍጠር ዲፕሎማሳዊ ስራዎችን መስራት ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታቱ እና የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን 2.የነበሩት ስምምነቶች ከወቅቱ ጋር መሆኑ፤የህም የሚገለጸው በሀጋዊ መንገድ በሚገባ በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት በማገናዘብ እንዲሻሸል ማድረግ እንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከፍተኛ መሆንና ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ 3.አስፈላጊ የሚሆኑ አቅርቦቶቹን በተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም በማሟት በተቀናጀ መልኩ ጠንከር ያለ 2 መሆኑ ነው፡፡ የሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት ክትትልና ቁጥጥር ምድረግ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 3